Ethio Facts 🇪🇹 ኢትዮ ፋክት️
391 subscribers
9.52K photos
1.46K videos
74 files
1.03K links
ኢትዮጵያ ትቅደም

Walk a mile in my shoes, Then you will know how I feel.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ይፈለግ የነበረ አደገኛ ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም)ን ከነግብረአበሮቹ በቁጥጥር ስር አውሏል።

ከ3 ሺህ በላይ ሰዎችን በሕገ ወጥ መንገድ በማዘዋወር፣ ከ100 በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገ እና ከ50 በላይ ሴቶች እንዲደፈሩ ያደረገው ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም)ን ከ9 ግብረአበሮቹ ጋር በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ አጠናቅቆ ለዓቃቢ ህግ መላኩን ነው ፌደራል ፖሊስ ያስታወቀው።

ይህንን ውስብስብና ድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ምርመራ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ከሚሰራ The Regional Operational Centre in support of the Khartoum process (ROCK) ከተባለ ድርጅት ጋር ባደረገው የመረጃ ልውውጥ ነው በቁጥጥር ስር ያዋለው።

በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ይፈለግ የነበረው አደገኛ ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊት አለሙን በትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ ላይ ፖሊስ በቅንጅት በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተገልጿል።

ተጠርጣሪው በፓስፖርት ስሙ ይትባረክ ዳዊት አለሙ ቤተሰቦቹ በልጅነቱ ያወጡለት ስም ጳውሎስ ዳዊት ወልዳይ ወንጀል መስራት ሲጀምር የሚታወቅባቸው ስሞች አድሀኖም ሱዳን፣ አህመድ ሱማሊያ ጅቡቲ እና ኬንያ የሚጠቀምበት ስም ሙኒር ሲሆን ክብሮም ደግሞ በስዊድን እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የሚጠቀምባቸው ሀሰተኛ ስሞች መሆናቸውን ፖሊስ በምርመራው ማረጋገጡ ተጠቁሟል፡፡

ፖሊስ እነዚህን ስሞች ለምርመራው አጋዥ አድርጎ ያደገ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተጠናከረ ምርመራና ክትትል በማድረግ ከ70 በላይ በሀገር ውስጥና በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ዋና ዋና የሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎችን ከለየ በኋላ ዋናውን ተጠርጣሪ ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን ተከታትሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራውን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

ፖሊስ የተያዙትንም ሆነ ያልተያዙትን ተጠርጣሪዎች በወንጀሉ ያፈሩትን ሀብት በጥናት በመለየት ሌሎች ሀብቶቻቸውንና በባንክ የሚገኝ ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ በፍርድ ቤት እንዲታገድ ማድረጉን ገልጿል፡፡

ሕገ ወጥ አዘዋዋሪ ቡድኑ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ወጣቶችን ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ በመመልመል ወደ ሊቢያ በመውሰድ ሊቢያ ውስጥ ባዘጋጁት መጋዝን እንዲታገቱ ማድረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡

ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በመፈፀም በርካታ ሰዎች ሕይወታቸው እንዲያልፍ፣ የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸው፣ ሴቶች እንዲደፈሩ እና ከፍተኛ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳት እንዲደርስባቸው ማድረጋቸውን ፖሊስ በምርመራ ማረጋገጡ ተጠቅሷል፡፡

ሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ሊቢያ ውስጥ ተጎጂዎችን አግተው የሚያሰቃዩባቸው አምስት ማከማቻ መጋዘን እንዳላቸው እና በዚህ አደገኛ ወንጀል ከ3 ቢሊየን ብር በላይ በሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ሲንቀሳቀስ እንደነበር ፖሊስ በሰበሰበው ማስረጃ ማረጋገጡ ተመላክቷል፡፡

በዚህም ከ100 በላይ ተጎጂዎችንና ቤተሰቦቻቸውን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምስክርነት ቃል የመቀበል ሥራ መሰራቱን ገልጿል፡፡

ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሊቢያ፣ ሱዳን፣ ቤልጂየም፣ እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ ኖርዌይ፣ ኔዘርላንድ፣ ሉግዘንበርግ እና ስዊዘርላንድ ከሚገኙ 16 ተጎጂዎች ላይ ቃል መቀበሉንም ፖሊስ አሳውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሀገርና በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለውን ይህንን ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ለመከላከል ዘመኑ ያፈራቸውን የምርመራ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም በተሟላ ፖሊሳዊ ስብዕናና ስነ ምግባር እየተመራ በላቀ ቁርጠኝነት ተልዕኮውን መወጣቱ ተገልጿል፡፡

ተቋሙ ከሀገራት ጋር በፈጠረው የፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነት ዓለም አቀፍ የወንጀል ተፈላጊዎችን ጭምር በቁጥጥር ሥር አውሎ በተለያየ ጊዜ ምርመራ በማጣራት በሀገር ውስጥ በሕግ እንዲጠየቁና የተወሰኑት ደግሞ ከሀገራት ጋር ባለው የወንጀለኛ ልውውጥ ስምምነት መሰረት ተላልፈው እንዲሰጡ እያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ሕብረተሰቡ ማንኛውንም የወንጀል ድርጊት ሲመለከት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp)፣ በ991 ነፃ የስልክ መስመር እና ሰው አልባ ፖሊስ ጣቢያ በመጠቀም ወይም በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት የዘወትር ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ተቋሙ ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ ጥሪ አቅርቧል፡፡
❤3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" ሻዕቢያም ለራሱ ሲል ነው ፤ እኛም ለራሳችን ስንል ነው።ማለትም የጋራ ጠላት መጥቶብናል። የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው እንደሚባለው ከሻዕቢያ ጋር የነበረን ግንኙነት ታክቲካል የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በአንድነት ልንዋጋ ወደምንችልበት ደረጃ አድጓል "

- ዶ/ር አዲሳለም ባሌማ ከዲያስፖራ የወያኔ ደጋፊዎች ጋር በነበረው የዙም ውይይት
NewsAlert ‼️የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዘዳንት ጄነራል ታደሰ ወረደ ከመቀሌ በቀጥታ ስርጭት በትግራይ ያለውን ውጥረትና ጦርነት ዝግጅት እየተናገሩ ነው::

“እኔ የማስረክበው ነገር የለም “መረካከብ” የሚባል አርቲፊሻል ጨዋታ ውስጥም አልገባም። ይህ አጥፊ አካሄድ ተገቢ እንዳልሆነ እየገለጽኩ ነው። የለም በዛ መንገድ እንሄዳለን ካሉ ግን እንደፈለጉ ያድርጉ”

ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ
(አሁን በርእዮት)
NewsAlert ‼️ “ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ሆነዋል ብዬ የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ አላቀርብም! እንደዛ የማድረግ መብት እንዳለኝ ባውቅም እኔ ግን አላደርገውም! የሚሆነውን እናያለን

ሌ/ጄነራል ታደሰ (ለርእዮት ሚዲያ)
"የድሮ ምክር ቤት መልሰናል" በሚል እየተደረገ ያለው የአንድ ወገን እንቅስቃሴ፣ እኔ አላምንበትም፣ ትግራይንም ችግር ውስጥ ይከታታል ብዬ አምናለሁ። ከዛ ግርግር ይልቅ በተለያየ አሰላለፍ አኩርፎ የተቀመጠ ብዙ ሐሳብ ያለው ትግራዋይ አለ። እሱን እንሰብስበውና ትግራይን ወደተሻለ ምእራፍ ስለማሸጋገር እንጨነቅ። ወደ ጦርነት የሚወስድ የእብደት አካሄድ ትተን አጋጣሚውን ለመልካም እድል እንጠቀምበት!"

ጄ/ል ታደሰ ወረደ
በርእዮት ሚዲያ አሁን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
//...አሁን እንደመጀመሪያው ደፍረው የሚመጡበት ሁኔታ የለም።ሁለትና ሶስት ጊዜ እንዲያስቡበት እያደረግናቸው ነው።ሁለትና ሶስት ጊዜ ማሰብ ካልቻሉ ደግሞ ከባድ ምት እንዲያርፍባቸው የሚያደርግ አደረጃጀት ይኖረናል።አሁን ብቻችንን አይደለንም።ፋኖ ከኋላ ምን እያደረጋቸው እንደሆነ ታውቃላችሁ።ከፋኖ ጋርም በትብብር እንሰራለን።ከማንኛውም ሃይል ጋር እንሰራለን። አሁን (ከፋኖና ከሌሎች ሃይሎች ጋር ) በትብብር የምንሰራበትን የትብብር alliance charter እና የስነምግባር ደንብ እያዘጋጀን ነው። ይሄ በጠላቶቻችን ላይ ጫና ይፈጥራል ብለን እናስባለን።ይሄን ሁሉ አልፈው ከመጡ ግን የተሻለና የተጠናከረ ምት የምናሳርፍበትን ሁኔታ እየፈጠርን ነው ያለነው ...//

-- አ/ር አዲስአለም ባሌማ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
// ....እንዲህ ያለው ነገር በሚዲያ እየወጣህ የምትናገረው አይነት አይደለም ፤ አደገኛና ከባድ ምስጢር ተደርጎ መያዝ የነበረበትን ነገር'ኮ ነው የምነግራችሁ።ከዚህ በላይ ባልናገር ይሻላል።የተሻለ ደረጃ ላይ እንደሆንን ከነገርኳችሁ ይበቃል - በቃ በራሳችሁ መንገድ ተረዱት ....//
-- አዲስአለም ባሌማ ነው ይሄንን ያለው።በዚህ የዙም ውይይት ላይ ከአንድ ተሳታፊ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ የተናገረው ነው።
ጥያቄው "የታደሰ ወረደን ጊ/አስተዳደር ለማፍረስ ለምን ዘገያችሁ ? ለምን ቀደም ብላችሁ አላፈረሳችሁትም? " የሚል ነበር።አ/ር አዲሳለም ጥያቄውን ዘርዘር አድርጎ ሲመልስ 👇
1- ጊ/አስተዳደሩን ቀደም ብለን ለማፍረስ ያልፈለግንበት ምክንያት አለ-አልተዘጋጀንም ነበር።አሁንበመጠኑ ተዘጋጅተናል።ያኔ ግን እኛን ከድተው ወደሱ የሄዱት ሰዎች ስለ ወጪያችንና መሰል ጉዳዮች ይነግሩት ስለነበረ ጊዜውን ያልጠበቀ ውሳኔ መወሰን ለኛ አደገኛ ነበር ፤
2- እኛ የጊዜያዊ አስተዳደሮችን ለጊዜ መግዢያ ነበር የምንፈልጋቸው።በተለይ ሁለተኛው ተሿሚ ጄ/ል ታደሰ ወረደ አስተዳደሩን ለመምራት ብቁ እንዳልነበር ሁላችንም እናውቅ ነበር።እኛ ግን እሱ ጉዳያችን አልነበረም።ሌላም ሰው በቦታው ቢሾም ለኛ ችግር አልነበረውም።ዋናው ነገር እኛ ለዝግጅት የሚሆን ጊዜ ነበር የምንፈልገው።የፈለግነውን ጊዜ በመጠኑም ቢሆን አግኝተናል ።
4- ባገኘነው መጠነኛ ጊዜ ምን ሰራን ቢባል..
*ሰራዊታችን የጎደለውንና የሚያስፈልገውን ሁሉ አሟልተንለታል።
* ከፋኖ ከሻዕቢያና ከሱዳን ጋር የጀመርነውን የትብብር ደረጃ ወደ ላቀ ደረጃ አድርሰነዋል።
5-ሁሉም ነገር በሚደያ አይነገርም።በተለይ እንዲህ ያለው ነገር በሚዲያ እየወጣህ የምትናገረው አይነት አይደለም ፤ አደገኛና ከባድ ምስጢር ተደርጎ መያዝ የነበረበትን ነገር'ኮ ነው የምነግራችሁ።
ሰበር ዜና

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የነበረውን የጦር መሳሪያ ገደብ አነሳች

ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ተጥሎ የነበረውን የጦር መሳሪያ ገደብ እና ከደህንነት ዘርፍ ጋር የተያያዙ እገዳዎችን ማንሳቷ ተሰምቷል። ይህ እርምጃ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማምጣት የተወሰደ መሆኑ ተገልጿል።

አሜሪካ እገዳውን የጣለችው በ2021 በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው የትግራይ ጦርነት ወቅት ነበር። በወቅቱ ዋሽንግተን በጦርነቱ ዙሪያ በተነሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና የሰብዓዊ ቀውስ ምክንያት የጦር መሳሪያ ሽያጭን እና የደህንነት ትብብርን ገድባ ነበር።

አሁን ግን የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለው የፀጥታ ሁኔታ፣ የቀይ ባሕር የንግድ መስመር ጠቀሜታ እና የኢትዮጵያ በቀጠናው ያላት ስትራቴጂካዊ ሚና አሜሪካን አዲስ ውሳኔ እንድትወስድ እንዳደረጋት ተንታኞች ይናገራሉ።

የአሜሪካ መንግሥት በተለይ “በአፍሪካ ቀንድ የሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን ለመቆጣጠር ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ትብብር አስፈላጊ ነው” የሚል አቋም መያዙ ተጠቁሟል።
ኢትዮ-ኤርትራ‼

የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊሸጋገር ነው እየተባለ ይገኛል‼

📌ከተለያዩ ወገኖች እንደሚሰማው ይህ ነገር የመሆን እድሉ ሰፊ ነው ተብሏል።

በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ያልተጠበቀና አስገራሚ የፖለቲካ ለውጥ እየታየ መሆኑን  ምንጮች ጠቁመዋል።የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ ያሸጋግራል የተባለ ታሪካዊ ስምምነት ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል።

📌 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ወደ አስመራ የሚያቀኑ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ ተገልጿል።

📌መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በላቀ ደረጃ የሚያጠናክር አዲስ ስምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ ድንገተኛ ክስተት በቀጠናው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ትስስር ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ይኖረዋል ተብሎ በከፍተኛ ጉጉት እየተጠበቀ ነው።
የአሜሪካና ኢራን የሰላም ስምምነት ተስፋ የዓለም የነዳጅ ዋጋን በከፍተኛ ሁኔታ አወረደው

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ሊደረግ የታቀደው የሰላም ስምምነት ይፋ ሊሆን ይችላል የሚለው ተስፋ የዓለምን የነዳጅ ዋጋ እንዲያሽቆለቁል ማድረጉን ተገለጸ።

በዚህም መሠረት የብሬንት (Brent) የነዳጅ ዋጋ በ5.5 በመቶ ቀንሶ በአንድ ባሬል 97.90 ዶላር የገባ ሲሆን፣ የአሜሪካው ድፍድፍ ነዳጅ ደግሞ በ5.9 በመቶ ቅናሽ አሳይቶ 90.93 ዶላር ደርሷል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጠንካራ የሰላም ረቂቅ በጠረጴዛ ዙሪያ መኖሩንና ስምምነቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስምምነቱ በአብዛኛው ተደራድሮ ማጠናቀቂያ ላይ መሆኑንና ዝርዝር ጉዳዮች በቅርቡ ይፋ እንደሚሆኑ የገለጹ ሲሆን ይህ ስምምነት ከየካቲት 28 ጀምሮ በጦርነቱ ምክንያት ተዘግቶ የነበረውንና የዓለምን አንድ አምስተኛ የነዳጅና የፈሳሽ ጋዝ (LNG) አቅርቦት የሚያስተናግደውን ወሳኙን የሆርሙዝ ወሽመጥ በድጋሚ ለመክፈት የሚያስችል በመሆኑ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ከፍተኛ መረጋጋትን ፈጥሯል።

(BBC)
የጀነራሉ እገታ እና ያሉበት መታወቅ!

ጀነራሉ መታገታቸው ተረጋገጠ፡፡ አንድ ወር ለሚሆን ጊዜ ከአደባባይ የጠፉት ጀነራሉ፤ መታገታቸውን የፈረንሳዩ ጋዜጣ ይፋ አድርጓል፡፡ ጀነራሉ ወደ አዲስአበባ እንዳይጓዙ እና ለፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ጋር እንዳይገናኙ በሚል ነው የታገቱት ተብሏል፡፡

ጀነራሉ ታግተዋል፡፡ የተረጋገጠ መረጃ ነው፡፡ ህውሃት ከአንድር ወር በፊት ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን ፕሬዝዳንት አድርጎ ጀነራል ታደሰ ላይ መፈንቅለ መንግስት ካከናወነ በኋላ፤ ጀነራሉ ጠፍተው ከርመዋል፡፡ ከዚህ የመፈንቅለ አስተዳደር በኋላ በአደባባይ ያልታዩት ጀነራል ታደሰ፤ የት ጠፉ በሚልም ብዙ ሲጠየቅ ነበር፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሆን መረጃ ዛሬ ይፋ ሆኗል፡፡

ታማኙ የፈረንሳይ ጋዜጣ አፍሪካን ኢንተለጀንስ ስለ ጉዳዩ ሰማሁት ያለውን መረጃ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡ ጀነራል ታደሰ ወረደ ከመቀሌ እንዳይወጡ እና እንዳይንቀሳቀሱ ታግተው እንደሚገኙ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ ‹‹ጀነራሉ ወደ አዲስአበባ እንዳይጓዙ በዚያም ከፌዴራል ባለስልጣናት ጋር እንዳይገናኙ በሚል በህውሃት ቁጥጥር ስር ናቸው›› በማለት ዘግቧል፡፡

የአፍሪካን ኢንተለጀንስ ዘገባ እንደሚያመላክተው፣ ይህ እገዳ የተጣለው በጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ እና ጌታቸው ረዳ አሰባሳቢነት ባለፈው ሳምንት በአዲስአበባ ምክርቤት መመስረቱን ተከትሎ ነው፡፡ የእነ ጀነራል ፃድቃን የአዲስአበባው ምክርቤት ሕውሓትን ባጭር ጊዜ አስወግዶ ክልሉን ለመቆጣጠር አቅዷል፡፡ ህውሓት ጀነራል ታደሰ ወደ አዲስአበባ ኮብልለው ከአዲሱ ምክርቤት ጋር እዳይቀላቀሉ በሚል ነው ጀነራል ታደሰን የቁም እስረኛ ያደረጋቸው ብሏል ዘገባው፡፡ ጀነራሉ ብዙ ሚስጥር የሚያውቁ እና ህውሃት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ሰው በመሆናቸው እንደሆነ ጋዜጣው አብራርቷል፡፡

ከአፍሪካን ኢንተለጀንስ መረጃ መረዳት እንደተቻለው ህውሓት ጀነራሉን ለማገት የወሰነው በሁለት አበይት ምክንያቶች ናቸው፡፡ አንደኛው ጀነራሉ የእነፃድቃንን ምክርቤት እንዳይቀላቀሉ በሚል ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጀነራሉ እጅ ላይ በርካታ የሕውሓት ሚስጥሮች በመኖራቸው ነው፡፡
❤1
ፊልድ ማርሻሉ ስለ ጽምዶ‼️

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ አዲስ ለተመረቁ ወታደራዊ መኮንኖች ትእዛዝ ሰጡ። ‹‹እናነት ወደ ሰራዊቱ ስትቀላቀሉ ጣረሞት ላይ ያለውን ባንዳ ጨርሳችሁ ማስወገድ ይኖርባችኋል›› ሲሉ ዛሬ ለተመረቁ መኮንኖች ትእዛዝ ሰጥተዋል፡፡ ጽምዶን በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግረዋል፡፡ ፊልድ ማርሻሉ ህልማቸው መክኗል፣ የጥፋት እጃቸው ተቆርጧል፣ ወሮ በላዎችን ተዋጓቸው የሚሉ አገላለጾች በመጠቀም ባወዛጋቢ ንግግር ተከስተዋል፡፡ ‹‹ጠላቶቻችን ጽምዶ ብለው መጥተዋል›› ያሉ ሲሆን፤ ሊበትኑን የዶለቱ ኃይሎች ህልማቸው መክኗል ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
‹‹ማወቅ ያለባችሁ ጽምዶ አሁን የመጣ ጉዳይ አይደለም፤ ጽምዶ የ1960ዎቹ ስትራቴጂ ነው፤ የ60ዎቹ ትውልድ ማለት የዛሬ ጽምዶ ማለት ነው፤ የዚያን ዘመን ትውልድ ማርክሲዝም ሌኒኒዝም እያለ ታሪካዊ ጠላቶቻችንን እየጋበዘ፣ ሞቃዲሾ እና ካይሮ እየሄደ፤ የሱዳን፣ ግብጽ እና ኤርትራ ቅንጅት በመፍጠር ኢትዮጵያን ከባህር በር የማባረር ዘመን ነበር፤ የ1960ዎቹ ትውልድ›› በማለት የአሁኑን ጽምዶ ከ60ዎቹ ትውልድ እንቅስቃሴ ጋር አጋምደው አብራርተዋል፡፡

ቀጥለውም፣ ‹‹ያን ጊዜ ካይሮ እና ሞቃዲሾ ሄደው ደጅ የጠኑ የዚያድ ባሬ እና የፈርኦን ቤተሰብ ተላላኪዎች ግንባር ፈጥረው የዛሬ 60 አመት ኢትዮጵያን ከባህር በር በማባረር፤ ኢትዮጵያን በእርስ በርስ ጦርነት በማዳከም፣ በቀጠናው ተርጉም ያላት አገር እንዳትሆን አድርገዋል›› በማለት የ60ዎቹን የፖለቲካ ኃይሎች ተችተዋል፡፡  በወቅቱ ከባህር በር የተገፋንው ‹ጠላቶቻችን› ጎበዝ ስለሆኑ አይደለም ያሉም ሲሆን፤ ‹‹የተሳካላቸው እነርሱ ባንዳ ስላገኙ ነው›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ‹‹አሁንም እየተደረገ ያለው እርሱ ነው፤ ያን ጊዜ የነበሩ ባንዳዎች መልካቸውን ቀይረው እንጂ ያሉት እነርሱ ናቸው›› በማለት በጽምዶ እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ የአገር ውስጥ ኃይሎችን ባንዳ በማለት ጠርተዋል፡፡

‹‹ታሪካዊ ጠላቶች እና ምቀኛ ጎረቤታችን ተቀናጅተው የውስጥ ባንዳ ቀጥረው፤ አገራችሁን ለማፍረስ እየሰሩ ያለበት ጊዜ ነው፤ ነገር ግን እድሜ ለመከላከያ ሰራዊት አከርካሪያቸውን መትቶ ተሸመድምደው ጣረሞት ላይ ያሉበት ጊዜ ላይ ነን›› ሲሉም አክለዋል፡፡ ‹‹እናነት ወደ ሰራዊቱ ስትቀላቀሉ ጣረሞት ላይ ያለውን ባንዳ ጨርሳችሁ ማስወገድ ይኖርባችኋል›› ሲሉ ዛሬ ለተመረቁ መኮንኖች ትእዛዝ ሰጥተዋል፡፡
❤1