የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
"የጀግኖች መፍለቂያ ፤ የድል ምልክት " በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 4ኛ ዓመት የኮሩ ምስረታ በዓልን ይፋዊ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓትን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያስጀመሩት የቴዎድሮስ ኮር አዛዥ ኮሎኔል ረሺድ ኢብራሂም እንዳሉት ቴዎድሮስ ኮር የተመሠረተበትን 4ኛ ዓመት ሲያከብር ተቋሙ የጣለበትን ሃላፊነት በጀግኖች አባላቱ ክቡር መስዋዕትነት በድል እየፈፀመ ነው።
የኮሩ አዛዥ በንግግራቸው እንደገለፁት ቴዎድሮስ ኮር በጦርነት ውስጥ ተወልዶ ያደገና በእሳት ተፈትኖ እንደ ወርቅ ነጥሮ የወጣ ፈተናን የሚፈትን እንጅ በፈተናዎች የማይዝል ፤ የጀግኖች መፍለቂያ እና የምዕራብ ዕዝ መተማመኛ ክንድ ነው።
እኛ የቴዎድሮስ ኮር አባላት በፈፀምናቸው ስኬታማ ተልዕኮዎችና ባስመዘገብናቸው አንፀባራቂ ድሎች የምንረካ አሊያም የምንዘናጋ አይደለንም ያሉት አዛዡ ኮሎኔል ረሺድ ኢብራሂም በተለዋዋጭና ተቀያያሪ የተልዕኳችን ባህሪ ውስጥ ከዕለት ወደ ዕለት የሚጎመራና የሚያብብ የድል ፍሬን ለሀገር እና ለህዝባችን ማበርከታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
የምስረታ በዓሉ በተለያዩ ኩነቶች ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት እንደሚከበር መሆኑን የገለፁት ኮሎኔል ረሺድ ኢብራሂም ፓናል ውይይት ፤ የፎቶ አውደ ርዕይ ፤ የእውቅና አሠጣጥ ስነ- ስርዓትን ጨምሮ የተለያዩ መርሃ- ግብሮች እንደሚከናወኑ ገልፀዋል። የሆሮ ጉድሩ ዞን አባገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች መድረኩን በባህላዊ ምርቃትና ምስጋና አስጀምረዋል።
"የጀግኖች መፍለቂያ ፤ የድል ምልክት " በሚል መሪ ቃል እየተከበረ በሚገኘው የቴዎድሮስ ኮር 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሜጄር ጄኔራል ሙላት ጀልዱ ፤ የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ፤ የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምሬሳ ፍጤ ፤ የሻምቡ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባን ጨምሮ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና እና የሃገር ሽማግሌዎች፤ አባገዳዎችና ሃደ ስንቄዎች ፤ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የሻምቡ ከተማ ነዋሪዎችና በየደረጃው የሚገኙ የኮሩ አመራሮችና አባላት ታድመዋል።
ዘጋቢ ሲሳይ ደመቀ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

YouTube
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# የመከላከያ ሠራዊት ቁልፍ እሴቶች፡-
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
👍33❤17👎7🥰6🔥1👏1
የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ መከላከያ ሚኒስትር ሪምአውክስ ክላውድ የአየር ወለድ ማሰልጠኛን ጎበኙ፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሪምአውክስ ክላውድ የተመራው ልዑክ ከልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ እና ከክፍሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በቢሾፍቱ የሚገኘውን የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም አጠቃላይ የልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማዕከልን እና በስሩ የሚገኙትን አራት ትምህርት ቤቶች በተመለከተ የዕዙ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ለቡድኑ ማብራሪያና ገለፃ የሰጡ ሲሆን የልዩ ሀይሎች ስልጠናን የሚያሳይ አጠር ያለ ዶክመንተሪ ፊልምም ቀርቧል፡፡
በሀገራዊ ለውጡ ተቋሙ ባደረገው ሪፎርም የልዩ ሀይሎች ማሰልጠኛ ማዕከል የማሰልጠን አቅሙን ወደ ላቀ ደረጃ በማሳደግ በሀገር ደረጃ የውጊያ ማሪሽ ቀያሪ የምድር ድሮን የሚል ስያሜ የተሰጣቸውን የኮማንዶ፣ አየር ወለድና ልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር ሀይል መፍጠር መቻሉን አብራርተዋል፡፡
ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ተልዕኮ እና አሁናዊ ብቃቱን ለልዑካን ቡድኑ የገለፁ ከመሆኑም በላይ ማሰልጠኛ ማዕከሉ የራሱን ብቁ አሰልጣኞች በማፍራት ለኢትዮጵያ የሚመጥናትን ሀይል እያሰለጠነ ከመሆኑም በላይ ለአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮችም በስልጠና መስክ ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አውስተዋል፡፡
የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ መከላከያ ሚኒስትር ሪምአውክስ ክላውድ በበኩላቸው ዕዙ ባደረገላቸው አቀባበል መደሰታቸውን ገልፀው የኢትዮጵያ የኮማንዶ፣ አየር ወለድና ልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር የስልጠና ሂደት መደነቃቸውን በመግለፅ ስልጠናው የኢትዮጵያ ሠራዊት ጥንካሬ ያሳዬ ነው ብለዋል፡፡
የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወጣቶች በዚህ ደረጃ እዚህ ሰልጥነው ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸውና ይህም በሁለቱ ሀገሮች ወታደራዊ ትብብር ስምምነት መሰረት እንደሚፈፀም ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል። ዘጋቢ አብዱራህማን ሀሰን ነው

❤21👍10🔥2🏆1