ብራዚላዊው የማንቼስተር ዩናይትድ ኮከብ ካስሚሮ…
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማንቼስተር ዩናይትድ ቤት ምርጥ ብቃታቸውን እያሳዩ ከሚገኙ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው ብራዚላዊው ተጫዋች ካስሚሮ፡፡
የእግር ኳስ ሕይወቱን በሀገሩ ክለብ ሳኦፖሎ የጀመረው ካስሚሮ የቡድኑን ሚዛን በመጠበቅ ችሎታው ይታወቃል፡፡
በወቅቱ በተከላካይ አማካይ ስፍራ ላይ ባሳየው ድንቅ እንቅስቃሴ የሪያል ማድሪድን ቀልብ የሳበ ሲሆን÷ በ2013 ሎስብላንኮቹን መቀላቀል ችሏል፡፡
ካስሚሮ ሪያል ማድሪድን ከተቀላቀለ በኋላ በዋናው ቡድን ውስጥ የመጫወት ዕድል ባለማግኘቱ በውሰት ለፖርቶ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
በፖርቶ ቆይታው ካስሚሮ አስደናቂ እንቅስቃሴ በማድረግ ቡድኑን በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ለሩብ ፍፃሜ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡
ካስሚሮ በፖርቶ ባሳየው ምርጥ ብቃት ሪያል ማድሪድ በ2015 ተጫዋቹን ወደ ሳንቲያጎ ቤርናባው መልሶ አምጥቶታል፡፡
ካስሚሮ ወደ ክለቡ ከተመለሰ በኋላ ለሪያል ማድሪድ ስኬት ወሳኝ ሚና በመጫወት ዓለም ላይ ካሉ ምርጥ የተከላካይ አማካዮች አንዱ መሆን ችሏል፡፡
ብራዚላዊው ተጫዋች በሪያል ማድሪድ በነበረው ቆይታ አምስት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ፣ የስፔን ላሊጋ፣ የዓለም ክለቦች፣ የኮፓ ዴል ሬይን ጨምሮ የተለያዩ ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡
በሪያል ማድሪድ ቤት በቆየባቸው ዓመታት ከክሮሺያዊው ሉካ ሞድሪች እና ከጀርመናዊው ቶኒ ክሩስ ጋር የነበረው ጥምረት አስደናቂ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በሦስቱ ተጫዋቾች አስገራሚ ጥምረት የሪያል ማድሪድ የመሀል ሜዳ ክፍል ለዓመታት አስፈሪ ሆኖ መቆየት... 👇
https://web.facebook.com/fanasport/posts/pfbid02CXDLZHsvh1kdENwrbC3DYV1Ep67H1u27QqKhDpMBUWMEeBCQhyyMHpLvG8Tdp4tNl

ማንቼስተር ዩናይትድ ከኤቨርተን
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኤቨርተን በሜዳው ምሽት 5 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡
ከአራት ተከታታይ ድል በኋላ የአቻ ውጤት ያስመዘገበው ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ድል ለመመለስ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ሁለቱን ሲያሸንፍ ኤቨርተን በአንዱ ድል አድርጎ በሁለቱ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ማንቼስተር ዩናይትድ የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ነጥቡን ወደ 48 ከፍ በማድረግ 4ኛ ደረጃን ከቼልሲ የሚረከብ ይሆናል፡፡

መቐለ 70 እንደርታ ምድረ ገነት ሽረን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር መቐለ 70 እንደርታ ምድረ ገነት ሽረን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ቀን 10 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የመቐለ 70 እንደርታን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ስንታየሁ መንግሥቱ አስቆጥሯል፡፡

በሜክሲኮ ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሜክሲኮ ጓዋዳላሀራ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በወንዶች ግማሽ ማራቶን አትሌት ገመቹ ዲዳ ርቀቱን 1 ሰዓት 3 ደቂቃ ከ38 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆኗል፡፡
በሴቶች ምድብ ደግሞ ኮሎሌ መካሹ 1 ሰዓት 12 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቅቃለች፡፡

👍4😢1
በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ 16ቱን ለመቀላቀል የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ፡፡
ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ አትሌቲኮ ማድሪድ በሜዳው ክለብ ብሩዥን ያስተናግዳል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ሦስት አቻ በሆነ ውጤት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል፡፡
ምሽት 5 ሰዓት ላይ የጣሊያኑ ክለብ ኢንተር ሚላን በጁሴፔ ሜዛ ከቦዶ ግሊምት ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
ኢንተር ሚላን ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ባደረገው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ በቦዶ ግሊምት 3 ለ 1 መሸነፉ አይዘነጋም፡፡
በዚህም የአምና መድረኩ የፍጻሜ ተፋላሚ ኢንተርሚላን 16ቱን ለመቀላቀል በሚያደርገው ጉዞ ዛሬ ምሽት ትልቅ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡
በሌላ ጨዋታ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ኒውካስል ዩናይትድ ከካራባግ እንዲሁም ባየር ሊቨርኩሰን ከኦሎምፒያኮስ ይገናኛሉ፡፡

👍4
በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ወደ 16ቱ ለመግባት አራት የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ።
በመልስ ጨዋታዎች ቤነፊካን በመጀመሪያው ዙር 1 ለ 0 ያሸነፈው ሪያል ማድሪድ በቤርናቦው ምሽት 5 ሰዓት ላይ የመልሱን ጨዋታ ያደርጋል።
በተመሳሳይ ሰዓት ሞናኮን ከሜዳው ውጪ 3 ለ 2 ያሸነፈው ፒኤስጂ የመልሱን ጨዋታ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ሲያካሂድ፤ በጋላታሳራይ የ5 ለ 2 ሽንፈት የገጠመው ጁቬንቱስ ውጤቱን ለመቀየር በሜዳው ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል።
ከዚህ ቀደም ብሎ ደግሞ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ በመጀመሪያ ዙር ጨዋታ በዶርትሙንድ የ2 ለ 0 ሽንፈት የገጠመው አታላንታ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ወደ 16 ውስጥ ለመቀላቀል ይጫወታል።
ትናንት ምሽት በተደረጉ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የመልስ ጨዋታዎች 4 ቡድኖች ወደ 16ቱ መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።
በዚህም ባየር ሊቨርኩሰን ኦሎምፒያኮስን 2 ለ 0፣ ቦዶ ግሊሚት ኢንተር ሚላንን 5 ለ 2፣ ኒውካስል ዩናይትድ ካራባግን 9 ለ 3 እንዲሁም አትሌቲኮ ማድሪድ ክለብ ብሩዥን 7 ለ 4 በሆነ ድምር ውጤት በማሸነፍ ወደ 16ቱ ተቀላቅለዋል።

ኢትዮጵያ መድን ቅዱስ ጊዮርጊስን 3 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ21ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ቅዱስ ጊዮርጊስን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ የኢትጵያ መድንን የአሸናፊነት ግቦች ብሩክ ሙሉጌታ (ሁለት) እና ብሩክ በላቸው ከመረብ አሳርፈዋል።

👍4😢3
በሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ21ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አዳማ ከተማ ከሸገር ከተማ እንዲሁም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ነገሌ አርሲ ከኢትዮጵያ ቡና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ደግሞ ቀን 9 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከወላይታ ድቻ እንዲሁም ምሽት 12 ሰዓት ላይ መቻል ከመቐለ 70 እንደርታ ይገናኛሉ፡፡

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የስፔኑ ክለብ አልሜሪያ የባለቤትነት ድርሻ ገዛ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፖርቹጋላዊው የአልናስር ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የስፔኑ ክለብ አልሜሪያ ድርሻ ባለቤት ሆኗል፡፡
የአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው የአልሜሪያን 25 በመቶ ድርሻ መግዛቱ ነው የተገለጸው፡፡
አልሜሪያ በስፔን ሁለተኛ ሊግ እየተወዳደረ ሲሆን በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ሦስተኛ ላይ ተቀምጧል።
ሮናልዶ የክለቡ የድርሻ ባለቤት ከሆነ በኋላ ሜዳ ላይ ከመጫወት ባለፈ ለእግር ኳስ የበኩሌን አስተዋፅኦ ለማድረግ የረዥም ጊዜ ምኞት ነበረኝ ብሏል፡፡
በተጨማሪም አልሜሪያ ጠንካራ መሰረት ያለው የስፔን ክለብ ነው ያለው ሮናልዶ ከክለቡ አመራሮች ጋር በጋራ ለመስራት መጓጓቱን ተናግሯል፡፡

👍4👏4
ወላይታ ድቻ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ21ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የወላይታ ድቻን የማሸነፊያ ሁለት ግቦች ካርሎስ ዳምጠው አስቆጥሯል፡፡
በዚሁ ስታዲየም የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ መቻል ከመቐለ 70 እንደርታ ይገናኛሉ፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ በሌላ የሊጉ ጨዋታ አዳማ ከተማ እና ሸገር ከተማ 3 አቻ ተለያይተዋል፡፡
የአዳማ ከተማን ግቦች አህመድ ሁሴን እና አላዛር ሽመልስ (ሁለት) ሲያስቆጥሩ የሸገር ከተማን ግቦች ደግሞ ቢኒያም ፍቅሩ፣ ጀቤሳ ምኤሳ እና ሔኖክ አዱኛ (በፍጹም ቅጣት ምት)ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
በዚሁ ስታዲየም የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ነገሌ አርሲ ከኢትዮጵያ ቡና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

🙏3😢1
ኢትዮጵያ ቡና ነጌሌ አርሲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ21ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ነጌሌ አርሲን 1 ለ 0 አሸንፏል።
አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡናን ማሸነፊያ ግብ ራምኬል ጄምስ (ፍ) ከመረብ አሳርፏል።
በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተደረገው የመቻል እና መቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ተጠናቅቋል።
ቀደም ሲል በተደረገው የሊጉ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ አዳማ ከተማ እና ሸገር ከተማ 3 አቻ ተለያይተዋል፡፡