ፋና አማርኛ FBC Amharic
496 subscribers
446 photos
447 links
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አማርኛ ዜናዎች

For English: https://t.me/fbcenglish
Download Telegram
ቦርዱ የትግራይ ክልል ምክር ቤት ክልላዊ ምርጫ ለማድረግ ያቀረበውን ጥያቄ እንደማይቀበል አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የትግራይ ክልል ምክር ቤት ክልላዊ ምርጫ ለማድረግ ያቀረበውን ጥያቄ እንደማይቀበል አስታወቀ።

ቦርድ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ የትግራይ ክልል ምክር ቤት “ኮቪድ 19ኝን እየተከላከለ 6ኛውን ዙር ምርጫ ለማካሄድ የወሰነ በመሆኑ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በሚያዘው መሰረት ቦርዱ ውሳኔውን ተቀብሎ ምርጫውን እንዲያስፈፅም፣ ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስፈልግ የሰው ሃይልና ሎጂስቲክስ ዝግጅት እንዲያደርግ እና ውሳኔውን ለምክር ቤቱ እንዲያሳውቀን” ሲል ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር አስታውሷል።

6ኛው ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድበት ጊዜ እንዲራዘም ምክንያት የሆነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሁኔታ እንደገና ተገምግሞ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩ እስከረጋገጥ ድረስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በየትኛውም የሃገሪቱ ክልል ምርጫ አያካሂድም ብሏል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መመዝገብ፣ መቆጣጠር እና ማስተዳደር፣ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳን ማውጣት፣ የምርጫውን ከተጽእኖ ነጻ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ማስፈጸም ስልጣን ያለው ብቸኛ ተቋም መሆኑንም አንስቷል።

https://www.fanabc.com/ቦርዱ-የትግራይ-ክልል-ምክር-ቤት-ክልላዊ-ም
የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ምረቃ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ምረቃ እየተካሄደ ነው።

በፋብሪካው ምርቃ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ሸገር ዳቦ በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ የሚያመርት ሲሆን፥ በቀን በሶስት ፈረቃ እስከ 2 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርት መሆኑ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ በአቃቂ ክፍለ ከተማ በ41 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ፋብሪካው፤ ከዳቦ በተጨማሪም የስንዴ ዱቄት ፋብሪካ እንዳለውም ይታወቃል።

https://www.fanabc.com/የሸገር-ዳቦ-ፋብሪካ-ምረቃ-ስነ-ስርዓት-እየ
ኢራን አሜሪካ ከኒውክሌር ስምምነቱ በመውጣቷ ሳቢያ ለደረሰባት ኪሳራ ካሳ የምታገኝ ከሆነ መነጋገር እንደምትችል አስታወቀች

ቴህራን አሜሪካ ከኒውክሌር ስምምነቱ በመውጣቷ ሳቢያ ለደረሰባት ኪሳራ ካሳ የምትከፍልና ይቅርታ የምትጠይቅ ከሆነ ከዋሽንግተን ጋር መነጋገር እንደምትችል አስታወቀች።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋሽንግተን ከኢራን ጋር በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ዙሪያ መወያየት ትፈልጋለች በሚል ተደጋጋሚ የእንወያይ ጥያቄዎችን ማቅረባቸው ይታወሳል።

ፕሬዚዳንቱ ሃገራቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደርና ከፕሬዚዳንት ሮሃኒ ጋር በአካል ተገናኝተው የመወያያት ፍላጎታቸውንም በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል።

ኢራን በበኩሏ የአሜሪካን ግብዣ ለማስመሰል የሚደረግ ነው ስትል በተደጋጋሚ ስታጣጥለው ቆይታለች።

የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሮሃኒም “አሜሪካ ከ2015ቱ የኒውክሌር ስምምነት በመውጣቷ ምክንያት ቴህራን ለደረሰባት ጉዳት ዋሽንግተን ይቅርታ ጠይቃ ማካካሻ የምትሰጥ ከሆነ አሁንም ቢሆን ከዋሽንግተን ጋር መነጋገር እንችላለን” ብለዋል።

https://www.fanabc.com/ኢራን-አሜሪካ-ከኒውክሌር-ስምምነቱ-በመው
ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ

በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባውና በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ የሚያመርተው ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ።

በፋብሪካው ምርቃ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በምረቃው ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ፋብሪካው የዳቦ ፋብሪካ ብቻ ሳይሆን፤ በምግብ ራሳችንን የመቻል ፍላጎታችንን፣ ከድህነት የመውጣት ጥማትን እና የብልፅግና ጎዳናን አመላካች ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ በ10 ወራት ፋብሪካ ገንብቶ ማጠናቀቅ የሚታሰብ አልነበረም፤ በተለይም ለሚድሮክ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ ሚድሮክ ከነበረበት ድክመት ተላቆ ፋብሪካውን በዚህ ፍጥነት ማጠናቀቅ መቻሉ ለሌሎችም ትምህርት የሚሆን ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አክለውም መንግስት በቀጣይ 2 ዓመታት ስንዴን ከውጭ ማስገባት የማቆም ፍላጎት እንዳለው በመግለጽ፤ ለዚህም የሙከራ ምርቶች መጀመራቸውን አስታውቅዋል።

https://www.fanabc.com/የሸገር-ዳቦ-ፋብሪካ-ምረቃ-ስነ-ስርዓት-እየ
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ሱዳን አቀኑ

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ሱዳን ማቅናታቸው ተነገረ።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጉብኝቱን የሚያደርጉት በሱዳን የሽግግር መንግስት ሉአላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በቀረበላቸው ግብዣ ነው።

በካርቱም ቆይታቸውም የሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት የሚያደርጉ መሆኑን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ በሱዳን ቆይታቸውም የኤርትራን እና የሱዳንን የሁለትዮሽ ትብብሮችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ላይ የሚመክሩ ሲሆን፥ በቀጠናዊ ትብብር እና ውህደት ዙሪያ ውይይቶችን እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።

https://www.fanabc.com/የኤርትራ-ፕሬዚዳንት-ኢሳያስ-አፈወርቂ-ለ
በደቡብ ክልል የአስፈጻሚ ተቋማት ግምገማ ተጀመረ

በደቡብ ክልል የአስፈጻሚ ተቋማት የ2012 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የስራ ክንውን ግምገማ ተጀመረ ።

የክልሉ መንግሥት አስፈጻሚ ተቋማት በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፍ በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸውን ተግባራት እንደሚገመግሙ ተገልጿል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ÷በክልሉ ለውጡን ተከትሎ የተፈጠሩ ችግሮችን በመፍታት የህዝብን ደህንነትና ሠላም ለማረጋገጥ መንግሥት የወሰዳቸው እርምጃዎች ውጤታማ ናቸው ብለዋል።

ከአደረጃጀት፣ መልካም አስተዳደርና ልማት ጥያቄዎች ጋር ተያይዞ ተፈጥሮ የነበረው የተዛባ አመለካከትና አለመተማመን ህዝብን በማዳመጥ ለመመለስ ጥረት ሲደረግ መቆየቱንም አንስተዋል።

አቶ ርስቱ አያይዘውም ከፌዴራል መንግስት ጋር በመቀናጀት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉንና የጸጥታ ችግር ከምንጩ ለማድረቅ የተከናወኑ ስራዎች መልካም እንደነበሩ አስረድተዋል።

በተለይ የህዝብ የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በተደረገው ጥረት የዘገዩ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት እንዲበቁ መመቻቸታቸውንም አስታውቀዋል።

መንግሥት የህዝብን እርካታ ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ የፈጠረው ችግር ፈታኝ እንደነበር ጠቅሰው ÷”ስርጭቱን ለመቆጣጠር ህዝብና መንግሥት ርብርብ እያደረጉ ነው ” ብለዋል።

የክልሉ መንግስት አስፈጻሚ ተቋማት የበጀት ዓመቱ የስራ ክንውን ግምገማ ዓላማ የነበሩ መልካም ተሞክሮዎችን ለማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም በቀጣዩ ዘመን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲመቻቹ ለማስቻል መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

https://www.fanabc.com/በደቡብ-ክልል-የአስፈጻሚ-ተቋማት-ግምገማ
በደቡብ አሜሪካና በካሪቢያን በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ አልፏል

በደቡብ አሜሪካና በካሪቢያን በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ ማለፉ ተነገረ።

ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በብራዚል መመዝገቡን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም በሜክሲኮ ከ23 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው።

በሁለቱ ሃገራት ከቫይረሱ ጋር ተያይዞ ምንም አይነት የእንቅሳቀሴ ክልከላም ሆነ ገደብ አልተጣለም።

ይህም ለቫይረሱ መዛመት አይነተኛ ሚና እንዳለው ባለሙያዎች ገልጸዋል።

ደቡብ አሜሪካ አሁን ላይ ከየትኛውም አካባቢ በበለጠ የቫይረሱ መገኛ ሆኗል ነው የተባለው።

ቫይረሱ ከፍ ያለ ጉዳት ያስከትል እንጅ አሁንም በከፍተኛ ደረጃ ተዛምቷል የሚባልበት ደረጃ ላይ አለመድረሱን ባለሙያዎች እየገለጹ ነው።

ይህ ደግሞ ቀጣዮቹን ሳምንታት ከባድ ያደርገዋል ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

https://www.fanabc.com/በደቡብ-አሜሪካና-በካሪቢያን-በኮሮና-ቫይ
የአለም ኢኮኖሚ ክፉኛ እየባሰ እንደሚመጣ የዓለም ምጣኔ ሀብት (IMF) ትንበያ ገለጸ

ዓለም አሁን ካለው የኢኮኖሚ ችግር በባሰ ሁኔታ እንደሚቀጥል የዓለም ምጣኔ ሃብት ግምቱን አስታውቋል፡፡

ዓለም አቀፉ የዓለም ምጣኔ ሃብት ተቋም በዚህ ዓመት የአለም ኢኮኖሚ 4ነጥብ 9 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅሶ በዚህም ድርጅቱ የኮሮና ቫይረስ ካስከተለው ችግር ለመውጣት እየታገለ መሆኑን አሰታውቋል፡፡

አነስተኛ እና ትላልቅ የንግድ ድርጅቶችና ኢኮኖሚያቸው በዚህ ወቅት ክፉኛ እየተጎዱ መሆናቸውን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ የሚያደርገው ድጋፍም እንዲሁ በቀጣዩ ዓመት ሊቀንስ እንደሚችል ነው ግምቱን ያስቀመጠው ፡፡

አሁን ከሚመጣው ሚያዝያ ትንበያ ጋር ሲነፃፀር በሚቀጥለው አመት የአለም ዕድገት በ5ነጥብ4 ዝቅ ሊል ይችላል ነው የተባለው፡፡

ኢኮኖሚስቶች ድንበሮች ሲዘጉ ፣ የንግድ ተቋማት መዘጋት እና የአለም አቀፍ ምጣኔ ሀብት ዘርፎች በሙሉ መዘግየት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የሚደረጉ እርምጃወችን በአግባቡ በመተግበር ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቀውን የኢኮኖሚ ውድቀት ለመቋቋም እየተሞከረ ነው ብለዋል፡፡

ድርጅቱ ባወጣው የቅርብ ጊዜ የአለም ኢኪኖሚ ሁናቴን የሚያሳይ እትም ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ለረጅም ጊዜ የእንቅስቃሴ እግድ መጣል ኢኮኖሚው ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ላይ ጥንቃቄ እንዲወሰድ አስጠንቅቀዋል።

https://www.fanabc.com/የአለም-ኢኮኖሚ-ክፉኛ-እየባሰ-እንደሚመጣ
የ114 የእድሜ ባለፀጋ ከኮሮና ቫይረስ ሙሉ በሙሉ አገግመው ከኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ወጡ

የ114 የእድሜ ባለፀጋ ከኮሮና ቫይረስ ሙሉ በሙሉ አገግመው ከኤካ ኮተቤ ሆስፒታል መውጣታቸው ተገለፀ።

አዛውንቱ ለተጨማሪ ህክምና የካቲት 12 ሆስፒታል እንደሚገኙ የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ያሬድ አግደው በፈስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው አዛውንቱ በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ እንዲመገኙም በመግለፅ ለዚህ ስኬትም ለጤና ባለሞያዎች ምስጋና አቅርበዋል።

https://www.fanabc.com/የ114-የእድሜ-ባለፀጋ-ከኮሮና-ቫይረስ-ሙሉ-በሙ
ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚያስችል አለም አቀፍ የበይነ መረብ ዘመቻ ሊካሄድ ነው

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚያስችል አለም አቀፍ የበይነ መረብ ዘመቻ በኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች እና የኢትጵያ ወዳጆች ሊካሄድ ነው።

አለም አቀፍ ዘመቻው የተባበሩት ኢትዮጵያዊያን ለሰላምና እርቅ የተሰኘው ድርጅት ከዓለም አቀፉ የእውቀት ልውውጥ ኔትወርክ ጋር በተመባበር የሚያዘጋጁት ነው።

የዘመቻው ዓላማ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስለህዳሴ ግድብ እና የድርድር ሂደት ግንዛቤን ለመፍጠር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

እንዲሁም የታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለማጠናቀቅ ገቢ ለማሰብሰብ የሚያስችል ዘመቻ መሆኑ ተጠቁሟል።

https://www.fanabc.com/ለታላቁ-ህዳሴ-ግድብ-ግንባታ-ድጋፍ-ለማሰባ
ጠ/ሚ ዐቢይ ከሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዲኤታዎች ጋር በእንጦጦ አረንጓዴ ዐሻራን አሳረፉ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዲኤታዎች ጋር ዛሬ በእንጦጦ አረንጓዴ ዐሻራን አሳርፈዋል።

ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ÷በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ ብለዋል።

አገር አቀፉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በሀዋሳ ከክልል እና ፌደራል መንግስታት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ከአካባቢው ሀገር ሽማግሌዎችጋር በመሆን በጋራ በታቦር ተራራ ላይ ማስጀመራቸው ይታወሳል።

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል እቅድ ተይዟል።

https://www.fanabc.com/ጠ-ሚ-ዐቢይ-ከሚኒስትሮች-እና-ሚኒስትር-ዲኤ
ጠ/ሚ ዐቢይ “እንሥራ” የሸክላ ስራ ማዕከልን ጉበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ “እንሥራ” የሸክላ ስራ ማዕከልን በዛሬው እለት ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ጉብኝቱን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፥ “እንሥራ በተሰኘው አዲስ የሸክላ ሥራ ማዕከል ለምትሠሩት እህቶቼ እና እናቶች እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እወዳለሁ” ብለዋል።

“የድካማችሁን ፍሬ በማየቴ ደስ ብሎኛል” ሲሉም ገልፀዋል።

“እንሥራ” የተሰኘው አዲስ የሸክላ ሥራ ማዕከል ግንባታው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ባሳለፍነው ቅዳሜ መመረቁ ይታወሳል።

በማዕከሉ 1 ሺህ በሸክላ ስራ ላይ የተሰማሩ እናቶች የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎች ከተሟላ የማምረቻ ቦታ እና ከተሟላ ቁሳቁሶች ጋር የሚያገኙበትም ነው።

https://www.fanabc.com/ጠ-ሚ-ዐቢይ-እንሥራ-የሸክላ-ስራ-ማዕከል
ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ ከጅቡቲና ሩዋንዳ ጋር በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ መስጠት ስምምነት አዋጅን አፀደቀ

የኢፌዴሪ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል።

ምክር ቤቱ በዛሬው መደበኛ ስብሰባውም የተለያዩ አጀንዳዎችን ተመልክቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የተጓደሉ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ሹመትን የተመለከተ ሲሆን፥ በዚህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቀረቡለትን የተጓደሉ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ለማሟላት አምስት አባላቶችን ሹመት አጽድቋል።

በዚህም መሰረት ሬቭናንድ ደረጀ ጀምበሩ፣ አቶ ደመላሽ ያደቴ፣ ዶክተር እዝራ አባተ፣ ወይዘሮ ፋጡማ ሀሴ እና ጋራድ ኩልሜ መሃመድ በተጓደሉ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ምትክ ተሹመዋል።

ሹመታቸው የፀደቀው አምስቱ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

ምክር ቤቱ በመቀጠልም የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአፍሪካ ሕብረት ሰንደቅ ዓላማ፣ መዝሙር እና የአፍሪካ ቀን ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ተመልክቷል።

https://www.fanabc.com/ምክር-ቤቱ-ኢትዮጵያ-ከጅቡቲና-ሩዋንዳ-ጋር
በ2013 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት በጀት ዝግጅት ላይ ውይይት ተካሄደ

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በ2013 በጀት ዓመት የበጀት ዝግጅት ላይ ተወያይቷል።

በውይይቱም የበጀት ዝግጅቱን አስመልክቶ በገንዘብ ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ዶክትር እዮብ በዘህ ወቅት እንደገለጹት የ2013 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ሲዘጋጅ የ2012 ዓ.ም የበጀት አፈጻጸም ግምገማ ከመካሄዱም ባለፈ የኮረና ወረርሽኝ ተጽዕኖ ታሳቢ ተደርጎ በቅርብ ጊዜያት በአገራችን በኢኮኖሚው ዘርፍ የተገኙ ድሎችን ለማስጠበቅ ታስቦ የታቀደ በጀት ስለመሆኑ አስረድተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ለካፒታል እና ለብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት ድጋፍ እንዲሁም ለዘላቂ ልማት ግቦች ማጠናከሪያ በጥቅሉ 476 ቢሊዮን ብር መመደቡን ገልጸው÷ ከዚህ ውስጥ 350 ቢሊየን ብሩ ከሀገር ውስጥ የገቢ ምንጮችና ከዕርዳታ ለመሰብሰብ መታቀዱንም ነው ሚኒስትር ዴኤታው የተናገሩት፡፡

አያይዘውም ለ2013 በጀት ዓመት የቀረበው በጀት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃጸር መጠነኛ ጭማሪ እንዳለው ጠቁመው÷ በጀቱ በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ ለምለም ሐድጉ÷ በቀጣይ በረቂቅ በጀቱ ላይ ተጨማሪ ውይይት መኖሩን መጠቆማቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

https://www.fanabc.com/በ2013-በጀት-ዓመት-የፌደራል-መንግስት-በጀት-ዝ
በኢትዮጵያ 157 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለ3 ሺህ 693 የላቦራቶሪ ምርመራ 157 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 846 ደርሷል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 97 ወንዶችና 60 ሴቶች ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸውም ከ7 እስከ 83 ዓመት ውስጥ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል።

ከጠቅላላው የላቦራቶሪ ምርምራ ውስጥ 52 ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላቦራቶሪ ምርምራ ሲሆን 4 ሰዎች (3 ሰዎች ከአዲስ አበባ እንዲሁም 1 ሰው ከትግራይ) የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በህክምና ማዕክል ህክምና ላይ የነበረ የ18 ዓመት ወጣት የአዲስ አበባ ነዋሪ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን በጠቅላላ አምስት ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ህይወታቸው አልፏል፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 103 ደርሷል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት 298 ሰዎች 200 ከአዲስ አበባ፣ 87 ከሶማሌ ክልል፣ 9 ከአማራ ክልል፣ 1 ከድሬዳዋ ከተማ እና አንድ ከኦሮሚያ ክልል ያገገሙ ሲሆን በዚህም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 430 መድረሱ ነው የተነገረው።

https://www.fanabc.com/በኢትዮጵያ-157-ሰዎች-የኮሮና-ቫይረስ-ሲገኝባ
ሁለት የአሜሪካ ሴናተሮች ሀገራቸው በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ገለልተኛ አቋም እንድትይዝ በደብዳቤ ጠየቁ

ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተሮች አሜሪካ በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ገለልተኛ አቋም እንድትይዝ በደብዳቤ ጠየቁ።

ሴናተር ኮሪ ቡከር እና ሴናተር ክርስቶፎር ኩንስ ለአሜሪካ የግምጃ ቤት ሀላፊ ስቴቨን ሙኑሸን በፃፉት ደብዳቤ ዩናይትድ ስቴትስ በህዳሴ ግድብ ላይ በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ መካከል እየተደረገ ባለው ድርድር የያዘችው አቋም እንዳሳሰባቸው በመጠቆም በዚህ ድርድር ላይ ራሷን ገለልተኛ እንድታደርግ አሳስበዋል።

ሴናተሮቹ ከዚህ ቀደም በአሜሪካ ተረቆ ለፊርማ የቀረበው ስምምነት ኢትዮጵያ ለግብፅ የወገነ መሆኑን በመጥቀስ አለመፈረሟን አስታውሰዋል።

ያንን ተከትሎም ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ ሲደርግ የነበረው ድርድር በስምምነት ተቋጨ አልተቋጨ ግድቡን የውሃ ሙሌት በያዘችው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደምትሞላ መግለጿን ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት መፈጠሩን ነው ያመለከቱት።

የግድቡ ግንባታ እየተጠናቀቀ እና የሁለቱ ሀገራት ተቃርኖ አየሰፋ በመጣበት በዚህ ወቅት ታዲያ ዩናይትድ ስቴትስ ሁኔታውን ልታበርድ ይገባል ብለዋል።

ሆኖም በጉዳዩ ላይ አሜሪካ ገለልተኛ ባለመሆኗ ይህንን ውጥረት የማብረድ ሚና መጫወት እንዳትችል እንዳደረጋት ሴናተሮቹ አስረድተዋል።

https://www.fanabc.com/ሁለት-የአሜሪካ-ሴናተሮች-ሀገራቸው-በህዳ
ኢራን በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ኢራን ከቀድሞው የሃገሪቱ አብዮታዊ ዘብ ጠባቂ ሃይል አዛዥ ጀኔራል ቃሲም ሱሌይማኒ ግድያ ጋር በተያያዘ በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥታለች።

https://www.fanabc.com/ኢራን-በአሜሪካው-ፕሬዚዳንት-ዶናልድ-ትራ
የሃገሪቱ ጠበቆችም ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ 30 ሰዎች በቀድሞው አዛዥ ግድያ እጃቸው አለበት ብለዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ቴህራን ዶናልድ ትራምፕ ተይዘው ይቅረቡልኝ ብላለች።

ዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖልም እርሳቸውን በማቅረቡ በኩል ይተባበረኝ ስትልም ጠይቃለች።

የኢራኑ ጠበቃ አሊ አልቃሲምመርም ቴህራን ትራምፕን ለህግ ለማቅረብ ጥረቷን ትቀጥላለች ብለዋል።

እርሳቸውን በህግ የመጠየቁ ሂደትም ከስልጣን ከወረዱ በኋላም ይቀጥላል ነው ያሉት።

ከጉዳዩ ጋር ከኢራን በኩል ጥያቄ የቀረበለት ኢንተርፖል ግን እስካሁን ያለው ነገር የለም።

የኢራን የቀድሞው አብዮታዊ ዘብ ጠባቂ ሃይል መሪ ጀኔራል ቃሲም ባግዳድ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በድሮን በተፈጸመ ጥቃት መገደላቸው ይታወሳል።
ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የሙከራ በረራ ሊያደርግ ነው

ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የሙከራ በረራ ሊያደርግ መሆኑ ተሰማ።

አውሮፕላኑ ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ ሶስት ቀናት የሙከራ በረራውን እንደሚያደርግ ታውቋል።

ነገር ግን የዚህ የሙከራ በረራ ስኬታማነት ማክስ 737 ወደ ገበያ የመመለስ ዋስትናን አይሰጠውም ነው የተባለው።

አውሮፕላኑ ወደ ገበያ ለመመለስ ሌሎች ፈተናዎችን ማለፍ ይጠበቅበታል ተብሏል።

የቦይንግ ምርት በሆኑት 737 ማክስ አውሮፕላኖች በኢትዮጵያ እና በኢንዶኔዢያ በደረሰ አደጋ በድምሩ የ346 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትትሎ ካሳለፍነው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ አውሮፕላኖቹ በረራ ማቆማቸው ይታወሳል።

https://www.fanabc.com/ቦይንግ-737-ማክስ-አውሮፕላን-የሙከራ-በረራ-ሊ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 18ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ነገ በሚያካሂደው ስብሰባው የምክር ቤቱን 5ኛ አመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ በማጽደቅ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን እንደሚያዳምጥ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

https://www.fanabc.com/የሕዝብ-ተወካዮች-ምክር-ቤት-18ኛ-መደበኛ-ስብ
ተጨማሪ 304 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ3 ሰዎች ሕይወት አልፏል

ባለፉት 24 ሰዓታት ለ5 ሺህ 56 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርግ 304 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በቫይረሱ የተገኘባቸው ከአዲስ አበባ ከተማ 157፣ ከትግራይ ክልል 36፣ ከኦሮሚያ ክልል 46፣ ከጋምቤላ ክልል 26፣ ከአማራ ክልል 12፣ ከአፋር ክልል 17፣ ከሶማሌ ክልል 7፣ ከሐረሪ ክልል 2 እና ከደቡብ 1 ናቸው።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ለ336 ሺህ 322 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 10 ሺህ 511 ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት የ3 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 173 ደርሷል።

56 የኮሮና ቫይረስ ታካሚዎች ደግሞ በፅኑ ህክምና መከታታያ ክፍል ውስጥ ይገኛሉም ነው ያለው።

በተያያዘም 153 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን ይህን ተከትሎም 5 ሺህ 290 ሰዎች በአጠቃላይ ከቫይረሱ አገግመዋል።

https://www.fanabc.com/ተጨማሪ-304-ሰዎች-የኮሮና-ቫይረስ-ሲገኝባቸው