😎ጠላፊዎቹ
፡
#ክፍል_ሃምሳ_አንድ
#የመጨረሻው ክፍል
፡
#በኬንፎሌት
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
ጎረምሳውና ጆ ውሃ ውስጥ እየሰጠሙ ስታይ ጮኸች፡፡
ወጣቱ ልጅ ወደ ላይ ለመውጣት ሲሞክር ጆ ደግሞ ህይወቱን ለማትረፍ ወጣቱን ወደ ታች ይጎትታል፡፡ በጣም አስፈሪ ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡
ማርጋሬት መጮኋን ሰምቶ ሉተር በመስኮት ተመለከተና ‹‹ባህሩ ውስጥ ወድቀዋል››› ሲል ጮኸ በጭንቀት፡፡
‹‹እነማ ናቸው?›› አለ ቪንቺኒ፡፡
‹‹ጎረምሳውና ጆ›› አለ ሉተር፡
የጀልባው ነጂ ገመድ ቢወረውርላቸውም ሁለቱ ሰዎች አላዩትም፡፡ እነሱ
የሚይዙትን አጥተው በፍርሃት ውሃ ውስጥ እየተንቦራጨቁ ሲሆን ጆ
ጎረምሳውን ልጅ ወደ ባህሩ ውስጥ እየደፈቀው ነው፡፡
‹‹እባክህ እርዳቸው›› አለ ሉተር እሱም በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ፡፡
‹‹ምን?›› አለቪንቺኒ ‹‹ምንም ልንረዳቸው የምንችለው ነገር ያለ
አይመስለኝም፡ እነሱም ራሳቸውን ለማዳን አቅም የላቸውም፡፡›› በመጨረሻም
ሁለቱን ሰዎች ጨካኙ ባህር ሰለቀጣቸው፡
‹‹እንዴት ሊሆን ቻለ?›› ሲል ጠየቀ ሉተር ‹‹በመጀመሪያ ውሃ ውስጥዐእንዴት ሊወድቁ ቻሉ?››
‹‹ምናልባት የሆነ ሰው ገፍቷቸው ይሆናል›› አለ ቪንቺኒ፡
‹‹ማን?››
‹‹እዚህ አይሮፕላን ውስጥ የሆነ ሌላ ሰው ይሆናል፡›› ማርጋሬት የሁለቱን ሰዎች ንግግር ስትሰማ ስለነበር ሄሪ ሊሆን ይችላል› ስትል
ገመተች፡ ሄሪ ጀልባው ውስጥ ይኖር ይሆን?
ፖሊሶቹ አይሮፕላኑን
ሲፈትሹ እሱ የሆነ ቦታ ተደብቆ አይሮፕላኑ ባህሩ ላይ ሲያርፍ ከተደበቀበት
ወጥቶ ይሆን? ሁለቱን ወሮበሎች ውሃ ውስጥ ገፍቶ የጨመራቸው እሱ
ይሆን? እያለች መልስ የሌለው ጥያቄ በአዕምሮዋ ተጉላላ፡፡
በኋላ ደግሞ ወንድሟ ትዝ አላት ፔርሲ የወሮበሎቹ ጀልባ ከአይሮፕላኑ ጋር በሚታሰርበት ጊዜ ነው የጠፋው፡፡ ‹ምናልባትም መጸዳጃ ቤት ሄዶ ግርግሩ እስኪያልቅ እዚያው ሊቆይ አስቦ ይሆናል› አለች በሆዷ፡
እሱ ደግሞ እንዲህ አይነት ባህሪ የለውም፡፡ እሱ እንደውም ሁሉን ነገር
ለማወቅ ስለሚፈልግ ችግር አይፈራም፡፡
ሉተር ‹‹ሁሉ ነገር ከእጃችን እየወጣ ነው ምን ብናደርግ ይሻላል?›› ሲል ጠየቀ፡
‹‹አሁን በመጣችው አይሮፕላን እንሄዳለን እንዳቀድነው፡፡ አንተ፣ እኔና
ሳይንቲስቱ›› አለ ቪንቺኒ፡ ‹‹መንገዳችንን ሊያሰናክል የሚሞክር ሰው ካለ
በሆዱ ጥይት ልቀቅበት፡ አሁን ረጋ ብለን እንውጣ፡፡››
ማርጋሬት ወሮበሎቹ ፔርሲን ደረጃው ላይ ያገኙትና በሆዱ ጥይት
ይለቁበታል ብላ ሰጋች፡
ሶስቱ ሰዎች ከምግብ ቤቱ ሲወጡ የፔርሲ ድምጽ ከበስተኋላቸው
ተሰማ፡፡ ድምጹንም ከፍ አድርጎ ‹‹እንዳትነቃነቁ!›› አለ፡፡
ፔርሲ ቪንቺኒ ላይ ሽጉጡን መደገኑን ስታይ ማርጋሬት ዓይኗን ማመን አቃታት፡፡ የሽጉጡን አፈሙዝ አይታ ካፒቴኑ ከኤፍ.ቢ.አዩ ሰውዬ
ላይ የነጠቀው መሆኑን ገመተች፡
ቪንቺኒ ቀስ ብሎ ወደ ፔርሲ ዞረ፡፡
ማርጋሬት የወንድሟ ህይወት አደጋ ላይ ቢሆንም በፔርሲ ኮራች፡፡
የመብል ክፍሉ በሰው
ተሞልቷል፡፡ ከቪንቺኒ ኋላ ማርጋሬት ከተቀመጠችበት አጠገብ ሉተር በሃርትማን ላይ ሽጉጡን ደግኗል፡ በሌላኛው በኩል ናንሲ፣ መርቪን፣ ዳያና፣ ኤዲ እና ካፒቴኑ ቆመዋል ቪንቺኒ ፔርሲን ዘለግ ላለ ጊዜ አየውና ‹‹ልጅ ከዚህ ጥፋ›› አለው፡፡
‹‹ሽጉጥህን ጣል!›› ሲል ፔርሲ አዘዘ፡፡
በመሃል አንድ ጥይት ጮኸች፡፡ የጥይቱ ድምጽ ጆሮ ያደነቁራል፡
ማርጋሬት ጩኸቷን አቀለጠችው: ማን ማን ላይ እንደተኮሰ አላወቀችም:: ፔርሲ ምንም አልሆነም፡፡ ትንሽ ቆይቶ ቪንቺኒ ከደረቱ ላይ ደም እየተንፎለፎለ ተንገዳገደና መሬት ዘፍ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ቦርሳው
ሲወድቅ ተበረገደና ብሮቹ በደም ታጠቡ፡
ፔርሲ ቪንቺኒን ሲያይ ሽጉጡን ጣለ፡፡ ደንግጧል፡
ሁሉም ሰው ሽጉጥ የያዘው የመጨረሻው ወሮበላ ላይ አፍጧል፡
ካርል ሃርትማን በተፈጠረው
ሁኔታ ከተዘናጋው ሉተር መንጭቀው ራሳቸውን ነጻ አደረጉና መሬት ያዙ ማርጋሬት ሳይንቲስቱን ይገድላቸዋል ብላ ሰግታለች ፔርሲንም እንዲሁ፡ ነገር ግን ወዲያው የሆነው ግን
አስደንግጧታል፡፡
ሉተር አፈፍ አድርጎ ያዛት፡ ከወንበሯ ጎትቶ አነሳትና ጭንቅላቷ ላይ ሽጉጡን ደገነባት፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉም በድንጋጤ በድን ሆኑ።
ማርጋሬት ፍርሃት ስለገባት መንቀሳቀስ መጮህ አልቻለችም፡ የሉተር
ሽጉጭ ጭንቅላቷን እየወጋት ነው፡ ሉተር ራሱ ይንቀጠቀጣል፡፡ ከዚያም
ሳይንቲስቱን ‹‹ውጣና ጀልባ ውስጥ ግባ፡፡ ትዕዛዜን ካልፈጸምክ ልጅቷ
ጭንቅላት ላይ ጥይት እቀረቅርበታለሁ›› አለ፡፡
ወዲያው ፍርሃቷ ሲለቃት ታወቃት፡፡ ሉተር ብልህ መሆኑን ተገንዝባለች፡፡ ሽጉጡን ሃርትማን ላይ ደግኖ ቢሆን ኖሮ ሃርትማን ግደለኝ ጀርመን አገር ከምመለስ ሞቴን እመርጣለሁ› እንደሚሉ እርግጠኛ ሆኗል፡ አሁን ግን የእሷ ህይወት አደጋ ላይ ነው፡ ሃርትማን ምናልባት
ህይወታቸውን ለመስጠት ዝግጁ ይሆኑ
ይሆናል፡፡
ሃርትማን ቀስ ብለው ተነስተው ቆሙ፡፡
ሁሉም ነገር በማርጋሬት ላይ የተጣለ ነበር፡ ራሷን ሰውታ ማዳን ትችላለች፡ ሆኖም ይህ አድራጎት ጥሩ አይደለም፡፡ እሷም ይህን አደርጋለሁ ብላ አልጠበቀችም፡፡ ለዚህ ራሴን አላዘጋጀሁም፡፡ ማድረግ አልችልም› አለች
በሆዷ፡
ከአባቷ ጋር ዓይን ላይን ግጥም አሉ፡፡ አባቷ በጣም ደንግጠዋል ሲያበሻቅጧት እንደኖሩ ምን ያህል
አቅመቢስ እንደሆነች ጦሩንም ተቀላቅላ አንድ ቀን እንኳን እንደማትቆይ
የነገሯት ሁሉ ትዝ አላት፡፡
አባቴ ያለው እውነት ይሆን?› አለች ለራሷ፡
ስለዚህ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባት ወሰነች፡፡ ሉተር ሊገላት ይችላል ነገር ግን አንድ ነገር ከማድረጉ በፊት ሌሎች ሰዎች ዘለው ይረባረቡበታል ጊዜው እየሄደ ነው፤ አንድ ነገር ማድረግ አያቅተኝም, አለች በሆዷ፡
ከዚያም ‹‹ሁላችሁም ደህና ሁኑ›› አለች፡፡ አፍታም ሳይቆይ የሄሪን ድምጽ ከኋላዋ ሰማች፡፡
‹‹ሚስተር ሉተር ጠላቂው መርከብህ ደርሷል›› አለ፡፡
ሁሉም ሰው በአይሮፕላኑ መስኮት ተመለከተ፡፡ ማርጋሬት ሄሪ በተናገረው ነገር ሉተር ልቡ መወሰዱን አወቀች፡፡ ከዚያ አንድ ጥይት ጮኸች፤ እሷ ግን ምንም አልሆነችም፡፡ ሁሉም አንድ ጊዜ ተንቀሳቀሰ፡፡ ኤዲ ዘለለና እንደ ተቆረጠ ዛፍ ሉተር ላይ ወደቀበት፡፡ ሄሪ የሉተርን ሽጉጥ
መንጭቆ ወሰደ፡፡
ፔርሲ ወደ ማርጋሬት ሄደና አቀፈችው፡፡ ‹‹አንተ ግን ደህና ነህ?››ቸ ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ ይመስለኛል››
‹‹በጣም ጎበዝ ነህ››
‹‹አንቺም እንዲሁ››
‹አዎ እኔ ጎበዝ ነኝ አለች ለራሷ፡
ፀጥ ብሎ የቆየው ተሳፋሪ ሁሉ በአንድ ጊዜ ተንጫጫ፡፡ በዚህ ጊዜ
ካፒቴኑ ‹‹ፀጥታ እባካችሁ ዝም በሉ›› አለ፡፡
ማርጋሬት ዙሪያውን ቃኘች፡፡
ሉተር ኤዲ እና ሄሪ ላዩ ላይ ወጥተውበት ከመሬቱ ላይ እንደተደፋ ነው፡፡ አይሮፕላኑ ውስጥ ያንዣበበው አደጋ ተወግዷል፡ ሃርትማንና
ሉተርን ሊወስድ የመጣው ጠላቂ መርከብ ተንሳፎ ይታያል፡
ካፒቴኑም የባህር ኃይል መርከብ በቅርብ ርቀት ይታያል፡ ‹‹ጠላቂ
መርከብ እዚህ እንዳለ የሬዲዮ መልእክት እናስተላልፋለን፡፡››
‹‹ቤን›› ሲል ተጣራ፡
‹‹አቤት ጌታዬ›› አለ የሬዲዮ ኦፕሬተሩ ‹‹የጠላቂው መርከብ አዛዥ
ሬዲዮ መልእክት ማስተላለፋችንን ካወቀ ወደ እኛ ሊተኩስ እንደሚችል
ተገንዝበኸዋል?›› አለ ቤን፡፡
‹‹ደህና ይቅር›› አለ ካፒቴኑ ‹‹ተሳፋሪዎቻችን እስካሁን የደረሰባቸው መከራ
ይበቃል፡››
ጠላቂው መርከብ መግቢያው እንደተዘጋ ነው አዛዡ አንድ ነገር
ይሆናል ብሎ እየጠበቀ ነው፡፡
‹‹ቤከር አንድ ያልተያዘ ወሮበላ ይቀረናል፡ እዚህ እንዲመጣ እፈልጋለሁ፡፡ የጀልባዋ ነጂ፡ ኤዲ ሂድና ቪንቺኒ እንደሚፈልገው ንገረው አለው

📕ተአምራተ_ኬድሮን
#ክፍል_ሃምሳ_አንድ
#ተከታታይ ልቦለድ
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
መኝታ ቤቷ ገብታ ልብሷን ከቀያየረች በኋላ የጀመሩትን አይነት መጠጥ አምጥታ ለሁለቱም ቀዳችና ወደጫወታቸውን እዲመለሱ ተመቻቸች..
‹‹እሺ አሁን ካቆምክበት ጀምርልኝ››
‹‹ምን….? ››አለት ሁሉን ነገር የረሳው ይመስላል
‹‹ታሪክህን እየነገርከኝ ነበር››
‹‹እ..አዎ…ግን የት ላይ ነበር ያቆምኩት….?››
‹‹ስለፍቅረኛህ ጀምረህልኝ ነበር..በህይወት የምትኖርበት ምክንያት እሷን አንድ ቀን አገኛት ይሆናል በሚል ጉጉት ምክንያት እንደሆነ ነግረኸኝ ነበር ያቆምከው››
‹‹አዎ….አይገርምሽም …
እስከጥቂት ቀናት ድረስ እኮ ምንም አይነት ተስፋ አልነበረኝም…››
‹‹ቆይ ጠይቀሀት እንቢ ብላህ ነው….?››
‹‹አረ መጠየቅ…ትቀልጂያለሽ እንዴ ….?ቀና ብዬ እንኳን ሰላምታ ልሰጣት ድፍረቱ የለኝም.››
‹‹ግን እኮ እንደዛ አይነት ሰው አትመስልም..በጣም ደፋር ግልጽ እና በራስ መተማመን ያለህ ሰው ነህ››አለችው ከልቧ..
‹‹እኔም እንደዛ ነኝ ብዬ አምናለሁ..ፍቅር የሚባለው ነገር ግን ዋና ባህሪው ያልሆንሺውን ሆነሽ እንድትገኚ ማድረግ ይመስለኛል…እጅግ ክፉ የነበርሽው ሰው በፍቅር ውስጥ ስትሆኚ ስጋዬን ግፈፉት እስከማለት ድርስ የሚደርስ ደግነት ያጓናጽፍሻል….ደንዳናና ኮስታራ የነበርሽው፤አልቃሽና ተርበትባች ሆነሽ ቁጭ….ፍቅር እንደዛ አይነት በሽታ ነው፡፡››
‹‹ቢሆንም ….ይህን ያህል ካፈቀርካት የሆነ ነገር ማድረግ ነበረብህ ..ለመሆኑ የት ነው የምትኖረው….?››
‹‹የሚገርመው እሱ ነው..በእሷ ቤት እና በእኔ ቤት መካከል ያለሁ እርቀት ግማሽ ኪሎ ሜትር አይሆንም…. ሁለታችንም ሳሪስ በአንድ ሰፍር ተወልደን እዛው አንድ ሰፈር ያደግን ነን…ቤተሰቦቻን የአንድ እድር አባል ሆነው፤አንድ የጽዋ ማህበር መስርተው ዕድሜያቸውን በጉርብትና የኖሩ ናቸው….አንድ ቄስ ትምህር ቤትፊደል መቁጠር ጀምረን .አብረን ኤለመንተር የገባን የእድሜ እኩዬች ነን››
‹‹ይገርማል!!››
‹‹እውነትሽን ነው በጣም ይገርማል…. ከ1ኛ ክፍል አንስቶ እስከ አስረኛ ክፍል አብረን ነበር የተማርነው…በተለይ ዘጠነኛ ክፍል አንድ ወንበር ላይ ነበር የምንቀመጠው…ግን በወቅቱ እኔ ግማሽ ልቤ ነበር ክፍል ውስጥ የሚገኘው… እሷ ደግሞ አካሏም ነፍሶም ትምርቱ ላይ የተጣበቀ ነበር፡፡ግን የሚያመሳስለን አንድ ነገር ቢኖር ሁለታችንም ተአምር ካልተፈጠረ በስተቀር ከትምህርት ቤት አንቀርም ነበር..››
‹‹ለምን ….?››አለችው ገለጻው ገርሞት
‹‹እሷ ለትምህርት ባላት ፍቅር የተነሳ እኔ ደግሞ ለእሷ ካለኝ ፍቅር የተነሳ….››
አሳቃት….ብርጭቆውን አንስቶ ከተጎነጨለት በኃላ ቀጠለ
‹‹እሷ እንደማንኛውም የክፍል ጓደኛ ግን ደግሞ ከዛም ትንሽ ከፍ ባለ የሰፈር ልጅነት እና አብሮ አደግነት ነው የምትቀርበኝ…እኔ ደግሞ በዚህ አለም ላይ ሁለት ሴቶች ብቻ ናቸው ያሉኝ.. እናቴ እና እሷ ብቻ..በቃ..ያኔ አብሬት በምማርበት በዛ ጊዜ ብቻ አልነበረም እንደዛ የሚሰማኝ.. አገር ለቅቄ በስደትም እያለው እንደዛ ነበር እምነቴ…የሆነች ሴት በሆነ ነገሮቾ ትንሽም እንኳን ከእሷ ጋር ካልተመሳሰለችልኝ..የሆነ የእሷን ነገር እንዳስታውስ ካላደረገችኝ አንድ ደቂቃም ላወራት ወይም አጠገቧ ልቀመጥ አይቻለኝም….ከአስር አመት መለያየት በኃላ ከ10 ዓመት ናፍቆት በኃላ እሷን እና እናቴን አንዴ አይቼ ለመሞት ወስኜ ወደሀገሩ ስመጣ…እሷን በተመለከተ ጭራሽ ተስፋ የሚያስቋርጥ ነገር ነው ያጋጠመኝ…፡፡አፍላ ልጃገረድ ገና አጎጠጎጤ ሆና ጥያት የሄድኳት ልጅ አድጋና ፈክታ ሙሉ ሴት ሆና ጠበቀችኝ…፡፡የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሆና የተለየኋት ልጅ ዶክተር ተብላ ትልቅ ሆስፒታል ውስጥ ትልቅ ባለሞያ ሆና አገኘኋት..እና የሩቅ ህልሜ የነበረችው ልጅ ጭራሽ መቼም የማትፈታ ቅዠቴ እንደሆነች አሰብኩ…ሳያት በሩቅ መሸሽ ጀመርኩ፡፡ድንገት መንገድ ላይ ስንገጣጠም እንኳን ቅንድቤን ከፍ ዝቅ በማድረግ አንገቴን አቀርቅሬ ሰላምታ ለመስጠት ከመሞከር ውጭ እሷ እንኳን ለሰላምታዬ አፀፋውን መመለሷ እና አለመመለሷን እርግጠኛ ሆኜ አላውቅም፡፡ይህቺ ልጅ የእኔ ልጅነቴ ነች….የሩቅ እሩቅ ትዝታዬ …ብዙ ብዙ ለሊቶች በህልሜ ያየኋት… ብዙ ብዙ ታሪክ ያጫወተችኝ….ብዙ ብዙ ነገር ያወጋኋት…ያወጋችኝ..፡፡እንደዛ ብቻ ሳይሆን ደጋግሜ ያገባኋት…ብዙ ብዙ ልጆች የወለደችልኝ…ብዙ የሳምኳት፤ ብዙ የሳመችኝ…ብዙ ያፈቀርኳት፤ብዙ የወደደቺኝ…ግን ሁሉም በህልሜ የሆነ ነበር …››
‹‹ምን አይነት ፍቅር ነው..ስል አሰብኩ ደግሞ ከዚህች ልጅ ጋር የሚያመሳስለኝ አንድ ነገር ይኖር ይሁን .. ….?አዎ መኖርማ አለበት ….እደዛ ቢሆን ነው ይሄን ሁሉ ሰዓት አብሮኝ ያሳለፈው…እቤቴ ድረስ ተከትሎኝ በለሊት የመጣው…አዎ እንደዛ ቢሆን ነው ሚስጥሩን ዘክዝኮ የሚነግረኝ…››ስትል የራሷን ግምት ወሰደች…ግምቷ እውነት ሆኖ እስከአልጋ መዋደቅና መዋሰብ ድረስ ያደርሷቸው እንደሆነ አሁንም በውስጧ እያሳላሳላች ነው ፡
ቀጠለ እሱ…‹‹እና ይገርምሻል ከሶስት ቀን በፊት ያልጠበቅኩት አጋጣሚ ተከሰተ…››
‹‹ምን ተከሰተ….?››
‹‹ወደሀገሬ ከተመለስኩ ከሁለት ዓመት ተኩል በኃላ ትናንት….ድብር እና ጭፍግግ ብሎኝ ሰፈር ላዳዬ አቁሜ እኔም ላዳዬ ውስጥ ወንበሬን ወደኃላ ለጥጬ መፅሀፍ በማንበብ በተመስጦ ላይ እያለሁ...በሀይለኛው የላዳው የኃላዋ በራፍ ሲንኳኳ የሆነ የእብድ ድርጊት መስሎኝ በርግጌ ተነሳሁና አንገቴን በመስኮት አስግጌ ወደ ኃላው ተመለከተኩ…
‹‹እንዴ ሰላም…!!!!!››
‹‹ክፈትልኝ››
‹‹እሺ ››ተረብትብቼ ከፈትኩላት..ተስፈንጥራ ገባች…የሆነ ሰው ከኃላ እያባረራት ይመስላል..ፀጉሯ ሁሉ ጭብርር ብሏል…የአይኖቾ ደም መልበስ ምን አልባት ለቀናት ስታለቅስ እንደቆየች ምስክር ናቸው…..አለባበሶም እንደነገሩ እና ያልታሰበበት ነው….››የአመታት ህልሜ የሆነች ልጅ በእንዲህ አይነት ያልታሰበበት አጋጣሚ ላዳዬ ውስጥ ትገባለች ብዬ እንኳን ማሰብ አልሜ እንኳን አላውቅም…..
‹‹ንዳው ››አለችኝ
ህልም ውስጥ ያለሁ ነበር የመሰለኝ ፡፡ ትዛዞን ተቀብዬ …ሞተሬን አንቀሳቀስኩ እና ነደሁት
‹‹-የትኛው ፖሊስ ጣቢያ እንሂድ….?››ጠየቅኳት
‹‹የምን ፖሊስ ጣቢያ….?›› አለችን ግራ በመጋባት
-‹‹አይ እንዲሁ ነገር ስራሽን ስገመግመው የሆንሽው ነገር ያለ ስለመሰለኝ ነው..››
‹‹ሆኜያለሁ...አዎ የሆነ ነገር ሆኜያለሁ… መች አልሆንኩም አልኩህ …ግን ወደ ፖሊስ ጣቢያ መሄድ ምን ይፈይድልኛል..….?››አለቺኝ.‹‹ይቅርታ እሺ የት ልወስድሽ..….?››አልኳት
በመለማመጥ..እወነቴን ነው በዛች ላዳ ጆሀንስበርግ አድርሰኝ ብትለኝ እንኳን እድሜ ልክ ይውሰድብኝ እንጂ እንቢ አልላትም…በምን አቅሜ…በእሷ መታዘዝ እኮ ለእኔ እድል ነው…የአለምን ህዝብ አጥፋልኝ ብትለኝ እንኳን ባልችልም ከመሞከር ወደኃላ አልልም፡፡
‹‹እኔ እንጃ የሆነ ሰው እንደእኔ ሲሆን የት ነው የሚሄደው..….?ወይም የት ነው መሄድ ያለበት..››በቀላሉ ልመልሰው የማልችለውን ውስብስብና ግራአጋቢ ጥያቄ ጠየቀችኝ ‹‹እኔ እንጃ ምን አልባት ቤተክሪስትያን ልውሰድሽ….?››ይሻል የመሰለኝን አማራጭ አቀረብኩላት ፡