FMC Sport ፋና ስፖርት
37.8K subscribers
46.7K photos
326 videos
20 files
17.8K links
This is Fana Media Corporation’s (FMC) Sport official Telegram channel.

For more updates please visit
https://fanamc.com/amharic/
Download Telegram
አርሰናል ከዎልቭስ ጋር አቻ ተለያየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከሜዳው ውጭ ከዎልቭስ ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 2 አቻ ተለያይቷል።

የሊጉ መሪ አርሰናል በቡካዮ ሳካ እና ሂንካፒ ግቦች 2 ለ ዐ ሲመራ ቢቆይም፥ በሊጉ መጨረሻ ደረጃ ላይ ለሚገኘው ዎልቭስ ቡዪኖ እና ካላፊዮሪ (በራሱ ላይ) ባስቆጠሯቸው ግቦች ሁለቱ ቡድኖች ነጥብ ተጋርተዋል።

ውጤቱን ተከትሎ 27 ጨዋታዎችን ያደረገው አርሰናል በ58 ነጥብ ሊጉን ሲመራ፥ 26 ጨዋታዎችን ያደረገው ማንቼስተር ሲቲ በ5 ነጥብ ልዩነት ይከተላል።
🙏10👎3
ወላይታ ድቻ መቻልን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወላይታ ድቻ መቻልን 4 ለ 3 አሸንፏል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የወላይታ ድቻን የማሸነፊያ ግቦች ቴዎድሮስ ሀይለማሪያም፣ ካርሎስ ዳምጠው እና ዮናታን ኤልያስ (2) አስቆጥረዋል፡፡

መቻልን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦችን ቸርነት ጉግሳ(2) እና በረከት ደስታ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ በሌላ የሊጉ ጨዋታ ባህርዳር ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

የባህርዳር ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ግርማ ዲሳሳ (በፍጹም ቅጣት ምት) አስቆጥሯል፡፡

የሊጉ ጨዋታዎች ሲቀጥሉ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፋሲል ከነማ እንዲሁም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ኢትዮጵያ መድን ከአዳማ ከተማ በተመሳሳይ አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ አዲስ ታሪክ የጻፈው ጀምስ ሚልነር…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብራይተኑ ተጫዋች ጀምስ ሚልነር በፕሪሚየር ሊጉ ብዙ ጨዋታዎችን ያደረገ ተጫዋች በሚል በሊጉ የታሪክ መዝገብ ስሙን አስፍሯል፡፡

ሚልነር በአሁኑ ሰዓት ክለቡ ብራይተን ከብሬንትፎርድ ጋር እያደረገው በሚገኘው የ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ በቋሚነት በመሰለፍ 654ኛ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታውን አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት የ40 ዓመቱ እንግሊዛዊ የዛሬውን ጨዋታ ጨምሮ በብራይተን፣ ማንቼስተር ሲቲ፣ ሊቨርፑል፣ ኒውካስል ዩናይትድ፣ አስቶን ቪላ እና ሊድስ ዩናይትድ በአጠቃላይ በ654 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡

ይህን ተከትሎም በሊጉ 653 ጨዋታዎችን በማድረግ ቀዳሚ የነበረውን የቀድሞ የማንቼስተር ሲቲ፣ አስቶን ቪላ እና ዌስትብሮሚች ተጫዋች ጋሪዝ ባሪ ክብረወሰን በመብለጥ አዲስ ታሪክ ጽፏል፡፡

በፈረንጆቹ 2002 የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታውን በ16 ዓመቱ ለሊድስ ዩናይትድ ያደረገ ሲሆን፥ በወቅቱ በሊጉ መሰለፍ የቻለ 2ኛው በእድሜ ትንሹ ተጫዋች ነበር፡፡

ከሊቨርፑል ጋር አንድ የሻምፒየንስ ሊግ እና አንድ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ያሳካው ጀምስ ሚልነር ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ሁለት ጊዜ የሊጉ ባለክብር መሆን ችሏል፡፡

ጀምስ ሚልነር 27ኛ ሳምንቱ ላይ በሚገኘው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጨማሪ ጨዋታዎችን በማድረግ ቁጥሩን ከዚህም ከፍ የማድረግ እድል አለው፡፡

የቀድሞው የማንቼስተር ዩናይትድ ተጫዋች ሪያን ጊግስ (632) እንዲሁም ፍራንክ ላምፓርድ (609) በሊጉ በርካታ ጨዋታዎችን በማድረግ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡

በኃይለማርያም ተገኝ
ቼልሲ እና በርንሌይ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቼልሲ እና በርንሌይ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡

የቼልሲን ግብ ጇ ፔድሮ በመጀመሪያው አጋማሽ ሲያስቆጥር ፍሌሚንግ የበርንሌይን የአቻነት ግብ በመጨረሻ ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በሌላ የሊጉ ጨዋታዎች ብራይተን ብሬንትፎርድን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ አስቶንቪላ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር 1 አቻ ተለያይቷል፡፡

የሊጉ ጨዋታዎች ሲቀጥሉ ምሽት 2 ሰዓት 30 ላይ ዌስትሃም ዩናይትድ ከቦርንማውዝ እንዲሁም ምሽት 5 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ሲቲ ከኒውካስል ዩናይትድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲል ከነማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲል ከነማን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ምሽት 12 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች ሲሞን ፒተር፣ ሁዘይፋ ሻፊ እና ሳምሶን ቹቹ አስቆጥረዋል፡፡

ፋሲል ከነማን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ታምራት እያሱ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ በሌላ የሊጉ ጨዋታ አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

የአዳማ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ቢንያም አይተን (በፍጹም ቅጣት ምት) ከመረብ አሳርፏል፡፡

አስቀድሞ በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ወላይታ ድቻ መቻልን 4 ለ 3 እንዲሁም ባህርዳር ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወቃል፡፡
‎ማንቼስተር ሲቲ ከኒውካስል ዩናይትድ - የጨዋታ አሰላለፍ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት ላይ በሜዳው ኒውካስል ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡

ሲቲ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ለማጥበብ ወደ ሜዳ የሚገባ ሲሆን፥ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቋሚ አሰላለፋቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

በዚህም መሰረት ዶናሩማ፣ አይት-ኑሪ፣ ጉሂ፣ ሩበን ዲያዝ፣ ማታያስ ኑኔዝ፣ ኒኮ ኦሬሊ፣ ሮድሪ፣ በርናርዶ ሲልቫ፣ አንቱዋን ሴሜንዮ፣ ማርሙሽ እና ሃላንድ በቋሚ አሰላለፍ ወደ ሜዳ ይገባሉ፡፡

በእንግዳው ቡድን ኒውካስል ዩናይትድ በኩል ኒክ ፖፕ፣ ትሪፒየር፣ ቲያው፣ በርን፣ ሀል፣ ዊሎክ፣ ቶናሊ፣ ጃኮብ ራምሴ፣ ኤላንጋ፣ ቮልትማደ እና ጎርደን በመጀመሪያው አሰላለፍ የተካተቱ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
👍6
አርባምንጭ ከተማ እና ነጌሌ አርሲ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር አርባምንጭ ከተማ እና ነጌሌ አርሲ አቻ ተለያይተዋል።

ቀን 9 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተካሄደው የአርባምንጭ ከተማ እና ነጌሌ አርሲ ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል።

በጨዋታው የነጌሌ አርሲን ግብ በመጀመሪያው አጋማሽ ዳዊት ተፈራ ሲያስቆጥር በፍቅር ግዛቸው ለአርባምንጭ ከተማ የአቻነቷን ግብ ከመረብ አሳርፏል።

በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው የሐዋሳ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።

የሐዋሳ ከተማን ግብ ሽመልስ በቀለ ሲያስቆጥር የድሬዳዋ ከተማን ግብ ደግሞ ድልአዲስ ገብሬ ከመረብ አሳርፏል።

የሊጉ መርሐ ግብር ቀጥለው ሲደረጉ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ ሸገር ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ይገናኛል።

እንዲሁም በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ሊቨርፑል ኖቲንግሃምን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታ ሊቨርፑል ኖቲንግሃም ፎረስትን አሸንፏል።

አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ሊቨርፑል 1 ለ 0 ነው ያሸነፈው።

የጨዋታው ሙሉ ጊዜ ተጠናቅቆ በተጨመረ የባከነ ደቂቃ ላይ አሌክሲስ ማካልስተር የማሸነፊያ ግቧን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ ወልቭስን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ኢቫን ጉሳንድ የማሸነፊያ ግቧን ከመረብ አሳርፏል።

እንዲሁም ፉልሃምን ከሰንደርላንድ ባገናኘው ጨዋታ ፉልሃም 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ራውል ሂሚኔዝ በጨዋታና በፍጹም ቅጣት ምት እና አሌክስ ኢዎቢ የፉልሃምን ግቦች ሲያስቆጥሩ ኢንዞ ለፊ ደግሞ የሰንደርላንድን ብቸኛ ግብ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል።

የሊጉ ጨዋታ ቀጥሎ ሲካሄድ ምሽት 1:30 ላይ ቶተንሀምን ከአርሰናል የሚያገናኘው የሰሜን ደርቢ ጨዋታ ይጠበቃል።
ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አቻ ተለያዩ።

ሁለቱ ቡድኖች አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ነው የተለያዩት።

በተመሳሳይ ሰዓት ሸገር ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ተለያይተዋል፡፡

ቀደም ሲል ቀን 9 ሰዓት በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች አርባምንጭ ከተማ እና ነጌሌ አርሲ 1 አቻ ሲለያዩ÷ ሐዋሳ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ በተመሳሳይ ውጤት 1 አቻ መለያየታቸው ይታወሳል።