FDRE Education and Training Authority
18.6K subscribers
2.63K photos
31 videos
45 files
376 links
በኢፌድሪ የትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን
http://www.eta.et/

9799 "በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ነጻ የስልክ ጥሪ ማዕከል"
Download Telegram
ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ!
እንኳን ለነብዩ መሐመድ የልደት(ለመውሊድ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!
መልካም በዓል!

የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።
12👎3
በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 መሠረት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በውጭ ሀገር ተምረው የመጀመሪያ ዲግሪ በሀገር ውስጥ መማር ለሚፈልጉ ማቅረብ ያለባቸው ህጋዊ ሰነዶች፡-

የአቻ ግመታ አገልግሎትን ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ህጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
** የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት ወይም ዲፕሎማ፤
** ማስረጃው በተገኘበት ሀገር የዲግሪ የትምህርት መስክ ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያለው የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት ወይም ዲፕሎማ እና ትራንስክሪፕት ፤
** የአመልካቹ የትምህርት ማስረጃ ትምህርቱን ከተከታተለበት ሀገር ስርዓተ ትምህርት ውጪ በሌላ ሀገር ስርዓተ ትምህርት መሠረት ከሆነ የመግቢያ ውጤቱ የሚወሰነው አመልካቹ ትምህርቱን በተከታተለበት የትምህርት ስርዓት ውጤት አወሳሰን መሠረት ይሆናል፤
** አመልካቹ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኝ እና የኢትዮጵያ መንግስት ፈቃድ በሰጠው ዓለም አቀፍ ወይም ማህበረሰብ ትምህርት ቤት የተማረ ከሆነ ከትምህርት ቤቱ የድጋፍ ደብዳቤ ያቀርባል፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።
25
በዓለም ዓቀፍ፣ የማህበረሰብ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመና የበጎ አድራጎት ትምህርት ቤቶች ፈቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪያ 992/2016 መሠረት ለዓለም ዓቀፍ ትምህርት ቤት ፍቃድ የሚሰጠው የሚከተሉት መስፈርቶች ሲሟሉ ነው፡-

** የኢንቨስትመንትፍቃድ፤
**
የንግድ ፍቃድ፤ ወይንም የስራ ፍቃድ
** ስርዓተ-ትምህርቱ ከተዘጋጀበት በሀገሪቱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ለማስተማር የተሰጠ ፍቃድ ወይንም ስምምነት፤
** የትምህርት ቤቱ መተዳደሪያ ደንብ እና መመስረቻ ሰነድ፣
** ለትምህርት ቤት የሚመጥን አካዳሚያዊና አስተዳደራዊ አደረጃጀትን የሚያሳይ፣ ስለተማሪዎች የትምህርት ክፍያ መምህራን ሊያሟሉት ስለሚገባው : አነስተኛ መመዘኛ ፣ ነጻ የትምህርት እድል ስለሚሰጡበት ሁኔታ፣ የመምህራን እንዲሁም የተማሪዎች መብትና ግዴታ፣የተማሪዎችን የቅበላ ስርዓት የሚመለከት ይዘት ያለው መተዳደሪያ ደንብ፤
** የትምህርት ቤቱን ደረጃ የሚመጥን የትምህርት ቤት ግቢና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ማደራጀቱን ሲረጋግጥ ፍቃድ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።
14🕊2🥱2👎1
በዓለም ዓቀፍ፣ የማህበረሰብ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመና የበጎ አድራጎት ትምህርት ቤቶች ፈቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪያ 992/2016 መሠረት የማስፋፊያ ፈቃድ፡-

** ፈቃድ ተሰጥቶት በስራ ላይ ያለ የዓለም ዓቀፍ እና በውጭ ባለሃብት የተቋቋመ ትምህርት ቤት ደረጃውን ማሳደግ ሲፈልግ የኢንቨስትመንት ፈቃድን መሠረት አድርጎ ለባለሥልጣኑ ሲያመለክት የትምህርት ዓመቱ ከመጀመሩ ከ3 ወራት በፊት አስፈላጊው ምልከታ ተደርጎለት ጥያቄው አሳማኝ ሆኖ ሲገኝ የደረጃ ማሳደግ ፈቃድ ይሰጣል፤
*** ፈቃድ ተሰጥቶት በስራ ላይ ያለ የማህበረሰብ ትምህርት ቤት ደረጃውን ማሳደግ ሲፈልግ የትምህርት ዓመቱ ከመጀመሩ ከ3 ወራት በፊት ለባለሥልጣኑ በሚያቀርበው ጥያቄ መሠረት የትምህርት ቤቶች የሱፐርቪዥን ቡድን አስፈላጊው ምልከታ ተደርጎ ጥያቄው አሳማኝ ሆኖ ሲገኝ የማስፋፊያ ፍቃድ ይሰጣል።
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።
2
በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በአቤቱታ እና ቅሬታ አፈታ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

ነሀሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለባለሥልጣኑ ሠራተኞች በአገልግሎት አሰጣጥ፣በአቤቱታ እና ቅሬታ አፈታ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የስልጠናው ዓላማ ከሥራ ክፍል ኃላፊዎች ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ ባለሙያዎችና ሠራተኞች የደንበኛ አያያዝ ክህሎታቸውን አዳብረው የተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት እና የደንበኞች እርካታን በተግባር እንዲያሳድጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በባለሥልጣኑ የተቋማዊ ለውጥ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ደስታ ተ/አረጋይ ደንበኛን በፈገግታ፣ በትህትና እና በፍጥነት መቀበል የአገልግሎቱን ጥራት ግማሽ መንገድ የሚያሳካ መሆኑን ገልጸው አገልግሎት በሚሰጠበት ጊዜ ንቁ አዳማጭ መሆን ፤የተገልጋዩን ስሜት መረዳት ፤ግልጽ መረጃ መስጠት ፤ አዎንታዊ የአካል እንቅስቃሴ መገለጫ የሆኑትን ፈገግታና ትህትና ማሳየት፣ የሥራ ቦታን ለአገልግሎት ምቹና ዝግጁ ማድረግ ፣ ቀልጣፋ እና ፈጣን ምላሽ መስጠት እንዲሁም ደንበኛን በአግባቡ የማስተናገጃ ደረጃዎች የሆኑትን አቀባበል፣ ፍላጎት መለየት፣አገልግሎትን በስታንዳርዱ ላይ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ፤አቅጣጫ መጠቆም እና ደንበኛን በአክብሮትና በፍቅር መሸኘት የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ፣ ቅሬታዎችን ለመፍታት እና የአገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በስልጠናው ላይ ስለደንበኛ አያያዝ መሠረቶች፤ ስለደንበኛን የማስተናገድ ደረጃዎች፤ ስለቅሬታዎችን የመደራደር ዘዴ፤ስለደንበኞች እርካታመለኪያ እና ስለአስቸጋሪ ግንኙነቶች ማስተዳደር ዙሪያ ሰፋ ያላ ማብራሪያና ገለጻ ተደርጓል፡፡
የቀረቡትን መነሻ ሀሳቦች መሠረት በማድረግ በተደረገው ውይይት ላይ ለተነሱ ሐሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች በባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ታምሩ መስፍን፣ የሥራ አዘመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት ወ/ሮ ጥሩወርቅ ታደሰ እና የተቋማዊ ለውጥ ስራ አስፈጻሚ በሆኑት አቶ ደስታ ተ/አረጋይ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።
4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ አገልግሎት ለማግኘት እንዴት ማመልከት እንችላለን?
ይህን ቪዲዮ ይከታተሉ👇👇
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት www. neta.gov.et ይከታተሉ።
15👍2