ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው በሊድስ ዩናይትድ ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሊድስ ዩናይትድ ማንቼስተር ዩናይትድን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በኦልድትራፎርድ በተካሄደው ጨዋታ የሊድስ ዩናይትድን ሁለቱንም የማሸነፊያ ግቦች ኦካፎር አስቆጥሯል።
ማንቼስተር ዩናይትድን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ግብ ካስሚሮ ከመረብ አሳርፏል።
በጨዋታው የማንቼስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

👍3
ሊቨርፑል ከፒኤስጂ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት መደረግ ይጀምራሉ፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሮድ የፈረንሳዩን ክለብ ፒኤስጂን ያስተናግዳል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች በፓርክ ደ ፕሪንስ ያደረጉትን የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ፒኤስጂ 2 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
ሊቨርፑል ዛሬ ምሽት በሜዳው በሚያደርገው ጨዋታ ውጤቱን ቀልብሶ ግማሽ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የአምና የመድረኩ አሸናፊ ፒኤስጂ በበኩሉ ውጤቱን አስጠብቆ ቀጣዩን ዙር ለመቀላቀል የሚያደርገው ፍልሚያ ተጠባቂ ነው፡፡
በ2024/25 የውድድር ዓመት በ16ቱ ጥሎ ማለፍ ተገናኝተው ፒኤስጂ ሊቨርፑልን ከውድድሩ ውጪ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ፒኤስጂ ሦስቱን ሲያሸንፍ ሊቨርፑል በሁለቱ ድል አድርጓል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት አትሌቲኮ ማድሪድ በሜዳው ዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ከባርሴሎና ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
የመጀመሪያውን ዙር የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድ 2 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ባርሴሎና ሦስቱን ሲያሸንፍ አትሌቲኮ ማድሪድ በሁለቱ ድል አድርጓል፡፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ቀን 7 ሰዓት ላይ አዳማ ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም ቀን 10 ላይ ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ ቡና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ደግሞ ቀን 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና እንዲሁም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ወላይታ ድቻ ከፋሲል ከነማ ይገናኛሉ፡፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዳማ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዳማ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ቀን 7 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የኢትዮ ኤሌክትሪክን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ያሬድ የማነ አስቆጥሯል፡፡
በዚሁ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ ቡና ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የሲዳማ ቡናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አቤል ያለው አስቆጥሯል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል በተመሳሳይ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ወላይታ ድቻ ከፋሲል ከነማ ይገናኛሉ፡፡
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ቀን 7 ሰዓት ላይ አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዳማ ከተማን 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወቃል፡፡
በዚሁ ስታዲየም ቀን 10 ላይ መደረግ በጀመረው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 እየመራ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናን የመሪነት ግቦች ዘላለም አባተ እና ራምኬል ጀምስ ሲያስቆጥሩ የሀድያ ሆሳዕናን ግብ ደግሞ ኢዮብ ዓለማየሁ ከመረብ አሳርፏል፡፡

👎1
ፋሲል ከነማ ወላይታ ድቻን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ወላይታ ድቻን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የፋሲል ከነማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ታምራት ኢያሱ አስቆጥሯል፡፡
በተመሳሳይ ስታዲየም አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በአቤል ያለው ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወቃል፡፡
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረጉ በሌሎች የሊጉ ጨዋታዎች ኢትዮ ኤሌክትሪክ አዳማ ከተማን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናን ግቦች ዘላለም አባተ እና ራምኬል ጀምስ ሲያስቆጥሩ የሀድያ ሆሳዕናን ግቦች ደግሞ ኢዮብ ዓለማየሁ እና ብሩክ በየነ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ሊቨርፑል እና ባርሴሎና ከአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሰናበቱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ተደርገዋል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሮድ የፈረንሳዩን ክለብ ፒኤስጂን አስተናግዶ 2 ለ 0 ተሸንፏል።
በዚህም ቡድኖቹ በፓርክ ደ ፕሪንስ ያደረጉትን የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ፒኤስጂ 2 ለ 0 በማሸነፉ በድምር ውጤት 4 ለ 0 በመርታት ወደ ግማሽ ፍጻሜ ገብቷል።
በተመሳሳይ ሰዓት አትሌቲኮ ማድሪድ በሜዳው ዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ከባርሴሎና ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 1 ቢሸነፍም፤ የመጀመሪያውን ዙር የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ 2 ለ 0 በማሸነፉ በድምር ውጤት 3 ለ 2 አሸንፎ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።