FMC Sport ፋና ስፖርት
37.7K subscribers
46.7K photos
326 videos
20 files
17.8K links
This is Fana Media Corporation’s (FMC) Sport official Telegram channel.

For more updates please visit
https://fanamc.com/amharic/
Download Telegram
ክሪስታል ፓላስ ብራይተንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ25ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ክሪስታል ፓላስ ብራይተንን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ዛሬ ቀን 11 ሰዓት ላይ በአሜክስ ስታዲየም በተደረገው የኤም-23 ደርቢ ጨዋታ የእንግዳውን ቡድን ክሪስታል ፓላስ የማሸነፊያ ብቸኛ ግብ ኢስማኤላ ሳር አስቆጥሯል፡፡

ሊቨርፑል ማንቼስተር ሲቲን የሚያስተናግድበት የሳምንቱ ተጠባቂና የመጨረሻ መርሐ ግብር ምሽት 1 ሰዓት ከ30 በአንፊልድ ይጀምራል፡፡
👍4
የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ15 የስፖርት አይነቶች በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 10ኛው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ተጠናቋል፡፡

አዘጋጁ ጅማ ዩኒቨርሲቲ 21 የወርቅ ሜዳልያዎችን ጨምሮ 128 ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ እንዲሁም አምስት ዋንጫዎችን በማንሳት ውድድሩን በበላይነት ማጠናቀቅ ችሏል፡፡

በመዝጊያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሽኔ፥ የፌስቲቫሉ ዋነኛ ዓላማ ስብዕናው የተገነባ፣ ስነምግባር ያለውና የአካል ጤንነቱ የዳበረ ዜጋ መፍጠር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች የየአካባቢያቸውን ባህልና ወግና የሚያንጸባርቁ ሁነቶችን በማስተዋወቅ ለፌስቲቫሉ ድምቀት በመሆናቸው ምስጋና ይገባቸዋል ነው ያሉት፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ታይተው፣ ተሰምተውና ተቀምሰው የማይጠገቡ ባህሎች ያሏቸው ህዝቦች ሀገር መሆኗን ያንጸባረቀ ፌስቲቫል መሆኑን ተናግረዋል።

ስፖርተኞቹ በጅማ ከተማ ቆይታቸው ከስፖርታዊ ክንውኖች ባሻገር በዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አቀፍ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ላይ መሳተፋቸውን አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ማህበር ፕሬዚዳንት አባይ በላይሁን በፌስቲቫሉ ላይ የባህል ልውውጥ መካሄዱን ገልጸው፥ የታየውን አብሮነትና ስፖርታዊ ፍቅር ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ 11ኛውን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል እንዲያዘጋጅ ተመርጧል፡፡

በወርቅአፈራው ያለው
ማንቼስተር ሲቲ ሊቨርፑልን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ25ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ሊቨርፑልን 2 ለ 1 አሸንፏል።

የማንቼስተር ሲቲን ግቦች በርናርዶ ሲልቫ እና ሀላንድ (በፍጹም ቅጣት ምት) አስቆጥረዋል።

ባለሜዳውን ሊቨርፑል ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ከመረብ ያሳረፈው ዶሚኒክ ሶቦዝላይ በጨዋታው መገባደጃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር ሲቲ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የዘጠኝ ነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት ማጥበብ ችሏል።

ፕሪሚየር ሊጉን አርሰናል በ56 ነጥቦች ሲመራ፥ ማንቼስተር ሲቲ በ6 ነጥቦች ዝቅ ብሎ ይከተላል።

አስቶን ቪላ በ47፣ ማንቼስተር ዩናይትድ በ44፣ ቼልሲ በ43 እንዲሁም ሊቨርፑል በ39 ነጥብ ከ3 እስከ 6 ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
👍12👎2
በፈረንሳይ ሜትዝ በተደረገው የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በፈረንሳይ ሜትዝ በተከናወነው የሴቶች 3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል።

በዓለም አትሌቲክስ የብር ሜዳልያ በተሰጠው የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትሎ በመግባት ድል ተጎናጽፏል።
በዚህም አትሌት ብርቱካን ሞላ በ8:40.49 በመግባት ውድድሩን ስታሸንፍ÷ አትሌት ሽቶ ጉሜ በ8:41.18 2ኛ፣ አትሌት በ8:41.75 3ኛ ደረጃ በመያዝ ተከታትለው ገብተዋል።

ትናንት በተካሄደው በዚህ ውድድር የተሳተፈችው ሌላኛዋ አትሌት ቤተልሔም ኦላና 6ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቅቃለች።

በወንዶች ምድብ አትሌት አብዲሳ ፈይሳ በ7:44.83 በመግባት ሶስተኛ፣ አትሌት ኤርሚያስ ግርማ በ7:51.80 አምስተኛ፣ አትሌት ለሚ ተሾመ በ7:55.07 ሰባተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል።
በእግር ኳስ ሕይወቱ 13ኛ ክለቡን የተቀላቀለው ሮድሪጌዝ…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ2014 የብራዚል ዓለም ዋንጫ በኋላ በምርጥ ብቃቱ መቀጠል ያልቻለ ተጫዋች ነው ኮሎምቢያዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሀሜስ ሮድሪጌዝ፡፡

በፈረንጆቹ 1991 የተወለደው ሀሜስ ሮድሪጌዝ እግር ኳስን መጫወት የጀመረው በሀገሩ ክለብ ኢንቪጋዶ ነው፡፡

ከዚያ በመቀጠል በተለያዩ ሊጎችና ክለቦች መጫወት የቻለ ሲሆን የተጠበቀውን ያህል ውጤታማ መሆን አልቻለም፡፡

ሀሜስ ለሪያል ማድሪድ፣ ባየርን ሙኒክ፣ ፖርቶ፣ ሞናኮ፣ ኤቨርተን እና ኦሎምፒያኮስን ለመሳሳሉ ክለቦች ተጫውቶ አሳልፏል፡፡

ተጫዋቹ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ጨምሮ ለተለያዩ ክለቦች ተጫውቶ ቢያሳልፍም በእግር ኳስ ሕይወቱ ምርጡን ጊዜ ያሳለፈው ከሀገሩ ኮሎምቢያ ጋር በ2014ቱ የዓለም ዋንጫ ነው፡፡

በፈረንጆቹ 2014 በብራዚል አስተናጋጅነት በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ክስተት ከነበሩ ተጫዋቾች መካከል ኮሎምቢያዊው ሀሜስ ሮድሪጌዝ ትልቁ ክስተት ነበር፡፡

በወቅቱ ጀርመን ዋንጫውን ስታሸንፍ ሀሜስ ሮድሪጌዝ ደግሞ የስፖርት ቤተሰቡን ልብ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

በወቅቱ 22 ዓመቱ ላይ ይገኝ የነበረው ተጫዋቹ ብራዚላውያን በደገሱት የዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ በውብ ግቦች ደጋፊውን እያዝናና የእርሱን ያህል የነገሰ አልነበረም።

በውድድሩ ከሀገሩ ጋር እስከ ሩብ ፍጻሜ መጓዝ የቻለ ሲሆን፥ ስድስት ግቦችን በማስቆጠር የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የወርቅ ጫማ አሸናፊም ነበር፡፡
👇
https://web.facebook.com/fanasport/posts/pfbid0EYwCrksKnwVU3KEYd7Eapi841GmFkRYPHP9Kqn7WQtJGZN7dU8XKv9s73Tn1gTaZl
ፋሲል ከነማ የሊጉ መሪ ለመሆን የሚያደርገው ፍልሚያ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ16ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከሀድያ ሆሳዕና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ፋሲል ከነማ የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ነጥቡን ወደ 36 ከፍ በማድረግ ሊጉን መምራት ይጀምራል፡፡

ያለፉትን 3 ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለው ሀድያ ሆሳዕና በበኩሉ ድል የሚያደርግ ከሆነ ነጥቡን ወደ 24 ከፍ በማድረግ ደረጃውን ማሻሻል ይችላል፡፡

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም መደረግ ይጀምራል፡፡
ሀዲያ ሆሳዕና ፋሲል ከነማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ16ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ የጨዋታ መርሐ ግብር ሀዲያ ሆሳዕና ፋሲል ከነማን 1ለ0 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የሀዲያ ሆሳዕናን የማሸነፊያ ግብ ሱራፌል ተመስገን ከእረፍት መልስ በ60ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

ያለፉትን 3 ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለው ሀዲያ ሆሳዕና የዛሬውን ጨዋታ በማሸነፍ ነጥቡን ወደ 24 ከፍ በማድረግ ደረጃውን አሻሽሏል።

ፋሲል ከነማ በበኩሉ 33 ነጥብን በመያዝ በሊጉ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ማንቼስተር ዩናይትድ በሊጉ 5ኛ ተከታታይ ድሉን ለማሳካት…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

ምሽት 5 ሰዓት 15 ላይ ዌስትሃም ዩናይትድ በሜዳው ማንቼስተር ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡

በሊጉ ያለፉትን አራት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው ማንቼስተር ዩናይትድ 5ኛ ተከታታይ ድሉን ለማሳካት ወደ ሜዳ ይገባል፡፡

ወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘው ዌስትሃም ዩናይትድ በበኩሉ ተከታታይ ሁለተኛ ጨዋታውን ለማሸነፍ ይፋለማል።

ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ ምሽት 4 ሰዓት 30 ላይ ቼልሲ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

በሊጉ ያለፉትን አራት ተከታታይ ጨዋታዎች ያሸነፈው ቼልሲ አሸናፊነቱን ለማስቀጠል ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡

ቶተንሃም ሆትስፐር ከኒውካስል ዩናይትድ እንዲሁም ኤቨርተን ከቦርንማውዝ በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት 30 ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡

ፕሪሚየር ሊጉን አርሰናል በ56 ነጥቦች ሲመራ፥ ማንቼስተር ሲቲ በ6 ነጥቦች ዝቅ ብሎ ይከተላል።

አስቶን ቪላ በ47፣ ማንቼስተር ዩናይትድ በ44፣ ቼልሲ በ43 እንዲሁም ሊቨርፑል በ39 ነጥብ ከ3 እስከ 6 ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
👏1
ቼልሲ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር አቻ ተለያየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር 2 ለ 2 አቻ ተለያይቷል።

በስታምፎርድ ብሪጅ በተደረገው ጨዋታ የቼልሲን ግቦች ዦአዎ ፔድሮ እና ኮል ፓልመር ሲያስቆጥሩ፥ ንሜቻ እና ኦካፎር የሊድስ ዩናይትድን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።
👍1
ማንቼስተር ዩናይትድ እና ዌስትሃም ዩናይትድ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ እና ዌስትሃም ዩናይትድ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል።

በጨዋታው ዌስትሃምን መሪ ያደረገችውን ግብ ሶቼክ ሲያስቆጥር፥ የማንቼስተር ዩናይትድን የአቻነት ግብ ሼሽኮ 96ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል።

ቀደም ብለው በተደረጉ የዛሬ ምሽት ጨዋታዎች ቼልሲ እና ሊድስ ዩናይትድ 2 ለ 2 አቻ የተለያዩ ሲሆን፥ ኒውካስል ዩናይትድ ቶተንሃም ሆትስፐርን እንዲሁም ቦርንማውዝ ኤቨርተንን በተመሳሳይ 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
👍4
አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ምሽት 5 ሰዓት ላይ አርሰናል ከብሬንትፎርድ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች አርሰናል አራቱን በማሸነፍ የበላይነቱን ሲይዝ በአንዱ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡

ትናንት ምሽት ማንቼስተር ሲቲ ፉልሃምን በማሸነፍ የነጥብ ልዩነቱን ወደ ሦስት ያጠበበ ሲሆን አርሰናል ልዩነቱን ወደ 6 ከፍ ለማድረግ ይፋለማል፡፡

ትናንት ምሽት በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ፣ ሊቨርፑል፣ አስቶንቪላ እና በርንሌይ ተጋጣሚዎቻቸውን ማሸነፋቸው ይታወቃል፡፡
ራሂም ስተርሊንግ ፌይኖርድን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ራሂም ስተርሊንግ እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ በሚያቆይ ውል የኔዘርላንዱን ክለብ ፌይኖርድ ተቀላቅሏል፡፡

እንግሊዛዊው የመስመር አጥቂ በቼልሲ የሚያቆየው ቀሪ የ18 ወራት ውል ቢኖረውም ባሳለፍነው ጥር ወር በስምምነት ውሉን ማቋረጡ ይታወሳል፡፡

የ31 ዓመቱ ራሂም ስተርሊንግ በቀድሞው የማንቼስተር ዩናይትድ እና አርሰናል አጥቂ ሮበን ቫንፔርሲ የሚሰለጥነውን ፌይኖርድ መቀላቀሉን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡
አርሰናል እና ብሬንትፎርድ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር የሊጉ መሪ አርሰናል ከብሬንትፎርድ ጋር 1 ለ 1 አቻ ተለያይቷል፡፡

በጨዋታው የባለሜዳውን ቡድን ብሬንትፎርድ ግብ ሊውስ ፖተር ሲያስቆጥር፥ የአርሰናልን ግብ ኖኒ ማዱዌኬ ከመረብ አሳርፏል።