ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ via @like
ተዘጋጀ፡፡
ግራ ገባት ከእሷ ጋር አብሮ ለማየት የሚጓጓለት ፊልም ከዚህ ቀደም አጋጥሟት
አያውቅም፡፡
‹‹እየቀለድክ ነው?›› አለችው
‹‹በፍፁም እንደዛሬም አምርሬ አላውቅም፡፡ አንቺ መሪ ተዋናይ ሆነሽ
የተወንሽበትን ፊልም አብረን ብናይ ምን አለበት? ምንም ቢሆን እኮ ታማኟና ተወዳጇ
ባለቤቴ ነሽ›› በማለት ከፈተውና ወደ እሷ አስጠጋላት፡፡
በፍራቻ እና ግራ በመጋባት መመልከት ጀመረች፡፡ አፏን የምታረጥብበት
ምራቅ አጣች፡፡ ጉሮሮዋ ደረቀባት፡፡ ሠውነቷ ሲንቀጠቀጥና እየዛለ ሲሄድ ለራሷ
ይታወቃታል፡፡ መንቀሳቀስም ሆነ መናገር አልቻለችም፡፡ ከምትመለከተው ፊልም
ላይም ፊቷን ዞር ማድረግ አልሆነላትም፡፡ እስኪጠናቀቅ አየች፡፡
ሠሎሞን ማለቁን ሲያይ ዘጋውና ከጎኗ ተነስቶ ፊት ለፊቷ ተቀመጠ፡፡
‹‹እሺ አሁን መነጋገር የምንችል ይመስለኛል››
ለመናገር ከንፈሯን ማላቀቅ አልቻለችም፡፡ በፍራቻ የቀዘቀዙ ዓይኖቿን
አንከባለለችበት፡፡
‹‹መልስ ስጪኝ እንጂ?››
‹‹ምን ል..በልህ?››
‹‹መነጋገር አለብን እኮ ነው የምልሽ››
‹‹መ..ቼ?››
‹‹ዛሬ .. አሁን … እዚሁ››
‹‹አልችልም ነገ›› እየተጎተተችበት ከተቀመጠችበት ለመነሳት ስትሞክር ተንጠራርቶ ክንዷን ጨመቀና
መልሶ አስቀመጣት፡፡
‹‹ትሰሚያለሽ! እንደውም ካንቺ ጋር መነጋገር አልፈልግም፡፡ ውሳኔዬን ግን በጥሞና
እንድታደምጪኝ እፈልጋለሁ፡፡ ከአሁን ሠዓት ጀምሮ እቤቱን ለቅቄልሽ እወጣለሁ፡፡
የግል ዕቃዎቼን ብቻ ይዤ ፡፡ የምትጠቀሚበትን መኪና አንዴ ገዝቼልሻለሁ አሁንም
ያንቺው ነው፡፡ እቤቱንም ከጎረምሳሽ ጋር ቅበጪበት፣ ጨፍሪበት፣ እንዳሻሽ
ሸርሙጪበት፡፡ ስሙ ባንቺ ስላልሆነ የመሸጥ የመለወጥ መብት ግን የለሽም፡፡ ከዛ
በተረፈ ለልጆቼ ከሚያስፈልገው ውጪ በስተቀር ሠባራ ሳንቲም ከእኔ አታገኝም፡፡ ወደ
ክስ እሄዳለሁ ብትይ ግን ይሄንን ጉድሽን በአስር ሺ ኮፒ አባዝቼ ፣ለእነዛ ተመፃዳቂና
ጉረኛ ዘመዶችሽ በነፍስ ወከፍ አድልልሻለሁ፡፡ በጠበቃዬ በኩልም ለፍርድ ቤቱም
በማስረጃነት አቀርበዋለሁ፡፡ ከዛ በኋላ ምን አልባት ከእኔ ንብረት መካፈል ብትችይ
እንኳን ከዘመዶችሽና ከጎረቤቶችሽ የሚደርስብሽን ውርደት ተቋቁመሽ እዚህ ከተማ
ውስጥ መኖር የምትችይ አይመስለኝም፡፡ ለማንኛውም የሚሻልሽን ከውሽማሽ ጋር
ተማክረሽ መወሰን ትችያለሽ ››በማለት ተነስቶ እርምጃ ከጀመረ በኃላ ቆሞ ንግግሩን
ቀጠለ፡፡
‹‹…ሌላ አንድ ነገር ይቀረኛል፡፡ በማንኛውም ሠዓት ልጆቼን ማየት ስፈልግ መኪና
እልካለሁ ፣ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ትልኪልኛለሽ፡፡ ሁኔታዎችን አመቻችቼ ወደ ራሴ
እስክውስዳቸው ድረስ ማለት ነው፡፡
ሳስብሽ ትክክለኛ ሚስት ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ እናትም የመሆን ብቃቱ ያለሽ
አይመስለኝም››
እንባዋን እያረገፈች ፣አንደበቷ ተሳስሮ ፣ሠውነቷ በድንጋጤ እና በፀፀት ተኮማትሮ እያያት
ያለ ምንም ሀዘኔታ ጥሏት ወደ መኝታ ቤቱ ገባ፡፡ እቃዎቹን ሠብስቦ ቤቱን ጥሎላት ሊወጣ።
..............ይቀጥላል..............✍
#ቀጣዩን#ክፍል 8⃣ እንዲቀጥል👍
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
📖📖📖📖

ማድረግ ያለበትን ሁሉ
አደረገ...በመጨረሻ ሃይሌ ተሟጠጠ…ተስፋ ቆረጥኩ.
.. እያለከለከ ሱሪውን አውልቆ
ቀሚሴን በመግለብ ጭኔን ሲፈለቅቅ አክስቴ ልጇን እንደታቀፈች ዘው ብላ መኝታ ቤቱ
መሀል አይኖን አጉረጥርጣ ታየን ጀመር፡፡እሱ ሲያያት አልደነገጠም፡፡ ተበሳጨ እንጂ፡፡
‹ምን አይነት ምቀኛ ነሽ› በማለት የወለቀውን ሱሪ በእጁ እንደያዘ ገፍትሯት መኝታ
ክፍሉን ለቆ ወጣ፡፡ እሷም እንደመደንዘዝ ካለችበት ነቃችና መጮኸ ማልቀስ እና
መራገም ጀመረች፡፡እንደምንም እየተጎተትኩ ከአልጋው ላይ ተነሳሁና በተዳከሙ ቀጫጫ
አግሮቼ ወለሉ ላይ ቆምኩ
‹አንቺ ሸርሙጣ የልጆቼን አባት...› ጮኸችብኝ፡፡ ግራ ገባኝ፤ የተበደልኩት እኔ፤
እርግማኗንም የምታወርደው በእኔ ላይ...
‹‹ስሚ አሁኑኑ ጨርቅሽን ይዘሽ ከቤቴ እንድትወጪልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ልጆቼን
ላሳድግበት፡፡ ከፈለግሽ ሽርሙጥና ቤት ግቢና እንደፈለግሽ ሁኚ፤አልፈልግሽም››
በማለት ጨርቄንና ደብተሮቼን ሠብስባ አስታቅፋኝ እየገፈተረችኝ ከቤቷ አውጥታ
አባረረችኝ፡፡በእንደዚህ ሁኔታ ነበር ታሪኳን ያስረዳችው፡፡ ከዛም እንደ እህቱ አድርጎ
ተቀበላት፡፡ ትምህርቷንም እንድትቀጥል አደረጋት፡፡ በወቅቱ እሱ ጋር ስትመጣ የአስረኛ
ክፍል ተማሪ ነበረች፡፡ አሁን በዲፕሎማ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሦስተኛ አመት
ተማሪ ነች፡፡
ከሀሳብ ነቅቶ ዞር ሲል እቤቱ ተጫጭሷል፡፡ ፎዚያ ቅድም የለበሠችውን ልብስ
አውልቃ ድርያ ለብሳለች፡፡ ብዙውን ጊዜ የምትሸፍነውን ፀጉሯን በነፃነት ለቃዋለች፡፡
አጭር ቢሆንም ሉጫ ስለሆነ ለውበቷ ልዩ ድምቀት ለግሷታል፡፡
‹‹እሺ ፎዚያ ትምህርት እንዴት ነው?›› አላት
‹‹አሪፍ ነው፡፡አሁንማ ልጨርስ አራት ወር ብቻ ቀረኝ እኮ!››
‹‹በጊዜ ስራ ፈልጉ ማለትሽ ነው?››
‹‹ለስራው እንኳን ብዙም ጉጉት የለኝም፡፡ ዋናው ተምሬ እዚህ ደረጃ መድረሴ ነው፡፡
ከዚህ በኋላ ዕቅዴ አንተን በተሻለ መንገድ መንከባከብ ነው››
‹‹እንዴት ባክሽ? እኔን ለመንከባከብ እኮ ሦስት ዓመት ሙሉ ኮሌጅ ገብቶ መሠቃየት
አያስፈልግሽም ነበር››
‹‹አንተ እኮ ለእኔ አባቴ እና ምርጥ ወንዴሜም ነህ..ምንም ነገር ባደርግልህ
ያንስብሀል››
‹‹ፎዚ ለእኔም እኮ ምርጥ እህት ሆነሽኛል፡፡ ይሁን እንጂ እህትም አንድ ቀን የታለቅ
ወንድሟን ቤት ጥላ የራሷን ቤት ትገነባለች፡፡ የወንድም ሃላፊነት ደግሞ እህቱ እዚህ
ደረጃ እንድትደርስለት ማበረታታት እና መደገፍ ነው፡፡ እርግጥ ነገሮች ቀላል
አይደሉም፡፡ እኔም እኮ ስራ ይዘሽ የፍቅር ጓደኛ አበጅተሸ ትዳር መስርተሸ ጥለሺኝ
እንደምትሄጂ ሳስብ በጣም ይጨንቀኛል፡፡ ቢሆንም ግን የግድ መቀበል እንዳለብኝ
አምናለሁ››
የፈላውን ቡና በመቅዳት ስኳር ጨምራ በማማሰል አቀበለችውና ለራሷም ቀድታ
ንግግሯን ቀጠለች፡፡
‹‹እንግዲህ ውሳኔዬ የማይቀየር ነው፡፡ ምን አልባት አግብተህ ባለቤትህ እቤቱን
ከተረከበችኝ እና ከልብ እንደምትንከባከብህ እርግጠኛ ከሆንኩ ያልከውን አደርግ
ይሆናል፡፡››
‹‹ዝም ብለን በባዶ ሜዳ እኮ ነው የምንጨቃጨቀው››
‹‹እንዴት ማለት?›› ሁሴን ሊላት የፈለገው ምን እንደሆነ ስላልገባት ጠየቀችው፡፡
‹‹እኔ አሁን በቅርብ ማገባ ይመስልሻል? ››
‹‹ለምንድነው የማታገባው?››
‹‹ማን ነች ፍቃደኛ ሆና እኔን ልታገባኝ የምትችለው?››
‹‹በጣም ዕድለኛዋ ሴት ነቻ›› ፎዚያ ከምሯ ነው እውነተኛ ስሜቷን የምታወራው፡፡
‹‹አይምሰልሽ .. በዙሪያዬ ያሉ ሴቶች ሁሉ በፍቅር እንጂ ትዳርን ለሚያህል ቁም ነገር
ብቁ እንዳልሆንኩ ጠንቅቀው ያውቃሉ››
‹‹እውነት ነው ብዬ አላስብም›› አለች ቅሬታን በዛለ ድምፅ
‹‹እንዴት … ? ሌላው ይቅር በአንቺ አመለካከት እኔ ለትዳር የምሆን ግለሠብ
እመስልሻለሁ?›› ሲል ጠየቃት ሁሴን
‹‹እውነቱን ልንገርህ›› በታፈነ ድምፅ ጠየቀችው፡፡
‹‹አዋ! .. ንገሪኝ … ትክክለኛ ስሜትሽን ንገሪኝ››
‹‹እንግዲያው እኔ ሙሉ በሙሉ ያንተ አይነት ወንድ እስከማገኝ ድረስ ለጋብቻ ቀርቶ
ለአንድ ቀን አዳር ቢሆን አልሞክረውም፡፡››
ደነገጠ፡፡ እንደምትወደው ያውቃል፡፡ ይሄን ያህል ተፅዕኖ ውስጥ እንደከተታት ግን ልብ
ብሎ አስተውሎት አያውቅም፡፡ እና ውይይታቸው ከወትሮው በመጠኑም ቢሆን ጠንከር እያለ
ስለመጣ ርዕስ ለመቀየር ተገደደ፡፡
‹‹ኦ! ይሄ ቡናሽ ልዩ ነው፡፡ ከደባሪው እራስ ምታቴ ገላገለኝ›› አላት
‹‹ስለተሸለህ ደስ ብሎኛል፡፡ … በነገራችን ላይ ቀን ትንግርት መጥታ ነበር፡፡››
‹‹እንዴት ሳትደውልልኝ መጣች …?››
‹‹እኔ እንጃ፡፡ ሁኔታዋ ግን ከወትሮው የተለየ ሆነብኝ፡፡ ሁሉ ነገሯ ወደ ኖርማል ተመልሷል፡፡ አገባች
እንዴ?›› የገረማትን ነገር ጠየቀችው፡፡
‹‹አይመስለኝም፡፡ .. ስራ ግን ቀይራለች›› መለሠላት
‹‹ለማንኛውም የሆነ ዕቃ አምጥታልሃለች››
‹‹ምን አይነት ዕቃ? ›› ለማወቅ በተጣደፈ ስሜት ጠየቃት
‹‹እኔ እንጃ ሥዕል መሠለኝ፡፡ ታሽጓል፡፡ መኝታ ቤት አስቀምጬልሃለሁ፡፡››
ተስፈንጥሮ ወደ መኝታ ክፍሉ ገባ፡፡ በግምት ሠማንያ በስልሳ የሚሆን በፍሬም የተወጠረ፤
በስጦታ ወረቀት የተጠቀለለ ሸራ አገኘ፡፡ በጥድፊያ ልባሱን አነሳው፡፡
የሚያፈዝ ስዕል ነው፡፡ የጥንት ንግስቶች የሚለብሱትን አይነት አብረቅራቂ ልብስ የለበሠች እንስት
ትታያለች፡፡ እግሮቿ መሬት አረገጡም፡፡ በአየር ላይ የምትራመድ ትመስላለች፡፡ ፀጉሯን ንፋሱ
እያንሳፈፈው ነው፡፡ የእጆቿ ጣቶች ውበታቸው የማርያምን ይመስላሉ፡፡ በቀኝ እጇ ዓይነ ሥውሮች
የሚጠቀሙበትን አቅጣጫ መጠቆሚያ ዘንግ ይዛለች፡፡ ፊቷ የተለየ ነው፡፡ እንደ ሠው ዓይን፣ አፍንጫ
ከንፈሯ ሳይሆን በቦታው የሙሉ ጨረቃ ቅርፅ ይታያል፡፡ በጨረቃዋ ዙሪያም በህብረ ቀለም የደመቀ
የብርሃን አምድ ያንፀባርቃል፡፡የሥዕሉ ጥልቀትና ምጥቀት... ውስጡ የተዳፈነውን የፍቅር ጉጉት
ቀሠቀሠበት፡፡ ከውስጡ የናፍቆት እሳት ሲለበልበው ተሠማው፡፡ ትንግርት መጽናኛ የሚሆነውን ውድ
ስጦታ ስላበረከተችለት ከልብ አመሠገናት፡፡ ፊት አልባ ሥዕል የተሳለላት ድብቋ ደራሲ ግን በምን ተአምር
በአካል ሊያገኛት እንደሚችል ከመቼውም ጊዜ በላይ ግራ ገባው፡፡
..............ይቀጥላል..............✍
#ቀጣዩን#ክፍል 9⃣ እንዲቀጥል👍

▶ሼህ መሐመድ ቢን ረሺድ
🔥የበረሃው ንብ
#ክፍል 1
#ቀጣዩን ክፍል ከስር ያለው ሊንክ ላይ በመጫን ያገኙታል👇👇👇
https://youtu.be/Z1D7EM0v-uw?si=IxM67RzoSd50NsoW

YouTube
|ሼህ መሐመድ ቢን ረሺድ (የበረሃው ንብ)
#ethiopia #ethiopianmusic #habesha @weygood entertainment