FMC Sport ፋና ስፖርት
37.7K subscribers
46.8K photos
326 videos
20 files
17.8K links
This is Fana Media Corporation’s (FMC) Sport official Telegram channel.

For more updates please visit
https://fanamc.com/amharic/
Download Telegram
ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድርና የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 23ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድርና 19ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል፡፡

"የባህል ስፖርቶች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል ለአንድ ሳምንት በሀረር ከተማ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሕይወት መሐመድ በፍጻሜ መርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የባህል ስፖርቶች ውድድሮችና የባህል ፌስቲቫል ወንድማማችነትና እህትማማችነት የተረጋገጠበት ነው ብለዋል፡፡

በባህል ስፖርቶች ውድድር የኦሮሚያ ክልል በ61 ነጥቦች የአጠቃላይ ስፖርት ውድድሮች አሸናፊ ሆኗል።

በ19ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል ደግሞ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሸናፊ ሲሆን፥ ኦሮሚያና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመሆን አጠናቅቀዋል።

24ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድርና 20ኛው የባህል ፌስቲቫል በሲዳማ ክልል የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በተሾመ ኃይሉ
👎2
ነገሌ አርሲ አዳማ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ25ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ነገሌ አርሲ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የነገሌ አርሲን ግቦች ዳዊት ተፈራ እና ርሆቦት ሶላሎ አስቆጥረዋል፡፡

አዳማ ከተማን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ዳዋ ሆቴሳ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በሌላ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 እየመራ የመጀመሪያውን አጋማሽ አጠናቅቋል፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ በሚገኘው ጨዋታ ሀዋሳ ከተማን መሪ ያደረግቸውን ግብ ያሬድ ብሩክ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ሀዋሳ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ25ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ 2 አቻ ተለያይተዋል፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የሀዋሳ ከተማን ግቦች ያሬድ ብሩክ እና ሽመልስ በቀለ አስቆጥረዋል፡፡

የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ግቦችን ደግሞ ነፃነት ገ/መድህን እና ዳዊት ገብሩ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

አስቀድሞ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደ በሌላ የሊጉ ጨዋታ ነገሌ አርሲ አዳማ ከተማን 2 ለ 1 ማሸነፉ ይታወቃል፡፡
የፓሪስ ኦሎምፒክ ሻምፒዮኗ አትሌት ጋቢ በአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪክስ ውድድር ላይ እንደምትሳተፍ አሳወቀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፓሪስ ኦሎምፒክ 200 ሜትር ሻምፒዮኗ አትሌት ጋቢ ቶማስ በአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪክስ ውድድር ላይ እንደምትሳተፍ አሳውቃለች።

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምታስተናግደው የአንድ ቀን ዓለም አቀፍ ውድድር ሚያዚያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

በዚህ ውድድር ላይ አሜሪካዊቷ አትሌት ጋቢ ቶማስ እንደምትሳተፍ ተረጋግጧል፡፡

ጋቢ በፈረንጆቹ 2024 በፓሪስ ኦሎምፒክ በ200 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ስትሆን÷ ከቡድን አጋሮቿ ጋር ደግሞ የወርቅ ሜዳልያ ለሀገሯ ማስገኘቷ ይታወሳል።

አትሌቷ በቡዳፔስት የብር ሜዳልያ፣ በቶኪዮ ዓለም ሻምፒዮና ደግሞ የነሐስ ሜዳልያ አሸናፊ መሆኗ ይታወቃል፡፡
ሀሪ ማጓየር በማንቼስተር ዩናይትድ ውሉን አራዘመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዛዊው የተከላካይ ሥፍራ ተጫዋች ሀሪ ማጓየር በማንቼስተር ዩናይትድ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለመቆየት ውሉን አራዝሟል፡፡

ተጫዋቹ በዩናይትድ ቤት አስቀድሞ የነበረው ውል በመጪው ሰኔ ወር ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን፥ እስከ ፈረንጆቹ 2027 ለመቆየት ውሉን ማራዘሙ ነው የተገለጸው፡፡

በአዲሱ ውል ላይ ለተጨማሪ አንድ ዓመት የማራዘም አማራጭ ያለው አንቀጽ መካተቱም ተመላክቷል፡፡

እንግሊዛዊው ተጫዋች ሀሪ ማጓየር በፈረንጆቹ 2019 ከሌስተር ሲቲ በ80 ሚሊየን ዩሮ ማንቼስተር ዩናይትድን መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡

የ33 ዓመቱ ተጫዋች ለማንቼስተር ዩናይትድ 266 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን፥ ከክለቡ ጋር የኤፍ ኤ እና የካራባኦ ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡
አሮን ራምሴ ራሱን ከእግር ኳስ ዓለም አገለለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች አሮን ራምሴ ራሱን ከእግር ኳስ ዓለም ማግለሉን ይፋ አድርጓል።

በሜክሲኮው ፑማስ ክለብ እየተጫወተ የነበረው ራምሴ በ35 ዓመቱ ጫማውን ሰቅሏል።

ተጫዋቹ ለአርሰናል፣ ጁቬንቱስ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት፣ ካርዲፍ ሲቲ እና ሬንጀርስን ለመሳሰሉ ክለቦች ተጫውቷል።

ራምሴ ከአርሰናል ጋር የኤፍ ኤ እና የኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫዎችን አሳክቷል።

ከጣሊያኑ ክለብ ጁቬንቱስ ጋር ደግሞ የጣሊያን ሴሪ አ እና ኮፓ ኢታሊያ ዋንጫዎችን ማሳካቱ ይታወሳል።
የማራቶን ውድድር ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሊቀነስ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከፈረንጆቹ 2030 ጀምሮ ማራቶን ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ውጪ እንደሚሆን የዓለም አትሌቲክስ ይፋ አድርጓል፡፡

ማራቶን በፈረንጆቹ 2027 እና 2029 በሚካሄዱት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የውድድሩ አካል ሆኖ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ከፈረንጆቹ 2030 ጀምሮ ማራቶን ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር እንደሚወጣ ነው የተገለጸው፡፡

የዓለም አትሌቲክስ አዲስ ዓመታዊ የአትሌቲክስ ውድድር እንደሚያዘጋጅ ተጠቁሟል፡፡

በዚህም በፈረንጆቹ 2030 የዓለም አትሌቲክስ ማራቶን ሻምፒዮና የሚል ራሱን የቻለ ውድድር እንደሚጀመር ተመላክቷል፡፡

በፈረንጆቹ 2030 የሚጀምረው አዲሱ የዓለም አትሌቲክስ ማራቶን ሻምፒዮና በየአመቱ የሚካሄድ ሲሆን፥ የመጀመሪያውን ውድድር አቴንስ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡
የሪያል ማድሪድ እና ባየርን ሙኒክ አሰላለፍ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ተጠባቂ ጨዋታዎች አሰላለፍ ይፋ ሆኗል፡፡

በዚህም ሪያል ማድሪድ አንድሬ ሉኒን፣ ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ፣ አንቶኒዮ ሩዲገር፣ ዲን ሁጅሰን፣ አልቫሮ ካሬራስ፣ ፌዴሪኮ ቫልቬርዴ፣ ቲያጎ፣ ቹሀሚኒ፣ አርዳ ጉለር፣ ኪሊያን ምባፔ እና ቪኒሸስ ጁኒየርን በመጀመሪያው አሰላለፍ ውስጥ አካትቷል፡፡

ባየርን ሙኒክ በኩል ማኑኤል ኑየር፣ ኡፓሜካኖ፣ ታህ፣ ኪሚቺ፣ ናብሪ፣ ሀሪኬን፣ ዲያዝ፣ ኦሊሴ፣ ላይመር፣ ስታኒሲች እና ፓቭሎቪች በቋሚነት የሚጀምሩ ይሆናል፡፡

በሌላኛው የምሽቱ ጨዋታ ደግሞ ዴቪድ ራያ፣ ቤንዋይት፣ ሳሊባ፣ ጋብሬል ማጋሌሽ፣ ካላፊዮሪ፣ ዙቢሜንዲ፣ ራይስ፣ ኦዴጋርድ፣ ማዱኬ፣ ትሮሳርድ እና ዮኬሬሽ ስፖርቲንግን በሚገጥመው የአርሰናል የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ ተካትተዋል፡፡

ተጋጣሚው ስፖርቲንግ ሊዝበን በበኩሉ ሩሂ ሲልቫ፣ ኢናሲዮ፣ ዳይሞንዴ፣ ፍሬስኔዳ፣ አራሆ፣ ሲሞስ፣ ሞሪታ፣ ትሪንካሆ፣ ካታሞ፣ ፖቴ እና ሰዋሬዝን በመጀመሪያው አሰላለፍ ይዞ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡

ሁለቱም የሩብ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ላይ መደረግ ይጀምራሉ፡፡
👍5
ባየርን ሙኒክ ሪያል ማድሪድን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ባየርን ሙኒክ ሪያል ማድሪድን 2 ለ 1 አሸንፏል።

የባየርን ሙኒክን የማሸነፊያ ግቦች ሉዊስ ዲያዝ እና ሀሪኬን አስቆጥረዋል።

ሪያል ማድሪድን ከሸንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ኪሊያን ምባፔ ከመረብ አሳርፏል።

በሌላ ጨዋታ አርሰናል ስፖርቲንግ ሊዝበንን 1 ለ 0 አሸንፏል።

የአርሰናልን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ካይ ሀቨርትዝ በሁለተኛው አጋማሽ አስቆጥሯል።
👏6👍2