ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
247K subscribers
290 photos
1 video
15 files
243 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ_አምስት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

ኤዲ ዲኪን ራሱን ለመቆጣጠር ቢሞክርም  ክዳኑ ተዘግቶ እንደሚንተከተክ ጀበና ሆኗል፡ በጭንቀት ሊፈነዳ ምንም አልቀረውም፡፡ ላቡ
አሁንም አሁንም ችፍ ይላል፡ ጨጓራው እየተቃጠለ በመሆኑ ሰውነቱ
እረፍት አጣ፡፡ ቀልቡን ሰብስቦ መስራት አልቻለም፡፡

ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ የእሱ ፈረቃ ያበቃል ወደ መውጫው ሰዓት ላይ የሀሰት የነዳጅ ፍላጎት መጠን አስልቶ በሰንጠረዡ ላይ አሰፈረ።

ካፒቴኑ ጉዞውን
ለማጠናቀቅ የሚያስችል በቂ ነዳጅ ያለው
ለማስመሰልና ወደ ኋላ እመለሳለሁ እንዳይል የአይሮፕላኑን የነዳጅ ፍጆታ
ፍላጎት መጠን አሳንሶ አስልቶ ነበር፡፡ የእሱ ተተኪ የሆነው ሚኪ ፊን ሲመጣ ልዩነቱን እንዳያውቅ የፍጆታ መጠኑን ከፍ አድርጎ በማስላት አካካሰው፡፡ የነዳጅ ፍጆታ መጠን በወጣ ገባነት መለዋወጡን ሚኪ ሲያይ ምን ተፈጠረ ብሎ መጠየቁ አይቀርም፡፡ ኤዲም ይህ የሆነው በወጀቡ ምክንያት ነው ሊለው ተዘጋጅቷል፡፡ የሆነ ሆኖ አሁን ሚኪ ምን እንደሚል ሳይሆን ያስጨነቀው፣ አዕምሮውን የውጥር የያዘው አይሮፕላኑ ኒውፋውንድ ላንድ (ካናዳ) ሳይደርስ ነዳጅ ይጨርስ ይሆን የሚለው ሃሳብ ነው፡፡

የበረራ ህጉ መያዝ ያለበትን መጠባበቂያ የነዳጅ መጠን ቢያስቀምጥም
አይሮፕላኑ የራሱ የሆነ ዝቅተኛ የነዳጅ ፍጆታ መጠን ደንብ የለውም:
አይሮፕላኑም ከአቅም በላይ ለሆነ ችግር የመጠባበቂያ ነዳጅ የለውም::በነዳጅ ችግር ምክንያት አንድ ችግር ቢከሰት አይሮፕላኑ ያለ ጥርጥር ማዕበል በበዛበት አትላንቲክ ውቂያኖስ ውስጥ መውደቁ አይቀርም፡፡ ከወደቀ
ደግሞ በትንሽ ደቂቃ ውስጥ ስለሚሰምጥ ለወሬ ነጋሪ እንኳን የሚተርፍ
የለም፡፡

ሚኪ እንደወትሮው ነቃ ብሎና ለስራ ተነሳስቶ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት
ሲል ደረሰ፡፡ ‹‹ያለን ነዳጅ አነስተኛ መሆኑን ለካፒቴኑ ነግሬያለሁ›› አለው
ኤዲ፡፡

ሚኪም ያለው ነገር ብዙም ስሜት እንዳልሰጠው ሁሉ ራሱን በማነቃነቅ ብቻ መረዳቱን ገለፀለትና ባትሪውን አነሳ፡፡ የመጀመሪያ ስራው የአይሮፕላኑ አራት ሞተሮች በዓይን መቃኘት ነው፡፡

ኤዲ ሚኪን ባለበት ቦታ ትቶ ወደ ተሳፋሪዎች ክፍል አመራ፡ ረዳት.ካፒቴኑ ጆኒ ዶት ናቪጌተሩ ጃክ አሽፎርድና ሬዲዮ ኦፕሬተሩ ቤን ቶምስን ተከትለውታል፡፡ ጃክ ለራሱ ሳንድዊች ሊያዘጋጅ ወደ ኩሽና ሄደ፡፡ ኤዲ ምግብ መብላት አይደለም ምግብ ሲያይ ሊያስታውከው ስለሚደርስ አንድ ሲኒ ቡና ብቻ ጠጣ

ስራ በሌለው ሰዓት ባለቤቱ ካሮል አን በነዚያ አፋኞች መዳፍ ስር መሆኗ ብቻ ነው አዕምሮው ውስጥ የሚመጣው፡፡

አሁን በአሜሪካ ሜይን ስቴት ውስጥ ሰዓቱ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በመሆኑ ጨለማ ነው፡፡ ይሄን ጊዜ ካሮል አን ከመንገላታት ብዛት ዝላና ልቧ
ተሰብሮ ቁጭ ብላ ይሆናል፡፡ ነፍሰ ጡር ከሆነች ወዲህ በጊዜ ነው
የምትተኛው፡ ታዲያ እንድትተኛ ይፈቅዱላት ይሆን? መተኛት ቀርቶ
ጎኗን የምታሳርፍበት ቦታ ቢሰጧት ጥሩ ነበር፡፡

ምሽቱ እየገፋ ሲሄድ ሚስቱን ያገቷት ወሮበሎች ሌላ ክፉ ነገር ያውጠነጥኑ ይሆን? ሲል መጨነቅ ጀመረ፡፡

ወጀቡ እንደገና ተነሳ፡፡

አይሮፕላኑ መናጡ ባሰበት፡ በማዕበል ላይ የሚጓዝ መርከብ መስሏል፡ ግዙፍ አይሮፕላን አንዴ ከፍ እያለ አንዴ ዝቅ እያለ በንፋስ ወዲህ ወዲያ የተንገላታ ይጓዛል። ተሳፋሪዎቹ ስጋት ገብቷቸው ከእንቅልፋቸው ተነሱ አስተናጋጁንም ይጣሩ ጀመር፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ሆዳቸው ታውኮ ወደ
መጸዳጃ ክፍል ይሮጣሉ አስተናጋጆቹም ወደ ተሳፋሪዎቹ ተራወጡ፡
ኤዲ ቡና ለመጠጣት ሲሄድ ቶም ሉተር ፊቱ መጥቶ ድቅን አለ፡፡ሉተር በአይሮፕላኑ መናወጥ ደንግጦ ፊቱ አመድ መስሏል፡ ሰውነቱ በላብ
ርሷል፡ ኤዲም ጅንን ብሎ ያየዋል፡፡ ቶምን ጉሮሮውን ፈጥርቆ ሊይዘው ትንሽ ነበር የቀረው፤ ነገር ግን ንዴቱን ውጦ ዝም አለ፡፥

‹‹ይሄ ግን የተለመደ ነው?›› ሲል ጠየቀ ቶም በፍርሃት፡

ኤዲ ያለ ምንም ሀዘኔታ ‹‹ያለ ዛሬ እንደዚህ ሆኖ አያውቅም›› ሲል መለሰለት ‹‹ከዚህ በኋላ በወጀቡ ውስጥ ነው የምንጓዘው፤ ነገር ግን በቂ ነዳጅ ስለሌለን አደገኛ ነው››

‹‹እንዴት?›› ሲል ጠየቀ ቶም፡፡

‹‹ነዳጅ እያለቀ ነው››
ሉተር በድንጋጤ እንደተረበሸ ‹‹ታዲያ ነዳጅ እንደማይበቃ ከታወቀ
በጊዜ ወደ ኋላ እንመለሳለን ብለህ አልነበረም?››

ኤዲ ውስጡ ከሉተር በላይ ተሸብሯል፡፡ ነገር ግን ጠላቱ ቶም በመንቦቅቦቁ ረክቷል፡ ‹‹ወደ ኋላ መመለስ እንችል ነበር ነገር ግን የነዳጅ
ፍጆታ ስሌቱን አሳስቼ ስላሰላሁት የአይሮፕላኑ ሰራተኞች በቂ ነዳጅ ያለ
መስሏቸዋል፡፡ ከእናንተ ጋር ያለኝን ውጊያ ለማጠናቀቅ በቂ ምክንያት እንዳለኝ አስታወስክ?››

‹‹አንተ እብድ!›› አለ ሉተር ተስፋ ቆርጦ ‹ሁላችንንም ልትጨርሰን አስበሃል?››
‹‹እኔማ ሚስቴ በእናንተ እጅ መሆኗ ነው እንጂ እያንዳንድሽን ወሮበላ
ሁሉ አጠፋሽ ነበር››

‹‹ሁላችን ከሞትን ሚስትህን አታገኛትማ››

‹‹አውቃለሁ›› አለ ኤዲ ነገር ግን ሚስቱን በነዚያ አረመኔዎች እጅ ለአንድ ቀን እንኳን ሊተዋት አይፈልግም፡፡ ‹‹ምናልባተም አብጄ ሊሆን ይችላል›› አለ ኤዲ፡

ሉተር በጭንቀት እንደተወጠረ ‹‹ይሄ አይሮፕላን ባህር ላይ ያርፋል አይደል?››

‹‹የተገኘው ባህር ላይ ያርፋል ማለት አይደለም፡፡ አይሮፕላኑ ለማረፍ ፀጥ ያለ ባህር ይፈልጋል፤ ማዕበልና ወጀብ የበዛበት ባህር ላይ ልረፍ ካለ ብትንትኑ ነው የሚወጣው።

‹‹ወይ አምላኬ! እዚህ አይሮፕላን ውስጥ የተሳፈርኩት ምን አቅብጦኝ
አለ ቶም።

‹‹ሚስቴን ለማፈን የተነሳኸው ምን አቅብጦህ ነው?›› አለ ኤዲ ጥርሱን ነክሶ።

አይሮፕላኑ ድንገት ዘጭ ሲል ሉተር ወደ መጸዳጃ ክፍል ሮጠ፡፡

ኤዲ ተሳፋሪዎቹ ወዳሉበት ክፍል አመራ፡፡ ካርታ የሚጫወቱት ሰዎች
የመቀመጫ ቀበቶዎቻቸውን አስረዋል፡፡ አይሮፕላኑ ሲንዘፈዘፍና ሲወዛወዝ
ብርጭቆዎች ካርታዎችና ጠርሙሶች ምንጣፍ ላይ ይንከባለላሉ፡ኤዲ
ኮሪደሩ ላይ አማተረ፡፡ አሁን አይሮፕላኑ ፀጥ ብሎ መጓዝ ስለጀመረ
መኝታቸው ተመልሰው
ተሳፋሪዎች ተረጋግተዋል፡፡ አንዳንዶቹ ወደ መኝታቸው ተመልሰው በመቀመጫ ቀበቶዎች ተጠፍረዋል። በአይሮፕላኑ መወዛወዝ ከመውደቅ ለመዳን ከመታሰር ውጪ ሌላ ምርጫ እንደሌላቸው አውቀዋል፡፡ አንዳንዶቹ
ደግሞ መጋረጃቸውን ከፍተው ጋደም ብለዋል፡፡ አንዳንዶቹ ተሳፋሪዎች
ጉዞው ሰላማዊ ባይሆንም ፍርሃታቸውን ዋጥ አድርገው ይጫወታሉ።
አንዳንዶቹ ደግሞ ፍርሃቱ ሰቅዞ ይዟቸው መጫወቱንም ትተውታል
መጽሐፍት፣መነጽሮች፣ፒጃማዎች፣ አርቲፊሻል ጥርስ፣ሳንቲሞችና
አምባሮች ወለሉ ላይ ተበታትነው ይታያሉ፡፡ ኤዲ እሱ በፈጠረው ችግር
አይሮፕላኑ በወጀቡ ውስጥ ለመጓዝ በመገደዱ ምክንያት ያለ ቅጥ
በመወዛወዙ ተሳፋሪዎች መሰቃየታቸውን ሲያስበው በፀፀት ልቡ ተነካ፡፡ ይሄ
ሁሉ ሰውስ በእሱ ምክንያት ያልቅ ይሆን?›

ኤዲ ወደ መቀመጫው ሄደና ተቀመጠ፡፡ ከዚህ በኋላ ስለነዳጁ ፍጆታ
ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ካሮል አንን ከነዚያ አረመኔዎች እጅ መንጭቆ
ለመውሰድ ያለው አማራጭ በዕቅዱ መሰረት የተባለው ቦታ ላይ አይሮፕላኑን በድንገት ማሳረፍ ብቻ ነው፡፡
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሰላሳ_አምስት

#ተከታታይ ልቦለድ

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹የትናንቶቹን ልጆች ሙሉ ታሪክ ማወቅ እፈለጋለሁ››ለንስሯ ነው እየነገረችው 

‹‹ይቻላል››መለሰለት ዛፉ ላይ ሆኖ
‹‹በቃ አሁን ዝናቡ ሊዘንብ ነው …ዝናቡ ሲያባራ ታጣራልኛለህ››
በእሷ በማሾፍ በሚመስል ሁኔታ  ክንፉን አርገፈገፈ…እሷ እንዲህ ያለችው ግቢዋ ውሰጥ ያሉ አዕዋፋት ዝናቡን ሽሽት በየዛፎቹ ቅርንጫፎች ሲሸሸጉ እና ወደጎጆቸው ሲገቡ ..ዝንጀሮዋችና ጉሬዛዎቾ ወደመጣለያቸው ሲሸጎጡ አይታ… እሷም ውሽንፍሩን  በመፍራት ወደቤት ልትገባ መነሳቷን ከግምት በማስገባት ንስሯም እየዘነበ ካለው ዝናብ ለመጠለል አብሮኝ ተከትሎ ወደቤት  ይገባል በሚል ግምት ነው…..በሀሳብ ውስጥ ሆና በዝንጉነት ያሰበችው ሀሳብ 
ለካ ንስር ነው…
ንሰሯ አይኖ እያየ ወደላይ ተምዘገዘገ .እያነሰ እያነሰ ደመናውን ሰንጥቆ ከአይኗ ተሰወረ ….አዎ ከደመናው በላይ ብቻ ሳይሆን ከሚዘንበውም ዝናብም በላይ ነው የሆነው..እሷ ዝናብን ስትጠለል ንስሯ ንፍስ የቀላቀለውን ውሽንፍር እየሰነጠቀ በኩራትና በአሸናፊነት ከተዘረጋው ደመና እና ከሚረግፈው ዝናብ በላይ  በመምጠቅ  ቁልቁል እያየ ሊዝናናበት..
በንስሯ ሁኔታ ፈገግ አለችና ወደ ውስጥ ገባች…..ቁርስ ልታበስል አስባ ነበር …ግን ምንም አይነት የምግብ ፈልጎት ስለሌላት ወደመኝታ ክፍሏ ገባችና መልሳ አልጋዋ ላይ ወጣች..አዎ በዝናብ መኝታ ውስጥ ሆኖ ማሰብ ወይም ሙዚቃ ማዳመጥ የሚያስደስታት ነገር ነው…

‹‹እስቲ ንስሬ ስለትናንቱ ባሪያ ልጅ እና በቅርቡ  ሟች ስለምትሆነው  ፍቅረኛው ምን አይነት ታሪክ ይዞልኝ ይመጣ ይሆን ……….?የልጅቷስ የማይድነው  በሽታዋስ ምን  ይሆን….?እንድትሞት ልተዋት ..ወይስ ከንስሬ ጋር ሆኜ ላድናት……….?ቆይ እሱ እንደታሪካቸው ሁኔታ ነው የሚወሰነው….አሁን ንስሬ ከቅኝት ሲመለስ ልክ እንደተካታታይ የሆሊውድ ፊልም ታሪካቸውን ይዘረግፍልኛል….››
ምክንያቱን ባታውቅም ንስሯ ካሰበችው በላይ ቆየባት፡፡
ቆይ ቆይ እስኪ ድምጽ ይሰማኛል………….
ገርበብ ያለው መኝታ ቤት ተበረግዶ ተከፈተ…ሌላ ሰው አይደለም ንስሯ ነው….በራፉን  በመንቁሩ ስቦ በመበርገድ በሮ አልጋዋ ላይ ከጎኗ ጉብ ያለው… ክንፎቹን ወደ ውስጥ ሰብስቦ አንገቱን  ቀብሮ ሽብልል ብሎ ተኛ…ጥሩ ነገር ይዞላት እንዳልመጣ ገባት…ሁልጊዜ የሆነ ነገር እንዲያጣራላት ልካው ያገኘው መረጃ አና ከምፈልገው በተቃራኒ ከሆነ እንዲህ ነው ዝልፍልፍ የሚለው…ዝልፍልፍ ማለት ደግሞ በእሱ አያምርም፡፡ 
የንስሯን ሁኔታ ሰለልጁ ታሪክ  ለማወቅ ያለቻትን ጉጉት በእጥፍ ጨመረበት..እራሷን አስተካክላ ሀሳቧን ሰብስባ ወደንስሯ አዕምሮ ዘልቃ ገባች..ያየውን ለማየት…ያወቀውን ለማወቅ
//
የትናንትናው ቀልቧን ሰልቧት የነበረው ባሪያው  ልጅ መላኩ ይባላል ..እሷ ማለት ከሞት ጋር ቀጠሮ ይዛ በስጋት ኑሮ ላይ ያለችው ፍቅረኛው ስም   ደግሞ ሰሚራ ትባላለች…ሁለቱ የተገናኙት ከአራት አመት በፊት ነው….
ንስሯም ስለሁለቱ ፍቅረኛሞች ይዞላት የመጣው ታሪክ መነሻው ከተገናኙበት የዛሬ አራት አመት ወዲህ ያለውን ነው……
አዎ ሰሚራ ነርስ ነች …በአንድ የግል ሆስፒታል ውስጥ በነርስነት በምትሰራበት እና ተረኛ ሆና የስራ  ገበታው ላይ በነበረችበት በአንድ ቀን ከ4 ዓመት በፊት ማለት ነው፡፡አንድ ወጣት በሞት እና በህይወት መካከል ተንጠልጥሎ  አረፋ ደፍቆ  እያቃተተ በአንብላንስ ተጭኖ  ይመጣል..
አጋጣሚ ሆኖ በዕለቱ  ሰሚራ ተረኛ እንደመሆኗ  መጠን   ከሌሎች  ዶክተሮች ጋር ሆና የመጣውን በሽታኛ ህይወት ለማትረፍ  ባለአቅማቸው እና  ቴክኖሎጂውን በመጠቀም  ይሯሯጣሉ…. ወጣቱ ኃይለኛ ገዳይ መርዝ በመላ ሰውነቱን ተሰራጭቶ  አንጀቱን እየበጣጠሰው ነበር ....ከዛ በእነሱ ጥረት  የእግዜርም  በጎ  ፍቃድ  ተጨምሮበት   ከመሞት ይተራፋል… ግን ጉዳቱ ከፍተኛ ስለነበር  ከገባበት ኮማ ለመንቃት አልቻለም ነበር….ስለሆነም  የጤናው ሁኔታ በአስተማማኝ ሁኔታ እስኪስተካከል  እዛው ሆስፒታል ተኝቶ ክትትል እንዲያደርግ ይወሰናል…
ያ ወጣት ሆስፒታል  ከገባበት ቀን አንስቶ አብረውት የነበሩ አንድ ሴት እና አንድ ወንድ ጎልማሶች ነበሩ….ሰሚራ በወቅቱ ከእነሱ ከራሳቸው  ጠይቃ እንደተረዳችው ሴቷ የበሽተኛው  ፍቅረኛ ወንዱ ደግሞ በአባት የሚገናኘው ግማሽ ወንድሙ  …..….በተጨማሪም ፖሊሶችም ገባ ወጣ ይሉ ነበር…የበሽተኛውን መንቃት ተከትሎ  የሚሰጠውን ቃል ለመቀበል…
እሷም ምንም እንኳን የስራዋ አንዱ ግዳጅ እና ኃላፊቷ  ቢሆንም  ግን በማታውቀው ሌላ ተጨማሪ የተለየ ስሜት እየተገፋፋች በከፍተኛ ሁኔታ ስትንከባከበው ትቆያለች…አብረውት የሚያሰትምሙት ቤተሰቦቹ  እስኪገረሙባት ድረስ፡፡በሽተኛው እስከ ሶስተኛው ቀን ድረስ ከገባበት ኮማ መንቃት አልቻለም ነበር ፤በአራተኛው ቀን ግን ለ5 ደቂቃ ያህል አይኖቹን መግለጥ እና አንደበቱን ማላቀቅ ቻለ..የመዳን ተስፋው በእጥፍ ጨመረ፤ይሄ ሁኔታ  ሰሚራን እና ጓደኞቾን በጣም ቢያስደስታቸውም የመላኩን አሰታማሚ  ቤተሰቦች ግን  በሚገርም ሁኔታ አለመረጋጋት እና ድንጋጤ ውስጥ ከተታቸው፤ይህንንም ጉዳይ ሰሚራ መታዘብ ስለቻለች ግራ ተጋብታ ትዝብቷን በውስጧ ቀብራ ስትብሰለሰል  ትሰነብታለች፤በአምስተኛው  ቀን ግን  ሰሚራ የእለት ስራዋን አጠናቃ ወደቤቷ ስትመለስ  የመላኩ  አስታማሚዎች እቤቷ  በራፍ ላይ ቆመው ሲጠብቋት አገኘች
ሰሚራም  ደንግጣ‹‹ምን  ተፈጠረ..….?ምን እግር ጣላችሁ….?››
ሰላም ምትባለው…የመላኩ  እጮኛ‹‹ተረጋጊ አንድ ነገር ልናማክርሽ ነው….?››አለቻት፡፡
‹‹ምንድነው ምታማክሩኝ …….?ደግሞስ ሆስፒታል ተገናኝተን አልነበር..እዛው እኮ ልትጠይቁኝ  ትችሉ ነበር…?››
የበሽተኛው ግማሽ ወንድም የሆነው ሰሎሞን‹‹አይ እዛማ በስራ ወከባ ላይ ስለሆንሽ የግል ጉዳይ ለማውራት  አይመችም ብለን ነው››
ግራ ትጋባና ‹‹የግል ጉዳይ …….?ማለት ስለ መላኩ ጤንነት ማለታችሁ ነው….?›› ብላ ጠየቀች…ሌላ ከእሷ ጋር የሚያገናኘው ጉዳይ አልታይሽ ብሏት፡፡
ሰላም እያቅማማች ‹‹አዎ ግን ካላስቸገርንሽ  ወይ እቤትሽ ገብተን ወይ ደግሞ ሌላ ቦታ ሄደን ብናናግርሽ››
ሰሚራ ምታደርገውም ምትናገረውም ግራ ገብቷት  ወደ ቤቷ  ይዛቸው ትገባለች…ወደቤት ከገቡ በኃላ ለውይይት ያቀረቡላት ርዕስ  ከጠበቀችው በጣም የራቀና  አስደንጋጭ ነበር…››
የግማሽ ሚሊዬን ብር ቼክ በእጇ ላይ ካስቀመጡላት በኃላ ….‹‹መላኩን  እንዳይድን አድርጊልን››ነበር ያሏት፡፡
‹‹እንዴ ለምን…….?ለአንቺ ፍቅረኛሽ ለአንተ ደግሞ ወንድምህ አይደል…….?ነው ወይስ ዋሽታችሁኛል….?፡፡››
‹‹አይ እሱን አልዋሸንሽም…ግን አንቺ ማይገባሽ ብዙ ጉዳዬች አሉ..አሁን ብታድኝው እራሱ ሙሉ ጤነኛ አይሆንም ..አካሉ እንደልብ ላይታዘዝለት ይችላል..ወይም አዕምሮው የማሰብ አቅሙ ተዛብቶ  ዘገምተኛ ሆኖ ሊቀር ይችላል….እንደዛ የመሆን እድል እንደሚገጥመው  ደግሞ  የነገራችሁን እናንተው ናችሁ፡፡››