ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
243K subscribers
288 photos
1 video
16 files
239 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
ሰላም ቤተሰቦች ዛሬ አንድ የምስራች ልነግራችሁ ነው የ YouTube channel subscribe በማድረግ የሞባይል ካርድ እና🎁የኢንተርኔት ፓኬጅ መሸለም ትችላላችሁ።

ማሳሰቢያsubscribe ማድረጋችሁን ለማረጋገጥ comment ላይ ስልካችሁን አስቀምጡልን ወይ ደሞ የቴሌግራም username አስቀምጡልን።
#ለወዳጅ ለጓደኛዎ #ሼር ያድርጉ አብረው ይሸለሙ🎁

🧑‍💻ከስር ያለውን link በመጫን አሁኑኑ ተሸላሚ ይሁኑ👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/Fxn9M8wu_vw?si=ElBRM5mckhzQDnRE
😳እንዲቆጩ አድርጉ!

በሰው የመገፋትን ህመም ለማወቅ የግድ መገፋት የለባችሁም፣ ከሰዎች መሃል ተመርጦ የመጠቃትን ክብደት ለመረዳት የግድ በግል መጠቃት አያስፈልጋችሁም። ሰዎች መርጠው ይቀርቧችኋል መርጠው ይርቋችኋል፤ ሰዎች ፈልገው ይወዳጇችኋል ፈልገው ይለዩአችኋል። ፍቅር በግዴታ የሚሰራ ነገር አይደለም። መሔድ የሚፈልጉት ይሂዱ ነገር ግን በመሔዳቸው ምን እንዳጡ አሳዮአቸው፤ በምርጫቸው የገፏችሁ ይግፏችሁ ተዎቸው ይሔንን ስላደረጉባችሁ ግን እንዲቆጩ አድርጉ። ለማንኛውም ለሚጠላችሁ፣ ለሚገፋችሁ፣ ለሚጠየፋችሁ ሰው ትክክለኛው በቀል ከእርሱ ተሽሎ በመገኘት በድርጉቱ እንዲፀፀት ማድረግ ነው። ጥሩ የሰራን የማይፈልግ ሰው አይኖርም። ከዚህ ቀደም የነበራችሁ ቦታ ቢነሳችሁና መገፋት ቢደርስባችሁ ብዙ አትደነቁ። ብዙ ጊዜ ሰዎች ስንባል መዳቡን ስናሳድድ በእጃችን ያለውን ወርቅ መግፋታችን አዲስ ነገር አይደለም። እራሳችሁን እንደ ወርቅ የምትመለከቱ ከሆነ ውድነታችሁን የማሳየት ግዴታ አለባችሁ። ሰው ሁሉ አዙሪት ውስጥ ነው። ከራስወዳድነቱ የተነሳ አጥብቆ የሚፈልገው የሚጠቅመውን ሰው ብቻ ነው።

አዎ! እንዲቆጩ አድርጉ! እናንተን በማጣታቸው፣ እናንተን በመግፋታቸው፣ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ እናንተን በመጥላታቸው እንዲቆጩ፣ በእራሳቸው እንዲያዝኑና አንገት እንዲደፉ አድርጉ። የመገፋት ስቃይ የማንም ሰው እጣፋንታ አይደለም፤ ተመርጦ መጣል፣ መናቅና መንቋሸሽ ማንም ላይ ሊደረግ የሚገባ ነገር አይደለም። በብዙ ፍላጎቶችና ምርጫዎች የታጠረ ቢሆንም ሰውነት ክብር ነው። ማንም ሰው የመጣውን ሰው ሁሉ የህይወቱ አንድ አካል ማድረግ አይችልም፤ ነገር ግን አንዴ ወደ ህይወቱ ካስገባ ቦሃላ ልክ እንደ ሸንኮራ አገዳ አኝኮ የመትፋት መብቱ የለውም። የሰው በደል ዕድሜ ልክ ይከተላል። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ማንም ሰው ላይ ያደረሰውን ጥፋት መክፈሉ አይቀርም። ከሰው ለመለየት ስታስቡ፣ ሰውን መተው ሰትፈልጉ በቻላችሁት አቅም የሰውዬው ስሜት እንዳይጎዳ ጥንቃቄ አድርጉ፤ እናንተም እንዲሁ የክፋትና የጭካኔ ስም እንዳይሰጣችሁ ተጠንቀቁ። የትኛውም ሰው የሚበጀውን ያውቃልና እጅና እግሩን አስራችሁ ማስቀመጥ አትችሉም። መሔድ ከፈለግ ይሒድ ሲሔድ ግን ምን እንዳጣ ማወቅ አለበት፤ መለያየት የመጨረሻ ውሳኔው ከሆነ ያድርገው ፍቀዱለት ነገር ግን መለያየቱ ከእርሱ በላይ እናንተን እንደጠቀመ በተግባር አሳዩት።

አዎ! ጀግናዬ..! ዋጋህን የማያውቅ ሰው ብዙ ይልሃል፣ ብዙ ያደርግሃል። ረጅም ጊዜ አብረሀው ስትሆን መሔጃ ያጣህ ይመስለዋል፣ የገጠመህን ችግር ሁሉ ስታማክረው ሌላ የምታማክረው ሰው እንደሌለህ ያስባል፣ ከብዙ ሰዎች መሃል መርጠህ ዝቅ ብለህ ስትታዘዘውና ስታገለግለው ሌላ አንተንም የሚያገለግልህ ሰው የሌለህ ይመስለዋል። አንተ ዋጋህን ማሳየት ካልቻልክ ማንም በማቅረቢያው ወይም በአጉሊው መነፅር ዋጋህን ሊያይልህ አይችልም። እንዴትም እራስህን በየበታችነት አዙሪት ውስጥ አታስቀምጥ፤ በምንም መንገድ መሔጃ እንዳጣ ሰው ከሚመርዝህ ሰው ጋር አትቆይ። ሰው ዋጋህን እስካላወቀ ድረስ በፍፁም ቦታ አይሰጥህም፤ ማንም ልክህን እስካልተረዳ ድረስ ሊያከብርህ አይችልም። ዓለም ሰፊ ነች፣ ሰው ይሔዳል ሰው ይመጣል፣ ሰው ይጠላሃል ሰው ይወድሃል፣ ሰው ይገፋሃል ሰው ይቀርብሃል፣ ሰው ይጠየፍሃል ሰው ያፈቅርሃል። ሰው ገፋኝ ብለህ ህይወትህን እንደ ሲዖል አትመልከት፣ ሰው ወደደኝ ብለህም መቼም የማይቀየር የደስታ ዓለም ውስጥ ገባው ብለህ አትመፃደቅ። ከሚጠላህና ከሚወድህ ሰው በላይ ለእራስህ የምታስፈልገው እራስህ እንደሆንክ እወቅ። ከተገፋው ማንነትህ ተሽለህ እስከተገኘህ ድረስ የገፉህን ሁሉ በስራቸው እንዲፀፀቱ የማድረግ አቅሙ እንዳለህ እመን።


       LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/fpn1FQlM_X4?si=VgYsjN8SaeD4KRDr

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
ለምሺታችን ተጋበዙልኝ ካነበብኩት🙏

"ራሳችሁን ሁኑ፣ ሁሉም ሰው ተይዟል!"

Oscar Wilde


የራሳችሁን መልክ ለቃችሁ ሌላ ሰው ለመምሰል አትሞክሩ። ሌላ ሰው ሌላ ሰው ነው፣ እናንተም እናንተ ናችሁ። ራሳችሁን በመሆናችሁ የሚቀርባችሁ ነገር ካለ ቀድሞውኑ የእናንተ አልነበረምና ይቅርባችሁ። ናቹ ተብሎ በተሰጣችሁ ማንነት መቼም ሀፍረት አይሰማችሁ።

   LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/fpn1FQlM_X4?si=VgYsjN8SaeD4KRDr

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇
       
@Mtshaf_bicha
       
@piyasa188
❤️ለወዳጅዎ
#ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩
@Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                 
@EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
ፍትህ ..!!!
ገና እንቡጥ ጮርቃ
ሳትጠግብ ቦርቃ
ምኑን ከምኑ ሳትለየው
የአለምን ጣዐም ሳትቀምሰው
እህል በወጉ ጠግባ ሳትበላ
እንዲህ ስትቀር ድፍት ብላ...!
እግዚኦ እግዚኦ ለፍርድህ
ምነው ?ጌታ ሆይ ዝም ማለትህ
ሳጥናኤሎች በዙ ፍርድ ከምድር ጠፋ
እንዲህ ሆነና ሰው ከአራዊት ከፋ
እንደጭዳ ዶሮ አንገቷን ቆልምመው
እንደውሻ ሬሳ ቅዱሱን ሰው ጥለው
ዝንት አለም ያልነበር ለወሬ የከፋ
ስንት ግፍ ተሰራ ስንት ህይወት ጠፋ😭


ለፍትህ ስትሉ ለ100 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/fpn1FQlM_X4?si=VgYsjN8SaeD4KRDr

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇
       
@Mtshaf_bicha
       
@piyasa188
❤️ለወዳጅዎ
#ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩
@Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                 
@EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
ራሳችሁን አድኑ!

ሰውነት ደካማ ነው፤ በምንንና እንዴት እንደሚንሸራተት አይታወቅም። ከምንም በላይ ግን በሰው እጅ ላይ ከወደቀ ቆይታው አደጋ ላይ ነው። ምንምያህል ችግርና ማጣት ቢጠናባችሁ፣ ምንምያህል ከባድ ሁኔታ ውስጥ ብትወድቁ እንኳን በቻላችሁት አቅም ራሳችሁን ለሰው አሳልፋችሁ አትስጡ። ሰው ወዳለው ያደላል፣ ሰው ለተሻለው ማጎብደዱ አይቀርም፣ ሰው የሚጠቅመውን ይመርጣል። እናንተ የማትረዱትና ከእናንተ ምንም የሚያገኘው ነገር ከሌለ ለትንሽ ጊዜ ቢታገሳችሁ እንጂ ያለምን ጥርጥር በስተመጨረሻ አውላላ ሜዳ ላይ ጥሏችሁ ይሔዳል፣ የናንተ ጉዳትና ህመም ምኑም የማይሆንበት ጊዜ ይመጣል። ከየትኛውም ፍጡር በላይ የጭካኔ ጥግ የሚገለጠው በሰው ልጅ ላይ ነው፤ ሰውም ከየትኛውም ፍጡር በላይ የሚጨክነው አምሳያው በሆነው የሰው ልጅ ላይ ነው። የሰው እጅ ላይ ከወደቃችሁ በትልቁ ጋን ክንችር ተደርጎ እንደተቆለፋባችሁ አስቡት። ሰውየው ሲፈልግ ብቻ በፈለገው ሰዓት ይከፍታችኋል፣ እንደፈለገው ተጠቅሞም መልሶ ቆልፎ ያስቀምጣችኋል።

አዎ! ሁሉም ቢመቸውና ቢሆንለት ሊጠቀምባችሁ ይፈልጋልና ራሳችሁን አድኑ፣ ራሳችሁን ከሰዎች ድራማ ውስጥ አውጡ። ከሰው እጅ እየጠበቃችሁ የተንጣለለ ቪላ ውስጥ ከምትኖሩ እራሳችሁን ችላችሁ በትንሽዬ ጎጆ ውስጥ በነፃነት ብትኖሩ ይሻላችኋል። የሰው ልጅ ፈጣሪ አይደለም ከእናንተ ምንም ሳይጠብቅ የሚያስፈልጋችሁን በሙሉ የሚያሟላላችሁ፣ እርሱን የማድረግ ግዴታም የለበትም። የትኛውም ሰው የመጀመሪያ ሀላፊነቱ እራሱን ማዳን ነው፣ ከርሱም ካለፈ ወዶና ፈቅዶ በዙሪያ ላሉ ሰዎች የአቅሙን ማድረግ ነው። የሰው ነገር ዞሮ ዞሮ የሰው ነው። ከዛም በላይ አብዛኛው ሰው አስመሳይ ነው። ዛሬ አፈር ነገ እሳት ይሆናል፣ አሁን ደግ ቦሃላ ክፉ ይሆናል። ከማን ምን መቀበል እንዳለባችሁ፣ ከማን ጋርስ እስከመቼ እንደምትዘልቁ በሚገባ እወቁ። እድሜ ልካችሁን የሰዎች ተረጂና ተመፅዋች አትሁኑ። ወደዳችሁም ጠላችሁም ብቸኛ ምርጫችሁ ራሳችሁን መቻል ነው። አንድ ቀን ከፍተኛ አውሎ ነፋስ በተነሳ ጊዜ ተገንጥሎ እንደሚወድቀው ቅርንጫፍ አትኑሩ። የራሳችሁን ሰር በጥልቀት ወደምድር አስርጉት፣ በሚገባ ተደላድላችሁ መሬቱን ቆንጥጣችሁ ያዙት፣ የትኛውም ከባድ አውሎ ነፋስ ቢመጣ በቀላሉ እጅ አትስጡት።

አዎ! ጀግናዬ..! ምድር የመፅዋቾች እንጂ የተመፅዋቾች አይደለችም፣ ዓለም የረጂዎች እንጂ የተረጂዎች አይደለችም። የሰው እጅ ላይ ወድቀህ፣ ሰው እየደገፈህና እያገዘህ የምትኖር ግፋ ሲልም ምንም ነገር ሳትሰራ ከሰው እየጠበክ የምትኖር ከሆነ በአደገኛ አጥር በታጠረ ቅጥር ጊቢ ውስጥ እንደሆንክ እወቅ። በምንም መንገድ የነፃነትን አየር መተንፈስ አትችልም፤ እንዴትም ያሰኘህን ነገር ማድረግ አትችልም፤ በምንም ተዓምር ራስህን ልታድን አትችልም። ማውራት፣ መጮህ፣ መንቀሳቀስ ትችላለህ ነገር ግን ሁለቱ እጆችህ በሰንሰለት ታስረዋል፣ አንዳች ተጨባጭ ነገር ማድረግ አትችልም። የሰው ነገር የሰው ነው፣ መቼና እንዴት እንደሚወሰድብህ አታውቅም። ሲኖርህ የሚያሳድድህን ስታጣም የሚያሽሟጥጥብህን ሰው ተማምነህ አትቀመጥ። ራስህን ለማዳን መገንባት ያለብህ ግንብ ካለ ጊዜ አታጥፋ ዛሬውኑ መሰረቱን ጣል፣ ቀስ በቀስ እየገነባሀው ሂድ። ከሰው እጅ ከመጠበቅ ተላቀቅ፣ በሰው መተማመን አቁም። ይብዛም ይነስም የራሴ የምትለውን ነገር መገንባት ላይ አተኩር።

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/fpn1FQlM_X4?si=VgYsjN8SaeD4KRDr

መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇
       
@Mtshaf_bicha
       
@piyasa188
❤️ለወዳጅዎ
#ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩
@Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                 
@EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
👍በሳል ሁኑ!

💚ለውብ ምሺታችን

በሳልና ብልህ የተባሉ ሰዎች ከምንም በላይ የተካኑባቸው ሁለት ጥበቦች አሏቸው። አንደኛው ነገሮችን አርቆመ መመልከት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ስሜትን መቆጣጠር ነው። እንደማንኛውም ሰው የግል ህይወት አላቸው፣ እንዲሁ የሚመሩበትም የግል መርህ አላቸው። ብስለታቸው ምናልባት በእድሜ የመጣ ሊሆን ይችላል፣ ከእዴሜያቸው በፊትም የበሰሉ ግን ብዙ አሉ። እነዚህ ከዕድሜያቸው የቀደሙ ሰዎች ህይወታቸው ያስቀናል፣ በሚያደርጉት እያንዳንዱ ነገር ውስጥ ህይወት አለ፣ ሀሳባቸው በጣም ያስገርማል፣ የገጠሟቸውን ችግሮች የሚመለከቱበትና ሊቀርፉት የሚሞክሩበት መንገድ እጅጉን አስደናቂ ነው። በቅድሚያ ይረጋጋሉ በመቀጠል የገጠማቸው ጉዳይ በእነርሱ አቅም መስተካከል ስለመቻሉ እርግጠኛ ይሆናሉ፣ ከዛም ቀስ በቀስ እርምጃ ይወስዱበታል ደረጃ በደረጃም ችግራቸውን በራሳቸው መንገድ ሲፈቱት ይታያሉ። ብስለትና ብለሀት በገንዘብ አይገዛም፣ በአንድ ሌሊትም ተዋህዶን መገለጫችን አይሆንም። በየቀኑ እራሳችሁን በማሻሻል ስትጠመዱ፣ በየጊዜው እራሳችሁ ላይ ስትሰሩ፣ አዳዲስ ፈተናዎችን ስትጋፈጡ፣ ከሰዎች ውድቀትና ስኬት መማር ስትችሉ ያኔ በሂደት ወደ ብስለት ከፍታ መምጣት ትጀምራላችሁ።

አዎ! በሳል ሁኑ! ዛሬ ስለገጠማችሁ የህይወት ማዕበል ብቻ እያሰባችሁ ህይወታችሁን አትገድቡት። ሩቅ ተመልከቱ፣ የአሁን ገደቦቻችሁን ተሻገሩ፣ የሚወራባችሁን አሉታዊ ነገር እለፉት፣ ለእውቀት ቸኩሉ፣ ጥበብን አሳዱ፣ በሀሳብ ግዘፉ፣ በተግባር ቅደሙ። በቻላችሁት አቅም ህይወት ለእናንተ እንድታዳላ አድርጉ። ቀድመው የነቁ ሁሌም ቀድመው ያተርፋሉ፣ ከሰዎች የተሻሉ ሰዎች ሁሌም የተሻለ ነገር ያገኛሉ። ብስለት ሁነኛው የአሸናፊነት መሳሪያ ነው። ምንም ነገር በስሜት ከማድረጋችሁ በፊት ቆም ብላችሁ ደጋግማችሁ አስቡ፤ ምንም መጥፎ ነገር ከመናገራችሁ በፊት ከጀርባው ስለሚያስከትለው ነገር አስቡ። የህይወትን ሚስጥር ለመረዳት የግድ ችግርና ፈተና እስኪፈራረቅባችሁ አትጠብቁ። ከሰዎች ተማሩ፣ ከተፈጥሮ ተማሩ፣ ከራሳችሁ ተማሩ፣ ሁሌም በእድገት መንገድ ስለመሆናችሁ እርግጠኛ ሁኑ። አስቡ ስታስቡም በትልቁ አስቡ፣ በተለየ መንገድ አስቡ፣ ከመደበኛው አካሔድ ለመውጣት ደፋር ሁኑ። መሪነትን በራሳችሁ ላይ ተማሩ፣ በጫና ውስጥ ተሽሎ መገኘትን ራሳችሁ ላይ ተግብሩት።

አዎ! ጀግናዬ..! የብስለት ተቃራኒ ልጅነት ነው። ልጅ ህይወቱ እንደ ልጅ ነው። ምንም እንኳን ሀሳቡ ነፃና መልካም ቢሆንም ተግባሩ ግን የተገደበ ነው፣ ነገሮችን አርቆ የመመልከት ክፍተት አለበት፣ የሚፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ አሁኑኑ እንዲሆኑ ይፈልጋል፣ ሚዛናዊ እይታና የጠለቀ ግንዛቤ ላይ አጥጋቢ ክንውን የለውም። የብስለትህን ክህሎት ከልጅነት እሳቤዎች ለመውጣት ተጠቀመው። ዕድሜህ ቢያንስም ተግባርህ ግን በጥበብ የተሞላ መሆን ይችላል። ዋናው ጉዳት የቆይታ ዘመን ሳይሆን በትንሿ ዘመን የተረዷትን የህይወት ሚስጥር ምድር ላይ ማውረድ መቻል ነው። ከፍታም ዝቅታም የህይወት አንድ አካል ናቸው፣ ችግርም ድሎት የመኖር ገፆች ናቸው፣ ውድቀትም ስኬትም በፈረቃ የሚመጡ ክስተቶች ናቸው። በብስለት ጎዳና የሚያራምደው ጥበብ ግን እነዚህን ሁሉ ተረድቶ እንደ አመጣጣቸው ምላሽ መስጠት መቻል ነው። አስታውስ ብስለት ከዕድሜ በላይ የአዕምሮ ጫወታ ነው። ህይወትን ቀድመህ በተረዳህ ቁጥር ከዕድሜህ በፊት እየበሰልክና ጥበበኛ እየሆንክ ትመጣለህ። በሳል ሁን፣ ከማንም በላይ ህይወትን ተረዳት።

#LIKE👍👍እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/fpn1FQlM_X4?si=VgYsjN8SaeD4KRDr

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
💚ልባችሁን አሙቁት!

ከማንም የሚለያችሁ፣ ከማንም በላይ ከፍታችሁን የሚጨምርላችሁ አንድ ጥበብ አለ። እርሱም ራሳችሁን ከማንምና ከምንም በላይ ማወቃችሁ ነው። እውቀት የታላቅነት መሰረት ነች፤ እውቀት የከፍታው መንገድ ከፋች ነች፤ እውቀት ለለውጥ የመጀመሪያዋ ፈርቀዳጅ ነች። ማንም ስለራሱ በጥልቀት የሚያውቅ ሰው ምርጫዎቹ የተጠኑ ናቸው፤ እርምጃዎቹ በጥንቃቄ የተሞሉ ናቸው፤ ሀሳቦቹ ከፍ ያሉ፣ ድርጊቶቹም ውጤታማ ናችው። አሉባልታ አትስሙ፣ ትርኪሚርኪ ነገር ወደ አዕምሯችሁ አታስገቡ፣ የማይረባ ንትርክ ውስጥ አትግቡ። ራሳችሁን በምታውቁት ልክ ከለላ ሁኑለት፣ ራሳችሁን በተረዳችሁት መጠን ወደፊት ግፉት፣ ከባዱን ትግል አታግሉት፣ ችግር መከራውን አጋፍጡት፣ ልባችሁን አደንድኑት፣ ልቦናችሁን አጠንክሩ። ትክክለኛውን አቅማችሁን ካልተረዳችሁ ወደፊት ልራመድ እንኳን ብትሉ አትችሉም፣ ፍላጎታችሁን ካላወቃችሁ ትልቅ ነገር ላሳካ፣ ህይወቴን ልቀይር፣ ለሰዎች ልድረስ ብትሉ እንኳን አትችሉም። ሀሳባችሁ እውን ይሆን ዘንድ እቅዳችሁም ይሳካ ዘንድ ዋናውን መሰረታዊ እውቀት ወደ ልባችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል።

አዎ! ልባችሁን ክፈቱ፣ ለራሳችሁ ቀናተኛ ሁኑ፣ ውስጣችሁን ተረዱት፣ ልባችሁን አሙቁት። የሚመጣ ሁሉ ሊያውቃችሁ ይሞክራል ነገር ግን ሳያውቃችሁ ተመልሶ ይሔዳል። የሰው ልጅ ረቂቅ ነው። ከርቀቱም የተነሳ አንዳንዴም ራሱ ሰውዬው እንኳን እራሱን በጥልቀት ለማወቅ ሊቸገር ይችላል። ዓለም የምታቀርብላችሁን ጌጣጌጥ መመራመር አቁም፤ በሰዎች ከመስመር የወጣ ድርጊት መበሳጨት አቁሙ፤ የዓለምን አሰራር ለመረዳት መድከማችሁን ተውት፣ አዕምሯችሁን በውጫዊውን እውቀት ዙሪያ ማስጨነቃችሁን አቁሙ። ሁሉም ራስን ከማወቅ ቦሃላ እንደሚመጣ ተረዱት። አሁን ገባችሁም አልገባችሁ፣ አሁን አወቃችሁም አላወቃችሁም በስተመጨረሻ ህይወት በቀዳሚነት የምትፈልገው የእናንተን ህልውና ነው። ጨርቃችሁን ጥላችሁ እስክታብዱለት የምትፈልጉት የትኛውም ምድራዊ ነገር ከእናንተ ህይወት አይበልጥም። አመናችሁም አላመናችሁም ህይወታችሁን የምትመሩት ራሳችሁን በምታውቁትና ለራሳችሁ በሰጣችሁት ትኩረት ልክ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ግብግብ ውስጥ አትግባ። ምንም ቢፈጠርብህ ከሁሉም በፊት የገዛ ስሜትህንና በነገሩ ዙሪያ ያለህን ግንዛቤ ለማወቅ ሞክር። ማንም ያላንተ ፍቃድ እንዲጠቀምብህ ካልፈለክ ከማንም በላይ ራስህን ጠንቅቀህ እወቅ። የትኛውም ሰው ከሚያውቅህ በላይ ራስህን የማወቅ ግዴታ እንዳለብህ አስተውል። ውስጣዊ አቅምህን፣ የመረዳት ችሎታህን፣ ክህሎትህን፣ የደስታህን ምንጭ፣ የወደፊት እርምጃህን፣ ከፈጣሪህ ጋር ያለህን ቅርበት፣ ጥንካሬህን፣ ድክመትህን፣ የልብ ፍላጎትህን በሙሉ ጠንቅቀህ እወቅ። ከራስህ የሚበልጥ የቤት ስራ የለህም። ስሜትህን የመግዛቱ አቅም አለህ፤ ምርጫዎችህን የማስተካከሉ ተሰጥዖ አለህ። ስህተትን እንደ ስህተትነቱ፣ ጥፋትንም እንደ ጥፋትነቱ ተቀበል። ማራኪ ሆነህ ለመታየት ሳይሆን የእውነትም ማራኪ ለመሆን ራስህ ላይ ጨክን፣ ከሰው በላይ ለራስህ ታመን። በጥንቃቄ የተጠናን እርምጃ ተራመድ፣ በእውቀት ላይ የተመሰረተን ተግባር ፈፅም፣ በጥበብ መንገድም በልበሙሉነት ተመላለስ።

LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/fpn1FQlM_X4?si=VgYsjN8SaeD4KRDr

መልካም ቀን ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇
       
@Mtshaf_bicha
       
@piyasa188
❤️ለወዳጅዎ
#ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩
@Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                 
@EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
"ጦቢያ" የተሰኘው ዘመናዊ ልብወለድ መፅሐፍ የፃፉት ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረኢየሱስ ከባለቤታቸው ጋር በሀገረ ጣሊያን በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የተነሱት ፎቶግራፍ ፤

ጳጉሜ 1 ቀን 1927 ዓ.ም
ጣሊያን - ሮም

    LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

መልካም ቀን ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
🌼እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችው🌼
አዲሱ አመት ሀገራችን ሠላም የምትሆንበት ያድርግልን 🙏
                
    ❤️መልካም
በዓል❤️

    LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

🌼መልካም አዲስ አመት ተመኘሁ🙏
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌻
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
እናቴ በጣም ጎበዝ ነርስ ናት። አንድ ጊዜ በአመት በአል ቀን ተረኛ ሆና ወደስራ ልትሄድ ስትነሳ ሁላችንም ተማርረን አንድትቀር ስንለምናት ያለችን ፈጽሞ አይረሳኝም። '' እኔ እኮ ተረኛ የሆንኩት ስዎችን ለመርዳትና ከደረሰባቸው ስቃይ ነጻ ሆነው ወደቤታቸው እንዲሄዱ ለማድረግ ነው። ለዛውም ከስምንት ሰአት በኃላ ወደቤቴ እመለሳለሁ። እስኪ አስቡ! ዛሬ በሽተኛ ለመሆን ተረኛ ሆነው በህይወትና በሞት መካከል ያሉትን የሌሎች ልጆች ወላጆች። ምናልባት ፈፅመው ወደቤት ተመልሰው ሌላ አመት በአልም ላያከብሩም ይችላሉ።'' ነበር ያለችን። ሁላችንንም የለወጠ አባባል ነበር። እናቴ የምትገርም ደግ ሰው ናት። በእርግጥ ታመው የተሻላቸው ሲያመሰግኑ ያልታመሙት ለምን ይሆን የሚያማርሩት? በህይወትና በሞት መካከል ያሉት አንድ ተጨማሪ ደቂቃ ለመኖር ባለ በሌለ ሃይላቸው ሲፍጨረጨሩ በህይወትና በጤና ያሉት ግን ሞትን የሚያስመኛቸው ምክንያት ግን ሁሌም ይደንቀኛል።

📕ከተቆለፈበት ቁልፍ

በዶክተር ምህረት ደበበ


    ❤️መልካም በዓል❤️

  LIKE👍👍 እና Share
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

🌼መልካም አዲስ አመት ተመኘሁ🙏
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌻
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄