ወለጋ በአስደማሚ የሠላም አየር ላይ ናት ሚስጥሩ ምን ይሆን ?
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
ተፈጥሮ አብዝታ ፀጋዋን የቸረችው፤ በከርሠ ምድር እና ገፀ ምድር ሃብት የተንበሸበሸው የወለጋ ምድር ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮጉዱሩ ወለጋ በተሠኙ አራት ሠፋፊ ዞኖች ተዋቅሯል።
ይህ ከባቢ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተለይም ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ በአሸባሪው ሸኔ የጥፋት ስትራቴጂ ትግበራ ምክንያት ሠላም ርቆት ቆይቷል። ብቻም ሳይሆን በንፁሃን ላይ ኢ-ሠብዓዊና ድርጊቶች ተፈፅመውበታል። ንፁሃን ተገድለውበታል፤ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፤ ሆሮጉድሩ ወለጋም የዚህ አስከፊ የታሪክ ገፅታ ሠለባ ብቻም ሳይሆን ዋና ማዕከል ሆኖ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።
በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች በሚባል ደረጃ የአሸባሪው የሸኔ ቡድን እንዳሻው ሲፈነጭ እና የህዝቦችን በጋራ የመኖር እሴት ለማጥፋት ማድረስ የሚችለውን ጥፋት ሁሉ የፈፀመበት አካባቢ እንደነበር ከማንም የተሠወረ አይደለም። የህዝብን ዘመን ተሻጋሪ እሴቶች ጥላሸት ለመቀባትና የህዝቡን የመልማትና የመበልፀግ ጉዞ በማምከን ብሎም ዘልዓለማዊ እድሜ ለመስጠት የጥፋት ቡድኑ ብዙ ርቀቶችን ተጉዟል። ግን አልተሳካለትም።
ወለጋ ዛሬ በአስደማሚ የሠላም አየር ስር በማንሠራራት ጉዞ ውስጥ ይገኛል። በአራቱም የወለጋ ዞኖች ዛሬ የሠላም፣ የተስፋ፣ የልማትና የአብሮነት መልካም መዓዛ ማወድ ጀምሯል። በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ በነበረን ቆይታ ይህንኑ መታዘብ ችለናል። የአካባቢው አገር ሽማግሌዎችና የአስተዳደር አካላትንም በአካባቢው ስለተፈጠረው ሠላምና ምክንያቱ ጠይቀን ሚስጥሩ ምን ይሆን ያስባለንን ቋጠሮ ፈተናል።
ሚስጥሩ ምን ይሆን ይቀጥላል...
በሲሳይ ደመቀ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

YouTube
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# የመከላከያ ሠራዊት ቁልፍ እሴቶች፡-
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
❤26👍12🔥1
ማሠልጠኛው የዕዙን አመራር የብቃት ደረጃ የሚያሳድጉ ሥልጠናዎችን እየሠጠ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
የደቡብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀኔራል አድማሱ አለሙ የዕዙን የአመራር አቅም በየጊዜው በማሳደግ ዕዙ የሚሰጠውን ተልዕኮ በጀግንነት የሚፈፅም በጠንካራ ስልጠና የተፈተነ አመራር ማፍራትና መገንባት መቻሉን ተናግረዋል፡፡
ሜጀር ጄኔራል አድማሱ የዕዙን የሠራዊት አባላት በተለያዩ የመሬት ገፅና የአየር ፃባይ ማሰልጠን ፅኑ እምት ያለው ከአላማው ዝንፍ የማይል እንደ ወርቅ በስልጠና የተፈተነ ግዳጅን ጀምሮ በድል የሚያጠናቅቅ አመራር ለመፍጠር የሚያስችል እንደሆነም ገልፀዋል።
ሰልጣኝ አመራሩ ከግል እስከ ቡድን የነገን ተልዕኮ ታሳቢ ያደረገ ውጤታማ ሥልጠና እየወሰደ እንደሆነም ተናግረዋል።
የማሰልጠኛው ማዕከሉ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ቦጋለ ተገኔ በበኩላቸው ማዕከሉ በማሰልጠን የብዙ ጊዜ ተሞክሮ ያለው በመሆኑ በትኩረት ሰውንና ንብረትን በማቀናጀት ውጊያን መምራት የሚችል ሃይል እያፈራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ዘጋቢ በላይ ታደለ
ፎቶ ግራፍ ቦጋለ አዲሴ

❤18👏8👍5🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ መከላከያ ማርችንግ ባንድ በሞስኮ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
ሩሲያ ባዘጋጀችው የማርችንግ ባንድ ፌስቲቫል ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ማርችንግ ባንድ ቡድን በሞስኮ የሙዚቃ እና ባህል ትርዒቱን በማቅረብ ላይ ይገኛል።
ዛሬም የመጀመሪያ ሥራውን ተመልካቹን ባስደመመ ብቃት እና ቀልብን የመያዝ ስሜት አቅርቧል። የሩሲያው የዜና ወኪል ስፑትኒክ እንደዘገበው ኢትዮጵያ ባህሏን እና ሙዚቃዎቿን በታዋቂው ቀዩ አደባባይ በማስተዋወቅ በሞስኮ ደምቃ ታይታለች፡፡
ኢትዮጵያ በሩሲያ የማርችንግ ባንድ ፌስቲቫል ላይ መሳተፏ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር እና ወታደራዊ የልምድ ልውውጥን ለማሳደግ የሚያግዝም ነው።

❤53🏆12🔥3🥰3
የመከላከያ የሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ
ውጤታማ ሥራ ማከናወኑን አሥታወቀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
የመከላከያ ሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ የ2017 በጀት አመት የሥራ አፈፃፀም ከማዕከል እና ከዕዞች የሰው ሃብት አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የመከላከያ ሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ የሰው ሃብት አመራር የሰው ሃይሉን በመመልመል በማሰልጠንና በማብቃት በማንኛውም ሁኔታ የሚሰጡ ግዳጆችን በሙሉ አቅም መወጣት የሚያስችል ቁመና የተላበሰ ሠራዊት መገንባት መቻሉን ገልፀዋል።
ሌተናል ጀኔራል አጫሉ ሸለመ የምንሰራቸውን ስራዎች ነጥበን በማስቀመጥ የሚጎድሉትን ክፍተቶች በመለየት እና በተጠያቂነት እዲሁም በታማኝነት መንፈስ በመስራት በበጀት አመቱ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችለናል ይህንን አቅማችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን ብለዋል።
በአገልግሎት አሰጣጥ በኩልም ለተገልጋዩ የተጣራ መረጃ በመስጠት እና የሰው ሃይል በመቆጣጠር ዳታን በማደራጀትና ሠራዊቱ በግዳጅ ላይ ደስተኛ እንዲሆን በማድረግ በኩል ሁሉም የሰው ሃይል ሙያተኛ በላቀ ደረጃ ስራውን በመስራት ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ ገልፀዋል።
በመከላከያ የሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ የእድገትና ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዲየር ጀኔራል አምሳሉ ኩምሳ በበኩላቸው የሰው ሃብት አመራር ሙያተኞች የተሰጣቸውን ተግባራት በሚገባ ለመወጣት ሁሌም በጥረት እንደሚሠሩ እና ውጤት ማምጣት እንደቻሉ ገልፀው በበጀት አመቱ መጨረሻ ላይ በተቋሙ የተወሰኑ ክፍሎች ላይ የተሳካ ኢንስፔክሽን መደረጉን ተናግረዋል።
በመጨረሻም በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ በመወያየት የሠራዊቱን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተግባራት ተጠናክረው በሚቀጥሉበት ሁኔታ ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር ተችሏል።
ዘጋቢ ትግስት ሙላት
ፎቶ ግራፈር ዮዲት በዛወርቅ

❤28👍3🔥2
ወለጋ በአስደማሚ የሠላም አየር ላይ ትገኛለች ሚስጥሩ ምን ይሆን ? ... የቀጠለ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
አቶ ጉዲና ገመዳ የሻምቡ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ፤ የስራ እድል ፈጠራና ኢንቨስትመንት ፅህፈት ቤት ሃላፊ ናቸው። የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አስተዳደር መቀመጫ የሆነችው ሻምቡ ከተማ ከዛሬ ሦስትና አራት ዓመታት በፊት የነበረችበትን የሠላም እጦትና በዚሁ ምክንያት በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ተፈጥሮ የነበረውን ሠብዓዊ ፤ ኢኮኖሚያዊ ፤ ማህበራዊ እና ስነ - ልቦናዊ ቀውሶች ለአፍታ አስታውሠው ሲያበቁ ዛሬ ለተጎናፀፈችው ሠላም እና የመልማት ተስፋ የምዕራብ ዕዝን በተለይም ደግሞ የቴዎድሮስ ኮርን መስዋዕትነት ፤ ፅናት እና ቁርጠኝነት አብዝተው ያደንቃሉ።
ምክትል ከንቲባ አቶ ጉዲና ገመዳ የቴዎድሮስ ኮር አመራርና የሠራዊት አባላትን የሚገልፁበት ቃል አጥሯቸው በብዙ ሲቸገሩ በመታዘባችን የሚስጥሩ ቋጠሮ ፍቺ እዚህ ጋር ስለ መኖሩ አልተጠራጠርንም።
የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አስተዳደር መቀመጫ የሆነችው ሻምቡ ከተማ ያንን ክፉ ዘመን እንድትሻገርና ዛሬ ለምትተነፍሰው የሠላም አየር ትበቃ ዘንድ ሁለንተናዊ መስዋዕትነትን ለከፈለው የቴዎድሮስ ኮር ከልብ የመነጨ ምስጋናን ቸረውታል።
ዛሬ ይላሉ ምክትል ከንቲባ ጉዲና ገመዳ በጀግናው ቴዎድሮስ ኮር አባላት ክቡር መስዋዕትነት ብሎም ጀግንነትና ፅናት ህዝባችን ሠቅዞ ከያዘው መከራ እና ስቃይ እፎይ ብሏል። ቴዎድሮስ ኮር በቀጠናው ከተሠማራ ጊዜ ጀምሮ በአካባቢው እንደፈለገ ሲፈነጭና ንፁሃንን የግፍ ፅዋ ሲግት የነበረውን የአሸባሪውን ሸኔ ቡድን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቷል።
የሽብር ቡድኑን አከርካሪ ሠብሮ እንዲበታተንና በየጥሻው የሚሽሎከሎክ ተራ ሽፍታነት ደረጃ እንዲወርድ አድርጎታል። ለዚህም ቴዎድሮስ ኮር ቀን ከሌት ተልዕኮውን በአስገራሚ ፅናትና ቁርጠኝነት እየተወጣ ሃገራዊና ህዝባዊ ፍቅሩን በመስዋዕትነቱ ስለማስመስከሩ ምክትል ከንቲባ ጉዲና ገመዳ ነግረውናል።
የሀገር ሽማግሌዎች በበኩላቸው በአሸባሪው ሸኔ የጥፋት ተግባራት ምክንያት የደበዘዘ የትላንት ትዝታቸውን በቁጭትና በሀዘን አስታውሠው ዛሬያቸው ብሩህ ይሆን ዘንድ ውድ ህይወቱን ሳይሰስት ለሠጣቸው ጀግናው ሠራዊት ምርቃትና ምስጋናን ሲያሽጎደጉዱለት መመልከት በመንፈሳዊ ቅናት ያቃጥላል። ምነው እኔም የዚህ ጀግና ሠራዊት አባል በሆንኩ እና እንዲህ ያለ የህዝብ ፍቅርና አክብሮትን በተጎናፀፍኩ ያሠኛል።
ከቅርብ ዓመታት በፊት ይላሉ የአካባቢው ተወላጅ የሀገር ሽማግሌዎች " ሆሮጉድሩ ወለጋን ጨምሮ አራቱም የወለጋ ዞኖች ለሠው ልጆች አደገኛ የሆኑ ምድራዊ ሲኦሎች ነበሩ። ንፁሃን በዘፈቀደና በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገደሉበት፤ እድሜልክ ያፈሩት ሃብት ንብረት በማንአለብኝነት የሚዘረፍበትና የሚወድምበት፤ ተወልደው ካደጉበት ቀዬ የሚፈናቀሉበትና የሚሠደዱበት ብቻ በጥቅሉ ሠዎች መፈጠራቸውን እንዲጠሉ የሚያደርግ ነውር የሚፈፀምበት በጣም አስቸጋሪ ስፍራ ነበር " ሲሉ ይገልፁታል።
ዛሬ ግን ታሪክ ተቀይሮ ያ ፀረ-ህዝብና አረመኔ ቡድን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ እና አከርካሪው ተሠብሮ ትርጉም የለሽ ቡድን ሆኖ ማየት ለእኛ ወደር የማይገኝለት ድል ነው ሲሉ ይገልፃሉ። ለዚህ ድል እና ትልቅ እፎይታ እንድንበቃ አንድ ህይወቱን ለሸለመን ጀግናው ሠራዊታችንም ልባዊ ክብርና ምስጋናችን ዘለዓለማዊ ነው ባዮች ናቸው የሀገር ሽማግሌዎቹ።
በቀጠናው የተሠማራው ቴዎድሮስ ኮር ለሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አንፃራዊ ሠላም መስፈን ሁለንተናውን ሳይሰስት የለገሠ ጀግና አሃድ ነው። በወለጋ ምድር ላይ እየነፈሠ ለሚገኘው አስደማሚ የሠላም አየር ሚስጥርም የቴዎድሮስ ኮር እጅን በአፍ ላይ የሚያስጭን ጀግንነትና ተጋድሎ ውጤት ሆኖ አግኝተነዋል።
ለመሆኑ የቴዎድሮስ ኮር ማነው የት? ፤ እንዴት? መቼና በማን ተመሠረተ? በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ከመሠማራቱ በፊትስ ምን ምን ግዳጆችን ፈፅሟል? እነዚህን እና ሌሎች ጉዳዮችን ይዘን እንመለሳለን...

👍23❤20🥰2👎1🔥1