ቼልሲ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር አቻ ተለያየ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር 2 ለ 2 አቻ ተለያይቷል።
በስታምፎርድ ብሪጅ በተደረገው ጨዋታ የቼልሲን ግቦች ዦአዎ ፔድሮ እና ኮል ፓልመር ሲያስቆጥሩ፥ ንሜቻ እና ኦካፎር የሊድስ ዩናይትድን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

👍1
ማንቼስተር ዩናይትድ እና ዌስትሃም ዩናይትድ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ እና ዌስትሃም ዩናይትድ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል።
በጨዋታው ዌስትሃምን መሪ ያደረገችውን ግብ ሶቼክ ሲያስቆጥር፥ የማንቼስተር ዩናይትድን የአቻነት ግብ ሼሽኮ 96ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል።
ቀደም ብለው በተደረጉ የዛሬ ምሽት ጨዋታዎች ቼልሲ እና ሊድስ ዩናይትድ 2 ለ 2 አቻ የተለያዩ ሲሆን፥ ኒውካስል ዩናይትድ ቶተንሃም ሆትስፐርን እንዲሁም ቦርንማውዝ ኤቨርተንን በተመሳሳይ 2 ለ 1 አሸንፈዋል።

👍4
አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት…
አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ምሽት 5 ሰዓት ላይ አርሰናል ከብሬንትፎርድ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች አርሰናል አራቱን በማሸነፍ የበላይነቱን ሲይዝ በአንዱ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ትናንት ምሽት ማንቼስተር ሲቲ ፉልሃምን በማሸነፍ የነጥብ ልዩነቱን ወደ ሦስት ያጠበበ ሲሆን አርሰናል ልዩነቱን ወደ 6 ከፍ ለማድረግ ይፋለማል፡፡
ትናንት ምሽት በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ፣ ሊቨርፑል፣ አስቶንቪላ እና በርንሌይ ተጋጣሚዎቻቸውን ማሸነፋቸው ይታወቃል፡፡

ራሂም ስተርሊንግ ፌይኖርድን ተቀላቀለ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ራሂም ስተርሊንግ እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ በሚያቆይ ውል የኔዘርላንዱን ክለብ ፌይኖርድ ተቀላቅሏል፡፡
እንግሊዛዊው የመስመር አጥቂ በቼልሲ የሚያቆየው ቀሪ የ18 ወራት ውል ቢኖረውም ባሳለፍነው ጥር ወር በስምምነት ውሉን ማቋረጡ ይታወሳል፡፡
የ31 ዓመቱ ራሂም ስተርሊንግ በቀድሞው የማንቼስተር ዩናይትድ እና አርሰናል አጥቂ ሮበን ቫንፔርሲ የሚሰለጥነውን ፌይኖርድ መቀላቀሉን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡

አርሰናል እና ብሬንትፎርድ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር የሊጉ መሪ አርሰናል ከብሬንትፎርድ ጋር 1 ለ 1 አቻ ተለያይቷል፡፡
በጨዋታው የባለሜዳውን ቡድን ብሬንትፎርድ ግብ ሊውስ ፖተር ሲያስቆጥር፥ የአርሰናልን ግብ ኖኒ ማዱዌኬ ከመረብ አሳርፏል።

ማይክል ካሪክ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ተብሎ ተመረጠ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማይክል ካሪክ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2025/26 የውድድር ዓመት የጥር ወር ምርጥ አሰልጣኝ ተብሎ ተመርጧል፡፡
አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ማንቼስተር ዩናይትድን እየመራ በጥር ወር ያደረጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች አሸንፏል፡፡
በጥር ወር ማንቼስተር ዩናይትድ የሊጉ መሪ አርሰናል እና ማንቼስተር ሲቲን ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
በሌላ በኩል የብሬንትፎርዱ የፊት መስመር ተጫዋች ኢጎር ቲያጎ የጥር ወር ምርጥ ተጫዋች በመሆን ተመርጧል፡፡
ኢጎር ቲያጎ በውድድር ዓመቱ ለሁለተኛ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ የወሩ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል።

👍2
በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ 16ቱን ለመቀላቀል የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ መደረግ ይጀምራሉ።
ምሽት 5 ሰዓት ላይ የፖርቹጋሉ ክለብ ቤኔፊካ በሜዳው ስታዲዮ ዳ ሉዛ ሪያል ማድሪድን ያስተናግዳል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች በዚህ የውድድር ዓመት በመድረኩ በስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ተገናኝተው ቤኔፊካ 4 ለ 2 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
ጁድ ቤሊንግሃም፣ ሮድሪጎ፣ ኤደር ሚሊታኦ እና ራውል አሴንሲዮ በዛሬው ጨዋታ ለሪያል ማድሪድ ግልጋሎት የማይሰጡ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 5 ሰዓት ላይ የወቅቱ የመድረኩ አሸናፊ ፒኤስጂ ከሞናኮ፣ ቦርሲያ ዶርትሙንድ ከአታላንታ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ከእነዚህ ጨዋታዎች አስቀድሞ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ ጋላታሰራይ ከጁቬንቱስ ይገናኛሉ፡፡

ቡካዮ ሳካ በአርሰናል የሚያቆየውን የረዥም ጊዜ ውል ተፈራረመ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጫዋች ቡካዮ ሳካ በአርሰናል የሚያቆየውን የረዥም ጊዜ ውል ተፈራርሟል፡፡
የ24 ዓመቱ ተጫዋች በሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እስከ ፈረንጆቹ 2031 ድረስ ለመቆየት ነው ውሉን ያራዘመው፡፡
ቡካዮ ሳካ በአዲሱ ውል መሰረት በሳምንት 300 ሺ ፓውንድ የሚከፈለው ይሆናል፡፡
ሳካ በዚህ የውድድር ዘመን ለአርሰናል በሁሉም ውድድር ባደረጋቸው 33 ጨዋታዎች በሰባት ጎሎች ላይ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

👏7😢4👎1
ዎልቭስ ከአርሰናል…
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ31ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ወደ ሞልኒው ስታዲየም በማቅናት ከዎልቭስ ጋር ይጫወታል፡፡
የሊጉ መሪ አርሰናል ምሽት 5 ሰዓት ወራጅ ቀጣና ላይ ከሚገኘው ወልቭስ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ከተከታዩ ማንቼስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት ቀደም ብሎ የቤት ስራውን መወጣት ይጠበቅበታል፡፡
በአርሰናል በኩል የክንፍ ተከላካዮቹ ካላፊዎሪ እና ቤን ኋይት ለዛሬው ጨዋታ ብቁ መሆናቸውን የጠቀሱት የቡድኑ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ÷ ማርቲን ኦዴጋርድ እና ካይ ሀቨርትዝ ለእሁዱ የሰሜን ደርቢ ፍልሚያ ይደርሳሉ ብለዋል።
የዛሬው የዎልቭስ እና የአርሰናል ጨዋታ በፈረንጆቹ መጋቢት 21 ይካሄዳል ተብሎ በሊጉ መርሐ ግብር የወጣለት ቢሆንም፤ ለካራባኦ ካፕ ፍጻሜ የደረሰው አርሰናል ባለበት ጨዋታ ምክንያት ነው ዛሬ የሚካሄደው።
መድፈኞቹ በ57 ነጥብ ከተከታያቸው ማንቼስተር ሲቲ አራት ነጥብ በመብለጥ ሊጉን እየመሩ ይገኛሉ፡፡

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 16 ውስጥ ለመግባት የሚደረጉ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይካሄዳሉ፡፡
በዚህም መሰረት ካራባግ ከኒውካስል ዩናይትድ፣ ቦዶ ግሊምት ከኢንተርሚላን፣ ክለብ ብሩዥ ከአትሌቲኮ ማድሪድ እንዲሁም ኦሎምፒያኮስ ከባየር ሊቨርኩሰን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ትናንት በተደረጉ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ ቤንፊካን 1 ለ 0፣ ፒኤስጂ ሞናኮን 3 ለ 2፣ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ አታላንታን 2 ለ 0 እንዲሁም ጋላታሳራይ ጁቬንቱስን 5 ለ 2 አሸንፈዋል።

👎1