ፋና አማርኛ FBC Amharic
493 subscribers
446 photos
447 links
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አማርኛ ዜናዎች

For English: https://t.me/fbcenglish
Download Telegram
የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያሪክ ኤሪኔጅ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው አለፈ

የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሪ ፓትሪያሪክ ኤሪኔጅ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በ90 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

ፓትሪያሪኩ ባለፈው ወር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ባለፈው ሊቀ ጳጳስ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ከታደሙ በኋላ በተደረገላቸው ምርምራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸው ነበር።

ይህንንም ተከትሎም ቤልግሬድ በሚገኝ ወታደራዊ ሆስፒታል የህክምና ክትልል ሲደረግላቸው ቆይቷል።

የፓትሪያሪኩን ህልፈት ይፋ ያደረጉት የሰርቢያ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ቩቺ “አንቱን በማወቄ እድለኛ ነኝ እንደ እርስዎ አይነት ሰው መቼም ከጎን አይለይም ብለዋል።

የፓትሪያሪኩ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ተከትሎ ባለፈው ማክሰኞ የመተንፈሻ መሳሪያ ተገጥሞላቸው እንደነበረ ቢቢሲ በዘገባው ላይ አስፍሯል።

ፓትሪያሪኩ ምንም አይነት ምልክት ሳያሳዩ እና በመልካም ጤንነት ላይ በነበሩበት ወቅት ካለባቸው የልብ በሽታ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ትኩሳት ማሳየታቸውን እና የጤናቸው ሁኔታም መዛባቱን የሰርቢያ ቤተክርስቲያን ማስታወቋን የኤ ኤፍ ፒ ዘገባ ያሳያል።

ፓትሪያሪኩ በወግ አጥባቂነታቸው የሚታወቁ ሲሆን በሰርቢያ ፖለቲካም ከፍ ያለ ተፅዕኖ እንዳላቸው ይነገራል።

https://www.fanabc.com/የሰርቢያ-ኦርቶዶክስ-ቤተ-ክርስቲያን-ፓት/
የዓለም ህፃናት ቀን በሃዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው

የዓለም ህፃናት ቀን በዓለም ለ31ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ15ኛ ጊዜ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሃዋሳ ከተማ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዓሉ የሚከበረው ትውልድን እንቅረፅ ሃገርን እንገንባ በሚል መሪ ቃል ነው፡፡

የዓለም ህፃናት ቀን በብሔራዊ ደረጃ ከህዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቷል፡፡

ዛሬ የበዓሉ ማጠቃለያ ፕሮግራም በሃዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተከናወነ እንደሚገኝ ከሴቶች፣ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

https://www.fanabc.com/የዓለም-ህፃናት-ቀን-በሃዋሳ-ከተማ-እየተከ/
የትግራይ ህዝብ ከደረሰበት የአምባገነኑ ጭቆና ነጻ ይወጣል – የብልፅግና ፓርቲ

የትግራይ ህዝብ ከደረሰበት የአምባገነኑ ጭቆና ነጻ ይወጣል ሲል የብልፅግና ፓርቲ አስታወቀ።

ዘራፊውና ጽንፈኛው የህወሓት ቡድን ዛሬም ድረስ ምሽግ ውስጥ ሆኖ እጅ አልሰጥም አሻፈረኝ እንዳለ ነው ያለው ፓርቲው፥ ተወደደም ተጠላም የፌደራል መንግስት ህግ የማስከበርና የህልውና ዘመቻውን አጠናክሮ በማስቀጠል እምቢተኛውን የህወሓት ቡድን ለህግ ማቅረቡ አይቀሬ ነው ብሏል፡፡

አምባገነኑ የህወሓት ቡድን ዛሬም እንደትናንቱ ከህዝብና ከሀገር ይልቅ የራስን ምቾት በማስቀደም ዕድሜያቸው ለውትድርና ያልደረሱ አያሌ ወጣቶችን አስከፊ ለሆነው ጦርነት መጠቀሚያ እያደረጋቸው ይገኛልም ነው ያለው፡፡

ይህ ግራ የተጋባው ከሃዲ ቡድን መሰረታዊ ዓላማው ሀገርን ማፈራረስ እንደሆነ ለማንም የተደበቀ አይደለም ሲልም ገልጿል፡፡

ከተቋማቱ ተልዕኮ ውጭ በሆነ መንገድ በማስፈራራት አልያም ሀይል በመጠቀም መቀሌ የሚገኙ ቤተ እምነቶችን እንደ ምሽግ እየተጠቀመባቸው የገለፀ ሲሆን ቤተ እምነቶችን ለመሳሪያ ክምችት እና ለፕሮፖጋንዳ ስራ መጠቀም ጀምሯል፤ ይህ አይነቱ አካሄዱ በዓለም ላይ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ አይታወቅም በማለትም አብራርቷል፡፡

https://www.fanabc.com/የትግራይ-ህዝብ-ከደረሰበት-የአምባገነኑ/
የኦሮሚያ አራት ዞኖች ለመከላከያ ሰራዊት 705 ሰንጋዎችና 7.6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የቦረና ዞን፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን፣ ምዕራብ ሀረርጌ ዞን እና ፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊቱ 705 ሰንጋዎችና 7.6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ከአራቱ ዞኖች የተወከሉ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና አባገዳዎች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች በኢፌዴሪ ምድር ሀይል ተገኝተው የነዋሪዎችን ስጦታ አስረክበዋል።

ተወካዮቹ ወደፊትም መከላከያ ሰራዊቱን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዚሁ የድጋፍ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሊዊጂ ከዞኖቹ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

https://www.fanabc.com/የኦሮሚያ-አራት-ዞኖች-ለመከላከያ-ሰራዊት-705/
ኮሚሽኑ የካርጎ ትራኪንግ አገልግሎት ለማሻሻል ስምምነት ተፈራረመ

የጉምሩክ ኮሚሽን የካርጎ ትራኪንግ አገልግሎትን ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ ለመደገፍ ከትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን የጉምሩክ ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ እና የትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ ኩባንያ ተወካይ አቶ ታደሰ ይማሙ ተፈራርመውታል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ እንደተናገሩት÷ ኮሚሽኑ በአዲስ መልክ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የጉምሩክ አገልግሎቱን ምቹ፣ ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

የራሱን አቅም ከማሳደግ ጎን ለጎን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተለይም በድንበሮች አካባቢ ያለውን የገቢና ወጪ ዕቃዎችን ፍሰት ጤናማ፣ ቀልጣፋና ግልፅ ለማድረግ የካርጎ ትራኪንግ ቴክኖሎጂ ወሳኝ በመሆኑ ከኩባንያው ጋር በዚህ ረገድ በትብብር ለመስራት ዝግጅት መጠናቀቁንም ጠቁመዋል፡፡

ቴክኖሎጂው በጉምሩክ ክልል ውስጥ የሚጓጓዙ ዕቃዎች ያሉበትን ሁኔታ፣ የደረሱበትን ቦታና አሁናዊ መረጃ በግልፅ ከማሳየቱም በላይ በህጋዊ ዕቃዎች ውስጥ የሚገቡ ህገወጥ ዕቃዎችን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል፡፡

የትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ ኩባንያ ተወካይ አቶ ታደሰ ይማሙ በበኩላቸው ÷ ድርጅታቸው በተለይም በምስራቅ አፍሪካ የጉምሩክ አገልግሎትን ለማቀላጠፍ በሚሰሩ ስራዎች በመሳተፍ ከፍተኛ ልምድ ያለው ነው ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በ18 ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ጠቅሰው ጥናቶች ተደርገው የማሽን ተከላ ከማድረግ ባሻገር ለሰራተኞች የተለያዩ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ መግለፃቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

https://www.fanabc.com/ኮሚሽኑ-የካርጎ-ትራኪንግ-አገልግሎት-ለማ/
በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እየተካሄደ ያለውን የህግ ማስከበር እርምጃ በተመለከተ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራ ተሰርቷል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እየተካሄደ ያለውን የህግ ማስከበር እርምጃ በተመለከተ ለጎረቤት የአፍሪካ ሃገራት ለማስረዳት ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኬኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጉብኝት በማድረግ መንግስት በሕወሓት ጁንታ ላይ እየወሰደ ያለውን የህግ ማስከበር እርምጃ በተመለከተ ለሃገራቱ ማስረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡

በወቅቱም ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራ መሰራቱንም ነው አምባሳደር ዲና የተናገሩት፡፡

ከዚህም ባለፈም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መንግሥት በቡድኑ ላይ እየወሰደ ያለውን የህግ ማስከበር እርምጃ በተመለከተ ለጎረቤት ሱዳን እና ጂቡቲ ማስረዳታቸውንም ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ከዲፕሎማሲው ባሻገር ፕሪቶሪያ፣ ካምቤራ እና ዱባይ መቀመጫቸውን ያደረጉ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት መስክ ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸውንም አንስተዋል፡፡

https://www.fanabc.com/በሰሜኑ-የኢትዮጵያ-ክፍል-እየተካሄደ-ያለ/
የህወሓት ጁንታ ንብረትነቱ የመከላከያ ሰራዊት ባልሆነ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ተፈጽሞብኛል የሚለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው- ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ

ስግብግቡ የህወሃት ጁንታ ንብረትነቱ የመከላከያ ሰራዊት ባልሆነ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ተፈጽሞብኛል የሚለው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑን የአየር ሀይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለፁ።

ሜጀር ጀኔራል ይልማ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ የኢፌዴሪ አየር ሀይል የሀገርን ሉዓላዊነት እና የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ በሚያስችል ደረጃ ቴክኖሎጂ የታጠቀ መሆኑን አንስተዋል።

አየር ሀይሉ የሀገሪቱን አየር ክልል ከጥቃት በብቃት የመጠበቅ እና እንዳሁኑ ደግሞ የከረሩ ነገሮች ሲፈጠሩ ለሰራዊቱ የቅርብ ድጋፍ የማድረግ ተግባሩን እየተወጣ ይገኛልም ብለዋል።

የጠላት ኢላማዎችን ያለምንም ርህራሄ እንዳልነበር ማድረግ ለሰራዊቱ ማነቆ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን በማፍረስ መንገዱን ቀና የማድረግ ተግባርም ይከውናልም ነው ያሉት፡፡

ሜጀር ጄኔራል ይልማ ከዚሁ ጋር በተያያዘ፥ ስግብግቡ የህወሓት ጁንታ ተቆጣጠርኩ ብሎት የነበረው መሳሪያ ክህደቱ ሳይሰማው ድንፋታውን በጎላበት ማግስት በአየር ሀይሉ ወደ አመድነት ተቀይሯል።

ኃላፊነት በማይሰማው ቡድን በዱር በገደሉ የኮንትሮባንድን መንገድ ተከትሎም ክልሉ የደረሰው የጦር መሳሪያ እጣ ፈንታም ቢሆን በአብዛኛው ተመሳሰይ እድል ገጥሞታል ብለዋል።

በመቐለ አቅራቢያ ክዊሃ እና አዲግራት ጭምር የነበሩ የነዳጅ ዴፖዎችም በጁንታው ቡድን ጥቅም ላይ ሳይውሉ መውደማቸውንም ተናግረዋል፡፡

https://www.fanabc.com/የህወሓት-ጁንታ-ንብረትነቱ-የመከላከያ-ሰ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያዘጋጁት ውይይት ተካሄደ

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያዘጋጁት ውይይት ተካሄደ።

ውይይቱን ከሚኒስቴሩ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት በአልጀሪያ፣ ቤልጂየም፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን እና ኔዘርላንድስ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ናቸው።

በውይይቱ ላይ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች፣ የባለሙያዎች ቡድኖች፣ የሚዲያ ተቋማት እና የተለያዩ ሀገራት የፓርላማ አባላት የተሳተፉ ሲሆን አምባሳደሮች ገለፃ አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ በህዳሴ ግድብ ላይ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን አባላት የሆኑት ዶክተር ዮሀንስ ገብረፃድቅ እና አምባሳደር ረታ አለሙ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በቤልጂየም የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ውይይቱን መርተውታል።

በዚህም በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪት ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ በህዳሴ ግድብ ላይ እያካሄዱት ስለሚገኘው ውይይት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በተመሳሳይ ከሶስትዮሽ ውይይት ጋር ተያይዞ የጋራ በሆኑ ነጥቦች ላይ እና በወሳኝ የቴክኒካል እንዲሁም ህጋዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለተሳታፊዎቹ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ተሳታፊዎቹ ማብራሪያውን ተከትሎ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተነስተው ምላሽ እንደተሰጠባቸው ነው ብራሰልስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያስታወቀው።

ይህ ውይይት ለተሳታፊዎቹ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ እየተካሄደ ስለሚገኘው ውይይት በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ነገሮቹን ግልፅ ያደርጋል ተብሏል።

እንዲሁም ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ ሁኔታ ላይ ለመድረስ ኢትዮጵያ ያላትን አቋም ለማሳየት የሚያስችል ውይይት እንደነበረም ተጠቁሟል።

https://www.fanabc.com/የውጭ-ጉዳይ-ሚኒስቴር-እና-በተለያዩ-ሀገራ/
ደረጃውን የጠበቀ የበግ ቆዳ በማምረት ውጤት ላስመዘገቡ ፋብሪካዎች እውቅና ተሰጠ

ከፍተኛ ጥራት ያለው የኢትዮጵያ የበግ ቆዳ በማምረት ውጤት ላስመዘገቡ አራት ፋብሪካዎች ዕውቅና ተሰጣቸው፡፡

በዘርፉ ዕውቅና ያገኙ ፋብሪካዎችም ባህርዳር፣ ኒው ዊንግ ፣ ፒታርድ እና ኤሊኮ የተሰኙ የቆዳ ፋብሪካዎች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር አስታውቋል፡፡

የቆዳ ፋብሪካዎቹ ደረጃውን የጠበቀ እና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳጅነት ያተረፈ የኢትዮጵያ የበግ ቆዳ በማምረት ነው ዕውቅና እና ሰርተፍኬት የተሰጣቸው ፡፡

በጃይካ የቴክኒክ እና ገንዘብ ድጋፍ የቆዳ ፋብሪካዎቹ ከፍተኛ ጥራት ያለውን እና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳጅነት ያተረፈውን የኢትዮጵያ ደጋ የበግ ቆዳ እንዲያመርቱ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡

ለዚህም የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር፣ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢኒስቲቲዩት ከጃፓን የቴክኒክ ተራድኦ ድርጅት “ጃይካ” ጋር በቅንጅት መስራታቸውን ከማህበሩ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀጣይም በዓለም አቀፍ ደረጃ በጥራቱ እና በተመራጭነቱ ቀዳሚ የሆነውን የኢትዮጵያ የበግ ቆዳ ምርት በስፋት ለማስተዋወቅ የተለያዩ እቅዶችን በመቅረጽ እየተሰራ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

https://www.fanabc.com/ደረጃውን-የጠበቀ-የበግ-ቆዳ-በማምረት-ውጤ/
በአፍሪካ ቀንድና በአፍሪካ ለሚኖር ሰላምና እድገት አሜሪካ ለኢትዮጵያ አጋርነቷን ማሳየት እንዳለባት ተገለጸ

ስትራቴጂካዊ አካባቢ በሆነው የአፍሪካ ቀንድና በአጠቃላይ በአፍሪካ ለሚኖር ሰላምና እድገት አሜሪካ ለኢትዮጵያ አጋርነቷን ማሳየት እንዳለባት የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የአሜሪካ ቅርንጫፍ ገለጸ።

የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የአሜሪካ ቅርንጫፍ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ለአንዳንድ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ደብዳቤ አስገብቷል።

በደብዳቤው አሁን በኢትዮጵያ ለሚታዩ ችግር ያለፉትን ሰላሳ ዓመታት የፖለቲካውን ሂደት ማወቅ ያስፈልጋል ብሏል።

በእነዚህ ዓመታት ኢትዮጵያውያን በተለያዩ መንገዶች በመካከላቸው ቅራኔና መለያየት እንዲፈጠር መሠራቱን አመላክቷል።

አሸባሪው ሕወሓት ይመራው በነበረው መንግሥት መዋቅር ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የህዝብ ሀብት ዝርፊያ እና በመንግስታዊ የሽብር ወንጀሎች በተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ በጋዜጠኞችና በግለሰቦች ላይ ሲፈጸም ነበር ብሏል።

ህወሓት ከስልጣን ከተወገደ በኋላ ሰላማዊ መንገድን መምረጥ ትቶ ወደ ጦርነት መግባቱን አስታውሷል።

ባለፉት ሦስት አመታት የነበረ መዋቅሩን በመጠቀም ግጭቶች እንዲከሰቱ፣ ዜጎች ለሞት እንዲዳረጉና በኢትዮጵያ ሰላም እንዳይሰፍን መስራቱን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።

ጥቅምት 24 2013 ዓ.ም ደግሞ በሃገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመሰንዘር የፌደራል መንግስቱን በሀይል ከስልጣን ለማስወገድ ወደ እንቅስቃሴ መግባቱን አስታውቋል።

https://www.fanabc.com/በአፍሪካ-ቀንድና-በአፍሪካ-ለሚኖር-ሰላም/
የህልውና ዘመቻውን መደገፍ ሃገር እንዳትፈርስ ማድረግ ነው – የሐረሪ ክልል መንግስት

መከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ በህልውና ማስጠበቅ ዘመቻ ላይ ተሰልፈው መስዋዕትነት እየከፈሉ የሚገኙ የፀጥታ ሃይሎችን መደገፍ ሃገር እንዳትፈርስ ማድረግ መሆኑን የሐረሪ ክልል መንግስት ገለፀ፡፡
ሽብርተኞቹ ህወሓትና ሸኔ ሃገራችንን ለማፍረስና ህዝቡን ለማዋረድ ተቀናጅተው የከፈቱትን ሁለንተናዊ ጥቃት ለማክሸፍ እና የተጀመሩ የልማት፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማስቀጠል የሐረሪ ክልል መንግስትና ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊትእንዲሁም ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጎን ተሰልፎ ሁሉን አቀፍ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስሪያ አብደላ ተናግረዋል፡፡
መከላከያ ሰራዊት እና በህልውና ማስጠበቅ ዘመቻ ላይ ተሰልፈው መስዋዕትነት እየከፈሉ የሚገኙ የፀጥታ ሃይሎችን መደገፍ ሃገር እንዳትፈርስ ማድረግ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
“እንደ ክልል ወደ ሰራዊታችንን የሚቀላቀሉ ወጣቶችን መርቀን ሸኝተናል” ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ፥ በቀጣይም ወደ ሰራዊቱ ለመቀላቀል የሚፈልጉ ወጣቶች እየተበራከቱ መሆኑንም ነው የገለፁት፡፡
የክልሉ ልዩ ሃይልም ወደ ግንባር ሄዶ ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር ተቀናጅቶ የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት እየተወጣ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡
በክልል ደረጃ ያሉ የመንግስት ሰራተኞች የወር ደመወዛቸውን ለሰራዊቱ ድጋፍ ያደረጉ መሆኑን የጠቀሱት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ÷ በቀጣይም የንግዱ ማህበረሰብና ሌሎች አካላትን ያሳተፈ ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

https://www.fanabc.com/የህልውና-ዘመቻውን-መደገፍ-ሃገር-እንዳት/
ዜጎች ደም ለመለገስ ያሳዩት ፈቃደኝነት ደም የመለገስ ታሪክን የለወጠ ነው – ብሄራዊ የደም ባንክ

ዜጎች ደም ለመለገስ እያሳዩ ያለው ፈቃደኝነት በኢትዮጵያ የደም ልገሳን ታሪክ የለወጠና ያሳደገ መሆኑን ብሄራዊ የደም ባንከ አገልግሎት ገለጸ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የደም ባንከ አገልገሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ያረጋል ባንቴ እንዳሉት÷ አሸባሪው ህወሓት በመከላከያ ሰራዊት ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የተጀመረው ህግ የማስከበር ዘመቻ ከፍተኛው የደም መጠን እንዲሰበሰብ ምክንያት ሆኗል።

ይህን ተከትሎም በህዳር ወር 2013 ዓ.ም ብቻ ከዚህ ቀደም በዓመት ይሰበሰብ የነበረውን ያህል የደም መጠን ማለትም 38 ሺህ ከረጢት ደም ለመሰብሰብ ተችሏል ነው ያሉት።

ከህዳሩ ልገሳ በኋላም የቀጠለው የደም ልገሳ ተግባር በተለይ ከሀምሌ እስከ ነሐሴ ዜጎች ያለማቋረጥ በከፍተኛ ደረጃና ዓይነት ደም የለገሱበት ወቅት ሆኖ ተመዝግቧል ብለዋል።

ከዚያ በኋላም የታየው ለውጥ ተቋሙ በጎ ፈቃደኞች ደም እንዲለግሱ ከማግባባት የተሻገሩ ሌሎች የአገልግሎት ስራዎቹ ላይ እንዲያተኩር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም የነበረው ልምድ ዜጎች የሆነ አጋጣሚን መነሻ በማድረግ አንድ ጊዜ ደም ከለገሱ በኋላ ተመልሶ ለመምጣት ዓመታትን ይፈጅባቸው እንደነበርም ነው አቶ ያረጋል ያነሱት።

ዛሬ ላይ ለሀገራቸውና ለወገናቸው ህልውና የቆሙ ዜጎች በፈቃደኝነት ደም በመለገስ ላይ በመሆናቸው የነበረው ልማድ መቀየሩን፣ የደም ለጋሹ ቁጥር መጨመሩንና የሚለገሰው የደም መጠንም በእጅጉ ማደጉን ነው የሚገልጹት።

https://www.fanabc.com/ዜጎች-ደም-ለመለገስ-ያሳዩት-ፈቃደኝነት-ደ/
የኮሜርሻል ኖሚኒስ ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

የኮሜርሻል ኖሚኒስ ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ።
የድርጅቱ ዳይሬክተር ጄነራል ኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ እንደተናገሩት፥ የአሸባሪው ህወሓትና ሌላኛው አሸባሪ ተባባሪው ሸኔ ወደመቃብራቸው እስከሚገቡ ድረስ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እስከ ዘመቻ የሚደርስ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ናቸው።
እንደ ኮማንደሩ ገለፃ ድርጅታቸው አሸባሪውን ሀይል ለመጣል የራሱን አስተዋፅኦ የሚያደርግ ሲሆን 107 ሰራተኞቹም ወደ ግምባር መዝመታቸውን ጠቁመዋል።
የቀዳማዊ ሀይለስላሴ ሀረር የጦር አካዳሚ አሉሙናይ ማህበርም ለሰራዊቱ ያዋጣውን ከ300 ሺህ ብር በላይ ገቢ አድርጓል።
የማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ሻምበል በቀለ ፀጋዬም በተመሳሳይ ማህበራቸው ከመንግስትና ሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆኑን ጠቁመው አሸባሪው ቡድን ወደ መቀመቅ እስከሚወርድ ድረስ የአቅማቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ከዚህ ቀደም ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ኢፕድ ዘግቧል።

https://www.fanabc.com/የኮሜርሻል-ኖሚኒስ-ሰራተኞች-የአንድ-ወር/
አሸባሪው ሕወሓት የከፈተብንን ጦርነት መክተን ሕዝባችንን እናኮራለን – ሌ/ጄ ደስታ አብቼ

አሸባሪው ሕወሓት የከፈተብንን ጦርነት መክተን ሕዝባችንን እናኮራለን ሲሉ የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ ገለጹ፡፡

ሌተናል ጄኔራል ደስታ ይህንን ያሉት የመከላከያ ሚኒስቴር ያስገነባው የአዋሽ በርታ የእግረኛ ሻለቃ ካምፕ በተመረቀበት ወቅት ነው ።

ግንባታው ማዘዣ ጣቢያን ጨምሮ የሠራዊት መኖሪያ ቤቶችን ያካተተ ሲሆን÷ አዋሽ በርታ ካምፕ የክሊኒክ ፣ የኢንፎርሜሽ ኮሙዩኒኬሽን፣ የመዋኛ ገንዳና ሌሎች አገልግሎቶችን ለሠራዊቱ እንዲሰጥ ተደርጎ በዘመናዊ መንገድ የተገነባ ነው።

የካምፑ ግንባታ ለሠራዊቱ ከፍተኛ ጥቅም ያለው መሆኑን የገለፁት የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊው÷ ሠራዊቱ የሀገርን ህልውና እያስከበረ ባለበት ወቅት ተጎዳኝ ሥራዎችን በብቃት እየፈጸመ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

አሸባሪው ሕወሓት የከፈተብንን ጦርነት መክተን ሕዝባችንን እናኮራለንም ብለዋል።

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የዲዛይንና ዋጋ ግምት መምሪያ ሀላፊ ኮሎኔል ያደታ አመንቴ በበኩላቸው፥ መምሪያው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ግንባታዎችን በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ገንብቶ እያስረከበ መሆኑን ገልጸዋል።

የካምፑ መገንባት ለሠራዊቱ ከሚሠጠው ቀጥተኛ አገልግሎት በዘለለ በሕክምና፣ በመብራትና በውሃ አቅርቦት የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ የበርታ ነዋሪዎች ደስታቸውን ገልፀዋል።

https://www.fanabc.com/አሸባሪው-ሕወሓት-የከፈተብንን-ጦርነት-መ/
በከተማ ግብርና አበረታች ውጤቶች መመዝገብ ጀምረዋል – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

በከተማ ግብርና ዘርፉ የሚገኘው ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ አበረታች ውጤቶች መመዝገብ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

ምክትል ከንቲባዋ በፌስቡክ ገፃቸው ባሰሰሩት ፅሁፍ÷ “ከተማችን የከተማ ግብርና ልምድ እንዲዳብር፣ ከዘርፉ የሚገኘው ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በርካታ ስራዎችን እያከናወንን ስለሆነ አበረታች ውጤቶች ማስመዝገብ ጀምረናል” ብለዋል።

በጓሮ አትክልት ልማት፣ በወተትና የወተት ተዋፅዖ፣ በዶሮና እንቁላል ልማት፣ በሰብል ምርት ላይ በጎ ጅምር መታየቱ በቀጣይ እንደ ከተማ ይበልጥ ውጤታማ መሆን እንደምንችል ማማሳያ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በምግብ ራስን መቻልም የክብራችን ማስጠበቂያ አንዱ መንገድ ነው ሲሉም ጠቅሰዋል።

https://www.fanabc.com/በከተማ-ግብርና-አበረታች-ውጤቶች-መመዝገ/
በካፋ ዞን 701 ወጣቶች በሰፈራ ፕሮግራም የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ

በካፋ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ በላይ ተሠማ የተመራ ልዑክ በሺሾ እንዴ ወረዳ በሽመሮ እና ሂሪዮ ቀበሌ በውስጥ ሰፈራ ፕሮግራም ስራ ዕድል የተፈጠረላቸው የ701 የወጣቶች ስራ እንቅስቃሴ ጉብኝት አድርጓል፡፡

የወረዳው ህብረተሰብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መልኩ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የወረዳው ዋና አሰተዳዳሪ አቶ አሰረስ አስፋው ተናግረዋል፡፡

በወረዳው በሽመሮ እና ሂሪዮ ቀበሌዎች በውስጥ ሰፈራ ለ701 ስራ አጥ ወጣቶች ስራ ዕድል እንደተፈጠረላቸውም ገልጸዋል።

ወጣቶቹ በቂ ምርት አምርተው ለገበያ እንዲያቀርቡ በወረዳው በኩል የትራክተር ድጋፍ የሚያገኙበት መንገድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ እንደሚገኝም ነው የገለፁት፡፡ ተጠቃሚ ወጣቶቹ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ስራ አጥ ሆነው የቤተሰብ ድጋፍ ሲጠይቁ እንደነበር ገልጸው÷ አሁን ግን የተለያዩ የግብርና ስራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በአካባቢው የሚስተዋለው የመሰረተ ልማት ችግር እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል።

የካፋ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ በላይ ተሠማ በበኩላቸው በሰፈራ ጣቢያው የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው የወጣቶች የስራ እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው÷ ተሞክሮውን በዞኑ በሁሉም ወረዳዎች የማስፋት ተግባር ይከናወናል ብለዋል።
ወጣቶቹ በተሰጣቸው መሬት ላይ ምርትና ምርታማነታቸው እንዲያድግ የግብዓትና የባለሙያ ድጋፍ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎች እንደሚደረጉላቸውም አንስተዋል፡፡

https://www.fanabc.com/በካፋ-ዞን-701-ወጣቶች-በሰፈራ-ፕሮግራም-የስራ/
በህወሓት በሬ ወለደ ወሬ የሚፈታ ህዝብ የለንም – አቶ ከበደ ካሣ

በህወሓት በሬ ወለደ ወሬ የሚፈታ ህዝብ የለንም ሲሉ የሀይቅ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ገለጹ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ እንዳሉት÷ አሸባሪው ህወሓት እየተጠቀመበት ያለው የውሸት ፕሮፓጋንዳ ጊዜው ያለፈበት ስልት ነው ብለዋል።

የከተማችን ወጣትና ነዋሪዎች የሽብር ቡድኑን እኩይ ተግባር በሚገባ ስለሚያውቅ በወሬ አይፈታም ፤ ደቡብ ወሎ ምድርን ሳይነካም ቀብሩን እንፈጽማለን ነው ያሉት።

የህወሓት ተላላኪወችን ወሬ የሚያናፍሱ ግለሰቦች የጁንታ ቡድኑ ተከፋዮች በመሆናቸው ማህበረሰቡ በያሉበት ለጸጥታ ሀይሉ እንዲጠቁምና ይዞም እንዲያስረክብ ጥሪ አቅርበዋል።

የከተማው ወጣቶች ተደራጅተው ወንበዴውን ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን ባለበት እየቀበሩት መሆኑንም ጠቁመዋል።

የከተማው ህዝብ ሰርጎ ገቦችን እየለየ አካባቢውን እንዲጠብቅም አሳስበዋል።

https://www.fanabc.com/በህወሓት-በሬ-ወለደ-ወሬ-የሚፈታ-ህዝብ-የለ/
በመዲናዋ ሕገወጥና የሌብነት ተግባርን ለሚያጋልጡ የማበረታቻ ስርዓት ተዘረጋ

ተከማችቶ የቆየውን ሕገወጥ እና የሌብነት ተግባር ለማጥፋት በተደራጁ ሌቦች ላይ ተገቢው እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

ሆኖም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከነዋሪው ጋር ተቀናጅቶ መሥራት እና እነዚህ ህገወጥ ተግባር ፈጻሚ ሌቦችን የሚያጋልጥ የከተማው ነዋሪ ሊያበረታታ የሚያስችል የማበረታቻ ሥርዓት በመዘርጋት ሕገወጥነትን መከላከል አስፈላጊ በመሆኑ የከተማው ካቢኔ ባሳለፈው ውሳኔ “ሕገ-ወጥነትን ለሚጠቁሙ መረጃ አቅራቢዎች ስለሚሰጥ ማበረታቻ ደንብ” አውጥቷል፡፡

ደንቡ ከለያቸው ዋና ዋና ህገ-ወጥ ተግባራት ውስጥ የመሬት ወረራ፤ በመሬት ባንክ ተይዘው የነበሩ ይዞታዎችን ሕገወጥ በሆነ መንገድ የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እንዲወጣባቸው ማድረግ፤ሕገ-ወጥ ግንባታ፤ የአርሶ አደር ይዞታዎችን በህገ ወጥ መንገድ ለማይገባው ሰው መብት እንዲፈጠር ማድረግ፤አላግባብ የመንግስት ቤቶችን፣ ሼዶችን፣ አረንጓዴ ቦታዎች እና ሌሎች ማንኛውም የመንግስት ይዞታዎችን ወደ ግለሰብ ማዞር ይገኙበታል፡፡

https://www.fanabc.com/በመዲናዋ-ሕገወጥና-የሌብነት-ተግባርን-ለ/