ይህን ሥርዓት በተቀሩት ዘጠኝ ምድብ ችሎቶች ለመጀመር ስካን በማድረግ በዘላቂነት ማስቀመጥ እና ለሥራ ማዋል ጥንቃቄ የሚፈልግ እና በእውቀት ላይ ተመርኩዞ የሚሠራ ሥራ በመሆኑ በስካኒንግ ሥራ ላይ ለተመደቡ ባለሙያዎች ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ በሰባት ምድብ ችሎቶች ለተመደቡ ባለሙያዎች በገለጻ እና በተግባር ልምምድ ላይ ያተኮረ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በዲጂታላይዝ የመዝገብ አያያዝ እና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አማካኝነት የአንድ ቀን ሥልጠና በዋናው መስሪያ ቤት ተሰጥቷል፡፡
ከስልጠናው ተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችን ለአብነትም፤ ስካን የማድረግ ሥራ አላማውን በተለይም ከዲጅታል ኢትዮጵያ ጋር ተያይዞ የዲጅታል ፍርድ ቤት ለመገንባት የተጀመረውን ጅማሬ በማሳየት እያንዳንዳቸው የሚያደርጉትን አስተዋጾ ማስገንዘብ፣ ስካን ከመደረጉ በፊት እና በኋላ የሚከናወኑ ክንውኖች መግለጽ፣ ዲጅታል መረጃው ከዋናው መዝገብ ጋር ትክክለኛ ቅጂ እንዲሆን ሊደረጉ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ከቀደመ ልምድ በመነሳት ማስገንዘብ፣ በተጨማሪም ስካን እንዴት እንደሚደረግ፣እንደሚስተካከል፣እንዴት ለዘለቄታው እንደሚቀመጥ በሙያው የቀደመ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የስካኒንግ ባለሙያ የተግባር ልምምድ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዋና ሬጅስትራር ወ/ሮ ፈትለወርቅ አንዳርጌ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው የዳኝነት አገልግሎት ይበልጥ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ ከተጀመሩ ዲጂታላይዝ ትግበራ አንዱ መዝገቦችን እስካን በማድረግ በ"ኢ-ፋይሊንግ ሲስተም (e-Filing System)" ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት መላክ በመሆኑ የኢፋይሊንግ ሲስተም ያልተጀመረባቸው ዘጠኝ ምድብ ችሎት ለመጀመር መዝገቦችን ስካን በማድረግ ዝግጅት ማድረግ የሚያስፈልግ በመሆኑ ሁሉም የስካነር እና የዲጂታላይዝ የመዝገብ አያያዝ እና አስተዳደር ባለሙያዎች በተሰጠው ስልጠና መሰረት የስካኒግ ስራውን እንዲጀምሩ መልእክት አስተላልፈው ስልጠናው ተጠናቋል፡፡

❤5👍3
ለአመራሮች የኢ-ፍሊት ማኔጅመንት ስልጠና ተሰጠ።
ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
በተሽከርካሪ ሥምሪት እና አጠቃቀም የሚባክነውን ሃብት ለመቆጣጠር የሚያስችል የኢ-ፍሊት ማኔጅመንት ትግበራ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለማስጀመር ለፍርድ ቤቱ የማኔጅመንት አባላት፣ የየምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኞች እና የስራ ክፍል ዳይሬክተሮች ነሐሴ 27 እና 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን በመጡ ባለሙያዎች ልደታ ፍርድ ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የፍርድ አፈፃፀም ህንፃ ላይ ባለው ስማርት ላብ የስልጠና ማዕከል ስልጠና ተሰጠ። የመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን የኢ-ፍሊት ማኔጅመንትን (e-Fleet Management) በተለያዩ ተቋማት በሙከራ ትግበራ በማረጋገጥ በሁሉም የፌደራል ተቋማት ተግባራዊ እንዲደረግ በተወሰነው መሰረት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱም ተግባራዊ ለማድረግ ስልጠናው መዘጋጀቱን አቶ ተስፋዬ ከበደ የፍርድ ቤቱ የህንፃ አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ በስልጠናው መክፈቻ ተናግረዋል።

😁2
ስልጠናውን የሰጡት የመንግስት ግዢ እና ንብረት ባለስልጣን ባለሙያዎች አቶ ኢሳያስ መንግስቱ ሲኒየር አፕሊኬሽን ዲቨሎፐር እና አቶ አለምሸት ክንፈ የኢጂፒ ድጋፍ ሰጪ ባለሙያ ሲሆኑ ሲስተሙ ፍርድ ቤቱን ወደ ዘመናዊ፣ ዲጂታል እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት እንዲዘረጋ ከመርዳቱ በተጨማሪ ኢ-ፍሊት ማኔጂመንት ሲስተምን መጠቀም ግልፅ እና ወቅቱን የጠበቀ ሪፖርት ለማግኘት፣ የወረቀት ስራዎችን ለማስቀረት፣ ከሰዎች ንኪኪ ነፃ የሆነ አሰራር ስርዓት ለመዘርጋት፣ የተጠቃሚዎች ጊዜን ለመቆጠብ እንዲሁም የነዳጅ ዘይት እና ቅባት ወጪን ለመቆጣጣር እና ለተሸከርካሪ የሚወጣዉን ወጪ ለማወቅ የሚያስችል አሰራር መሆኑን ገልፀዋል፡፡ እንደ አሰልጣኞቹ ገለፃ ኢ-ፍሊት ማኔጅመንት ክንውኖችን በጥራት፣ በብቃት፣ በሰዓት እና በበጀት መጥኖ መፈፀም የሚያስችል ዘመናዊ የአሰራር ስርአት እንደሆነ በተለይም የተሽከርካሪ ንብረት አጠቃቀም፣ አያያዝ፣ የግዥ ሂደት እና አወጋገድን በተመለከተ የላቀ ጠቀሜታ ያለው የአሰራር እና ቁጥጥር ስርአት መሆኑ ተገልጿል። መንግስት የግዥ ስርአቱን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ወደ ዲጂታላይዜሽን ስርአት በማስገባት ኢጂፒ (e-GP) ተግባራዊ እንደተደረገ ሁሉ በተመሳሳይ በተሽከርካሪ ሥምሪት እና አጠቃቀም የሚባክነውን ሃብት ለመቆጣጠር የሚያስችል በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የለማ የኢ-ፍሊት ማኔጅመት ሲስተም መተግበሪያን ተግባራዊ በማድረግ የተሽከርካሪ ሥምሪት እና አጠቃቀምን ከማሻሻል ባለፈ የሃብት ብክነትን ለማስቀረት እየተጋ መሆኑ ተነግሯል።
ኢ-ፍሊት ማኔጅመንት ሲስተም ከተሽከርካሪ ጥገና እና ነዳጅ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን በመግለፅ ለግልጽ አሰራር እና የሃብት ክትትል መተግበሪያውን በአግባቡ በመጠቀም ለአሰራሩ ውጤታማነትም አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ እና ትብብር በስልጠናው የተገኙ ኃላፊዎች በማድረግ በተገቢው ወደ ስራ እንዲገባ በስልጠናው ተገልፆል። ስልጠናው ከነሐሴ 29 እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ለሹፌሮች፣ ለዳይሬክተሮች ፀሃፊዎች እና በትራንስፖርት ስምሪት ቡድን መሪ ስር ላሉ ሁሉም ባለሙያዎች የሚሰጥ ይሆናል።

❤8
አንኳን ለ2019 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ!
መጪው ዘመን የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ ይሁንላችሁ!
መጪው ዘመን የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ ይሁንላችሁ!
👍6❤5👏1
#የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት “ርትዕ “ መጽሄት
ልዩ ዕትም
************
የ2018 ዓ.ም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ3ኛው ስትራቴጂክ ዘመን መብቂያ እንደመሆኑ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከ 2014-2018 ዓ.ም የዓመስት ዓመት ቁልፍ ተግባራት ክንውን በልዩ ዕትም በመጽሄት በማሳተም እያሰራጨ ይገኛል፡፡
በልዩ ዕትም መጽሄቱ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባለፉት 5 ዓመታት (2014-2018) ያከናወናቸውን ቁልፍ ተግባራት የያዘ ሲሆን የፍ/ቤቱን ፕሬዝዳንት መልዕክትን ጨምሮ -ምቹ የስራ አካባቢን መፍጠር፣ -የዳኝነት ቅልጥፍና፣ -የዳኝነት ተገማችነት ማጠናከር፣-የፍርድ ቤት መር አስማሚነትን፣ -የዳኞች እና የሰራተኞች የስራ አፈፃፀም ምዘና እና እውቅና፣-የህፃናት መብቶች ከማስተከበር አንፃር በተቋሙ ተገልጋዮች እና ሰራተኞች የተከናወኑ ተግባራት -የዳኝነት ግልጽነት ፣ -ፍ/ቤቱ ስለተወጣቸው ማህበራዊ ኃላፊነት፣ -ስለ አቅም ግንባታ ስራዎች፣ -የዲጂታላይዜሽን ስራ፣ -ቅንጅታዊ አሰራር፣ -ስለ ተገልጋዩ እርካታ ጥናት :- በተጠያቂነት ዙሪያ ስለተከናውኑ ተግባራት ፣ -በፍርድ ቤቱ ስለተቋቋሙ ልዩ ችሎቶች፣ -ስለ በጀት እና የሰው ኃይሉ፣ -ስለኮምዩኑኬሽን እና ተደራሽነትን እና መሰል ቁልፍ ክንውኖች ተዳሰዋል፡፡
በተጨማሪም ባለፉት ዓመታት ፍ/ቤቱ የገጠመው ተግዳሮት እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በመጽሄቱ የተካተቱ ሲሆን ይህ ልዩ ዕትም መጽሄት ለክቡራን ዳኞች፣ ለፍ/ቤቱ ሰራተኞች እና ለባለድርሻ አካላት እየተሰራጨ ይገኛል፡፡

❤12👍3
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል
መስከረም 27/2019 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለመስጠት ካቀዳቸው ስልጠናዎች መካከል የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል።
ከስልጠናዎቹ አንዱ ለሦስቱም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች በእቅድ ዝግጅት፣ በክትትልና ግምገማ፣ በሪፖርት አዘገጃጀት እንዲሁም በፕሮግራም በጀትና (Program Budgeting) አዘገጃጀት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል።
በተጨማሪም በአዲሶቹ የመንግሥት ግዢና ንብረት አስተዳደር አዋጅና መመሪያዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፤ በስልጠናው የሦስቱም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የግዢና ንብረት አስተዳደር ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የግዢ አጽዳቂ ኮሚቴና የንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ አባላት ተሳትፈዋል።
የ2019 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ እንደመሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ በዚህ ወቅት የተለያዩ ስልጠናዎችን በማዕከል በመስጠት በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ማቀዱ ተገልጿል።
ስልጠናዎቹ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተመላክቷል።

❤10