ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
187K subscribers
281 photos
1 video
16 files
204 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ወግ
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
🎯መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
☎️• 0922788490

📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_አርባ_አምስት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ናንሲ ባህሩ ዳር ቁጭ ብላለች፡፡ መርቪን ላቭሴይ አጠገቧ ተቀምጧል፡፡
የባህሩ ውሃ በማዕበል እየተገፋ ይመጣል፣ ይመለሳል፡፡ ናንሲ ዓይኗን
ጨፍናለች፡ ሌሊት በደምብ አልተኛችም:: መርቪንና እሷ
እሷ ማታ መጋጨታቸው ትዝ አላትና ፈገግ አለች ከእሱ ጋር የምር ግንኙነት
አለመመስረቷ ደስ ብሏታል፡ ለወሲብ መቻኮሉ ጥሩ
አይደለም፡፡የመጣችበትን ዓላማ ከግብ ማድረስ አለባት፡፡

ሼዲያክ የዓሳ ማጥመጃ ፤መንደርና የባህር ዳር መዝናኛ ከተማ ናት፡፡
በባህሩ ዳርቻ ላይ የዓሳ
ማጥመጃ ጀልባዎች፣ መርከቦች፣ ሌሎች ሁለት
አይሮፕላኖችና እነሱ የመጡበት አይሮፕላን ይታያል፡፡ ብዙዎቹ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪዎች በባህሩ ዳርቻ ላይ ወዲያ ወዲህ ይላሉ፡፡

ሁለት የፖሊስ መኪኖች እየበረሩ መጥተው ጎማቸውን ሲጢጥ
አድርገው ሲቆሙ የአካባቢው ፀጥታ ታወከ፡፡ ከመኪኖቹም ውስጥ ሰባት
ስምንት ያህል ፖሊሶች እየዘለሉ ወጡ፡፡  በቀጥታ ወደ ተሳፋሪዎቹ
ማስተናገጃ ሲያመሩ የሆነ ሰው ሊይዙ የመጡ ይመስላል›› አለች ናንሲ፡
እሱም በመስማማት ራሱን ነቀነቀና ‹‹ማንን ይሆን?›› አለ፡፡
‹‹ምናልባትም ፍራንኪ ጎርዲኖን››
‹ሊሆን አይችልም እሱ እንደሆነ እንደታሰረ ነው፡፡››
አይሮፕላን ውስጥ ሲገቡ ሁለቱ ወደ ባህሩ ዳርቻ ሲያመሩ ሁለቱ ደግሞ
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ፖሊሶቹ ከመናኸሪያው ወጡና ሶስቱ መንደሩ ውስጥ መንጎራደድ ጀመሩ፡፡

ፖሊሶቹ የሆነ ሰው እንደሚፈልጉ ያስታውቅባቸዋል፡ አንዱ
የአይሮፕላኑ ሰራተኛ ከአይሮፕላኑ ሲወጣ አየችና ናንሲ ‹ፖሊሶቹ ማንን ነው የሚፈልጉት?›› ስትል ጠየቀች:

ሰውየው ምስጢር ለማውጣት እየተጠራጠረ ሄሪ ቫንዴርፖስት
የተባለውን ሰው ነው የሚፈልጉት፤ ስሙ የሀሰት ነው›› አለ፡፡

ናንሲ ግንባሯን ከሰከሰችና ይሄ ልጅ ከኦክሰንፎርድ ቤተሰብ ጋር ተቀምጦ የነበረው ነው፡ ልጁ የማርጋሬትን ልብ ሳይሰርቅ አልቀረም›› ስትል
ገመተች ናንሲ፡

መርቪን ‹‹ከአይሮፕላኑ ወጥቶ ሄዷል እንዴ? እኔ ከአይሮፕላኑ ሲወጣ
አላየሁትም›› አለ፡፡

‹‹እኔም አላስተዋልኩም›› አለች ናንሲ፡

‹‹ልጁ አጭበርባሪ ይመስላል››

‹‹እውነት?›› አለች ናንሲ፡ እሷ ልጁ ከጥሩ ቤተሰብ የተገኘ ነበር የመሰላት፡ ‹‹ጥሩ ባህሪ አይቼበታለሁ: ማርጋሬት ከልጁ ጋር ፍቅር ሳይዛት አልቀረችም፡፡ ፖሊስ እንደሚፈልገው ስታውቅ ታዝናለች›› አለች

‹‹ወላጆቿ ፖሊስ እጅ መውደቁ ደስ ሳያሰኛቸው አይቀርም›› አለ
መርቪን፡፡ናንሲ ስለወላጆቿ ግድ የላትም፡ በአይሮፕላኑ መብል ክፍል ውስጥ
ሎርድ ኦክሰንፎርድ ያሳዩት የነበረው ጋጠወጥ ባህሪ መርቪንና ናንሲ
ያስታውሳሉ፡ ለእንደዚህ አይነት ሰው ውርደት ሲያንሰው ነው ናንሲ ከእንደዚህ አይነት ወመኔ ጋር ማርጋሬት ፍቅር ስለያዛት አዘነችላት፡

መርቪንም ቀጠለና ‹‹እኔ ስለሌላ ሰው ማውራት አልፈልግም›› አለ፡
ናንሲ ጆሮዋን ቀሰረች፡
መርቪን ቀጠለና ‹‹የተገናኘነው ከጥቂት ሰዓታት በፊት ስለሆነ በደምብ ላውቅሽ እፈልጋለሁ፡›› ናንሲም እርግጠኛ መሆን አትችልም አንተ ደደብ አለች በሆዷ
ሆኖም ይህን ማለቱ አስደስቷታል፡ ምንም መልስ አልሰጠችውም፡፡

‹‹ብፊት አንቺን ኒውዮርክ አድርሼ ወደ ማንቼስተር መመለስ ነበር የማስበው፡፡ አሁን ግን አላደርገውም›› አላት፡

ናንሲ ፈገግ አለች ይህን እንዲል ነበር ስትጠብቅ የነበረው:፡ እጇን ሰደደችና እጁን ያዝ አደረገች፡፡ ‹‹ይህን ስላልክ ደስ ብሎኛል›› አለችው፡

‹‹ደስ ብሎሻል? ችግሩ ከዚህ በኋላ አትላንቲክን ማቋረጡ የሚቻል አይሆንም፡፡ የጦር መርከቦች ብቻ ናቸው ይህን ማድረግ የሚችሉት፡››ናንሲ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች፡
አሁን ከተለያየን ምናልባትም የምንገናኘው ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው፡፡።
እኔ ግን ላጣሽ አልፈልግም›› አለ መርቪን፡፡

‹‹እኔም እንደዚያው›› አለች ናንሲ፡፡

‹‹ከእኔ ጋር ኢንግላንድ ትሄጃለሽ?›› ሲል ጠየቃት፡፡
ናንሲ ፈገግታዋ ከፊቷ ላይ ጠፋ፡፡ ‹‹ምን አልክ?››
‹‹ከእኔ ጋር ወደ ኢንግላንድ እንመለስ፡፡ ሆቴል ውስጥ ትቆያለሽ ወይም ቤት ትገዣለሽ ወይም አፓርትማ ትከራያለሽ››

ናንሲ ያቀረበላት ሃሳብ በጣም አስቆጣት፡፡ ጥርሷን በንዴት አፋጨች፡፡
‹‹አብደሃል እንዴ?›› አለችው፡፡ መርቪንን ፊት ለፊት ማየት ጠልታ
ፊቷን አዞረች፡፡ በእጅጉ አዘነችበት፡፡
መርቪን አባባሏ አስደነገጠው ግራ አጋባው፡፡ ‹‹ምነው?›› ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹እኔ አሜሪካ ውስጥ የራሴ ኑሮ፣ ቤት፣ ሁለት ልጆችና በሚሊዮንዐየሚቆጠር ዶላር ገቢ የሚያስገኝ ፋብሪካ አለኝ፡፡ አንተ እንዴት ይህን ሁሉ እርግፍ አድርጌ ትቼ በማንቼስተር ሆቴል እንድቀመጥ ትጠይቀኛለህ?››

‹‹ይህን ካልፈለግሽ ከእኔ ጋር ተጠቃለይ››

‹‹እኔ እኮ ባገሬ የተከበርኩ ሴት ነኝ እንደ ቅምጥ ልኖር አልችልም፡››

‹‹ይኸውልሽ ልንጋባ እንችላለን፤ ይህን አረጋግጥልሻለሁ፧ እኔ አሁን
በዚህ ደቂቃ ውስጥ እንድትወስኚ አይደለም የጠየቅሁሽ››

‹‹ይህ አይደለም ዋናው ነጥብ መርቪን›› አለች ‹‹እኔን የገረመኝ ሁሉን
ጣጥለሽ ተከትለሽኝ ኢንግላንድ ነይ ያልከኝ ነው፡፡››
‹‹ታዲያ እንዴት ነው አንድ ላይ ልንኖር የምንችለው?››
‹‹ታዲያ ጥያቄውን መጠየቅ ሲገባህ ወደ መልሱ ሄድክ››
‹‹አንድ መልስ ስላለ ብቻ ነው ይህን ያልኩት››
‹‹ሶስት መልሶች ናቸው ያሉት፤ አንተ እንዳልከው አንተን ተከትዬ ወደ
ኢንግላንድ መመለስ ወይም አንተ ወደ አሜሪካ መጥተህ ከእኔ ጋር መኖር
ወይም ሌላ ቦታ ለምሳሌ ቤርሙዳ እንኖራለን›› አለች፡፡
በአባባሏ አልተደሰተም፡፡ ‹‹አገሬ ጦርነት ላይ ነች፤ እኔም የድርሻዬን ማበርከት አለብኝ፤ ጦርነት ውስጥ ገብቼ ለመዋጋት እድሜዬ ቢያልፍም ለአየር ኃይሉ የአይሮፕላን ሞተሮች ሰርቼ አቀርባለሁ፡፡ በእዚህ መስክ ከእኔ የተሻለ እውቀት ያለው የለም፡፡ አገሬ በጣም ትፈልገኛለች››

አሁን ያላት ነገሩን አባባሰው፡ ‹‹ለምንድነው የእኔ አገር እኔን
እንደማትፈልገኝ አድርገህ የምታስበው?›› አለች እኔ የወታደር ጫማ አመርታለሁ፡፡ አሜሪካ ጦርነቱ ውስጥ ከገባች ብዙ የወታደሮች ጫማ
ያስፈልጋታል››
‹‹እኔ ማንቼስተር ውስጥ ፋብሪካ አለኝ››
‹‹እኔ ደግሞ ቦስተን ውስጥ ካንተ የበለጠ ፋብሪካ አለኝ››
‹‹ታዲያ ሴት እንደ ወንድ እኮ አይደለችም››
‹ሴት ከወንድ እንዴት ታንሳለች አንተ ጅል!›› ብላ ጮኸችበት፡፡
ጅል› ማለቷ ወዲያው ጸጸታት፡፡ ፊቱ ቅጭም ሲል ታያት፡፡ በጣም
እንዳበሳጨችው ገባት፡፡ ከወንበሩ ተነሳ፡፡ እንደከፋው እንዳይሄድ አንድ ነገር
ማለት ብትፈልግም ትክክለኛው ቃል አልመጣላት አለ፡፡ እሱም አፍታም ሳይቆይ ጥሏት ሄደ፡፡

ምን ማለቴ ነው? አለች ምርር ብሏት፡ አባባሉ  ቢያበሳጭም ስላስከፋችው ደግሞ ተናደደች፡፡ በዚህ ሁኔታ እንዲርቃት አልፈለገችም ወዳዋለች፡ ወንዶችን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል
እያደር ገብቷታል፡፡ ወንዶች ከወንዶች በኩል
የሚመጣውን ጠብ ለምደውታል፡ ከሴቶች የሚመጣውን ግን መቀበል ይከብዳቸዋል፡፡ በንግድ
ስራዋ ላይ ከሰራተኞች የሚመጣ ችግር ሲገጥማት ድምጿን አለስልሳና
አለዝባ ትመልሳቸዋለች እንጂ አታካሮ አትገጥምም፡፡ አሁን ግን ያ ባህሪዋ ሸሽቷት በአስር ዓመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ልቧን የወሰደውን ሰው
አበሳጭታ አባረረችው፡
📕ታምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_አርባ_አምስት

#ተከታታይ ልቦለድ

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹ግን ምን አይነት ዳቢሎስ ነሽ..?››ሙትት ባለ ድምጽ

‹‹ዳቢሎስ እንኳን አይደለሁም…. ምን አልባት የዳቢሎስ ልጅ ልሆን እችላለሁ…ግን የምትወዳትን ልጅ ላድንልህ እኮ ነው እያልኩህ ያለሁት .. ..?እንደዚህ አይነት በጎ ተግባር  ዳቢሎስ ያሰኛል እንዴ..?››

‹‹አዎ ዳቢሎስ ፍቅር አያውቅም..ፍቅር የማያውቅ ደግሞ ምንም ነገር በነፃ መስጠት አይችልበትም፤ለሰጠሸ ጥሩ የሚመስል ነገር ሁሉ ተመጣጣኝ የሆነ መከራና ስቃይ ያስከፍሉሻል…››

‹‹አልገባኝም..?››

‹‹ለምሳሌ …ያለፋሽበትን ገንዘብ ተመኝተሸ ስጠኝ ብትይው በደስታ ነው የሚሰጥሽ፤የገንዘብን ባለቤት ግደይና ነጥቀሺው ውስጂ ብሎ መንገድን እና ብልሀቱን ያሳይሻል…ከዛ ትገድይና ገንዘብን ታገኚያለሽ ሀብታም እና በፀፀት የሚሰቃይ ሰው ትሆኚያለሽ፡፡አንቺም ፍቅረኛህን ላድንልህ..እና ልንጠቅህ እያልሺኝ ነው…፡፡ያው እኮ ነው በስጋ ከመሞት ታድኛታለሽ ከዛ ፍቅርን በመንጠቅ በመንፈስ ትገያታለሽ…እኔንም እንደዛው፤ታዲያ አንቺ ዳቢሎስ ካልሆንሽ ማን ይሆናል....?››አላት ምርር ባለ የመጠየፍ ንግግር፡

‹‹እሺ እንግዲያው ይቅርብህ…ሁለተኛ አረብሽህም፤ደህና ሁን››ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳችና እንደ አመጣጧ ሳሎኑን ሰንጥቃ  በርፍን ከፍታ ወጣች እና መልሳ ዘግታ መንገዶን ቀጠለች…የግቢው አማካይ ስፍራ ስትደርስ   ነበር የበር መከፈት እና ‹‹ማን ነበር ስምሽ..?››የሚል  ከሙታን  መንፈስ የወጣ የሚመስል ድምጽ  ከጀርባዋ የተሰማው

እርምጃዋን ገታችና ቀኝ ኋላ ዞራ ‹‹ሶፊያ››ስትል መለሰችለት
‹‹ከቻልሽ አድርጊው..አድኚልኝ ፤ተስማም..ቼ…ያ….ለሁ››አላትና ከእሷ ምንም አይነት መልስ ሳይጠብቅ ፊቱን መልሶ ወደውስጥ በመግባት  በራፉን በመዝጋት ከእይታዋ ተሰወረ ..

‹‹እውነትም ዳቢሎስ ነገር ነኝ እንዴ..?….ምን እያረግኩ ነው…...?››ስትል አሰበች፡፡ቅድም እዚህ እሱ ጋር ስትመጣ ይሄንን ለማድረግ አልነበረም…ዝም ብላ ፍቅረኛው እደምታድንለት ልትነግረው እና በተስፋ ልታስፈነጥዘው ብቻ ነበር ፍላጎቷ…ያደረገችው ግን ተቃራኒውን ነው..በደስታ እና ሀዘን መካከል ነፍሱ ተንጠልጥላ እዲሰቃይ ፈረደችበት …

‹‹የእውነት ግን ያልኩትን አደርገዋለሁ…..?እሷን አድኜ እሱን ነጥቄያት አገባዋለሁ…..?.ማግባትስ በእውነት እኔ የምፈልገው ነገር ነው....?ወይስ በስቃዩ ለመደሰት…..?››ብላ ተደራራቢ ጥያቄ እራሷን ጠየቀች፡

ለማንኛውም ዛሬ ማታ ከንስሯ ጋር ለመብረር አቅዳለች….ለልጅቷ የሚሆን መድሀኒት የት እደሚገኝ ፍንጩን አግኝታለች ….ቦረና ባሌ መካከል መዳ ወላቡ አካባቢ ነው ለሰሚራ ፈውስ የሚሆነው መድሀኒት ሚገኘው….፡፡ 
የየትኛውም ሀገር አቨዬሽን  የማይቆጣጠረው በረራ ላይ ነች፡፡ግን ደህንነቱ ፍፅም የተረጋገጠ በረራ ….ከየትኛውም አይሮፕላን ጋር እጋጫለሁ ወይም አሞራና ወፎች ተላትመውብን አቅጣጫ ያስቀይሩናል…ነዳጅ አልቆ ወይም ሞተር ጠፍቶ ችግር ላይ እንወድቃለን  ብላ የማትሰጋበት ዥዋዝዌ የመጫወት ያህል ዘና የሚያደርግ በረራ…. ይሄን አይነት በረራ ሳታካሂድ ሶስት ወራት ስላለፋት ናፍቆት ነበር…
እየሄድ ያለው ከአዲስ አበባ ወደ መዳወላቡ ነው ፡፡መዳወላቡ የት እንደምትኝ መገመት ካቃታችሁ..ኬንያ ድንበር አካባቢ ብትሉት አካባውን ለመገመት ይቀላችኋል ፡፡እየበረሩን ያለነው ከንስሯ ጋር ነው…፡፡እሱ ክንፎች  መሀከል ዘና ብሎ ቁጭ ብላለች….
ከመሬት ያሉበትንን ከፍታ ገምታ ለመናገር አትችልም ..…ግን ትንሽ ግልፅ ለማድረግ  ምሳሌ ለመስጠት ያህል በዚህ ሰዓት ( ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ ነው) ሻሸመኔ ከተማ አካባቢ ደርሰዋል..እላይ ባሉበት ከፍታ ላይ ሆነው ከተማዋ ቁልቁል ስያዮት ከእሷ ቤት ጊቢ ብዙም ሰፍታ አይታያትም….ጭልጭል የሚሉ አንድ ቦታ የተሰበሰቡ መብራቶች ናቸው እንደምልክት የሚታዩት..
የሚፈልገበት ቦታ ላይ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነው የደረሱት…ከአውሬ ድምጽ እና ከጥቅጥቅ ጨለማ በተጨማሪ ብዙ ድምጽ ይሰማል..የደረቁ ቅጠሎች በንፋስ ተገፍተው ከዛፍ ሲወድቁ ይሰማል…..ካረፍበት ተራራ ወገብ ላይ እየፈለቀ ቁልቁል ወደ ታች እየተምዘገዘገ የሚወርድው  አረፋ ደፋቂ ፏፏቴ ድምጽ በጣም ይሰማል…የብዙ አውሬዎች መጣራራት እና ማስካካተ ድምጽ ይሰማል…. ….

‹‹የቱ ነው መድሀኒቱ….?››ጠየቀችው ንስሯን 
አንድ ከእሷ ቁመት ብዙም የማትበልጥ ቋጥኝ ላይ ዘና ብሎ ቁጭ በማለት ዝም አለት
የሚያስበውን ማወቅ ስለፈለገች..‹‹አዕመሮህን ክፈትልኝ…..….?››ስትል ጠየቀችው… ቁልፍ አደረገና ችላ አለት ..አንዳንዴ እንዲህ ግግም ብሎ ያስቸግራታል..

‹‹ምን እያሰብክ ነው… ….?ለሊቱን እዚሁ ጫካ ውስጥ ከአውሬ ጋር እናሳልፍ እንዴ…….?››ጠየቀችው
አዕምሮው ውስጥ ሰርስሯ እንዳትገባ እንደከረቸመባት በሹፈት መልክ አንገቱን አሸከረከረባትና ጀርባውን ሰጣት…በቃ ምንም ማድረግ አልችለችም …እስኪለቀው ድረስ መጠበቅ እንዳለባት ስለተረዳች እራሷን አረጋጋች..የሆነ የሚጠብቀው ወይም ለጊዜው ያልጣመው ነገር አለ ማለት ነው ስትል አሰበች..ተወችውና አካባቢውን በመቃኘት ዘና ማለት ጀመረች..
ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ ስታይ.. በአካባቢው በቅርብ ርቀት  ከሚገኙ የገጠር መንደሮች ጭል ጭል የሚሉትን  የኩራዝና የፍኖስ መብራቶችን  ..ወደ ላይ አንጋጣ የዘወትር አጫዋቾን ጨረቃን ስትመለከት ሰዓቱ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ሆነ …ንስሯ ፀባይ ላይ ምንም የተለወጠ ነገር የለም …አሁንም የነበረበት ቋጥኝ  ላይ በተመስጦ… አረ እንደውም የፀሎት በሚመስል ሁኔታ ያለእንቅስቃሴ አንገቱን ወደጨረቃዋ አንጋጦ ተደምሟል ..
የተቀመጠችበት የወደቀ የግንድ ጉማጅ ቂጧን ስላሳመመት ተነሳችና ቀስ እያለች እሾህ እንዳይቧጭራ እና አውሬ ጉድጋድ ውስጥ ተንሸራታ እንዳትገባ እየተጠነቀቀች ወደ ፏፏቴው ተራመደች… እንደደረሰች ሙሉ ልብሷን ፓንቷንም ሳታስቀር ውልቅልቅ አድርጋ ገባችበት… ፏፏቴው ከላይ ከአለቱ እየተላተመ መቶ ጭንቅላቷ ላይ ሲያርፍ ያለውን ኃይል መቋቋም አቅቶት ልትወድቅ ነበር.. ለጥቂት ነው በአቅራቢያዋ የጋጠማትን የግንድ ቅርንጫፍ ይዛ የተረፈችው‹‹..ደግሞ ውሀው እንዴት አባቱ ይሞቃል…….?››አለችና ድክም እስኪላት ድረስ ሰውነቷን እየተገለባበጠች አስመታችውና ወጥታ ልብሷን ለብሳ ወደ ንስሯ ተመለሰች፡፡
ስሩ እንደደረሰች  ከፊት ለፊቱ ቆማ በትኩረት አየችው…መልኩ ተለየባት… የሆነ አመድ ላይ የተንከባለለ አህያ መስሏል..እንዴ ምን ላይ ተንከባሎ ነው….?..እዚህ ሰውነት ላይ ነው እንዴ ተጭኜ የመጣሁት…….?ነው ወይስ እኔ ውሀ ውስጥ  ሳለው የሆነ ነገር ከሰማይ አመድ ነፋበት..….?አረ አመድ ብቻ አይደለምል  አንገቱንም መሸከም አቅቶታል…››ስለንስሷ ቴና ሀሳ ገብቷት መነብሰልሰል ጀመረች

‹‹ምን ሆንክ….?››
አዕምሮውን ቀስ እያለ ከፈተላት፡፡እሷም እንደምንም እራሷን ለማረጋጋት ሞከረችና ወደአዕምሮው ገባች…አዎ መድሀኒቷን አየቻት …እሷ ካለችበት በ5 ሜትር ያህል ርቀት ላይ ትገኛለች…የተለየች አይነት ልዩ ተክል ነች ….?የአንድ ሰው የማህል ጣትን ነው የምታክለው…የበቀለችው ሌላ ትልቅ የብሳና ዛፍ ላይ ጥገኛ ሆና ነው….የሆነ ሀመራዊ አይነት የተለየ ብርሀን  ትረጫለች…