ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
242K subscribers
288 photos
1 video
16 files
237 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሃምሳ_አራት

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


የንስሯ ጭንቅላቷ ላይ ማረፍ ነበር ከእንቅልፏ ያባነናት….በመከራ አይኗን ገልጣ ዙሪያዋን ስትቃኝ እራሷን  እዛው ቅድም የተዘረረችበት ወለል ላይ እርቃኗን አገኘችው….ባለ ላደውም የሞተ እስኪመስል ድረስ ትንፋሹ ጠፍቶ እግሮቾ  መካከል ጭንቅላቱን ቀብሮ በተመሳሳይ እርቃኑን ተዘርሯል ….ቀስ ብላ ከላዮ ላይ ገልበጥ  አደረገችውና እና እራሷን በማላቀቅ  ሾልካ ወደ ሻወር በመሄድ ለ5 ደቅቃ ውሃ በላይዋ ላይ አፈሰሰችና..
ከዛ ወደመኝታ  ቤቷ ተመልሳ ቢጃማ ለበሰችና ባለ ላዳውን እንደምንም እየጎተተችም እየደገፈችውም ወስዳ አልጋው ላይ በማስተኛት ብርድልብስ ካለበስችው በኋላ ወደሳሎን አመራች…..ንስሯም ተከተላት..፡፡
አዎ ሊነጋ  መሆኑን ከውጭ የሚሰማውን የወፎች  ዝማሬ በማዳመጥ ተረዳች …ሳሎኖ እንደደረሰች ተስተካክላ ከተቀመጠች በኋላ ንስሯ ያየውን  እንዲያሳየት… ያወቀውን እንዲያሳውቃት አዕምሮዋን ከእሱ ጋ አቆራኘችው…
ሰላምና አባቷ…ፍቅራቸው ከአባትና ከልጅም የዘለል አይነት ነው..ኤርምያስ እንዳለው እናትም አባትም ወንድምም እህትም ሆነው ነው ያሳደጎት…ግን አሁን ስላለችበት ሁኔታ ብቻ ያለውን ታሪክ ከንስሯ በተረዳችው የሚከተለውን ነው
ቀጥታ ቤታቸው ገባች… መኝታ ቤት ወደመሰላት ክፍል ተጓዘች… አዎ ትክክል ነች ያልተነጠፈ እና የተዝረከረከ አልጋ … አልጋው ላይ የተዘረረች ውብ ለጋ  ሀዘን የሰበራት ወጣት ተኝታለች…..ወለሉ ጠቅላላ በመጠጥ ጠርሙሶች እና በተበታተኑት ልብሶች ተሞልቷል..አንድ ግዙፍ  አራት መአዘን  ፍሪጅ አልጋውን ተደግፎ   ይታያል…ትኩረቷን ወደፍሪጁ አመዘነበት… ውስጡን አየችው… .ህልም ውስጥ ነኝ እንዴ ያስብላል… …ነጭ ሱፍ ለብሶ ነጭ ሸሚዝና ቀይ ከረባት ያደረገ  እንቅልፍ የተኛ የሚመስል ሰው ፍሪጅ ውስጥ ይታያል.. ..አባቷ ነው ….የሰላም አባት..አሁን የሆነ ነገር የገባት ነው..ልጅቷ እንደጠረጠረችውም  አደጋ ላይ ነች…ሰላም አባቷን አጥታለች..ሰላም አባቷን መሬት ውስጥ ቀብራ ለዘላላም ለመለየት ድፍረቱንም ጭካኔውንም ለማግኘት አልቻለችም….
/////
ነገሩን በዝርዝር ለመረዳት  አምስት ቀን ወደኃላ እንመለስ 
እንደማንኛውም ቀን እየተጎራረሱ እራት በሉ…እያተሳሳቁ ዜናና ፊልም አዩ…አራት ሰዓት አካባቢ ወደመኝታቸው አመሩ….ሰላም አባቷን መኝታ ቤት አስገብታ እንዲተኙ ካደረገች  በኃላ ግንባራቸውን ስማ ተሰናብታ ወደመኝታዋ ልትሄድ ስትል

‹‹ሰላሜ››ሲሉ ጠሯት

‹‹አቤት አባ›››

‹‹አብረሺኝ ተኚ››
ዘላ አልጋው ላይ ወጣችን ብድርብሱን ገልጣ ከውስጥ በመግባት እቅፋቸው ውስጥ ገባች…..ይህ አዲስ ነገር አይደለም..ተለያይተው ከሚተኙበት ይልቅ አንድ ላይ የሚተኙባቸው ቀናቶች የበዙ ነበሩ..ሁለቱም ትንሽ ሲከፋቸው ወይንም አመም ሲያደርጋቸው..ወይንም እንዲሁ ለብቻ መተኛት ሲደብራቸው ዛሬ እኔ ጋር ትተኚ..?ዛሬ አብረሀኝ ትተኛ..? እየተባባሉ አንድ ቀን እሷ ክፍል አንድ ቀን እሳቸው ክፍል ይተኛሉ..እና የተለመደ ነው፡፡
ችግሩ ንጊ ላይ ከእንቅልፏ ባና ከእቅፋቸው ስትወጣ ነበር የተፈጠረው….እጃቸውን ከሰውነቷ ላይ ሳታነሳ በተለየ ሁኔታ ቀዘቀዛት…..ቀስ ብለ ወጣችና አየቻቸው..ጸጥ ያለ ፊት ነበር..ዝም ያለ ፊት…እጇን ወደ አንገታቸው ላከች ….ትንፋሽ አልባ ሆነዋል..

‹‹አባዬ ..አባዬ›› ወዘወዘቻቸው…ጮኸች……..ወደመኝታ ቤቷ  በሩጫ ሄደችና የልብ ማዳመጫ መሳሪዋን አመጣች…ምንም  የለም..?…ጮኸች…ሁሉ ነገር ረፍዶ ነበር..ፀሀይ በጠለቀችበት ቀርታ ነበር…ጨረቃ በደመናው ሙሉ በሙሉ ተሸንፋ ከስማ ነበር…ምጽአት ደርሶ  ነጋሪት እየተጎሰመ እና መለከት እየተነፋ ነበር…..
አባቷ እርግጥ ህመም ላይ ከነበሩ ወራት አልፏቸዋል….ግን እየተንከባከበቻቸው እና በትክክል የህክምና ክትትል እያደረገችላቸው ነበረ…ምንም የተለየ እና ለሞት የሚያሰጋ ምልክት አልተመለከተችም….የት ጋር ነው የተሸወደችው…..?ማወቅ አልቻለችም…፡፡ ለሳዕታት እሬሳውን ላይ ተኝታ ስትነፈርቅ ቆየች…ስልክ ደውላ ለወዳጆቾ ልትናገር ፈለገችና መደወል ከጀመረች በኃላ መልሳ ተወችው

‹‹አባቴን ልቀብር…..?አባቴንም ፈጽሞ አልቀብርም…….ለሳዕታት ካሰበች በኃላ ወሰነች‹‹..አብሬው እሞታለሁ..ግን ለመሞት እስክቆርጥ ድረስ እሱም አይቀበርም›› አለችና…ባላት የህክምና እውቀት በመጠቀም ሬሳው እንዳይበሰብስ አድርጋ በባለመስታወት ፍሪጅ ውስጥ በማድረግ መኝታ ቤት ውስጥ ሬሳውን ደብቃ አስቀመጠች….እና ይሄ ነው የሚያስጨንቃት…እና በዚህ ጊዜ ነበር ኤርምያስ ላዳ ውስጥ የገባችው….ይሄን ችግር ነበር እሱ ሊያውቅና ሊረዳላት ያልቻለው…..በዚህ ከቀጠለች  በጥቂት ቀናት ውስጥ ወይ አዕምሮዋ ተነክቶ ጨርቋን ጥላ ይለይላታል ወይንም እዛው መኝታ ቤት ውስጥ እራሷን አጥፍታ ከአባቷ ጋር ወደመቃብር ትጓዛለች..ከሁለቱ የተለየ የነገ ዕጣ ፋንታ የላትም….
ንስሯ ይዞላት የመጣው ታሪክ ይሄ ነው..በእውነት ልብ የሚነካ ታሪክ ነው…‹‹እና እንዴት ልረዳት እችላለሁ…...?›ስትል እራሷን ጠየቀች፡መቼስ ምንም  ተአምረኛ ብትሆን ከሞተ  አራት ቀን የሆነው እና በፍሪጅ ውስጥ በቅዝቃዜ የደረቀ ሬሳን  ህይወቱን ካሄደችበት መልሳ በማዋሀድ ነፍስ  ልትዘራበት አትችልም…ይሄ የማይቻል ነው… ቢሆንም ቢያንስ ልጅቷ የአባቷን ሞት አምና እንድትቀበል እና እንድትቀብረው…ከዛም እንድትጽናና የሚያስችል አንድ ዘዴ መዘየድ እንዳለባት ተሰማት…አዎ ያንን ማድረግ ትፈልጋለች…
ሀሳቧን ሰብስባ ውሳኔ ላይ ሳትደርስ በፊት የሳሎኗ  በራፍ ተንኳኳ..ግራ ገባት …በዚህ ጥዋት ማን ነው የሚያንኳኳው .. ..?ገና አንድ ሰዓት እንኳን አልሆነም፡፡

‹‹…ማነው..?››ከተቀመጠችበት ሳትነሳ

‹‹እኔ ነኝ ..››

የፕሮፌሰር ድምጽ ነው..ተነሳችና ከፈተችላቸው‹‹እንዴ ፕሮፌሰር..በጥዋት እንዴት ተነሱ..?››

‹‹አረ ጨርሶውኑም አልተኛሁም…ከሰው ጋር ስለሆንሽ ነው እንጂ  ለሊቱን አብሬሽ ስጫወት ማደር ነበር የፈለግኩት››

‹‹ምነው በሰላም..?››

‹‹እኔ እንጃ ብቻ  ትናፍቂኛለሽ…ከፍቶኛል››

‹‹እንዴ ፕሮፌሰር..እስቲ ግቡ››

‹‹አሁን አልገባም.. በኋላ ግን እፈልግሻልሁ››

‹‹ለምን አይገቡም..?››

‹‹አይ አሁን እንግዳ ይፈልግሻል››

‹‹ማንን እኔን....?››ግራ ገብቷት 

‹‹አዎ አንቺን››ብለው ከበራፍ ላይ ገለል ሲሉ ከጀርባቸው በአዕምሮዋ ውስጥም የሌለ ሰው ብቅ አለ…አንድ ጥቁር ሻንጣ በእጁ አንጠልጥሎ አንገቱን ደፍቶ ቋማል..ፕሮፌሰሩ  ወደክፍላቸው ተመለሱ….

‹‹እንዴ መላኩ ..ምነው ሰላም አይደለህም እንዴ....?ሰሚራን አመማት እንዴ..?››

‹‹አረ እሷስ ደህና ነች››

‹‹ታዲያ ምነው በለሊት....?››እስቲ ግባ ብላ ወደውስጥ ገብቶ እንዲቀመጥ አደረገችው…

‹‹ምን ሆንክ..?››ፊት ለፊቱ ቆማ በገረሜታ እያየቸችው ዳግመኛ የመጣበትን ምክንያት ጠየቀችው፡፡

‹‹ምን ያልሆንኩት ነገር አለ..አሸንፈሻል …ሰሚርን አስመርምሬያታለሁ..ሙሉ በሙሉ ጤነኛ ሆናለች..››

‹‹አሪፍ ነዋ .ታዲያ ደስ አላለህም..?››

‹‹አዎ ብሎኛል…››
‹‹እና ታዲያ አሁን ለምን መጣህ..?››

‹‹ስምምነታችንን ላከብር ነዋ..በሶስት ቀን ውስጥ ትተሀት ካልመጣህ ብለሽ ፎክረሻ አድራሻሽን ሰጥተሸኝ ነበር  እኮ..የሆነ ነገር ለማድረግ ኃይል እንዳለሽ አሳይተሸኛል…እንቢ ብዬ በዛው ብቀር ደግሞ ፍቅሬን  መልሰሽ በሽተኛ ብታደርጊብኝስ..?››