ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
247K subscribers
289 photos
1 video
15 files
243 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

‹‹እሺ›› አለ ቪንቺኒ ወደ ጀልባዋ ፊቱን አዞረና ‹‹ጆ መጀመሪያ አንተ ና
ቀጥሎ ትንሹ ልጅ በመጨረሻ የኤዲ ሚስት፡፡›› ወደ ውስጥ ሲያዩ ካፒቴኑ ወደ አይሮፕላን መንጃው ክፍል ሲሄድ አየው፡፡ በዚህ ጊዜ ቪንቺኒ ሽጉጡን
መዘዘና ‹‹አንተ ባለህበት ቁም›› ሲል አዘዘው ቤከርን፡፡
ኤዲም ካፒቴን እንደሚልህ አድርግ እባክህ እነዚህ ሰዎች ቀልድ አያውቁም›› አለ ቤከር ባለበት ቆመና እጁን ወደ ላይ አነሳ፡፡

ጆ የተባለው ወሮበላ ‹‹እዚህ ውስጥ ብወድቅ መዋኘት አልችልም›› አለ
ከጀልባው ወደ አይሮፕላኑ መዝለል ፈርቶ፡፡

‹‹መዋኘት አያስፈልግም›› አለ ኤዲ እጁን ዘረጋለት፡፡

ጆም እንደምንም ዘለለና አይሮፕላኑ ውስጥ ገባ፡፡
ከእሱ በፊት ሁለት ሰዎች በደህና መዝለላቸውን አይቶ ትንሹ ልጅ ኮራ ብሎ ዘለለ፤ ነገር ግን ሲዘል ሚዛኑን ሳተና ወደኋላው ሊወድቅ ሲል ኤዲ የልጁን ቀበቶ ይዞ አዳነው ‹‹አመሰግናለሁ›› አለ ልጁ፡፡

አሁን የካሮል አን ተራ ደረሰ ለመዝለል ፈርታ የኤዲን አይን አይን ታያለች በተፈጥሮዋ ፈሪ ሆና ሳይሆን ከእሷ በፊት ትንሹ ልጅ ተንገዳግዶ ባህር ውስጥ ሊገባ ሲል ስላየች ነው የፈራችው፡፡ ኤዲም ፈገግ አለና
‹‹እንደነሱ ዝለይ ማርዬ›› አለ ‹‹አይዞሽ ውሃ ውስጥ አትወድቂም::››

ኤዲ በፍርሃት ልቡ እየደለቀ በጉጉት ጠበቀ ሚስቱ እስክትዘል፡፡ ካሮል
አን መዝለል መቻሏን ተጠራጠረች፡፡ ‹‹ተዘጋጂና ዝለይ!›› አላት እሱም የእሷ
ፍርሃት ተጋብቶበት፡፡

ካሮል አን ጥርሷን ነክሳ እንደ ምንም ዘለለች፤ ነገር ግን ግማሽ አካሏ ባህሩ ውስጥ ሆኖ ገመዱን ለመያዝ ተፍጨረጨረች፤ ‹‹ገመዱን አጥብቀሽ
ያዥ አይዞሽ›› አለ ወደ ባህሩ የምትወድቅ ከሆነ ለመዝለል ተዘጋጅቶ
ኤዲ ተንበረከከና እጇን ለመያዝ እጁን ሰደደ፤ ሆኖም ሚዛኑን ሳተና ወደ
ባህሩ ሲወድቅ እጇን መያዝ አልቻለም፤ የባህሩ ሞገድ ጎትቶ ውሃ ውስጥ
ሲያስቀራት በተስፋ መቁረጥ ጮኸች፡፡

ያለ የሌለ ሀይሏን ተጠቅማ ወደ ኤዲ እየዋኘች ተጠጋች፤ ኤዲ ጥርሷ
ሊንገጫገጭ አየ፧ እንደ ምንም ብሎ እግሯን ያዘ፤ ሆኖም የባህሩ ሞገድ
ሃይለኛ በመሆኑ ከእጁ አፈተለከችና እንደገና ባህሩ ላይ ወደቀች፤ ካሮል አን
እየሰመጠች ነው እሱም እጁን ሰደደና ወገቧን ያዘ፡፡

‹‹አይዞሽ የኔ ማር ይዤሻለሁ›› አለና እንደምንም ተሸክሞ ወደ
አይሮፕላኑ አስገባት፡፡ ካሮል አን ባሏ  እቅፍ ውስጥ ገብታ ማንባቷን ቀጠለች፡፡ እምባ ቢተናነቀውም እንደምንም ዋጥ አደረገው፡፡የምትንቀጠቀጠውን
ሚስቱን ለማረጋጋት አጥብቆ ደረቱ ላይ ለጠፋት
‹‹ደህና ነሽ የኔ ማር? እነዚህ ሰዎች አንገላቱሽ?›› ሲል ጠየቃት

‹‹ደህና ነኝ›› አለች ጥርሷ እየተንገጫገጨ፡፡

የካፒቴኑን ዓይን ለማየት ፈርቶ እየሰረቀ ያየዋል፡፡ ቤከር ወደ ካሮል
አን አማተረና
‹‹ያደረግኸው ሁሉ ለምን እንደሆነ አሁን እየገባኝ መጣ›› አለ፡፡
‹‹ይበቃል የምንሰራው ስራ አለን›› አለ ቪንቺኒም፡፡
ኤዲ ካሮል አንን ለቀቃትና ‹‹እሺ ወደምትፈልጉት ሰው እወስዳችኋለሁ››
‹‹እሺ›› አለ የወሮበሎቹ መሪ፡
‹‹ተከተሉኝ›› አላቸውና ወደ ውስጥ ገቡ፡ ሰራተኞቹ ምንም ነገር ለማድረግ እንዳይሞክሩ ኤዲ አስጠነቀቃቸው:
‹‹ሁላችሁም አደብ ግዙ፡፡ እነዚህ ሰዎች አድርጉ የሚሏችሁን ማድረግ
ብቻ ነው ያለባችሁ አለበለዚያ በጥይት ከመግደል ወደ ኋላ የሚሉ ሰዎች አይደሉም፡ ሰው እንዲጎዳ አልፈልግም፡ ካፒቴኑም ይህንኑ ነው የሚላችሁ አለ ኤዲ፡

‹‹ትክክል ነው›› አለ ካፒቴኑ ‹‹ጎበዝ! እነዚህ ሰዎች መሳሪያ የያዙ ናቸው፤ ብትወራጩ በጥይት ነው የሚሏችሁ ››
ኤዲ ወደ ቪንቺኒ ዞረና ‹‹እንሂድ እንግዲህ፤ ካፒቴን ተሳፋሪዎቹን ማረጋጋት ይኖርብሃል›› አለ፡፡

ቪንቺኒ በኤዲ አባባል መስማማቱን በራሱ ንቅናቄ አሳየ፡
‹‹ካሮል አን ከአይሮፕላኑ ሰራተኞች ጋር ሁኚ፧ እሺ›› አላት፡፡

ኤዲ ሚስቱ ከወሮበሎቹ ጥይት መራቋን ወዶታል፡ በተጨማሪም ባሏ
ለምን እነዚህን ሰዎች ሊተባበር እንደወሰነ ለተሳፋሪዎቹ ታስረዳለታለች፡
ኤዲ ቪንቺኒን ‹‹እባክህ ጠመንጃህን ከተሳፋሪዎች ብታርቅልኝ፧ ይፈራሉ››
‹‹ተነፋ!›› አለ ቪንቺኒ ‹‹እንሂድ›› ሲል አዘዘ ጓደኞቹን፡ ኤዲ ትከሻውን
በንዴት ነቀነቀ፡፡ ሁሉም ቦታ ቦታቸው ላይ እንደተቀመጡ ነው፡፡ ሁለቱ አስተናጋጆች ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ለማረጋጋት ጥረት እያደረጉ ነው፡፡
ኤዲ አይሮፕላኑ ውስጥ እየተዘዋወረ ሲያይ መብል ክፍሉ ትርምስምስ
ብሏል፡፡ ወለሉ በሸክላ እና በብርጭቆ ስብርባሪ ተሸፍኗል። ምግብ ተበልቶ
ስላለቀና ተሳፋሪዎች እየጠጡ ስለሆነ የተደፋፋ ነገር አይታይም፡:
ተሳፋሪዎቹ የቪንቺኒን ሽጉጥ ሲያዩ በፍርሃት ድምጻቸውን አጠፉ፡፡ ካፒቴን
ቤከር ወደ ፊት መጣና ‹‹ክቡራንና ክቡራት ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ
እጠይቃለሁ፡ ከመቀመጫችሁ እንዳትነሱ፡ አሁን ያለው ችግር ከተወሰነ
ደቂቃ በኋላ መፍትሄ ያገኛል›› አለ፡፡

ኦሊስ ፊልድና ፍራንኪ ጎርዲኖ አብረው ቁጭ ብለዋል አሁን ነፍሰ
ገዳይ እንዲያመልጥ ላደርግ ነው አለ ኤዲ ለራሱ፡ ወደ ጎርዲኖም ጣቱን እየጠቆመ ‹‹ያውልህ ሰውዬህ ውሰደው›› አለ፡፡
ኦሊስ ፊልድ ከተቀመጠበት ተነሳና ‹‹ይሄ የኤፍ ቢ አይ መርማሪ ቶሚ ማክ አርድል ነው›› አለ ‹‹ፍራንኪ ጎርዲኖ ትላንት በመርከብ ኒውዮርክ ደርሶ ወህኒ ገብቷል››
‹‹የአምላክ ያለህ!›› ሲል ኤዲ በግርምት ጮኸ፡፡ ይህን ሁሉ እኩይ ተግባር ሲፈጽም የነበረው ለአስመሳይ ሰው ነው?!

‹‹እኛ ከፍራንኪ ጉዳይ የለንም፡፡ ጀርመናዊው ሳይንቲስት የታለ?›› አለ ቬኒቺኒ

ኤዲ ተገርሞ ቪንቺኒ ላይ አፈጠጠ፡፡ ጎርዲኖን አይፈልጉትም፡፡ ታዲያ
ማንን ነው የሚፈልጉት?ተ

የቶም ሉተር ድምፅ ተሰማ ‹‹እዚህ ነው ያለው፤ በእኔ ቁጥጥር ስር  ነው›› አለ ሉተር ሃርትማን ላይ ሽጉጡን እየደገነ፡፡ተ

ኤዲ የበለጠ እንቆቅልሽ ሆነበት፡፡ የፓትሪያርካ ማፊያ ቡድን ለምንድን ነው ካርል ሃርትማንን ማገት የፈለገው?› ‹‹ሳይንቲስቱን ለምንድን ነው የምትፈልጉት?› ሲል ጠየቀ፡፡

ቀበል አድርጎ ‹‹ተራ ሳይንቲስት እንዳይመስልህ የኒኩሊየር ፊዚስት
ነው›› አለ ሉተር፡

‹‹እናንተ ናዚ ናችሁ?›› ሲል ጠየቀ ኤዲ፡፡

‹‹አይደለንም፧ እኛ ዲሞክራቶች ነን፡፡ እነሱ ሳይንቲስቱን አግተን
እንድንሰጣቸው ስራ አዘውን ነው፡ ረብጣ ገንዘብ ይከፍሉናል›› አለና ቪንቺኒ
ተንከተከተ፡

ሉተርም ‹‹እኔ ዲሞክራት አይደለሁም፡፡ የጀርመን አሜሪካን ትብብር
ማህበር አባል ነኝ፡፡ ይህ ማህበር በናዚ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ
የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው፡፡ ሂትለር ራሱ ነው ከአገር አምልጦ የወጣውን
ሳይንቲስት አፍኜ ወደ ጀርመን እንዳመጣው ያዘዘኝ›› አለ፡፡ ሉተር ይህን
ሲናገር በኩራት ነው፡፡ ‹‹እነዚህ ሰዎች ከፍዬ የማሰራቸው እኔ ነኝ፡፡ ስለዚህ ዶክተር ፕሮፌሰር ሃርትማንን ወደ ጀርመን መልሼ እወስደዋለሁ፡
ሳይንቲስቱ እዚያ በጣም ይፈለጋል›› አለ፡

ኤዲ ከሃርትማን ጋር ዓይን ላይን ግጥም አለ፡፡ ሰውዬው ፍርሃት
ጨምድዷቸዋል፡ ኤዲ ወዲያው ፀፀት ገባው፡፡ ሳይንቲስቱ ወደ ጀርመን
ሊመለሱ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ የኤዲ ጥፋት ነው፡፡

‹‹ምን ላድርግ ባለቤቴን ስላገቱብኝ ነው የተባበርኳቸው›› አለ፡፡

የሃርትማን አስተያየት ተለወጠ ‹‹ይገባኛል›› አሉ ሳይንቲስቱ ‹‹እንደዚህ
አይነት ክህደቶችን ጀርመን ውስጥ ለምደናቸዋል፡ አንዱን ለማዳን ስትል
ሌላውን አሳልፈህ ትሰጣለህ፡ ምንም ምርጫ አልነበረህም፡፡ በዚህ ራስህን አትውቀስ›› አሉት፡፡
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ

#ተከታታይ ልቦለድ

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ወደሸገር ተመልሰዋል..ማለት እሷ እና ንስሯ ፡፡ለእናቷ በመጨረሻው ቀን ተመልሳ እንደምታያትና ወደአባቷ ዘመዶችም በምትሄድበት ቀን አጠገቧ እንድትሆን እንደምትፈልግ   ነግራትና ቃል ገብታላት ነው የመጣችው፡፡
እስከዛው ያሉትን ቀጣዬቹን በስስት እየተሸራረፉ በመርገፍና በማለቅ ላይ ያሉትን ቀሪ 5  የሰቀቀን ቀናቶችን ሸገር ልታሳልፍ ወስናለች….ምን አልባትም አይታውቅም… በመሀል ሀሳቧን ልትቀይር ትችላለች፡፡
ግን አሁን ተረጋግታ እቤቷ መቀመጥ አልቻለችም … ሰዓቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ቢያልፍም ልትቆጣጠረው የማትችለው ከውስጧ ሚመነጭ ስውር ስሜት ውጪ ውጪ ይላት ጀመር….ልብሷን ቀያየረችና መኪናዋን ወዳለችበት መራመድ ከጀመረች በኃላ ሀሳቧን ቀየረችና ስልኳን አውጥታ ደወለች..አዎ ነፃ መሆን ነው የምትፈልገው….ላዳ ያለው የምታውቀው ልጅ ጋር ነው የደወለችው፡፡

‹‹ሄሎ››

‹‹ሰላም ነው… .ፈልጌህ ነበር…የት ነህ ያለኸው?››

‹‹ይቅርታ ዛሬ ስራ ላይ አይደለሁም መኪናዬ ተበላሽታ ገራዥ ነች››

‹‹በቃ አንተ ናልኛ ..የእኔ መኪና ስላለች ትይዝልኛለህ …ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆንኩ መንዳት አልፈለኩም››

‹‹ደስ ይለኝ ነበር.. ግን ያው ስራ የለኝም ብዬ ከከተማ ወጣ ብያለሁ…..ከፈለግሽ አንድ ጓደኛዬን ልልክልሽ እችላለሁ››

‹‹ደስ ይለኛል››

‹‹በቃ ንገረውና ቁጥርሽን ሰጠዋለሁ…ይደውልልሻል››

‹‹እሺ አመሰግናለሁ››ስልኳን ዘጋችውና ጊቢዋ ውስጥ እየተዘዋወረች እስኪደወልላት መጠበቅ ጀመረች….፡፡
ብዙም ሳይቆይ ስልኳ ላይ የማታውቀው ቁጥር ተንጫረረ …አነሳችው..አናገረችው ….በ15 ደቂቃ እንደሚደርስ ነገራት…..መጠበቅ ጀመረች…..

‹‹አዎ በዚህ ለሊት ምን አልባት ለመጨረሻ ጊዜ ማበድ እፈልጋለሁ..አዎ ብዙ ነገር ማድረግ አምሮኛል…የማሰብ አቅሜን አዳክሞ ጭንቀቴን የሚቀንስልኝን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ እፈልጋለሁ…..መጠጣትና መስከር …መቁላላትና መዋሰብ እፈልጋለሁ…መጣላትና መደባደብም ካገኘሁ አልጠላም…››
እግዜር ይስጠው የመኪና ጥሩንባ ድምጽ ሰማች...ጎበዝ ልጅ ነው… በነገረችው ምልክት መሰረት ሳይሳሳት መምጣቱ አስደሰታት… በራፍን ከፈተችና ወጣች…በምልክት ጠራት … የላዳውን በራፍ ከፈተላትና ገባች፡፡

‹‹ወዴት ልውሰድሽ….?››

‹‹መጠጣት ነው የምፈልገው››አለችው፡፡

‹‹መጠጣት›› አላት ግራ ተጋብቶ፡፡

‹‹መጠጣት ስልህ …ብሽቅጥ እስክል መጠጣት ነው የምፈልገው…የፈለከውን ያህል ከፍልሀለሁ እስከንጋትም ቢሆን አብረኸኝ ትቆይና እቤቴ ታስገባኛለህ››

‹‹ይመችሽ ››አላት….

እንዲሁ ወደደችው…አንድን ሰው አይተን በውስጣችን ስለሰውዬው ደስ የሚል ስሜት ሲሰማን ውቃቢዬ ወዶታል  የምንለው ነገር አለ አይደል..….? እሷም ይሄን የላዳ ሹፌር  እንዳየችው  እንደዛ ነው የተሰማት፡፡

‹‹ምርጫሽ የት አካባቢ ነው?››

‹‹የፈለክበት ውሰደኝ ››

‹‹ቺቺኚያ ይመችሻል››

‹‹ይመችህ››

ነዳው….ንስሯ አምኗት እቤት ሊቀር አልቻለም  …ከፊት ለፊታቸው  በላዳዋ   ፍጥነት መጠን  ሲበር በመኪናዋ መስታወት አሻግራ አየችው….

ደረሱና መኪናዋን ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀበት ቦታ ፓርክ አድርገው አንዱ ጭፈራ ቤት ገቡ……እሷ ደረቅ አልኮለሏን ስታዝ እሱ ዉሀ አዘዘ..

‹‹ለምን ትንሽ አትሞከርም….? ››

‹‹አይ …የሞያዬ ስነምግባር አይፈቅድልኝም›› ሲል መለሰላት በቀልድ መልክ

..ዝም አለችው… በላይ በላዩ መለጋቱን ቀጠለች….የሙዚቃው ከጣሪያ በላይ ጩኸት…የለሊት ንገስታቶች በገዢ መሳይ  ወንዶች ዙሪያ መሽከርከር፤  በስካር የሚናውዙና የሚደንሱ ወንዶችና ሴቶች የሆቴሉን ወለል መሙላት…የሆነ ትርምስምስ ያለ ነገር ነው የሚታየው….በዛ ላይ መብራቱ በአምስት አይነት ቀለም በመፈራረቅ ቦግ ብልጭ ሲል  እይታን ብዥ ያደርጋል…….ግን በምትፈልገው መጠን ባይሆንም ተመችቷታል ፡፡ቢሆንም ደስታዋን ሙሉ ማድረግ ፈለገች…

‹‹ሌላ ጓደኛ የለህም….?››ድንገት ከመሬት ተነስታ ጠየቀችው፡፡

‹‹ምን አይነት….?››

‹‹ሹፌር››..

‹‹ምን ያደርግልሻል….?››

‹‹ያንተን መኪና የሚነዳልን››

‹‹እኔስ….?››አላት በጥያቄዋ ግራ ተጋብቶ

‹‹አይ አንተማ እንድታጣጣኝ ፈልጌ ነው..ብቻዬን ደበረኝ››

‹‹እ ..ቆይ እስኪ ደዋውዬ ልሞክር››አለና ስልኩን እየጎረጎረ ከሆቴሉ ወጣ..ሲወጣ ከጀርባው ሳታየው ነበር…ቁመናው መስጧታል..በቃ የተለመደው ችግሯ እያገረሸባት ነው..ጭኗ መካከል አሳከካት…ምን አይነት መጥፎ አመል ነው…እዛም አባቷ  አለም ስትሄድ እንዲህ የሚበላት ነገር ወቅት እየጠበቀ ይፈታተናት  ይሆን እንደዛ ከሆነ ምንድነው የምታደርገው….….?

ሀሳቧን ሳትጨርስ መጣና መቀመጫው ላይ ተመልሶ እየተቀመጠ..‹‹ተሳክቶል…ተቀላቅዬሻለሁ››አላት

በደስታ እየፈገገች‹‹ምን ይምጣልህ..?››ሥትል ምርጫውን ጠየቀችው፡፡

‹‹አንቺ የያዝሺውን…››
ሙሉ ጠርሙስ አዘዙ…መጣላቸው…… ይገለብጡት ጀመረ…እየደነሱ እየተቀመጡ …ደግሞ ተመልሰው በመነሳት እየደነሱ ..ውልቅልቃቸው እስኪወጣ ድረስ አስነኩት‹‹  …አቤት ዳንሱ !!ፕሮፌሽናል ነው ፡፡ልቤን ስልብ ነው ያደረገኝ…›አለች በዳንስ ችሎታው ተመስጣ፡፡ይበልጥ ሰውነቱ ላይ ተለጥፋ በተሸሻችው መጠን የጭኗ መብላላ  አደብ እየነሳት ነው…በትርምሱ መካከል በዳንስ ስልት በማሳበብ እጣቷን  ወደጭኗ በመስደድ   ይሉኝታ እስክታጣ ድረስ እያሻሸች  ነው..ደግነቱ ሁሉም በመጠጥ የደመቀ እና በመብራቱ ቦግ ብልጭ ብዥ ያለበት መሆኑ በጃት …
ከለሊቱ አምስት  ሰዓት አካባቢ ሲሆን ግን ተዳከሙ…

‹‹ቤት እንቀይር ….?››አለችው… ቤት መቀየር የፈለገችው ሙዳችውንም ጭምር መቀየር ስለፈለገች  ነው… ተስማማ ..ሂሳብ ዘግተው ወጡ…

‹‹ጭፈራ ቤት ሳይሆን ዝም ብለን የምንጠጣበት ቦታ ነው የምፈልገው…››

ወደላዳዋ ይዟት ሄደ …ቅድም ተጠርቶ የመጣው ጓዳኛውን ገቢና ቁጭ ብሎ ጫቱን ሲቀመቅም  አገኙት..ሁለቱም ተደጋግፈው ከኃላ ገቡ… ላዳዋ ተንቀሳቀሰች… በመስኮቱ አንጋጣ ሰማዮን ሰታይ ንስሯን ቀድሟት ለመብረር ሲያኮበኩብ አየችው…ሰካራሙ ጓደኛው እይታዋን ተከትሎ ወደውጭ በተመሳሳይ ሁኔታ  ካየ በኃላ‹‹ አይገርምም ይሄ አሞራ ቅድምም ስንመጣ ከፊት ለፊታችን ሲበር  ነበር….እርግጠኛ ነኝ የተለየ ከለር ስላለው አስተውዬው ነበር››አለ

‹‹አሞራ አይደለም..ንስር ነው››አረመችው 

‹‹እንዴ.. አዎ ንስር ነው ትክክል ..አንቺ ግን እንዴት አወቅሽ….?››

‹‹የእኔ ነው››በልበ ሙሉነት መለሰችለት፡፡

‹‹የእኔ ነው ስትይ….?››ያዝ ያዝ በሚያደርገው የስካር አንደበት ጠየቃት 

‹‹ወንድሜ ነው››

ሁለቱም ተንከትክተው ሳቁ

‹‹..ቀልደኛ ነሽ..ይበልጥ ስትጠጪ  ደግሞ ይብልጥ ቀልደኛ የመሆን ተስፋ አለሽ ማለት ነው››አላት፡፡

….አስረድቶ ማሰማንም ሆነ ተከራክሮ ማሸንፈ እንደማትችል ስለተረዳች‹‹ይሁንልህ›› አለችው ፡፡
መገናኛ አካባቢ ደርሱ… ብዙም ትርምስ የሌለበት እሷ የማታውቀው ሁለቱ ግን የሚያውቁት ሆቴል ይዘዋት ገቡ..ሹፌሩ ከላዳዋ አልወረደም…‹‹ጫቴን ብቅም ይሻለኝል›› ብሎ ቀረ …እነሱ ተያይዘው ገቡና የተገነጠለ እና ከታዳሚ የራቀ ወንበር ይዘው ተቀመጡ፡፡