አርሰናል እና ቼልሲ በዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ ከዳኝነት ስህተት በትልቁ ያተረፉ ክለቦች ናቸው።
ቼልሲ በዳኝነት ስህተት በ8 አጋጣሚዎች ሲጠቀም፤ አርሰናል በ7 የዳኞች ስህተት ተጠቅመዋል።
አርሰናል በውድድር ዘመኑ በሊጉ ምንም ቀይ ካርድ ያልተመለከተና ፔናሊቲ ያልተሰጠበት ቡድን ቢሆንም የዳኞችን ውሳኔ የሚገመግመው ቡድን አርሰናል 3 ጊዜ የቀይ ካርድ ሊሰጠው ሲገባ መታለፉንና 3 ጊዜ የፍፁም ቅጣት ምት ሊሰጥበት ይገባ እንደነበር አምኗል።
በተጨማሪ በሊጉ ዘንድሮ 25 የVAR ስህተቶች ሲፈጸሙ ይህም ከአምናው በ7 የጨመረ ነው።
[BBC]
SHARE | @FN_SPORTS

❤17🤯4👌1🕊1
ሰላም ቤተሰቦቻችን እንደምን ዋላችሁ😊
በዛሬው የ 7ተኛው ክፍል የታላቁ መድረክ ቅኝታችን የ1994ቱን የዓለም ዋንጫ እንዳስሳለን አብራችሁን ቆዩ😍
SHARE | @FN_SPORTS
በዛሬው የ 7ተኛው ክፍል የታላቁ መድረክ ቅኝታችን የ1994ቱን የዓለም ዋንጫ እንዳስሳለን አብራችሁን ቆዩ😍
SHARE | @FN_SPORTS
🥰8❤2
1994 - ሮቤርቶ ባጅዮ ብቻውን ቆሟል!
በ1990 ጀርመን በአሰልጣኗ ፍራንዝ ቤከንባወር እየተመራች የዓለም ዋንጫውን ከፍ ካደረገች በኋላ የታላቁ መድረክ መሰናዶ ቀጣይዋ መዳረሻ የነበረችው አሜሪካ ነበረች።
ውድድሩን አስተናግዳ የማታውቀው ሀገሪቱ መሳ ለመሳ የምትጠራበትን ስፖርት ለመከወን ተመረጠች። ስሟ ከባስኬትቦል እና ሌሎች ስፖርቶች ጋር አብዝቶ የሚነሳው ሀገረ አሜሪካ ለታላቁ መድረክ ስትታጭ ብዙዎች ተጠራጥረዋት ነበር።
በተለይ አስቸጋሪ የአየር ፀባይዋ ውድድሩን አዳጋች ማድረጉ ሀገሪቱ በብዙዎች ዘንድ እንድትወቀስ ያደረገ ሁነት ነበር።
ነገር ግን ይህ ሁሉ ንግርት የውድድሩን ከባቢ አስቸጋሪ አድርጎት ቢቆይም መድረኩ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የታዳሚዎችን መጠን አስተናገደ። አሁንም ድረስ በቆየ ሪከርድ የአሜሪካው የዓለም ዋንጫ ብዙ ታዳሚዎች የተካፈሉበት ሆኖ ተመዘገበ።
ጨዋታዎች ከመጀመራቸው አስቀድሞ መድረኩ እጅግ የተለየ እንደሚሆን የአሜሪካ ጎዳናዎች አሳበቁ። ሁሉም ውድድሩን ለማየት ተሰናዳ!
ከዚህ በመቀጠል በሚኖረን ቆይታ በ1994 ስለተከወነው እና ሮቤርቶ ባጅዮ በባህታዊ ትካዜው በብዙዎች ልብ ውስጥ ስለተሳለበት የዓለም ዋንጫ እናስቃኛችኋለን አብራችሁን ቆዩ😊

❤3
የወቅቷ የዋንጫው ባለክብር ጀርመን ወደ ውድድሩ የመጣችው በታላቅ ኩራት እና በራስ መተማመን ነበር። ጥንቃቄን ባስቀደመው ፣ በአስፈሪው እና በከባድ አጨዋወቱ የሚታወቀው ስብስቡ ልክ በ1990ው ጣልያንን እንደተቆጣጠረው ሁሉ ያንን ለመድገም አሜሪካ ተገኘ። ነገር ግን እውነታው ከጠበቁት ተቃራኒ ሆኖ ታላቀበ ጀርመን በአጭሩ ቀረች።
በሌላ በኩል የዴዬጎ ማራዶናን የመጨረሻ ጉዞ በተስፋ ለመቋጨት የተለሙት አርጀንቲናውያን ታላቁን ንጉሳቸውን ይዘው ተከሰቱ። ከ1990ው አስቸጋሪ የዓለም ዋንጫ በኋላ ዲዬጎ አሁንም ለአርጀንቲና ያልጨረሰው ግዳጅ እንዳለው ሁሉ በትልቅ ተስፋ ወደ ውድድሩ መጣ።
ሀገሪቱ ከግሪክ ጋር ባደረገችው ጨዋታ ጎል አስቆጥሮ ያሳየው የደስታ አገላለፅ በብዙዎች ዘንድ እንደ ማስጠንቀቂያ ተቆጠረ። አርጀንቲና የ1986ቱን ገድል ልትደግመው ነው ተባለ።
ነገር ግን ሁሉን ነገር የቀየረ ሁነት የተፈጠረው እዚ ጋር ነው!
ማራዶና የፀረ አበረታች መድሃኒት ምርመራውን ወደቀ! በዚህም ከውድድሩ ውጪ ሆነ! ፀሀይን ምልክቷ ያደረገችው ሀገር ጥቁር የሀዘን ደመና ሸፈናት። ነጭ እና ሰማያዊ ለባሾቹ ልባቸው ተሰበረ! ዳግምም አላገገሙም!
ሌላኛዋ የደቡብ አሜሪካ ሀገር ኮሎምቢያ ወደ ውድድሩ ስትመጣ በብዙዎች ዘንድ በእጅጉ ነበር የተጠበቀችው። በተለይ በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች አርጀንቲናን 5-0 ያሸነፈችበት ውጤት ብዙዎች ለዋንጫው እንዲገምቷት ያስቻለ ነበር።
ነገር ግን በሮማንያ እና በአዘጋጇ ሀገር አሜሪካ የደረሰባት ሽንፈት ጥቁር ጠባሳ ሆኖ አለፈ። ከሁሉም የባሰው ሁነት ግን ከዚህ በኋላ እንደሚመጣ ማንም አላወቀም ነበር።
#ይቀጥላል

❤6
ከአሜሪካ ጋር ባደረገችው ጨዋታ ከውድድሩ የተሰናበተችው ተከላካይዋ አንድሬስ ኢስካቦር በራሱ ላይ ባስቆጠረው ጎል መሆኑን ተከትሎ ከስንብቱ መልስ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በሜደሊን መገደሉ ተሰማ!
በጨዋታው ላይ በራሱ ላይ ባስቆጠረው ጎል ምክንያት የቁማር ቀመረቸው የተበላሸባቸው ሰዎች እንዳስገደሉት ቆየት ታወቀ። ሁነቱ የዓለም ዋንጫውን ገፅ አጠለሸው። ሁሉም ሀዘኑን ገለፀ።
በአንፃሩ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ወደ ውድድሩ የመጣው ከባድ ሀላፊነትን ተሸክሞ ነበር። 3 ጊዜ የውድድሩ ባለክብር ለሆነች ሀገር 24 ዓመት ያለዋንጫው መቆየት ለደጋፊው የሚዋጥ አልነበረም።
ሴሌሳዎቹ ወደ ውድድሩ ሲመጡ ቀድሞ ከሚታወቁበት የሳምባ ዳንስ አጨዋወታቸው ይልቅ ጥንቃቄ የተሞላበትን የጨዋታ መርህ ይዘው ተከሰቱ። ታዲያ በመካከላቸው አንድ ጥበበኛ ይዘው ነበር ። አጨዋወቱ ሁሉ ወደ እርሱ የሚያጋድለው ። ሮማርዮ
በቁመቱ አጭር ቢሆንም ነገር ግን ተፅእኖው ያየለው ኮከቡ ከሌላው አጋሩ ቤቤቶ ጋር በመሆን ለብራዚላውያን የተስፋ ጮራ ይዘው መጡ። አምበሉ ዱንጋም ሌላው የቡድኑ የጥንካሬ ምንጭ ነበር። ብራዚል አሁን አዝናኝ ብቻ አይደለችም! ይልቅስ ግትር ፣ ፅኑ እና የማትደፈር ሆና መድረኩን ተቀላቀለች።
ሌላይቱ የመድረኩ ዓቢይ ርዕስ ጣልያን ነበረች። ሶስት ጊዜ ውድድሩን ማሸነፍ የቻለችው ሀገሪቱ አሜሪካ ስትደርስ ባለፖኒቴሉን ልዑል ይዛ ነበር ፤ ሮቤርቶ ባጅዮን
ብዙዎች በመሮጣቸው ለቡድን አቅም ሲሆኑ አሱ በጥቂት አስማታዊ እይታ ተቃራኒን ዶግ አመድ ያደርጋል። ኳሷን ሲነካት የማይጨንቀው ፤ እንደ መፅሀፍ ቅዱሱ ሶምሶም ጥበቡ ፀጉሩ ላይ ያለ ይመስል በፖኒቴል ወደ ኋላ በተገመደው ፀጉሩ የሚታወቀው አስማተኛ የአሜሪካን ስታድየሞች ሳር ረገጠ!

❤2
ውድድሩን በጠበቁት ልክ ያልጀመሩት ግሊ አዙሪ መድረኩን የባቱት በሽንፈት ተሞልተው ነበር። ሰዎች አሰልጣኝ አሪጎ ሳኪን መተቸት ተያያዙ። ባጅዮም በተመሳሳይ የትችቱ ሰለባ ነበር።ነገር ግን የእግር ኳስ ህይወቱን ጉዞ መስመር የሚሰብር አለት ከፊቱ እንደተደቀነ ማንም አላወቀም ነበር።
የውድድሩ ክስተቶች
ሮማንያ በወርቁ ልጇ ጂኦርጂ ሀጊ እየተመራች አስደናቂ ብቃትን ማሳየት ቻለች። አስደናቂው ጥበበኛ በታላቁ መድረክ ሀገሩን ከፍ አደረገ። በሌላ በኩል አፍሪካን ወክላ በውድድሩ የተሳተፈችው ናይጄሪያ ሌላኛዋ የመድረኩ ድምቀት ነበረች።
ከሁሉም የምትጎላው ግን የሂርስቶ ስቶይችኮቭ ሀገር ቡልጋርያ ናት። በውድድሩ የወቅቱን ሻምፕዮን ጀርመንን ከመድረኩ ያሰናበተችበት ሁነት አነጋጋሪነትን የፈጠረ ነበር።
የባለፖሊቴሉ ገድሎች
ሀገረ ጣልያን በወድድሩ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ከተቸገረች በኋላ ወደ ጥሎ ማለፍ ዙሮች ስትገባ የተአምረኛ ሌጆቿን ብቃት ሻተች። በዚህ ጊዜ ነበር አንበሳው ልዑሏ ሮቤርቶ ባጅዮ በአስፈላጊው ሰዓት የተገኘው።
በ16ቱ ጥሎ ማለፍ ከናይጄርያ ጋር ባደረገችው ጨዋታ ንስሮቹ አስቀድመው መምራት ጀመሩ። ሁሉም ጣልያን ወደቀች ብሎ አይኑን ሲተክል ሮቤርቶ ባጅዮ ለእናት ሀገሩ ደረሰ ፤ 1-1 በሆነ ውጤት ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰዓት አመራ! ጣልያን ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ቻለች።
በሩብ ፍፃሜው ከስፔን ጋር በነበረው ጨዋታ አሁንም ጀግና ሆኖ መገኘት የቻለው ፀጉራሙ አስማተኛ ነበር።
በግማሽ ፍፃሜው ጣልያን ቡልጋርያን ስታስተናግድ ሮቤርቶ ባጅዮ ከጉዳት ጋር ወደ ሜዳ እንደሚገባ ታወቀ። በትከሻው የተሸከማት ሀገር በመጨረሻም ምን ሊውጣት ይሆን ተባለ!

❤7
ነገር ግን ጉዳት ለብቃቱ ጎርፍ መሎጊያ ሊሆን አልቻለም ፤ ይልቅስ በአስቸጋሪው ሰዓት ባጅዮ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ሀገሩን ለፍፃሜ አበቃ።
ጣልያን በውድድሩ መገለጫዋ ባጅዮ ሆነ። ሀገሩን ተሸክሞ ለፍፃሜ አበቃ። ሁሉም ጣልያን እንዳስቆጠረች ሲሰማ ባጅዮ መሆኑን አይጠራጠርም ነበር። የጣልያን የፊት ገፅ ፣ መታያ እና መገለጫ ሮቤርቶ ነው ተባለ።
በሌላ አፅናፍ በውድድሩ የምትጠበቀው ብራዚል በግማሽ ፈፃሜ ከኔዘርላንድ ተደለደለች። ሁለት የእግርኳስ አቡጊዳን የሚያውቁ ሀገራት በትልቅ መድረክ ተፋጠጡ። ብራዚል በቤቤቶ እእና ሮማርዮ አማካኝነት የመጣውት ዋንጫውን ለማሸነፍ ነው ስትል መልዕክት አስተላለፈች።
በግማሽ ፍፃሜው መርሀ ግብር ስዊድንን በሮማርዮ ብቸኛ ጎል በማሸነፍ ከጣልያን ጋር ለመገናኘት ቀን ተቆረጠላት!
የፍፃሜው መድረክ ተዘጋጀ!
ሁሉም በፓሳዴና ተከማቸ። 100,000 ሰዎችን የሚይዘው የሮዝ ቦውል ስታድየም በካሊፎርኒያ ንዳድ በወበቃማው ሰማይ ስር ትልቁን መድረክ አሰናዳ። ሁለት ኋያላን ለታላቅ ገድል ተፋጠጡ! ጣልያን ከብራዚል!
ከፊሽካው መነፋት አስቀድሞ የዜና አውታሮች ቀስት እሱን ይጠቁማል - ሮቤርቶ ባጅዮን። በጉዳት እየተፈተነ ፣ በህመም እየተሰቃየ በችግር ጊዜ ደራሽ የሌላትን ሀገሩን ሊያኮራ አደራን በትከሻው ተሸክሞ ወደ ሜዳ ለመግባት ተዘጋጅቷል። በአንፃሩ የቆመውን የብራዚል ኮከብ ሮማርዮን ይመለከታል! የተጫዋቾቹ ስብስብ ውጥረትን እና ተስፋን ሰንቆ ወደ ሜማ
ዳ ገባ።
በተመሳሳይ 3 ጊዜ ዋንጫውን ያሸነፉት ቡድኖቹ አንድም ለማሸነፍ አንድም በሌላ ኃይል የታላቅነትን ስያሜ ላለመቀማት አላማ አንግበው ተሰደሩ!

ጨዋታው ተጀመረ!
አስቸጋሪው የአሜሪካ የአየር ፀባይ ከጨዋታው መደብዘዝ ጋር ታክሎ የደጋፊውን ስሜት በራድ አደረገው። ጨዋታው ጎል ጠፋበት ፤ ሙከራዎችም ቀዘቀዙ። የመጀመሪያው አጋማሽ 0-0 በሆነ ውጤት ተጠናቀቀ።
በሁለተኛው አጋማሽ በተመሳሳይ የውጤት ለውጥ መመልከት አልተቻለም። ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰአት አመራ። አሁንም ምንም ነገር ሊፈጠር አልቻለም። በመሆኑም የጨዋታው ሂደት ወደ ፍፁም ቅጣት ምት አቀና። በዓለም ዋንጫው ታሪክ የፍፃሜው ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ በፔናሊቲ ቁርጡን ሊያውቅ ተዘጋጀ።
ስታድየሙ በጭንቀት ታፍኗል። ሁሉም የራሱን መላምት ይሰነዝራል። ጨዋታው ባልጠበቁት መልኩ የሄደባቸው ጋዜጠኞች የአሸናፊውን ፍንጭ በማጣት በዝምት ቁልጭ ቁልጭ አሉ።
የፍፁም ቅጣት ምቱ መመታት ጀመረ። የጣልያን ተጫዋቾች በመሳት ዋንጫውን የሚያሸንፉ ይመስል በተደጋጋሚ ሳቱ! ፍራንኮ ባሬሲ ፣ ዳንኤሌ ማሳሮ አንገታቸውን ደፍተው ተመለሱ። ብራዚል በተደጋጋሚ በማስቆጠር ለዋንጫው ተጠጋች።
በዚህ ሰዓት ነበር ተስፋ ያጡት ደማቅ ሰማያውያን አንድያ ተስፋ ወደ ፊት ያመራው። ሮቤርቶ ባጅዮ ወደ ጎሉ ሲጠጋ ሁሉም በቅፅበት ረጭ አለ። ሀገሪቱን በማልያው የግራ ጠርዝ ብቻ ሳይሆን በትከሻው የተሸከመው ቁስለኛው ልዑል በቀስታ ተራመደ።
ሁሉም ለቅፅበት አንድ ትንፋሽ ሆኖ አይኑን ወደ እሱ ላከ! ሮቤርቶ ባጂዮዮዮዮዮ ተንደረደረረረረ! ሳተውውውውውው!
ማንም የሚሰማውንም ሆነ የሚያየውን አላመነም። ለደቂቃዎች ሁሉም ስሜቱ ተደበላለቀ። አንድ ለናቱ የሀነው ባጅዮ በሳተው ፔናሊቲ ብራዚል የዋንጫው አሸናፊ ሆነች!

ሁነቱን የማይረሳ ያደረገው ግን ፔናሊቲውን መሳቱ ብቻ አልነበረም ይልቅስ ከክስተቱ በኋላ ሮቤርቶ ሁለት እጆቹን ወገቡ ላይ አኑሮ ወደ መሬት እየተመለከተ የቆየባቸው የዝምታ ደቂቃዎች ናቸው እንጂ ። ይህ ምስል የሁሉንም ልብ አሸነፈ።
ከዋንጫው ባለቤቶች ጩኸት ይልቅ ሁሉም የሮቤርቶን የልብ ስብራት አዳመጠ። እንባ አይታይበትም ! ድምፅም አያወጣም! ነገር ግን ባዶነት እና ብቸኝነት የባጅዮ የዝምታ ቃላት ሆነው ታዩ ።
ዓለም ለደቂቃዎች በአርምሞ ቀዘቀዘች ።ለሀገሩ ነፍስያውን የሰጠው ጀብደኛ በተሰበረ ማንነት ገፁ ሲጠለሽ ሁሉም ተመለከተ። ያ በጣሊያን ሊጎች የደመቀው ባለፖኒቴል ከካሊፎርኒያ ሰማይ ስር ውስጡ ኩምሽሽ አለ።
ሲስተው እሩቅ እንደበረረው ኳስ ሁሉ የልዕሉም ተስፋ ከልቡ ከፍ ብሎ በረረ። ብራዚላውያን ደስታቸውን ያከብራሉ ። ካሜራው ግን ለቅፅበት ከሱ ላይ አልተነሳም ነበር። የሁሉንም ልብ የሰበረው የኳሱ መሳት አልነበረም ይልቅስ የሳቸው ልዕል ሰብዕ ማን እንደሆነ ማወቁ እንጂ።
በፍሎረንስ ሲደምቅ ፣ በአሮጊቷ ማልያ እሱነቱን ሲሆን ያዩት ያ ፈገግተኛ በጉልበቱ ተደፍቶ አለቀሰ። ዓለም ያ ፔናሊቲ መሳቱን ያስታውሳል ጣልያን ያንን ፔናሊቲ ለመምታት የቀረበችው በሱ ገድል እንደሆነ ግን ማን ትዝ ይለዋል?
ስብስቡን መርቶ ፍፃሜ ያደረሰው ጥበበኛ በእግሮቹ ቁስል ሳይመከት የተሸከማት ሀገር በባህር ስትሰምጥ መካተቻ ሆነ! ሁሉም ያንን ኳስ የሳተውን ባጅዮን እንጂ ጣልያንን በትዕንግርት ብቃቱ ለዛ ያበቃውን ቁስለኛውን ልዑል አያስብም ። እግር ኳስ እንዲህ ነውና!
ነገር ግን ባጅዮን ለዘመናት የሚገልፀው ቃል እንዲህ ይላል! እሱ ከምንግዜም ምርጥ ጣልያናውያን ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው!

❤4
❤14😁7👍2
ካይ ሃቨርዝ ከበርንሌይ ጋር ባደረገው ጨዋታ የለበሰው ማልያ በ26,700 ፓውንድ በጨረታ መሸጡ ተነግሯል።
በጨዋታው ብቸኛውን የማሸነፊያ ግብ ያስቆጠረው ሃቨርዝ ነበር።
SHARE | @FN_SPORTS
በጨዋታው ብቸኛውን የማሸነፊያ ግብ ያስቆጠረው ሃቨርዝ ነበር።
SHARE | @FN_SPORTS
❤17
በኢትዮጵያ የአለም ዋንጫውን የማስተላለፍ መብት ያገኘው የሃገሬ ቴሌቪዥን በአለም ዋንጫው በተንታኝነት የሚጠቀማቸውን ግለሰቦች ይፋ አድርጓል።
ያበደለት squad ነው።
SHARE | @FN_SPORTS
ያበደለት squad ነው።
SHARE | @FN_SPORTS
❤18
የነገውን ፍፃሜ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር መመልከት ይችላሉ።
ፕሮግራሙን ሱፐርስፖርትን(DSTV) ያዘጋጀው ሲሆን ኢንተርቪው መደረገን ጨምሮ በርከት ያሉ ፕሮግራሞች እንዳሉ ጋዜጠኛ ዮናስ አዘዘ ገልጾልናል።
SHARE | @FN_SPORTS
ፕሮግራሙን ሱፐርስፖርትን(DSTV) ያዘጋጀው ሲሆን ኢንተርቪው መደረገን ጨምሮ በርከት ያሉ ፕሮግራሞች እንዳሉ ጋዜጠኛ ዮናስ አዘዘ ገልጾልናል።
SHARE | @FN_SPORTS
❤11🔥1
TNT ከእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር የቀረበለትን ጥያቄ አልተቀበልም።
በዚህም የተነሳ በእንግሊዝ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በክፍያ ይተላለፋል።
SHARE | @FN_SPORTS
በዚህም የተነሳ በእንግሊዝ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በክፍያ ይተላለፋል።
SHARE | @FN_SPORTS
❤8
FN SPORTS በኢትዮጵያ™
ከ አምስት አመት በፊት ልክ በዚህች ቀን ቼልሲ ማንችስተር ሲቲን በማሸነፍ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን በታሪኩ ለሁለተኛ ጊዜ ማሸነፍ ቻለ። 🔥 SHARE | @FN_SPORTS
ከ 7 አመት ልክ በዛሬዋ ቀን ቼልሲ ጎረቤቱን አርሰናል በ አዘርባጃን ባኩ 4ለ1 ረምርሞ የአውሮፓ ሊግ ዋንጫን ለሁለተኛ ጊዜ ማሸነፍ ቻለ። 🏆
🔥9❤7🏆4😁2