ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
247K subscribers
290 photos
1 video
15 files
243 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
❇️ተአምረተ_ኬድሮነ

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሃምሳ_ሰባት

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ቫይብሬት ላይ የተደረገ ሞባይል ስልክ ላይ ሲደወል እንዳለ ንዝረት ተንቀጠቀጥችና አዕምሮዋን ከንስሯ ጋር አላቀቀች…
ሰላም ወደኬድሮን ተንደርድራ መጥታ እግሯ ሰር ድፍት አለችና‹‹በጣም አመሰግናለሁ….እግዜር ይስጥሽ››

‹‹ተነሺ ..እኔን አታመስግኚ…እሱ በጣም ስለለመነኝ ነው እንዲህ ያደረኩልሽ…››አለቻት

‹‹ኤርሚ እግዜር ይስጥልኝ….አንተንም በጣም  ነው የማመስግንህ..ምን አይነት ሰላም በውስጤ እንደተሰራጨ አትገምትም››አለች ወደመቀመጫዋ ተመልሳ በመቀመጥ

‹‹በነጋራችን ላይ በጣም ነው የሚያፈቅርሽ …እንደነገረኝ ከሆነ ከልጅነቱ ጀምሮ አንቺን ሲያፈቅርሽ ነው የኖረው….አንድም ቀን አንቺን ማፍቀር አቁሞ አያውቅም..ግን በኑሮ ደራጃ ስለምትለያዩ እሺ አትለኝም የሚል ፍራቻ በውስጡ ስላለ  ካንቺ ሲሸሽ ነው የኖረው››አፈረጠችለት

ባለማመን አንዴ ኬድሮንን አንዴ እሱን በማፈራረቅ ማየት ጀመረች..ኤርምያስም የተቀመጠበት ወንበር ላይ አንገቱን ወደወለሉ እንደደፋ ሚገባበት ጠፍቶታል እጆቹን እያፍተለተለ ነው…

‹‹አላውቅም ነበር…ኤርምያስ እኔን ማፍቀር….…?››

‹‹አዎ….ኤርምያስ አንቺን…››

‹‹እሺ ጥሩ ነው…አሁን ምን እናደርግ …ኤርሚ እርዳኝ ለእድር ሰዎች ንገራቸው…አባቴ ዛሬውኑ እንዲቀበር እፈልጋለሁ….››

‹‹አረ እሺ… ችግር የለውም… አሁኑኑ ነግሬያቸው ልምጣ …ስልካቸውን ስለማላውቅ እናቴ ጋር ሂጄ …››ብሎ ተነሳ 

ኬድሮን የተለየ ሀሳብ አመጣች‹‹ቆይ መጀመሪያ የሬሳ ሳጥን እንግዛና አባትሽኝ  በሳጥኑ ውስጥ በማድረግ  ማዘጋጀት አለመብን..አሁን ዕድርተኛው መጥተው ጓደኞቸው ተሰብስበው እንገንዝ ማለታቸው አይቀርም …እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሌላ ሀሚት ላይ ይጥልሻል…በህግም ሊያስጠረጥርሽ ይችላል››

‹‹ታዲያ ምን እናድርግ››አለች ግራ ገብቷትና ያለሳበችውን ነገር ስላነሳው ደንግጣ

‹‹ግድ የለም እኔና ኤርሚ ሳጥኑን ይዘን እንምጣ..ሁሉንም ከጨረስን  ብኃላ ለሌላው ሰው እንናገራለን….››

‹‹አስቸገርኮችሁ አይደል…?›› 

‹አረ አትጨነቂ …እኔን እንደእህትሽ ቁጠሪኝ… ኤሪሚም  ያው ያንቺው ነው..››አለችና ምትናገረው ጠፍቷት በመቁለጭለጨ ላይ ሳለች የደነዘዘውን ኤርሚያስን ይዛው ወጣች…

መኪናው ውስጥ ገብተን የሬሳ ሳጥን ወደሚሸጥበት ቦታ  እያመሩ ሳለ…

‹‹ምን አይነት ተአምር ነው ያደረግሽው……?.››ሲል ጠየቀት

‹‹ያው ላንተ ስል ነው››

‹‹በጣም ነው የማመሰግንሽ….ግን  እንደማፈቅራት ለእሷ ባትነግሪያት ጥሩ ነበር››

‹‹ለምን…?››

‹‹ያው አንደኛ መንገሩ ምንም ውጤት አይኖረውም ሁለተኛ እኔ እና አንቺ……››

‹‹አይ እኔና አንቺ የሚባል ነገር የለም…አኔን እርሳኝ…እኔ ሁለት ቀን ብቻ ነው የቀረኝ..››

‹‹ምን ለመሆን…?››

‹‹ለመብረር…››

‹‹እንዴ የት አሜሪካ ወይስ አውሮፓ……?››

‹‹በለው ከሁለት አንዱ….ስለዚህ እሷኑ ጠበቅ አድርግ.ደግሞ በትክክል ይሳካልሀል….

እንደምታፈቅራት ስነግራት የልቧን ምት በደንብ ታዝቤያለሁ. ዋናው ከዚህ ሀዘን እስክትወጣ ከስሯ አትለይ …….

‹‹እንዴ ወዴት ነው የምለየው….ከእሷ የሚበልጥ ምን ሌላ ጉዳይ ይኖረኛል››

‹‹ምንም ››

‹‹አንቺ ልትበሪ መሆንሽን መስማቴ  ግን ቅር አሰኝቶኛል››

‹‹እኔን እርሳኝ አልኩህ እኮ››

‹‹እኮ እንዴት አድርጌ ልርሳሽ…?››
/////

የሰላምን አባት የቀብር ሁኔታ ካመቻቸችና ከተጠናቀቀ በኃላ ሁለቱንም አንድ ላይ ከለቀስተኞች ጋር ጥላቸው እናም በውስጧ ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብታቸው መልካሙን ሁሉ እየተመኘችላቸው ወደቤቷ ነው የተመለሰችው…ድክምክም ብሏት ነበር…ግቢውን አስከፍታ ስትገባ ግን ድካሟን ሁሉ ከላዮ የሚያበንላት አስደሳች ሁኔታ ነው የጠበቃት…

ግቢው መሀል ላይ ባለች ክፍት ቦታ ጠራጴዛ እና ወንበር ወጥቷል፤…ጠረጵዛው በልዩ ሌዩ ምግቦችና መጠጦች ተሞልቷል …ከዛ አልፎ ዙሪያው በየጥጋጥጉና በየቦታው የዛፍ ቅርንጫፎች ላይም ሳይቀር የተለያዩ የምግብና የፍራፍሬ አይነቶች ተቀምጠዋል…የተለያዩ ጥራጥሬዋች በየቦታው ተበትኗል….በጊቤዋ ውስጥ ያሉ እንስሳት ብቻ ሳይሆኑ እንግዳ የሆኑ ወፎች ሳይቀሩ ግቢውን ወረውት የተበተነላቸውን ጥራጥሬ በደስታ ይለቅማሉ… ጦጣና ዝንጆሮዎቾም ሙዙን እየላጡ ይውጣሉ …የማይፈነጭ እና የማያስካካ ፍጥረት በግቢው አይታይም..  የሆነ እንስሳት አግብቶ ሌሎቹ ሠርግ ተጠርተው አሼሼ ገዳሜ ላይ ያሉ ነው የሚመስለው….ሌላው ይቅር እያንዳንዱ  ተክል   ስሩ ተኮትኩቶና አፈር ታቅፎ ውሃ ጠግቦ እስኪተፋ ድረስ ጠጥቶ ይታያል….በቃ በግቢው አንድም ያልተደሰተ ፍጥረት አልነበረም..ይሄ ሁሉ በፕሮፌሰሩ የተደረገው እነሱ በተደሰቱበት መጠን እኔ እንደምደሰት በደንብ ስለሚያውቁ ነው፡፡

‹‹አትመጪም…  ይሆን ብዬ በስጋት ላይ ነበርኩ …እንኳን በሰላም መጣሽ››አሏት ከእድሜ ጫና የተነሳ ያጎበደድት ፕሮፌሰር…

‹‹አይ እፈልግሻለሁ ብለውኝ የለ..…….?በዛ ላይ  አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረኝ …ማታ ወደ እናቴ  እሄዳለሁ.አዎ ነገ ሙሉውን ቀን ከእሷዋ ጋር ነው ማሳለፍ የምትፈልገው………››

‹‹ጥሩ ጥሩ..ነይ እዚህ ጋር ቁጭ በይ›› ብለው ምግብ በሞላበት ጠረጴዛ ዙርያ ከበው ከተቀመጡ ወንበሮች ውስጥ አንድን ሳቡላት… አመስግና ተቀመጠች፡፡

የእጅ ውሀ አመጡላት …‹‹አረ እራሴ እታጠባለሁ›› ብላ በራሷ ተጣበች… ሳሀን ስባ ምንም እንኳን የምግብ ፍላጎት ባይኖራትም እሷቸውን ለማስደሰት ስትል ብቻ መብላት ጀመረች… እሳቸውም ከፊት ለፊቷ ተቀምጠው በስስት እያዮት መመገብ ጀመሩ…

‹‹የሚጠጣ ምን ልቅዳልሽ…….?››

‹‹ውሀ ››

‹‹ወይን ወይም ሌላ ነገር አይሻልሽም…….?››ካለወትሮዋ ዉሀ ማለቷ አስገርሞታል

‹‹አይ ውሀ ነው የምፈልገው….››

‹‹እሺ ካልሽ ››ብለው ውሀ ቀዱላት፡፡

‹‹ጋሼ በዚህ ምድር በኖርኩበት ዓመት የተረዳሁት ነገር ቢኖር  ምድር መተኪያ የሌላቸው ሁለት ነገሮች መታዳሏን ነው ….አዎ  እናትና ውሃ የዚህ ዓለም ሁለት ልዩዎች  ናቸው…››

‹‹እንዴት ልጄ..…….?እንዴት እንደዛ ተረዳሽ…?››

‹‹እናታችን መጀመሪያ ገነታችን ነች..ከተፈጠርንበት ቀን አንስቶ እስክንወለድበት ቀን ድረስ በእናታችን መሀፀን ውስጥ ገነታዊ ኑሮ ነበር የምነኖረው… ያ ስፍራ ሁሉ ነገር በፍፅምና  እንከን አልባ  ስፍራ  ነበር..ሁላችንም ከዛ ያለፍላጎታችን ተገፍትረን ስንወጣ(ስንወለድ) እሪ ብለን ለቅሶችንን የምንለቀው  ምን እንዳጣን በደመነፍስ ስለሚገባን ነው…አዳም እና ሄዋን በሰሩት ሀጥያት ከገነት ወደምድር ተባረሩ የሚባለው ሌላ አይደለም ከእናት መህፀን ወደምድር ተገፍትሮ መውጣት ነው…ከዛ በኋላም ቢሆን  እናት ምን ጊዜም እናት እንደሆነች ነው ምትቀጥለው… እንዳላረጀን እና እንዳላበቃልን የሚሰማን እናታችን በሰላሳ አመታችንም እንደ ህፃን ስትቆጣን ስናይ ነው..ጭንቅላታችንን ስትዳብስልን…ተይ አንቺ ልጅ ብርድ ይመታሻል ስትለን  ነው፡፡