FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.5K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
በጋዜጠኛ ሌተናል ኮሎኔል ፈይሳ ናኔቻ የተፃፈው የወታደር ውሎ አዳር መፅሀፍ ተመረቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

የወታደር ውሎ አዳር የተሰኘው መፅሀፍ፣ የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማን ጨምሮ፣ ጄኔራል መኮንኖች ፅሀፊያን እና ደራሲያን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በአደዋ ድል መታሰቢያ ሁለገብ አዳራሽ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።

የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ ታሪኮች የሀገር ሀብት በመሆናቸው፣ሰንዶ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ጠቁመው የጋዜጠኛው መፅሃፍም የመከላከያ ሠራዊቱን ሁለንተናዊ የግዳጅ ውሎ አስገራሚ የኋላ ታሪኮች የሚያትት በመሆኑ አመሥግነውታል።

በመከላከያ ስነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት የሚዲያ ስራዎች ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል አስፋው ማመጫ፣ ለምርቃት የበቃውን መፅሀፉ ዳሰሳ በማድረግ የሰራዊቱን ህይወት በሚገባ የሚገልፅ እና የሚያሳይ መሆኑን አመላክተው በመፅሀፉ ውትድርና እና ኢትዮጵያዊነት ያላቸውን ግንኙነት፣ በግልፅ፣ማሳየት እንደተቻለም አብራርተዋል።

በመፅሀፉት ምርቃቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር  ፕሬዚዳንት፣ ደራሲ አበረ አዳሙ፣በመፅሀፉ ላይ የመመዘኛ ዳሰሳ አድርገዋል። በዚህም መፅሀፉ የመፅሀፍ መመዘኛ መስፈርትን በጥሩ ሁኔታ ማሟላቱን ገልፀው ወታደራዊ ታሪኮች ሀገርን በሚመጥን መልኩ ተሰንደው እና በመፅሃፍ ተዘጋጅተው ለትውልድ መተላለፍ እንዳለባቸው አመላክተዋል። ለሀገር መስዋዕት እየከፈለ ሠላምን እያረጋገጠ  ለሚገኘው የመከላከያ ሠራዊትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዘጋቢ ቢያድግልኝ መሪ
ፎቶ ግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
32👍22👏8🔥2🏆2🥰1
ጤና ይስጥልን ጠቂት ሥለጤናዎ ታይፈስ ልብስ በመልበስ የሚመጣ በሽታ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የሀገራችን  የብዙ ጤና ጣቢያዎች ደረጃ "ሀ" የበሽታ አይነት ተደርጎ መቆጠር ከጀመረ ሰነባብቷል። ይኸ ጉዳይ እየቆየ የመጣና ዛሬ ላይ ታይፈሴ ተነሳብኝ ፤ ታይፎይዴ ወደ ታይፈስ ተቀየረብኝ ወደ ሚል ሰፊ እና ሊቀለበስ ወደ ማይችል አስቸጋሪ የማህበረሰብ እሳቤ ሊደርስ ችሏል።

ታካሚዎች ወደ ህክምና ቤት የሚመጡት ለመመርመር ሳይሆን የተቀሰቀሰባቸውን ታይፈስ ለማከም የሚውል መድሐኒት ለመውሰድ ነው የሚመጡት ቢባል ይቀላል። ይኽ ሊሆን የቻለው በተደጋጋሚ ታይፈስ ነው እየተባሉ በመመለሳቸው ነው። ትልቁ ችግር ከኛው ባለሙያው ጋር ነው።

ታይፈስ አደገኛ እና ተላላፊ በሽታ ነው። በአለም ላይ በወረርሺኝ ደረጃ ከሚከሰቱ ቀዳሚ ነው። የብዙ ሚሊዮኖችን ህይወት ቀጥፎ  አልፏል። ታይፈስ ተስቦ በሚል ይተጠራል። ዛሬ ታይፈስን ከመኖር ብቻ አይደለም ከታሪክ ማህደራቸውም ያጠፉ ሀገራት ሞልተዋል። ምክነያቱም ታይፈስ የሰው ልጅ ስብዕና የሚነካ ፀያፍ ህመም ነው ብለው በማሰባቸው ነው።

ታይፈሰን ከሰው ወደ ሰው የሚያዛምቱት አካላት በሚለበስ ልብስ ውስጥ ምሽግ ሰርተው በሚኖሩ ነው። የግል እና የልብስ ንፅህና ባለመጠበቅ ተስቦን የሚፈጥር ጀርም ተሸካሚዎች የሚፈጡረበት እድል ስለተመቻቸ ነው። የታይፈስ መከላከያ ንፅህና መጠበቅ ነው። ሌላ ተዓምር የለም።

በተለይ ቀዝቃዛ አካባቢ ታይፈስ ይከሰታል። ለዚህ ትልቁ ምክነያት ቅዝቃዜን ለመከላከል ሰው ያለ የሌለውን ልብስ ደራርቦ በመልበሱና ቅዝቃዜን በመፍራት ልብስን አውልቆ ለማጠብ በሠስነፉ ነው። ታይፈስ ከገንዘብ እና አስተሳሰብ ድህነት ጋር የተቆራኘ ገዳይ እና አሳፋሪ ህመም ነው። ልብስን ከገላ አርቆ ቢያንስ ለ24ሰዓት ካስቀመጡ ጀርም ተሸካሚ አካላት ይሞታሉ።

ትክክለኛው ታይፈስ ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት ያለው ነው። ሙቀት የሌለው ሰውን ምንም አይነት ምልክት ቢኖረው ታይፈስ ነው ማለት ያስቸግራል። የሙቀት ልኬቱ ትክክልኛ የሆነን ሰው ታይፈስ ነው ከማለት ይቆጠቡ። በተረፈ ለታይፈስ የሚውል ምርመራ ለታካሚ የሚጠቅም ሳላልሆነ አይዘዙ ፤ ሌሎች ችግሮችም ውጤቱን እንዳለ አሳይተው ሊያሳሳቱ በመቻላቸው ነው።

ሌላው የታይፈስ የቅርብ ጓደኛ ታይፎይድ ነው። ሁለቱን መነጣጠል አቅቶናል። ታይፈስ ታይፎይድ ተባልኩኝ
የማይል የመኪና አደጋ ገጥሞት የሔደ ብቻ ይመስለኛል። ታይፈስን ወደ ታይፎይድ ፤ ታይፎይድን ወደ ታይፈስ ማቀያየር የተለመደ ክስተት ሆኗል። ይኸ ማለት ላምን ወደ በግ ፤በግን ወደ ላም እንደመቀየር ነው። ሁለቱ በፍፁም የተራራቁና አንዱ ወደ ሌላ ሊቀያየሩ የማይችሉ ናቸው። ሁለቱ ህመሞች ግን በአንድ ሰው ላይ ሊከሰቱ ይችላሉ። አንድ ሰው ብዙ አይነት ህመሞች ሊኖሩበት እንደሚችሉት ማለት ነው።

ታይፎይድ በምግብና ውሐ መበከል የሚመጣ ውሐና ምግብ ወለድ በሽታ ነው። የምግብ ንፅህናን የውሐ ንፅህናን መጠበቅ ሁነኛ መፍትሔ ነው። ሁለቱን የሚያመሳስላቸው በንፅህና ጉድለት መከሰት መቻላቸው ነው። የአኗኗር ደረጃን ፍትው አድርገው የሚያሳዩ የአንድ ሰው አኗኗር ማሳያ መስተውቶች ናቸው።

በሌላ መንገድ ታይፈስና ታይፎይድን የሚያዛምቱት የምግብና መኝታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ናቸው። ብዙ የሀገራችን የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ሆቴሎች ታይፈስ ቀጣይ ሆኖ እንዲቀር  እየሰሩ ያሉ ይመስላል። በዚህም ብዙ የግል ንፅህና የሚጠብቁ ሰዎች በሆነ አጋጣሚ ሆቴል ሲያድሩ ለታይፈስ የሚጋለጡ እንዳሉ ልብ ይበሉ። ምናልባትን ታይፈስ ሊሆን ይችላል ለማለትም የማይጠረጠርበት የአኗኗር ደረጃ ላይ ያለ ሰው በዚህ በሽታ ህይወቱ አደጋ ላይ ሊደርስ ይችላል።

ችግሩ ከግለሰብ አልፎ የማህበረሰብ ነው። የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ብዛት ያላቸው ሆቴሎች ከደረጃ በታች መሆን ብቻ አይደለም የተባይና የበሽታ አምጪ ነፍሳቶች መገኛና መፈልፈያም ጭምር ናቸው። ተቆጣጣሪ አካላት የበሩን ቀለም ብቻ ከማየት አንሶላና ብርድለብሱንም አየት አየት ማድረግ አለባቸው። በእውነቱ አሳፋሪ አገልግሎት የሚሰጡ ሰው ከመግደል ወንጀል በላይ ስብዕናን የሚነኩ በሚል መጠየቅ አለባቸው። ትክክለኛው ታይፈስ ገዳይና አጣዳፊ እንዲሁም ወረርሺኝ የሚያስነሳ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
14🔥1
ጄኔራል አበባው ታደሠ የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር የምስረታ በዓልን ለመታደም ሻምቡ ከተማ ገቡ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ እና ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች  የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር የምስረታ በዓል ላይ ለመታደም ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ እና ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በስፍራው ሲደርሱ የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች የዞንና የወረዳ አስተዳደሮችን ጨምሮ የሻምቡ ከተማ ከንቲባና የአካባቢው አባገዳዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጄኔራል አበባው ታደሠ  በቴዎድሮስ ኮር የተዘጋጀውን የፎቶ አውደ ርዕይን እና የኮሩን ሎጎ  መርቀዋል። በተጨማሪም  ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ ቴዎድሮስ ኮር በራስ ወጪ የሠራውን የአቅመ ደካማ እናት መኖሪያ ቤትን መርቀው በመክፈት ቁልፍ አስረክበዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው እናትም ረዳት አልባ በመሆናቸው እና አቅማቸው በመድከሙ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠው የቆዩ መሆናቸውን ተናግረው ዛሬ ሠራዊቱ ሠርቶ ላስረከባቸው ቤት ምስጋና አቅርበዋል።

አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች በሠጡት አስተያየትም እኝህ አቅመ ደካማ እናት  ከዚህ በፊት በፈራረሠ ቤት ውስጥ ብርድ እና ዝናብ ሲፈራረቅባቸው መቆየቱን ገልፀው ሠራዊቱ ባደረገው የበጎ አድራጎት ተግባር መደሠታቸውን ተናግረዋል።

የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ ኩነቶች ማክበሩን ቀጥሏል።

ዘጋቢ ሲሳይ ደመቀ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
39🔥1
የምዕራብ ዕዝ  ቴዎድሮስ ኮር 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው።
 
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

" የጀግኖች መፍለቂያ ፤ የድል ምልክት " በሚል መሪ ቃል እየተከበረ በሚገኘው በዚሁ የቴዎድሮስ ኮር 4ኛ ዓመት ምስረታ በዓል ማጠቃለያ ላይ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ ፣ ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና ፣ የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔሬል ዘውዱ በላይ ፣ የምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሠለ መሠረት፣ የሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ  ምሬሳ ፊጤ ጄኔራል መኮንኖች ፣ የምዕራብ ዕዝ አመራሮችን ጨምሮ የቴዎድሮስ ኮር የሠራዊት አባላት እና የሻምቡ ከተማ ነዋሪዎች ታድመዋል።

በምስረታ በዓሉ ማጠቃለያ የተለያዩ መርሃ - ግብሮች እንደሚከናወኑ አና ልዩ ልዩ መልዕክቶች እንደሚተላለፉ ይጠበቃል።

ዘጋቢ ሲሳይ ደመቀ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍1610🔥1