Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
46.1K subscribers
1.8K photos
116 videos
25 files
975 links
FDRE, Ministry of Labor and Skills
Download Telegram
ማብቃት ላይ ያተኮረ ድጋፍና ክትትል

የሥራና ክህሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚያካሄደውን ድጋፍና ክትትል እና የመስክ ምልከታ አስመልክቶ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ በሥራው ለሚሳተፉ  አካላት ኦረንቴሽን ሰጥተዋል፡፡

የመስክ ምልከታው ሚኒስቴሩ በዘርፉ የቀረጻቸው እሳቤዎች አተገባበር፣ ከአፈጻጸም አኳያ ወደኋላ የቀሩትን መደገፍ፣ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ሪፎርም ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ እንዲሁም በክህሎት ልማት፣ በሥራ ሥምሪት፣ በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍና በተቋም ግንባታ ዘርፎች የተገኙ ልምዶች እና ተሞክሮዎች ቀምሮ ለማስፋት ያስችላል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በበጀት አመቱ የተያዙ ትላልቅ ግቦችን ለማሳካት የተደረገው ዝግጅትና በግማሽ አመቱ የተከናወኑ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች የምልከታው አካል እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡

ድጋፍና ክትትሉ ከጥር 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን በሂደቱ የሚገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች የመቀመርና  የማስፋት ስራም እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡
ታህሳስ  28/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtT
18👍7👌5
👍2213
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia pinned «ይህ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ይፋዊና ትክክለኛው የቴሌግራም ቻናል ነው፦ 🔗 https://t.me/FDRE_MoLSofficial ⚠️ ጥንቃቄ በአሁኑ ወቅት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን ስምና አርማ (Logo) በመጠቀም፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያወጣቸውን መረጃዎች በማባዛትና በማስመሰል የሚንቀሳቀሱ በርካታ ሀሰተኛ የቴሌግራም ገጾች መኖራቸውን ደርሰንበታል። እነዚህ አጭበርባሪ አካላት ተገልጋዮችን የሚያታልሉባቸው…»
ይህ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ይፋዊና ትክክለኛው የቴሌግራም ቻናል ነው፦
🔗 https://t.me/FDRE_MoLSofficial

⚠️ ጥንቃቄ
በአሁኑ ወቅት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን ስምና አርማ (Logo) በመጠቀም፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያወጣቸውን መረጃዎች በማባዛትና በማስመሰል የሚንቀሳቀሱ በርካታ ሀሰተኛ የቴሌግራም ገጾች መኖራቸውን ደርሰንበታል።

እነዚህ አጭበርባሪ አካላት ተገልጋዮችን የሚያታልሉባቸው መንገዶች፦
👉የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ሽፋን በማድረግ በውስጥ መስመር (Inbox) ያነጋግሩዎታል፣

👉ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደተደወለ በማስመሰል ያልተገባ የገንዘብ ክፍያ ይጠይቃሉ፣

👉የተለያዩ የሐሰት ተስፋዎችን በመስጠት ንፁሃን ዜጎችን ለከፍተኛ ምዝበራ እየዳረጉ ይገኛሉ፣

ትክክለኛውን ገጽ እንዴት መለየት ይቻላል?
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይፋዊ ገጽ የሚከተሉት መለያዎች አሉት፦

ሰማያዊ የማረጋገጫ ምልክት (Verified Badge) ያለው ነው፣

46,000 በላይ ተከታዮች አሉት፣

ማንኛውም ይፋዊ መረጃ በድረ-ገጻችንና በሌሎች የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችን ላይ ከሰፈሩት አድራሻዎች ጋር የተናበበ ነው፣


🛡 የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ

• ለሌሎች ያጋሩ፦ ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ፣

• Unfollow ያድርጉ፦ በስህተት ሀሰተኛ ገጾችን እየተከታተላችሁ ያላችሁ ተገልጋዮች፣ በአስቸኳይ ከገጾቹ በመውጣት (Unfollow በማድረግ) ራሳችሁንና ወገኖቻችሁን ከማጭበርበር ይታደጉ፣

• ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ሁልጊዜ ይፋዊ ገጾቻችንን ብቻ ይከታተሉ!

🔗 ለወቅታዊ ትኩስ መረጃ
🌍 Official Website: mols.gov.et
📘 Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
36🥰11🙏9👏3
በውጭ ሥራ ስምሪት ሂደት ላይ የሚታዩ የአሠራር ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል የምክክር መድረክ በአቡዳቢ ተካሄደ

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ክቡር ዶ/ር ጀማል በከር ከስራና ክህሎት ሚኒስትር ተወካዮች ጋር በመሆን በአቡዳቢ እና አካባቢው ከሚገኙ የውጭ ሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች (ተድቢሮች) ባለቤቶችና ማኔጅመንቶች ጋር በዘርፉ ያለውን ትብብር ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አካሂደዋል።

ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ጀማል በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ መንግሥት ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የዘረጋው ሕግና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለሠራተኛ ፈላጊዎችና ቀጣሪዎች ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አፅንዖት ሰጥተውበታል።

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብርሀኑ አለቃ በበኩላቸው መንግሥት ያሻሻለውና ወደ ሥራ ያስገባው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (E-LMIS) ቀደም ሲል የነበሩ የአሠራር ጉድለቶችን የሚቀርፍ መሆኑን አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ መካከል ያለውን የሥራ ገበያ በአግባቡ መጠቀም የምትፈልግ መሆኑን ገልጸው ለዚህም በኤጀንሲዎች በኩል የሚነሱ የሲስተም እና የምዝገባ ችግሮችን ለመፍታት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኤርሚያስ ተክሉ በበኩላቸው ለረጅም ጊዜ ሲንከባለሉ የነበሩ የአሠራርና የቴክኒክ ችግሮች እንዲሁም በኢትዮጵያ ካሉ አጋር ኤጀንሲዎች ጋር የነበሩ አለመግባባቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፈትተው የሥራ ስምሪቱ ይበልጥ እንዲሳለጥ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የውይይቱ ተካፋዮች በበኩላቸው በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ለኢትዮጵያውን በርካታ የስራ ዕድሎች መኖራቸውን ገልጸው በኤምባሲው እና በሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች (ተድቢሮች) መካከል ያለውን የቴክኒክ ግንኙነት በማጠናከር የሥራ ዕድል ፈጠራውን ለማሳደግ ተስማምተዋል።

በመጨረሻም የሠራተኛ ስምሪት ሂደቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገርና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ተግባራት ላይ ኤምባሲውና ኤጀንሲዎች ይበልጥ ተቀራርበው ለመስራት  መግባባት ላይ  በመድረስ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

ዘገባው፡- በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው

ታህሳስ  30/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtT
26👍3🎉1
ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጠው የክህሎት ማበልጸጊያ ስልጠና ውጤታማነትን እያሳደገ ነው

በኢንተርፕራይዝ ለተሰማሩ ዜጎች የሚሰጠው የክህሎት ማበልጸጊያ ስልጠና ውጤታማነትን እያሳደገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ገለጹ።

ኮሌጆቹ ከመደበኛ መማር ማስተማር ተልዕኳቸው ጎን ለጎን የወጣቶችን የሥራ ውጤታማነት የሚያዳብር የክህሎት ማበልጸጊያ ሥልጠናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አመራሮችም፤ የመዲናዋን ኢንተርፕራይዞች ውጤታማነት የሚያሳድግ ተከታታይ የክህሎት ድጋፍ ስልጠና እየሰጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዲን መስፍን ቸሩ፤ የኢንተርፕራይዞችን ምርታማነት የሚያጎለብት በክህሎት የበለጸገ የሰው ሃይል የማፍራት ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።

በተለይም በአውቶሞቲቭ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ በጨርቃጨርቅና የሌዘር ዘርፎች ላይ ትኩረት በማድረግ የኢንተርፕራይዞችን የምርትና አገልግሎት ጥራት የሚያስጠበቅ የክህሎት ስልጠና እየተሰጠ ነው ብለዋል።

የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዲን ቢንያም አወቀ(ዶ/ር)፤ በአሁኑ ወቅት የ1ሺህ 100 ኢንተርፕራይዞችን ውጤታማነት የሚያሻሽል የክህሎት ማበልጸጊያ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢንተርፕራይዝ ድጋፍና ክትትልም የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠን የተመዘገቡ ውጤቶችን በጥናትና ምርምር በመለየት ውስንነቶች እንዲቀረፉ የማድረግ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ሸላማ ንጉሱ፤ ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጠው የክህሎት ማበልጸጊያ ስልጠና የአምራች ኢንዱስትሪ ሽግግሩን በማሳለጥ በተኪ ምርት ውጤት እየተገኘ ነው ብለዋል።

በማኑፋክቸሪንግ፣ በከተማ ግብርና እና መሠል መስኮች ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ ማኅበራትን ማፍራት ያስቻለ ስልጠና እየተሰጠነ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ ሚደቅሳ ከበደ፤ የኮሌጆች የክህሎት ማበልፀጊያ ስልጠና ለኢንተርፕራይዞች ውጤታማነት መሰረት ነው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችም የሥራ ፈላጊ ዜጎችን የክህሎት ዝንባሌ ታሳቢ በማድረግ የሚሰጡት ትምህርትና ስልጠና ኢንተርፕራይዞችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።  ዘገባው የኢዜአ ነው።

ታህሳስ  30/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
21🥰3
በክቡር ዳንኤል ተሬሳ የተመራው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ቡድን ጅግጅጋ ገብቷል፡፡

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሥራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዳንኤል ተሬሳ የተመራው የሚኒስቴሩ የድጋፍና ክትትል ቡድን ያለፉት ስድስት ወራት የዘርፉ ተግባራት አፈጻጸም እና በዘርፉ ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸም ላይ ትኩረት በማድረግ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል ተብሏል፡፡

የሚኒስቴሩና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ያካተተው ይህ ቡድን ጅግጅጋ ከተማ ሲደርስ በክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

ክቡር አቶ ዳንኤል በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ቡድኑ በዘርፉ ታቅደው እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት የሚገኙበትን ሁኔታ በአካል በማየት ጠንካራ ሥራዎች በመለየት ወደሁሉም እንዲሰፉ የማድረግ እና ክፍተቶች ካሉ ደግሞ የማገዝ ሥራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

የድጋፍና ክትትሉ ዋናኛ አላማም ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የዜጎችን ህይወት የሚቀይሩ የሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድጉ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ድጋፍ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡

ድጋፍና ክትትሉ ነገ በይፋ ሲጀመር በጅግጅጋ ከተማ የሶማሌ ክልልን ጨምሮ የሀረሪ ክልል እና የድሬዳዋ ከተማ የዘርፉ አመራሮች በተገኙበት የመግቢያ ውይይት ይደረጋል ተብሏል፡፡
👍1110🎉1
በክልሉ 1 ሺህ 73 የሚሆኑ ዜጎች በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት  ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀምን ከባለድርሻ አካላት ገመገመ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ አብዱሰላም ሸንገል  የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን ከማናበብ አንፃር እና የሪፖርት ቅብብሎሽን ከማሳለጥ አንፃር የተሰሩ ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውንም  ጠቅሰዋል።

በተዋረድ ላሉ የዘርፉ ተቋማት የተሰጠው የዕውቅና እና የማበረታቻ ማርሃ ግብር በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ ሥራዎች በዋነኛት የሚጠቀስ መሆኑንም ቢሮ ኃላፊው አውስተዋል።

በቢልድግሉ ወረዳ በክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር በቢሮው የተሰሩ ስራዎችን ለአብነት አንስተው በመርሃ ግብሩ የአቅመ ደካሞችና አረጋዊያንን ቤት የመገንባትና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል።

በበጀት ዓመቱ በርካታ የረዥም እና የአጭር ጊዜ የክህሎት ስልጠናዎች መሰጠታቸውን እና 1 ሺህ 73 ለሚሆኑ ሥራ ፈላጊ ዜጎች ስልጠና በመስጠት በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት  ማሰማራት መቻሉም ተገልጿል፡፡

መረጃው የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው፡፡

ጥር 1/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtT
8👍4👌3
🚨 የአጭበርባሪዎች ነው🚨

👆 ከላይ የምትከተሉት የቴሌግራም ቻናል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን ሥምና አርማ የሚጠቀምና ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የሚያሰራጫቸውን ይዘቶች ኮፒ በማድረግ ያሰራጫል።

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን በተመለከተም በውስጥ መስመር 📞 ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ነው በማለትና በማናገር 🗣 ብር ላኩ 💸 በማለት በርካታ ሰዎችን እያጭበረበሩ እንደሚገኝ መረጃዎች እየደረሱን ይገኛል።

ስለሆነም  የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይፋዊ ገፅ ሰማያዊ ማረጋገጫ ባጅ ያለውና ከ45 ሺህ በላይ ተከታዮች አሉት።

https://t.me/FDRE_MoLSofficial

❗️ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የማህበራዊ ትስስር ገፆቹን በመጠቀምም ሆነ አገልግሎቱን ለማግኘት ምንም አይነት ክፍያ 💰 ላኩ እንደማይል እያሳሰብን፤ ለትክክለኛና ወቅታዊ የዘርፉ መረጃዎች ይፋዊ የቴሎግራም ቻናላችን ሰማያዊ ማረጋገጫ ባጅ ያለውን ብቻን እንዲከታተሉ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመነድዎ በማጋራት ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቁ ያድርጉ!

❗️በስህተት follow እያደረጋችሂ ያላችሁም unfollow በማድረግ ራሳችሁንና ወገኖቻችሁን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ።

🏛 የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
🔗 ለወቅታዊ ትኩስ መረጃ
🌍 Official Website: mols.gov.et
📘 Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
📲 Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
13👍5👏2🤩2🙏2👌2
በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ነቢሃ መሐመድ የተመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን በኦሮሚያ ክልል በይፋ ሥራውን ጀምሯል

የተጠሪ ተቋማት አመራሮችንና ባለሙያዎችን ያካተተው የሱፐርቪዥን ቡድን፤ ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የመክፈቻ ውይይት አካሂዷል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ነቢሃ መሐመድ በመግቢያ ውይይቱ  ላይ እንደገለፁት፤ ድጋፍና ክትትሉ የዘርፉ የሪፎርምና የመደበኛ ሥራዎች ውጤታማነትን የማረጋገጥ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን የማስፋት፣ ክፍተቶችን የመሙላትና ቅንጅታዊ አሠራርን ለማጠናከር ያለመ ነው።

ለሚቀጥሉት ተከታታይ ቀናት የሚካሄደው ይህ የድጋፍና ክትትል ሥራ የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን እንዲሁም ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ሥራዎች ውጤታማነት በአካል ተገኝቶ ምልከታ ያደርጋል።

📅 ጥር 1/2018 ዓ.ም
🏛️ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
🔗 ለወቅታዊ ትኩስ መረጃ
🌍 Official Website: mols.gov.et
📘 Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
📲 Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
🎵 TikTok: tiktok.com/@mols_official
🐦 Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
💬 WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbP
5👏5👍2
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ቡድን ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የመስክ ምልከታ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በክልሉ ባምባሲ ወረዳ በተለያዩ ዘርፎች የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ኢንተርፕራይዞች በቡድኑ አባላት ተጎብኝተዋል።

ጥር 1/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtT
8👍2
ድጋፍና ክትትሉ ለቀጣይ ሥራዎች ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተገለፀ

በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራውን ጀመሯል።

የሚኒስቴር መ/ቤቱ፣ የተጠሪ ተቋማት አመራሮችንና ባለሙያዎችን ያካተተው የሱፐርቪዥን ቡድን፤ ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የተመዘገበው የሥራ ዕድል ፈጠራ ውጤት አበረታች መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ገልፀዋል።

በክልሉ ወጣቶችን በማህበር በማደራጀትና የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማዘመን ረገድ የጀመራቸው ሥራዎች ለኢኮኖሚ ዕድገቱ ትልቅ አቅም መሆኑንም አመላክተዋል።

ድጋፋዊ ክትትሉ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተጀመሩ የትኩረት መስኮች በትክክል መሬት መውረዳቸውን ለማረጋገጥና ክፍተቶችን ለማረም እንደሚረዳ ገልጸዋል።

ክልሉ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር የተጣጣመ መዋቅራዊ አደረጃጀት መፍጠሩንም አድንቀዋል።

​የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አማካሪ አቶ ማሄ ቦዳ በበኩላቸው፤ ክልሉ እንደ አዲስ ከተዋቀረ በኋላ በብቁ ባለሙያዎችና አመራሮች መመራቱ ለተመዘገበው ስኬት ቁልፍ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል።

ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሚደረገው ድጋፋዊ ክትትልና ሪፖርትን መሠረት ያደረገ ውይይት ለቀጣይ ሥራዎች ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር የጠቆሙት አቶ ማሄ በየወረዳው የተደራጁ ማህበራት አገራዊ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ረገድ ያላቸው ተሞክሮ ለሌሎች አካባቢዎች ተምሳሌት እንደሚሆን ተናግረዋል። መረጃው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ነው።

📅 ጥር 1/2018 ዓ.ም
🏛️ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
🔗 ለወቅታዊ ትኩስ መረጃ
🌍 Official Website: mols.gov.et
📘 Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
📲 Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
🎵 TikTok: tiktok.com/@mols_official
🐦 Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
💬 WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbP
17👌6👍2🤩1
ክህሎትን መሰረት ያደረገ የሥራ ዕድል ፈጠራ ቀጣይነት ያለው የዜጎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

በክቡር ዳንኤል ተሬሳ የተመራው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ቡድን ከሱማሌ ክልል፣ ከሀረሪ ክልል እና ከድሬዳዋ አስተዳደር የዘርፉ አመራር አካላት ጋር በጅግጅጋ ከተማ የመግቢያ ውይይት አካሂዷል፡፡


የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ኢብራሂም ኡስማን በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት መንግስት ከፍተኛ የሥራ ዕድል የመፍጠር አቅም ያላቸው ግብርና፣ ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪ እና አገልግሎት የመሳሰሉ ዘርፎች እየሠራ በሚገኘው ሥራ በሀገራችን በየቦታው ከፍተኛ መነቃቃት እየታየ ይገኛል፡፡

በክልሉም በግብርና፣ በኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፎች ለዜጎች በጣም በርካታ የሥራ ዕድሎች እየተፈጠረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ተግባራዊ እያደረገው የሚገኘው ክህሎት መሰረት ያደረገ የሥራ ዕድል ፈጠራ ቀጣይነት ያለው የዜጎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዳንኤል ተሬሳ በበኩላቸው ሚኒስቴሩ የተሰጡት ተልዕከዎች ቀጥታ ከማክሮ ኢኮኖሚ እድገት ጋር የተያያዙ፣ የዜጎችን ህይወት የሚቀይሩ፣ ማህበራዊ ፍትህ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያመጡ ናቸው ብለዋል፡፡

በመሆኑም ሚኒስቴሩ በተቋም ግንባታ፣ በክህሎት ልማት፣ በሥር ዕድል ፈጠራ እና በኢንዱስትሪ ሰላም ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት አዳዲስ እሳቤዎች ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ገልጸው ይህ ድጋፍና ክትትልም የእሳቤዎቹ ተፈጻሚነት እታች ድረስ ወርዶ በማረጋገጥ ጠንካራ ጎኖችን ለማስፋት እና ክፍቶች እንዲስተካከሉ ለማድረግ የሚካሄድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጥር 1/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtT
4👍2👏2👌1
🚨 የአጭበርባሪዎች ነው!🚨

እንዳይታለሉ - አንፎሎው ያድርጉ

👆 ከላይ የምትከተሉት የቴሌግራም ቻናል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን ሥምና አርማ የሚጠቀምና ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የሚያሰራጫቸውን ይዘቶች ኮፒ በማድረግ ያሰራጫል።

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን በተመለከተም በውስጥ መስመር 📞 ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ነው በማለትና በማናገር 🗣 ብር ላኩ 💸 በማለት በርካታ ሰዎችን እያጭበረበሩ እንደሚገኝ መረጃዎች እየደረሱን ይገኛል።

ስለሆነም  የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይፋዊ ገፅ ሰማያዊ ማረጋገጫ ባጅ ያለውና ከ46 ሺህ በላይ ተከታዮች አሉት።

https://t.me/FDRE_MoLSofficial

❗️ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የማህበራዊ ትስስር ገፆቹን በመጠቀምም ሆነ አገልግሎቱን ለማግኘት ምንም አይነት ክፍያ 💰 ላኩ እንደማይል እያሳሰብን፤ ለትክክለኛና ወቅታዊ የዘርፉ መረጃዎች ይፋዊ የቴሎግራም ቻናላችን ሰማያዊ ማረጋገጫ ባጅ ያለውን ብቻን እንዲከታተሉ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመነድዎ በማጋራት ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቁ ያድርጉ!

❗️በስህተት follow እያደረጋችሂ ያላችሁም unfollow በማድረግ ራሳችሁንና ወገኖቻችሁን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ።

🏛 የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
🔗 ለወቅታዊ ትኩስ መረጃ
🌍 Official Website: mols.gov.et
📘 Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
📲 Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
7👍4🙏2🎉1
አዲሱን የዘርፉን እሳቤ ወደ ተግባር የማስገባት  ጅምር

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል  የመስክ ምልታ እያደረገ የሚገኘው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር  የድጋፍና ክትትል  ቡድን በመጀመሪያ ቀን ውሎው በተለያየ ዘርፍ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸውን ኢንተርፕራይዞችን፣ እና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችን  ጎብኝቷል::

በባማባሲ ወረዳ በተካሄደው ጉብኝት  የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና የአካባቢው ማህበረሰብ በግብርና ሥራዎች ላይ የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ተስተውሏል፡፡

ተፈናቃዮችም ሆኑ ተቀባይ የማህበረሰብ አባላት ከአካባቢያቸው  ሀብት በጋራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከአጋር አካላት በተገኙ የፋይናንስ ድጋፍ  በዶሮና ፍየል እርባታ እንዲሁም በአትክልትና ፍራፍሬ ማምረት ላይ እንዲሰማሩ መደረጉም በጉብኝቱ ላይ ተገልጿል፡፡

በግብርና ሥራ ላይ የተሠማሩ ኢንተርፕራይዞች ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በክልሉ ከሚገኙ የግብርና ኮሌጆች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ የማመቻቸት ሥራ መሰራት እንደሚኖርበት ከድጋፍና ክትትል ቡድኑ  ሃሳብ ተሰጥቷል፡፡

ኢንተርፕራይዞች ከአጋር አካላት  ከሚገኝ  የፋይናንስ ድጋፍ  በተጨማሪ የብድር አገልግሎትን በማመቻቸት በቋሚነት የሚያድጉበት እድል ከመፍጠር አንፃር የክልሉ የሥራና ክህሎት ቢሮ ተገቢው ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡

የድጋፋና ክትትል ቡድኑ በአሶሳ የግብርና ኮሌጅ ባደረገው ክትትል ኮሌጁ  ግብርናውን ለማዘመን የጠብታ መስኖ እና የግሪን ሃውስ አገልግሎትን  ከማስተዋወቅ አንፃር እየሠራቸው የሚገኙ ሞዴል ሥራዎች ላይ ምልከታ ተደርጓል፡፡

በአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተደረገው ምልከታ ኮሌጁ  ከሚሰጣቸው  መደበኛና አጫጭር  ስልጠናዎች ጎን ለጎን   የገጠር ሞዴል መንደሮችን በክልሉ ለመመስረት  የሚያስችል  የጡብ እና ለከተማ የኮሪደር ልማት የሚውል ቴራዞ በስፋት  በማምረት ላይ እንደሚገኝ ተስተውሏል፡፡

ኮሌጆቹ   አዲሱን የዘርፉን እሳቤ መሠረት በማድረግ ገበያ መር ስልጠናዎችን  መስጠትና የኢንተርፕራይዝ መፈልፈያ ማዕከል የመሆን ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚኖርባቸው በድጋፍና ክትትል ቡድኑ ተጠቁሟል፡፡

ጥር 2/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtT
👏21
በኢፌድሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራ የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች በአርባምንጭ ከተማና በጋሞ ዞን በዘርፉ የተከናወኑ ስራዎችን  በሥፍራው ተገኝተው እየተመለከቱ ይገኛሉ።

ልዑካን ቡድኑ በአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ጉብኝት ያደረገ ሲሆን፣ በቆይታቸውም የቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎች፤​የተደራጁ ማህበራት እንቅስቃሴና የካይዘን አተገባበር፤​የጋርመንት ስራዎች እና የጄኔራል ፋብሪኬትድ ሜታል ወርክሾፕ ተግባራት፤ የባዮ ሜዲካል ክፎሎችና አተገባበር ​እንዲሁም አጠቃላይ የሥራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች ተጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የማህበራት አደረጃጀትና የስራ ዕድል ፈጠራ፤ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ የስራ ስምሪቶች፤ ሀገራዊ ኢኒሼቲቮችን የመተግበር ሂደት ትኩረት ተሰጥቷቸዋል።

አጫጭር ስልጠናዎች እና የሥራ ስምሪቱ ጋር በተያያዘ የተከናወኑ ተግባራትና ክህሎት መር የስራ ስምሪት ከሚሰራው ስራ አስቀድሞ ስለስራው ግንዛቤ የመፍጠር እንደመሆኑ በዘርፉ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም በምልከታው​ የኢፌድሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ  አንስተዋል።

የስልጠና ጥራት ተደራሽነት እና የገቢ ማመንጫ ስራዎች ላይም ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባም አንስተዋል።

ተቋሙ ያልተገቡ ስልጠናዎችን በመዝጋት ተፈላጊና ለወጣቱ የስራ ዕድል በሚፈጥሩ የስራ ስምሪቶች ላይ ማተኮሩ አበረታች መሆናቸውም ተነስቷል ።

የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ዲን አቶ በዛብህ ዳርዛ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትና መልካም አጋጣሚዎችን እና ተግዳሮቶችን ለቡዱኑ አቅርበዋል ።

የሙያ ምልከታዎችና ውይይቶች ለዘርፉ እድገትና ለወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።

ጉብኝቱ  በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሚታዩ ጠንካራ ጎኖችን ለማጠናከርና ክፍተቶችን በጋራ ለመፍታት ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።  መረጃው የክልሉ ነው።

ጥር 1/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtT
7👍6
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የተመራው የድጋፍና ክትትል ቡድን  በአሶሳ ከተማ የሚገኙ የሥራ ማዕከላት፣ ኢንተርፕራይዞችና  ኢንዱስትሪዎች ላይ ምልከታ አድርጓል፡፡

በኢንዱስትሪዎች ላይ በተካሄደው ጉብኝት ለሙያ ደህንነትና ጤንነት፣ የሠራተኞች ማህበር  ለማደራጀትና ለምርታማነት ውይይት ተገቢው ትኩረት መሰጠት እንደሚኖርበት   በክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ አስተያየት ተሰጥቷል፡፡

ለኢንተርፕራይዞችን አስፈላጊውን መንግስታዊ ድጋፍ ለማድረግ ራሱን የቻለ የሥራ ማዕከል መቋቋም እንደሚኖርበትም ተመላክቷል፡፡

የማደግ አለኝታ ላላቸው ኢንተርፕራይዞች ትኩረት በመስጠት  ተገቢውን መንግስታዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እና የሙያ ደህንነትና ጤንነት ላይ የኢንተርፕራይዞችን ግንዛቤ ማሳደግ  እንደሚገባም በድጋፍና ክትትል ቡድኑ ተመላክቷል፡፡ 

ጥር 2/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtT
4👌1
ምልከታው ስልጠናን ከገበያው ፍላጎት ጋር በማጣጣም ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑ  ተጠቆመ

በኦሮሚያ ክልል ድጋፍና ክትትል በማድረግ ላይ የሚገኘው የሱፐርቪዥን ቡድን፣ በሸገር ከተማ አስተዳደር የሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል።

በምልከታው ላይ የኦሮሚያ የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሸገር ከተማ የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ጽህፈት ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሞን  ጥሩነህ የተቋሙ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ለልዑካን ቡድኑ አቅርበዋል።

የመስክ ምልከታው በስልጠና ተቋማት እና በኢንዱስትሪው መካከል ያለውን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፣ በሂደት ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለይቶ በዘላቂነት ለመፍታትና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ፋይዳ እንዳለው ተመላክቷል።

ጉብኝቱ በዋናነት የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን ከወቅታዊው የገበያ ፍላጎት ጋር በማጣጣም፣ ወጣቶች በቂ ክህሎት ኖሯቸው ወደ ሥራ ዓለም እንዲቀላቀሉ ለማድረግ እንዲሁም በዘርፉ የተቀረፁ የሪፎርም አጀንዳዎች ውጤታማነትን ለማላቅ የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑ ተገልጿል።

የልዑካን ቡድኑ በሰበታ ከተማ በሚኖረው ቆይታ ከኮሌጁ ባሻገር፣ በከተማዋ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችን፣ ኢንዱስትሪዎችንና አጠቃላይ የሥራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴዎችን ይመለከታል።

ጥር 1/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtT
12👍2👏1
የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (E-LMIS) ዙሪያ የሥልጠና እና የውይይት መድረክ ተካሄደ፤

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የE-LMIS  ፕሮጀክት ፅ/ቤት ቡድን በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጀነራል ጽሕፈት ቤት በመገኘት፣ በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ አጠቃቀምና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከዲፕሎማቶች ጋር የሥልጠና እና የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስል ጀነራል ክቡር አቶ ዘሪሁን መገርሳ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፋት መልዕክት ሕጋዊና ምቹ የውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪትን ማሳደግ፣ የዜጎችን መብትና ጥቅም ማስከበር እንዲሁም ሕጋዊ የውጭ ሀገር ምንዛሬ (ሬሚታንስ) ፍሰትን ማቀላጠፍ የሚያስችሉ አሠራሮችን መዘርጋት ከዋነኛ የሚሲዮኑ ተግባራት አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ሥልጠናም እነዚህን ግቦች ይበልጥ ለማጠናከር ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት የፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ አለቃ አማካኝነት የቀረበው ገለጻና ሥልጠና፣ በዋናነት የመረጃ ሥርዓቱን በመጠቀም በ2017 በጀት ዓመት በተከናወኑ ተግባራት እና በ2018 በጀት ዓመት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለማከናወን በተያዙ ዕቅዶች ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

በተጨማሪም ከመረጃ ሥርዓቱ ጋር በተያያዘ እየተከናወኑ ያሉ የማሻሻያ ሥራዎች፣ በተለይም በሥርዓቱ "Version 3" ላይ የተካተቱ አዳዲስ ፋይዳዎች ለዲፕሎማቶች ቀርበዋል።

ከእነዚህ ማሻሻያዎች መካከል የልዩ ጥያቄ (Special Request) አዲስ ፊቸር፡ በሲስተሙ ላይ በልዩ ፓኬጅነት የቀረበው አሰራር፣ በከፊል የሰለጠኑና የሰለጠኑ የሰው ኃይል የሥራ ሥምሪት ሂደት ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ፈጣንና ምቹ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑ ተብራርቷል።

ተያይዞም በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሚገኙ የቅጥር ኤጀንሲዎች ይህንን አዲስ አሠራር እንዲጠቀሙ መረጃ ተላልፏል።

በመጨረሻም በሥልጠናው ወቅት በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ ክቡር ቆንስል ጀነራል አቶ ዘሪሁን መገርሳ በቀጣይ የተቀመጡ ዕቅዶችን ለማሳካትና ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የቆንስላ ጽ/ቤቱ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር ይበልጥ ተቀናጅቶ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ዘገባው በዱባይና በሰሜን ኤምሬትስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ /ቤት ነው፡፡

ጥር 2/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtT
8👌2