FMC Sport ፋና ስፖርት
37.7K subscribers
46.7K photos
326 videos
20 files
17.8K links
This is Fana Media Corporation’s (FMC) Sport official Telegram channel.

For more updates please visit
https://fanamc.com/amharic/
Download Telegram
ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አቻ ተለያዩ።

ሁለቱ ቡድኖች አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ነው የተለያዩት።

በተመሳሳይ ሰዓት ሸገር ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ተለያይተዋል፡፡

ቀደም ሲል ቀን 9 ሰዓት በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች አርባምንጭ ከተማ እና ነጌሌ አርሲ 1 አቻ ሲለያዩ÷ ሐዋሳ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ በተመሳሳይ ውጤት 1 አቻ መለያየታቸው ይታወሳል።
ቶተንሃም ከአርሰናል የመጀመሪያ አጋማሽ...

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የቶተንሃም እና አርሰናል የመጀመርያው አጋማሽ ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።

በጨዋታው የአርሰናልን ግብ ኤበሪቼ ኤዜ ከመረብ ሲያሳርፍ ኮሎ አሙኒ የቶተንሃምን ግብ አስቆጥሯል።
አርሰናል ቶተንሃምን 4 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አርሰናል ቶተንሃም ሆትስፐርን 4 ለ 1 አሸንፏል

በመጀመርያው አጋማሽ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ወደ እረፍት ያመራው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአርሰናል አሸናፊነት ተጠናቅቋል።

በጨዋታው የአርሰናልን ግቦች ኤቤሪቼ ኤዜ (2) እና ዮኬሬሽ (2) አስቆጥረዋል።

ኮሎ ሙአኒ የቶተንሃምን ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል።
👍20
ብራዚላዊው የማንቼስተር ዩናይትድ ኮከብ ካስሚሮ…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማንቼስተር ዩናይትድ ቤት ምርጥ ብቃታቸውን እያሳዩ ከሚገኙ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው ብራዚላዊው ተጫዋች ካስሚሮ፡፡

የእግር ኳስ ሕይወቱን በሀገሩ ክለብ ሳኦፖሎ የጀመረው ካስሚሮ የቡድኑን ሚዛን በመጠበቅ ችሎታው ይታወቃል፡፡

በወቅቱ በተከላካይ አማካይ ስፍራ ላይ ባሳየው ድንቅ እንቅስቃሴ የሪያል ማድሪድን ቀልብ የሳበ ሲሆን÷ በ2013 ሎስብላንኮቹን መቀላቀል ችሏል፡፡

ካስሚሮ ሪያል ማድሪድን ከተቀላቀለ በኋላ በዋናው ቡድን ውስጥ የመጫወት ዕድል ባለማግኘቱ በውሰት ለፖርቶ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

በፖርቶ ቆይታው ካስሚሮ አስደናቂ እንቅስቃሴ በማድረግ ቡድኑን በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ለሩብ ፍፃሜ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡

ካስሚሮ በፖርቶ ባሳየው ምርጥ ብቃት ሪያል ማድሪድ በ2015 ተጫዋቹን ወደ ሳንቲያጎ ቤርናባው መልሶ አምጥቶታል፡፡

ካስሚሮ ወደ ክለቡ ከተመለሰ በኋላ ለሪያል ማድሪድ ስኬት ወሳኝ ሚና በመጫወት ዓለም ላይ ካሉ ምርጥ የተከላካይ አማካዮች አንዱ መሆን ችሏል፡፡

ብራዚላዊው ተጫዋች በሪያል ማድሪድ በነበረው ቆይታ አምስት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ፣ የስፔን ላሊጋ፣ የዓለም ክለቦች፣ የኮፓ ዴል ሬይን ጨምሮ የተለያዩ ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡

በሪያል ማድሪድ ቤት በቆየባቸው ዓመታት ከክሮሺያዊው ሉካ ሞድሪች እና ከጀርመናዊው ቶኒ ክሩስ ጋር የነበረው ጥምረት አስደናቂ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በሦስቱ ተጫዋቾች አስገራሚ ጥምረት የሪያል ማድሪድ የመሀል ሜዳ ክፍል ለዓመታት አስፈሪ ሆኖ መቆየት... 👇
https://web.facebook.com/fanasport/posts/pfbid02CXDLZHsvh1kdENwrbC3DYV1Ep67H1u27QqKhDpMBUWMEeBCQhyyMHpLvG8Tdp4tNl
ማንቼስተር ዩናይትድ ከኤቨርተን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኤቨርተን በሜዳው ምሽት 5 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡

ከአራት ተከታታይ ድል በኋላ የአቻ ውጤት ያስመዘገበው ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ድል ለመመለስ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ሁለቱን ሲያሸንፍ ኤቨርተን በአንዱ ድል አድርጎ በሁለቱ አቻ ተለያይተዋል፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድ የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ነጥቡን ወደ 48 ከፍ በማድረግ 4ኛ ደረጃን ከቼልሲ የሚረከብ ይሆናል፡፡
መቐለ 70 እንደርታ ምድረ ገነት ሽረን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር መቐለ 70 እንደርታ ምድረ ገነት ሽረን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ቀን 10 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የመቐለ 70 እንደርታን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ስንታየሁ መንግሥቱ አስቆጥሯል፡፡
በሜክሲኮ ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሜክሲኮ ጓዋዳላሀራ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በወንዶች ግማሽ ማራቶን አትሌት ገመቹ ዲዳ ርቀቱን 1 ሰዓት 3 ደቂቃ ከ38 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆኗል፡፡

በሴቶች ምድብ ደግሞ ኮሎሌ መካሹ 1 ሰዓት 12 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቅቃለች፡፡
👍4😢1
ማንቼስተር ዩናይትድ  ኤቨርተንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሜዳው ውጪ የተጫወተው ማንቼስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡


ቤንጃሚን ሼሽኮ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ድል ያደረገው ማንቼስተር ዩናይትድ ነጥቡን 48 በማድረስ በሊጉ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
👍12
በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ 16ቱን ለመቀላቀል የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ፡፡

ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ አትሌቲኮ ማድሪድ በሜዳው ክለብ ብሩዥን ያስተናግዳል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ሦስት አቻ በሆነ ውጤት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል፡፡

ምሽት 5 ሰዓት ላይ የጣሊያኑ ክለብ ኢንተር ሚላን በጁሴፔ ሜዛ ከቦዶ ግሊምት ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

ኢንተር ሚላን ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ባደረገው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ በቦዶ ግሊምት 3 ለ 1 መሸነፉ አይዘነጋም፡፡

በዚህም የአምና መድረኩ የፍጻሜ ተፋላሚ ኢንተርሚላን 16ቱን ለመቀላቀል በሚያደርገው ጉዞ ዛሬ ምሽት ትልቅ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡

በሌላ ጨዋታ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ኒውካስል ዩናይትድ ከካራባግ እንዲሁም ባየር ሊቨርኩሰን ከኦሎምፒያኮስ ይገናኛሉ፡፡
👍4
በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ወደ 16ቱ ለመግባት አራት የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ።

በመልስ ጨዋታዎች ቤነፊካን በመጀመሪያው ዙር 1 ለ 0 ያሸነፈው ሪያል ማድሪድ በቤርናቦው ምሽት 5 ሰዓት ላይ የመልሱን ጨዋታ ያደርጋል።

በተመሳሳይ ሰዓት ሞናኮን ከሜዳው ውጪ 3 ለ 2 ያሸነፈው ፒኤስጂ የመልሱን ጨዋታ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ሲያካሂድ፤ በጋላታሳራይ የ5 ለ 2 ሽንፈት የገጠመው ጁቬንቱስ ውጤቱን ለመቀየር በሜዳው ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል።

ከዚህ ቀደም ብሎ ደግሞ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ በመጀመሪያ ዙር ጨዋታ በዶርትሙንድ የ2 ለ 0 ሽንፈት የገጠመው አታላንታ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ወደ 16 ውስጥ ለመቀላቀል ይጫወታል።

ትናንት ምሽት በተደረጉ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የመልስ ጨዋታዎች 4 ቡድኖች ወደ 16ቱ መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።

በዚህም ባየር ሊቨርኩሰን ኦሎምፒያኮስን 2 ለ 0፣ ቦዶ ግሊሚት ኢንተር ሚላንን 5 ለ 2፣ ኒውካስል ዩናይትድ ካራባግን 9 ለ 3 እንዲሁም አትሌቲኮ ማድሪድ ክለብ ብሩዥን 7 ለ 4 በሆነ ድምር ውጤት በማሸነፍ ወደ 16ቱ ተቀላቅለዋል።
ኢትዮጵያ መድን ቅዱስ ጊዮርጊስን 3 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ21ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ቅዱስ ጊዮርጊስን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ቀን 10 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ የኢትጵያ መድንን የአሸናፊነት ግቦች ብሩክ ሙሉጌታ (ሁለት) እና ብሩክ በላቸው ከመረብ አሳርፈዋል።
👍4😢3
በሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ21ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አዳማ ከተማ ከሸገር ከተማ እንዲሁም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ነገሌ አርሲ ከኢትዮጵያ ቡና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ደግሞ ቀን 9 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከወላይታ ድቻ እንዲሁም ምሽት 12 ሰዓት ላይ መቻል ከመቐለ 70 እንደርታ ይገናኛሉ፡፡