ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
247K subscribers
290 photos
1 video
15 files
243 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ወጀቡ እስኪጠፋ ወለሉ ላይ ተቃቅፈው ቆዩና ‹‹መርቪን አልጋው ላይ
እንውጣ ከወለሉ ይልቅ እዚያ ይመቸናል›› አለ፡
ናንሲ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች፡፡ ከዚያም በጉልበቷ እየዳኸች
አልጋው ላይ ወጣች፡፡ መርቪንም ተከተላትና አልጋው ላይ አብሯት ወጣ፡፡
እሱም እቅፍ አድርጎ ያዛት፡፡
በወጀቡ ምክንያት አይሮፕላኑ በተናወጠ ቁጥር ልክ መርከበኛ የጀልባ
ውን ምሰሶ እንደሚይዝ ሁሉ ናንሲ መርቪንን ጭምቅ አድርጋ ትይዛለች፡፡
ወጀቡ ሲቀንስና ዘና ስትል እሱም ሰውነቷን በፍቅር ይነካካቸዋል ከዚያ ትንሽ ቆየችና እንቅልፍ ይዟት ሄደ፡፡.
በሩ ተቆርቁሮ «አስተናጋጅ መቷል» የሚል ድምፅ ስትሰማ ከእንቅልፏ ነቃች።
ዓይኖቿን ስትከፍታቸው መርቪን ደረት ላይ መተኛቷን አወቀች
‹ወይ አምላኬ! አለች እየተርበተበተች፡

መርቪን ከተኛችበት እንድትነሳ በእጁ ገፋ አደረጋትና ‹‹ትንሽ ጠብቀን
አስተናጋጅ›› አለ፡፡

ከበሩ ውጭ የቆመው አስተናጋጅ በተደናገጠ ድምፅ እሺ ጌታዬ
እጠብቃለሁ›› አለ፡፡

መርቪን ከአልጋው ወረደና በአልጋ ልብስ ናንሲን ሸፈናት::

በዚህ አድራጎቱ በሆዷ አመሰገነችው፡፡ አስተናጋጁ እንዳያያት ፊቷን ወደ ግድግዳው አዞረች፡፡

መርቪን በሩን ሲከፍት አስተናጋጁ ገባና ‹‹እንዴት አደራችሁ›› አለ በፈገግታ፡፡

የትኩስ ቡና መዓዛ ናንሲን አወዳት፡፡ ‹‹በእንግሊዝ የሰዓት አቆጣጠር
የሶስት ሰዓት ተኩል ወደ ኋላ ነው ማለት ነው?›› አለ አስተናጋጁን

‹‹ልክ ነው ጌታዬ የኒውፋውንድ ላንድ የሰዓት አቆጣጠር ከግሪንዊች
የሰዓት አቆጣጠር  ሶስት ሰዓት ተኩል ወደ ኋላ ይዘገያል፡››

‹‹መቼም የአየር መንገዶችን የጉዞ መርሃ ግብር ለሚያዘጋጁ ሰዎች ይህ  የሰዓት አቆጣጠር  ችግር
ሳይፈጥርባቸው አይቀርም፡፡ ባህር ላይ ለማረፍ ምን
ያህል ሰዓት ይቀረናል?›› ሲል ጠየቀ መርቪን

‹‹ከግማሽ ሰዓት በኋላ እናርፋለን፡ ከመርሃ ግብሩ አንድ ሰዓት ጉዟችን
የዘገየው በወጀቡ ምክንያት ነው›› አለና አስተናጋጁ በሩን ዘግቶ ወጣ፡

ናንሲ በሩ ከተዘጋ በኋላ ‹የመስኮቱን መጋረጃ ክፈተው፡ ነግቷል››
አለችው:፡ መርቪን ቡና ሲቀዳ የትናንት ምሽት አዳራቸው ፊቱ ላይ መጥቶ
ድቅን አለ፡፡ ወጀቡ በተነሳ ቁጥር መርቪን እጇን የሚይዛት፣ ወለሉ ላይ
የሚወድቁት፣ የመርቪን እጆች ጡቶቿን ሲጨብጥ፣ አይሮፕላኑ ሲናወጥ፣
እሱ ደረት ላይ ልጥፍ የምትለውና እየደባበሰ የሚያስተኛት ትዝ አላት:
ይህን ሰው በጣም ወድጄዋለሁ› አለች በሆዷ።

‹‹ቡና እንደወረደ ወይስ ከወተት ጋር ነው የምትፈልጊው?›› ሲል
ጠየቃት፡፡

‹‹ጥቁር ቡና ይሁንልኝ፡ ስኳር አልፈልግም››
‹‹እንደ እኔ›› አለና ቡናዋን አቀበላት ናንሲ አመስግና ቡናዋን ጠጣች፡፡

ናንሲ ስለ መርቪን በደንብ ማወቅ ፈለገች፡፡ ቡናውን እየጠጣ ስለእሱ ልማዶች ግምቷን አስቀመጠች፡፡ ቴኒስ ይጫወታል፣ ልብ ወለድ ብዙ ማንበብ አይወድም፣ ገበያ መሄድም እንደዚሁ፣ ቁማር ጨዋታ የሚሳካለት ይመስላል፣ ዳንስ ግን የሚችል አይመስልም፡፡›
‹‹ምንድን ነው የምታውጠነጥኚው?›› ሲል
ጠየቀ ለሕይወት  ኢንሹራንስ አደገኛ እንደሆንኩ አድርገሽ የምታይኝ መሰለኝ፡፡››

ናንሲ ቀልዱ አሳቃት፡፡ ‹‹ምን አይነት ሙዚቃ ነው የምትወደው?›› ለሙዚቃ ጆሮ አልሰጥም›› አለ ‹‹መደነስ ባልጠላም ጥሩ ደናሽ ግን አይደለሁም፡፡ አንቺስ?››

እኔ ድሮ ደንሼያለሁ፡መደነስም ነበረብኝ፡፡ እሁድ እሁድ ሱፍ ከሚለብሱ ወንዶች ልጆች ጋር በዳንስ ትምህርት ቤት ዳንስ እማር ነበር፡፡ከላይኛው መደብ የቦስተን ማህበረሰቦች ጋር ለመግባባት ብቸኛው መንገድ ይህ ብቻ እንደሆነ እናቴ ትነግረኝ ነበር፡ እኔ ግን ከዛ ማህበረሰብ ውስጥ
ብገባ ባልገባ ግድ አልነበረኝም፡: የኔ ቀልብ ያለው ከአባቴ ፋብሪካ ጋር ነው፡፡ እናቴ ደግሞ ይሄን ባህሪዬን አትወደውም ነበር፡››

ሁለቱ አዲስ ፍቅረኛሞች ተያዩ፡፡ መርቪንም ትናንት ማታ እንዴት ሲላፉና ሲላላሱ እንዳመሹ እንደሚያስብ ነቃችበት፡፡ ይህም ሀሳብ እፍረት
ውስጥ ከተታትና ፊቷን ወደ መስኮቱ ስታዞር መሬት ታያት፡፡ አይሮፕላኑ
ቦትውድ ሲያርፍ ህይወቷን የሚለውጠውን የስልክ ጥሪ ማድረግ እንዳለባት ትዝ አላት፡ ‹‹ደርሰናል›› አለችና ከመኝታዋ ዘላ ተነሳች ‹‹ልብሴን ልልበስ›› አለች፡፡
‹‹እኔ ቀድሜ ልውጣ›› አለ መርቪን ‹‹ለአንቺ ጥሩ ነው››
እሺ፧ አሁንስ ምን ቀልብ አለኝ አለች በሀሳቧ። ይህን ለእሱ አልነገረችውም፡፡ መርቪን ልብሱን ስበሰበ፡፡ በሩን ከፍቶ ሊወጣ ሲል
ተጠራጠረና ቆመ፡፡ እሷም እንደገና ሊስማት እንደፈለገ አውቃ ወደ እሱ ሄደችና ከንፈሯን ሰጠችው፡፡ ‹‹ሌሊቱን በሙሉ እቅፍ አድርገህ ስላስተኛኸኝ
አመሰግንሃለሁ›› አለችው:

መርቪን ከአንገቱ ዝቅ አለና ሳማት፡፡ አሳሳሙ ልስልስ ያለ ነበር፡ አፏን በአፉ ግጥም አድርጎ ነው የሳማት፡፡ እየተሳሳሙ ትንሽ ቆዩና ተላቀቁ፡፡

ናንሲ በሩን ከፍታ ያዘችለትና ወጥቶ ሄደ፡፡

በሩን እንደዘጋች የደስታ ሲቃ ተናነቃት፡ ከዚህ ሰው ፍቅር ሊይዘኝ ነው አለች፡ በመስኮቱ ስታማትር አይሮፕላኑ ቀስ በቀስ እየወረደ ነው፡፡

መፍጠን አለባት፡፡

መስታወቱ ፊት ቆማ ፀጉሯን ቶሎ አሰረችና የመዋቢያ ዕቃዎቿን ይዛ የሙሽሮቹ ክፍል አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ሴቶች መታጠቢያ ቤት ሄደች፡፡እዚያ ሉሉ ቤልንና አንድ ሌላ ሴት አገኘች፡፡ የመርቪን ሚስት ግን የለችም:

ናንሲ ፊቷን እየታጠበች ጧት ከመርቪን ጋር ያደረገችውን ውይይት
አስታወሰች፡፡ እሱን ስታስብ ደስታ ቢሰማትም ደስታው የተሟላ ባለመሆኑ
ከጭንቀት ሊገላግላት አልቻለም፡፡ ስለሚስቱ ምንም አላለም፡፡ ትናንት ማታ ስለእሷ ስትጠይቀው ድንግርግር እንዳለው ነው የነገራት፡፡ ከዚያ በኋላ ግን
ይወዳት ይሆን? ትናንት ማታ ሌሊቱን ሙሉ ደረቱ ላይ ለጥፎ ነው ያሳደራት ይህ ብቻውን ጋብቻን ይፍቃል ማለት ግን አይደለም፡
እኔ የምፈልገው ምንድን ነው? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ ‹መርቪንን እንደገና ማግኘት እፈልጋለሁ ከእሱ ጋር ድብቅ ወዳጅነት  ልመስርት?ታዲያ ለኔ ብሎ ጋብቻውን እንዲያፈርስ እፈልጋለሁ? ከአንድ  ሌሊት
ወሲባዊ ልፊያና መሳሳም በኋላ ይህን እንዴት ማወቅ እችላለሁ?
ሊፕስቲክ ለመቀባት መስታወቱ ላይ አፈጠጠች ናንሲ መጠራጠርሽን አቁሚ
ስትል ለራሷ አሳሰበች እውነታውን ታውቂዋለሽ፤ ይሄን ሰው በጣም ፈልገሽዋል፧ ከአስር ዓመት ወዲህ እጅሽን የሰጠሸው ለዚህ ሰው ነው፡:
አሁን አርባ አመትሽን ደፍነሻል፡ አሁን ተገቢውን ሰው አግኝተሻል፡ እዚህ
እዚያ መርገጥሽን ትተሽ ይህን ሰው በእጅሽ አድርጊ፡፡›

ሰውነቷ ላይ ሽቶ አርከፈከፈችና ወጣች፡

ስትወጣ ከመታጠቢያ ቤቱ አጠገብ የተቀመጡትን ናት ሪጅዌይና ወንድሟን ፒተርን አገኘቻቸው ናት ‹‹ደህና አደርሽ ናንሲ›› አላት::

ይህን ስትሰማ ከአምስት ዓመት በፊት በዚህ ሰው የነበራትን ስሜት
አስታወሳት፡፡ እኔ ከእሱ ፍቅር ይዞኝ ነበር፡፡ እሱ ግን ከእኔ ይልቅ የፈለገው
ብላክ ቡትስ ኩባንያን ነበር፡፡ አሁንም ኩባንያውን በእጁ ለማስገባት
የሚፈልገውን ያህል እኔን አይፈልገኝም፡፡ ለሰላምታው በራስ ንቅናቄ ብቻ
አፀፋዊ ሰላምታ ሰጥታው ወደ ክፍሏ ሄደች፡፡

አስተናጋጆቹ መኝታዎቹን ወደ ሶፋነት ለውጠዋቸዋል። መርቪን ጢሙን ተላጭቶና በነጭ ሽሚዝ ላይ ሱፍ ልብሱን ለብሶ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ ‹‹በመስኮት ተመልከች ደርሰናል›› አላት፡፡