😎ጠላፊዎቹ
፡
#ክፍል_አርባ_አንድ
፡
#በኬንፎሌት
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
hቦትውድ ወደ ሼዲያክ
ኤዲ ዲኪን የበረራ ባልደረቦቹ ወደ ጀልባው ሲገቡ ሲያይ ሊፈጽመው
ያሰበው ክህደት በዓይነ ህሊናው ድቅን አለበት፡ መቼም ሊያደርግ ያሰበውን
ቢያውቁ ዓይንህን ላፈር እንደሚሉት ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ነዳጁ ባዶ መሆኑን እያወቀ አይሮፕላኑ ባህር ውስጥ ገብቶ ሁሉም እንዲያልቅ ሊያደርግ እንደነበር ያወቁበት መሰለው፡፡
የነዳጅ መጠኑን መቆጣጠር የበረራ መሀንዲሱ ስራ ነው፡፡ ስለዚህ ሰው በዚህ ምክንያት ቢያልቅ ተጠያቂ እሱ ነው፡፡
ሰሞኑን ያሳይ የነበረውን እንግዳ ባህሪ ቢያውቁ ምን ይላሉ? እነሱ በማያውቁት ነገር አዕምሮው ተወጥሮ ቆይቷል፡፡ ትናንት ማታ ራት ላይ ቶም ሉተርን ሲያስፈራራው ነው ያመሸው፡፡ የወንዶች መፀዳጃ ቤት ውስጥ
መስኮት ሲሰበር እሱ
እዚያው ነበር፡፡ ስለዚህ ኤዲን ቢጠረጥሩ
አይፈረድባቸውም፡፡ እንዲህ አይነት ነገር ቢታወቅ ወሬው በአንድ ጊዜ ነው
አይሮፕላኑ ውስጥ የሚዛመተው፡፡
የስራ ባልደረቦቹ በእሱ ላይ ከእንግዲህ እምነት ሊጥሉ እንደማይችሉ ማወቁ በራሱ የኮሶ መድኃኒት እንደመዋጥ ነው የሆነበት፡፡ ከሁሉም
የአይሮፕላኑ ሰራተኞች አቋመ ጽኑ መሆኑ ያኮራው ነበር፡ የሌሎችን ስህተት በቀላሉ ማለፍ ስለማይችል አንዳንዴ ሰዎች በግል ችግራቸው ምክንያት ግዴታቸውን መወጣት ሲያቅታቸው የሚሳደብበት ጊዜ አለ፡፡በይቅርታ ሊታለፍ አይችልም ይላቸዋል ስህተት ሲፈጽሙ ከተገኙ፡፡ አሁን ግን እሱ ራሱ የሚታመን ሰው አልሆነም፡፡
አሁን ለእንደዚህ አይነት ጉዳይ የሚጨነቅበት ጊዜ አይደለም፡፡ ሚስቱን
ለማዳን የማይፈነቅለው ድንጋይ የማይምሰው ጉድጓድ የለም፡፡ ስለዚህ
ሚስጥሩን በሆዱ ይዞ ለብቻው ሊፈጽም ቆርጦ ተነስቷል፡ ስለሌሎች ስሜት
አሁን መጨነቅ የለበትም፡፡ ሆነም ቀረ ህይወታቸውን አንዴ አደጋ ላይ ጥሏል፡፡ ውጤቱም እንዳሰበው ሊሆን ነው፡ አቋመ ጽኑው መሀንዲሱ ዲኪን
ወደማይታመነው ዲኪን መቀየሩ ነው፡፡
በርካታ ተሳፋሪዎች ትንሽ እንቅልፍ ብናገኝ ብለው አይሮፕላኑ ውስጥ
ቀርተዋል፡ የኤፍ.ቢ.አዩ ኦሊስ ፊልድና እስረኛው ፍራንክ ጎርዲኖም ከአይሮፕላኑ አልወረዱም፡፡ ቶም ሉተር ባለጸጉራም ጃኬቱን ለብሶና ቆቡን አናቱ ላይ ደፍቶ ጀልባው ላይ። ወጣ፡፡ ኤዲም ከኋላው መጣና ጠጋ ብሎ
‹‹የአየር መንገዱ ህንጻ ጋ ሂድና ስልኩ ያለበት ቦታ እወስድሃለሁ›› አለው፡
ቦትውድ ከእንጨት የተሰሩ ቤቶች የተገጠገጡባት ትንሽ ከተማ ስትሆን
የአይሮፕላኑ ተሳፋሪዎች በየሱቁ ብዙም የሚገዛ ነገር አላገኙም፡፡ መንደሪቱ
የስልክ አገልግሎት አላት፡፡ ኒውፋውንድ ላንድ አሁንም በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር ስለሆነች መኪኖች የሚሄዱት ግራቸውን ይዘው ነው፡፡
ተሳፋሪዎቹ ወደ ፓን አሜሪካ አየር መንገድ ህንጻ ሄዱ፡፡ ኤዲ ከቦትውድ ሰላሳ ስምንት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ አየር ማረፊያ ላይ ካረፈ አይሮፕላን በሬዲዮ የተላከ የአየር ጠባይ መረጃ አነበበ፡፡ ከዚያም ለሚቀጥለው ጉዞ የሚያስፈልገውን የነዳጅ መጠን ስሌት ሰራ፡
ሲሰራ አፉን ደም ደም አለው፡፡ ከዚህ በኋላ የበረራ መሀንዲስ አይሆንም።
ካፒቴኑ የኤዲን የነዳጅ ፍላጎት መጠን ስሌት አምኖ መቀበል ይኖርበታል፡፡ የሰራው ስራ እንዲታመንለት ስሌቱን ሁለት ጊዜ ቼክ አደረገና
‹‹ሌላ ሰው ቢያጣራው እወድ ነበር›› ብሎ ለካፒቴኑ ሰጠው።
‹‹ችግር የለውም›› አለ ካፒቴኑ ለነገሩ ትኩረት ባለመስጠት፡ ‹‹እስቲ
ተናፍሼ ልምጣ›› አለና ወጥቶ ሄደ፡ ኤዲም ካፒቴኑን ተከትሎ ወጣና ቶም ሉተርን ፓን አሜሪካን ህንጻ አጠገብ ሁለት እጁን ኪሱ ከቶ አገኘው፡፡ ‹‹ወደ ስልኩ እንሂድና ከጓደኞችህ
ጋር እንድትነጋገር አድርጌ ቶሎ ወደ ስራዬ እመለሳለሁ›› አለው፡ ሉተር
በመጀመሪያ ጎተት እያለ ነበር የሚሄደው፡፡ በኋላ ግን የትናንት ማታውን
ግብግብ አስታወሰና ቶሎ ቶሎ መራመድ ጀመረ፡፡ ኤዲን እንደገና ማናደዱ
ትርፉ ራስን መጉዳት መሆኑን ተረድቷል፡፡
በመንገዳቸው ላይ መርቪንና ናንሲን አገኙና የአንገት ሰላምታ
ሰጥተዋቸው አለፉ፡፡ ሁለቱም አንድ ላይ በመሆናቸው የተደሰቱ ይመስላሉ፡ሰዎች እሱና ካሮል አን አንድ ላይ ሲሆኑ እንደሚያስቀኑ ይነግሩት ነበር፡ እሷን ሲያስታውስ ብስጭቱ እንደገና ተቀሰቀሰበት፡፡
ስልክ ቤት ገቡና ሉተር የስልክ ቁጥሩን በብጣሽ ወረቀት ጽፎ ለስልከኛው ሰጠው:፡ ኤዲ የሚናገረውን እንዲሰማ አልፈለገም፡፡ ኦፕሬተሩ እስኪያገናኛቸው ድረስ የስልክ መደወያው ክፍል ውስጥ ገብተው ጠበቁ ማለዳ በመሆኑ ብዙ ስልክ ደዋይ የለም፡፡
ኤዲ ካሮል አንን አይሮፕላኑን የሚያሳርፍበት ቦታ ድረስ ይዘዋት እንዲመጡ ሉተር እንደሚነግራቸው ገምቷል።
ካሮል አንን በእጁ ካስገባ
በኋላ ደግሞ ሌላ ያሰበውን ነገር ለመስራት ነጻነት ያገኛል ነገር ግን ምን
ሊያደርግ ነው ያሰበው? ወዲያው ለፖሊስ ማሳወቅ? ሉተር ከጠረጠረ ድረስ ደግሞ ዝም ብሎ መጠበቅ የግድ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ጊዜ ውስጥ የሬዲዮ መገናኛውን ከመስበር አይመለስም፡፡ የፖሊስ እርዳታ እስኪደርስ
ጎርዲኖና ሉተር ከአይሮፕላኑ ወጥተው በመኪና ያመልጡና አንዱ ጋ
ይሸጎጣሉ፡፡ ካናዳ ይግቡ አሜሪካ ማንም የሚያውቅ አይኖርም፡፡ ኤዲ
እንዳያመልጡ አስቀድሞ ለፖሊስ ቢነግር ደግሞ ከፖሊሶች ጋር ሲታኮሱ
የካሮል አን ህይወት አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ ኤዲ እንዲህ እንዲሆን
አይፈልግም::
ስልኩ ሲጮህ ሉተር አነሳና ‹‹እኔ ነኝ የዕቅድ ለውጥ መኖሩን ልነግራችሁ የደወልኩት፡፡ ሴትየዋን በጀልባ አይሮፕላኑ ድረስ ካላመጣችሁ የምትፈልጉትን አልፈጽምም ብሏል ሰውየው፡፡ እኔ በበኩሌ ያለውን አምኜ
ተቀብያለሁ፡ ስለዚህ ይዛችኋት እንድትመጡ›› አለና መልሳቸውን ጠበቀ፡፡
ከዚያም ‹‹ሊያናግሩህ ይፈልጋሉ›› አለው ኤዲን፡፡
ሉተር በመጀመሪያ ትዕዛዝ ሲሰጠው ልክ የወሮበሎቹ መሪ መስሎ ነበር የሚታየው፡፡ ካነጋገሩ ግን ካሮል አንን ወደ መገናኛቸው ቦታ እንዲያመጣለት
ለማዘዝ ስልጣን የሌለው ሆኖ ታየው፡፡
‹‹ሊያናግረኝ የሚፈልገው አለቃችሁ ነው?››
‹‹እኔ ነኝ አለቃ›› አለ ሉተር እየከበደው ‹‹ነገር ግን ግብረ አበሮች አሉኝ››
የሉተር ግብረ አበሮች ካሮል አንን ቦታው ድረስ ማምጣት እንደማይፈልጉ ይታወቃል፡፡ ከእነሱ ጋር መነጋገሩ የሚፈይድለት ነገር አለ? የለም፡፡ ካሮል አንን ስልኩጋ ያመጡና አስለቅሰው የመንፈስ ጽናቱን ይፈታተኑታል፡፡ ‹‹ስትፈልጉ ገደል ግቡ በላቸው›› አለ ጮክ ብሎ
እንዲሰሙት፡፡
ሉተር የኤዲ አነጋገር አስደንግጦት እነዚህን ሰዎች እንዲህ ልትናገራቸው አትችልም›› አለ እሱም ጮክ ብሎ፡፡
ሉተር የወሮበሎቹ መሪ ከሆነ ምን አስፈራው? አሁን የሉተርን ስልጣን መገምገም አይረባውም፡፡ ዕቅዱን ማሳካት ነው ያለበት፡፡ ሉተርም ‹‹ወይ አናግራቸዋለሁ ወይም አላናግራቸውም በል›› አለው ኤዲን፡፡
ላናግራቸው እንደማልፈልግ ንገራቸው ለእነዚህ ድንጋይ ራሶች አለው።
አይ አምላኬ አለና ሉተር የስልኩን እጀታ አንስቶ ‹‹አላናግራችሁም
ብሏል፡፡ ሰውየው አስቸጋሪ ነው:›› ንግግሩን ቆም አደረገና ‹‹ጥሩ ሃሳብ ነው እነግረዋለሁ››ብሎ የስልኩን እጀታ እንደያዘ
‹‹ሚስትህ ቀርባለች
ታናግራታለህ?›› አለው ኤዲን፡፡
ኤዲ ስልኩን ሊቀበል እጁን ዘረጋና መልሶ ተወው፡፡ ከእሷ ጋር ከተነጋገረ ምህረት ጠያቂ ሊሆን ነው ነገር ግን ድምጿን ቢሰማ አይጠላም እንደማያነጋግራት በራስ ንቅናቄ ለሉተር አመለከተው፡፡
ሉተር ኤዲ ላይ አፈጠጠና ‹‹አላናግርሽም ብሏል ባልሽ፡፡ ዞር በይ አንቺ
ሸርሙጣ!›› አላት ካሮል አንን፡፡

📕ተአምረተ_ኬድሮን
#ክፍል_አርባ_አንድ
#ተከታታይ ልቦለድ
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
በ25ኛው ቀን ጥዋት ቁርስ ከበሉ በኃላ
‹‹ዛሬማታ ልሄድ ነው››
‹‹የት ነው የምትሄደው…..?››ደንገጥ ብላ ጠየቀችው ሰሚራ
‹‹ከከተማ ወጣ ብዬ ትንሽ ራቅ ብዬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ማሰብ እፈልጋለሁ….››
‹‹ስለምንድነው የምታስበው..…..?ክፉ ነገር አይደለም አይደል…..?››
‹‹እኔ እንጃ …ለጊዜው ምንም የመጣልኝ ነገረ የለም..እንደገደሉኝ ልግደላቸው…ወይስ ይቅር ልበላቸው …..?የማውቀው ነገር የለም…ገንዘቤን ግን ልጅነቴን የሰዋሁበትና ብዙ ፈተና ያየሁበት ስለሆነ ሰባራ ሳንቲም እንደማልተውላቸው እርግጠኛ ነኝ..ምን አልባት እስከዛው በደንብ ቢደሰቱበት ጥሩ ነው››
‹‹እንዴት አድርገህ ታስመልሳቸዋለህ……..?አሁን እኮ ንብረትህ በእነሱ እጅ ነው..በህይወት መኖርህን ካወቁ ባለ በሌለ ኃይላቸው ነው አሳደው የሚያስገድሉህ››
‹‹አይዞሽ አታስቢ… እጠነቀቃለሁ….ለዛም ነው ከዚህ ከተማ ራቅ ብዬ በጽሞና ምን ማድረግ እንደምችል ማሰብ አለብኝ የምልሽ››
‹‹ካልክ እሺ ..ቆይ መጣሁ›› ብላ ከነበሩበት ሳሎን ተነስታ ወደመኝታ ቤቷ ከሄደች ከ5 ደቂቃ በኃላ ተመልሳ መጣችና ቼክ እጁ ላይ አስቀመጠችለት፣..ግራ ገብቶት አንዴ የሰጠችውን ቼክ አንዴ ደግሞ እሷን በማፈራረቅና በመገረም ሲያያት ከቆየ በኃላ
‹‹ምንድነው ይሄ…..?››ጠየቃት
‹‹የራስህ ብር ነው..አንተን እንድገድልላቸው የከፈሉኝ ነው…ሁኔታዎችን እስቲስተካከሉልህ ለመንቀሳቀሻ ይሆንሀል››
‹እንዴ ምን አይነት ሰው ነሽ….?እንዲህ አይነት ሰው እኮ በዚህ ጊዜ አይገኝም››
‹‹አይ እንደምታስበኝ ደግ ሴት ሆኜ አይደለም..ለአንተ ብቻ ነው እንዲህ የሆንኩት..››
በንግግሯ ውስጡ ተነካና‹‹ለእኔ ለምን…..?››ጠየቃት
‹‹እኔ እንጃ….. ›አለችው
..ከተቀመጠበት ተነሳና ስሯ ተንበረከከ..ደነገጠች፡፡ አቀፋት …አንገቷ ሰር ገብቶ ሳማት…. ውርርር አደረጋት፣..አላቆመም… ወደታች አስጎንብሶ ግንባሯን …አይኖቾን… ጉንጮቾን በመጨረሻ ከንፈሯ ላይ ተጣበቀባት…አይኗን ከመጨፈን እና ከንፎሯን ከማነቃነቅ ውጭ ምንም ተቃውሞ አላሰማችም…ደስ የሚሉ እልፍ መሰል ሁለት ደቂቆች አለፉ….
የሚያደርገውን አድርጎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ሲቆም እሷ አፍራ አቀረቀረች…
የሰጠችውን ቼክ መልሶ ጉልበቷ ላይ እያስቀመጠላት..ይሄ ምን አልባት እኔን ለገደልሽበት ቢከፍሉሽም.. አንቺ ግን እኔን ለማዳን ለህክምና ይሄን ቤት ለመከራየት ላወጣሽው ወጪ መሸፈኛ ይሁንሽ…ውለታሽ ግን በዚህ ብር የሚመለስ ወይም የሚጣጣ ፍጽም አይደለም…በሕወቴም ጭምር ከፍዬ አልጨርሰውም››
‹‹ህይወትህን ስፈልግ ያኔ ትከፍለኛለህ …አሁን ግን ከእኔ ይልቅ አንተ ነህ ችግር ላይ ያለህው … ደግሞ ከራሴ ገንዘብ ምንም ያወጣሁት ነገር የለም…ከዚህ በተጫማሪ መቶ ሺ ብር ቦነስ ብለው ሰጥተውኝ ነበር…እርግጥ ከላዩ ላይ አንተን ለማሸሽ እና የሬሳ ሳጥኑን ቀይረው ለሰጡኝ አቶ ተካ 50 ሺ ብር ከፍያለሁ..ሌላውን 50 ሺብር ደግሞ እስከአሁን እየተጠቀምኩበት ነው ፡፡››
‹‹አይዞሽ ለእኔ አትስቢ አልኩሽ እኮ …እነሱም ሆነ ማንም የማያውቀው 5 ሚሊዬን ብር ባንክ አለኝ…..በዛ እጠቀማለሁ፡፡››
‹‹ግን ባረብሽህ ምትሄድበት ይዘህኝ ብትሄድ …..?››
‹‹አረ ደስ ይለኛል..ስራሽን ብዬ እኮ ነው…..?››
‹‹ስራው ይደርሳል››
‹‹በያ ተዘጋጂ….መኪና እንከራይ ››
‹‹ወደየት ነው ግን ምንሄደው…..?››
‹‹እግራችን ወደመራን….››
✨ይቀጥላል✨,,,,,,,,,✍
#ክፍል 42,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅
https://youtube.com/@Weygud18
#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18
❤መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
👇👇👇
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽»🎶••✿••🎶»✽┉┉┄