ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
187K subscribers
281 photos
1 video
16 files
203 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ወግ
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
🎯መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
☎️• 0922788490

📩@Eyos18
Download Telegram
📕ታምራተ_ኬድሮን

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹ከተለየኋት በኋላ ስለእሷ ማሰብ ላቆም አልቻልኩም ነበር..እንዴት አድርጌ ከዚህ ሀዘን ላወጣት  እችላለሁ….?እንዴት አድርጌ ላግዛት እችላለሁ….? የግድ አባቷ እስኪመጡ መጠበቅ የለብኝም..አባቷ ስል አባቷ ብቻ አይደሉም እናቷም ጭምር.. ጓደኛዋም ጭምር እንደሆኑ መላ ሰፈሩ ያውቃል..ብቻቸውን ነው ያሳደጎት….እድሜ ልኳን ከአባቷ ተለይታ ኖራ አታውቅም..ይሄንን ማንም ያውቃል…ዩኒቨርሲቲ ጎንደር ደርሷት መለያየት ግድ በሆነበት ጊዜ እንኳን  እሷ ከአንተ ተለይቼ መሄድ ስለማልችል ትቼዋለሁ ስትል..አባቷም እውነትሽን ነው አንቺ ትምህርትሽን ከምትተይ እኔ አብሬሽ ሄዳለሁ በማለት…ስራቸውን ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር በመቀየር አብረዋት ዘምተዋል…ይህ ሀገር የሚያውቀው ሀቅ ነው……..አሁን አባቷ ለጉዳይ ወደውጭ ሀገር እንደሄዱ ነግራኛለች….ስጨነቅ አንግቼ  በማግስቱ ያለውን ቀንም በተመሳሳይ መሸበር አሳለፍኩ

…..ግን……?››

ድንገት ንግሩን አቋረጥኩትና ‹‹አልደከመህም መኝታ ቤት ሄደን አልጋ ላይ አረፍ ብለን የቀረውን ትጨርስልኝ….?››አለችው  

‹‹በቀላሉ  ያልቃል ብለሽ ነው….?››

‹‹እንሞክረው….?››

ደስ እንዳሽ ብሎ ብርጭቆውን ይዞ ተነሳ.. ቀድማው ወደመኝታ ቤት አመራች፤ እየተንጋዳገደ ከኃላ ተከተላት….የእሱና የሰላም የፍቅር ታሪክ ብቻ ሳይሆን የእሷ እና የእሱንም መጨረሻ እንዴት እንደሚጠናቃቅ ማወቅ አጓጓት
///

መኝታ ቤት ገብተው አልጋ ላይ ጎን ለጎን ትራስ በመደገፍ ጋደም ብለው ከተመቻቹ በኃላ ወሬውን ካቆሙበት ቀጠሉ፡፡

‹‹እና እንደነገርኩሽ በእሷ ጉዳይ ስጨነቅ አድሬ ስጨነቅ ውዬ …ከእንደገና መልሼ መጥፎ ለሊት ካሳለፍኩ በኃ
ኋላ ዛሬ ጥዋት ስልኬ ጠራ …አነሳሁት‹‹ሄሎ››

‹‹ሄሎ››

‹‹ማን ልበል….?››ስል ጠየቅኩ፡፡

‹‹ትናንት ማታ ያደረስከኝ ልጅ ነኝ..ቁጥርህን ከተውክልኝ ካርድ ላይ አግኝቼው  ነው››አለቺኝ.…

እንደዛ በፍጥነት ትደውልልኛለች ብዬ አላሳብኩም ነበር..ትናንትና ስልክ ቁጥሬን ፅፌ ትቼላት ሰወጣ ለምን አልባቱ ብዬ ነበር..ምን አልባት በዛ ስካር ውስጥ  ሆና የሰጠኋትን ወረቀት ቀዳዳም ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ልትጥለው ትችላላች የሚልም ግምት ነበርኝ..እና ደወለችልኝ ..ለዛውም ገና በጥዋት4 ሰዓት…እንደደረስኩ መኪናዬን ዳር አስይዤ  አቆምኩና ወርጄ የውጩን በራፍ እንኳኳሁ…ከፈተችልኝ….

‹‹እሺ ደህና ነሽ ግን….?››
ጥያቄዬን ችላ ብላ ‹‹አሁን እየጠበቅኩህ ነው ና››አለችኝ 

‹‹አቤት….?››አልኳት ይበልጥ እንድታብራራልኝ ፈልጌ 
እሷ እቴ ስልኩን  ጆሮዬ ላይ ጠረቀመችው

‹‹ይህቺ ልጅ ጤናም የላትም እንዴ . ….?.››አልኩና የላዳዬን ሞተር በማስነሳት ወደቤቷ ተፈተለኩ..እንዴ እሷ ና ብላኝ እንዴት እዘገያለሁ….?፡፡ 

‹‹ታዲያ እቤት ስትሄድ አገኘሀት….?››ኬድሮን ነች የጠየቀችው በእጇ ከያዘችው ብርጭቆ መጠጥ አንዴ እየተጎነጨች
‹‹አዎ ..እንደደረስኩ መኪናዋን ዳር አስይዤ  አቆምኩና ወርጄ የውጩን በራፍ እንኳኳው…እራሷ ከፈተችልኝ….ጉስቁልናዋ እንዳለ ነበር..ስልችት ብሏታል…የሆነ ልቧን ስብብርብረ ያደረገው ነገር እንዳለ እርግጠኛ ነኝ..እንደውም የፍቅር ነገር ይመስለኛል….››

‹‹እሺ ማን ነበረ ስምህ….?›› አለችኝ ግድ የለሽ እና አናዳጅ በሆነ የድምጽ ቅላፄ….አይገርምሽም ዕድሜሽን ሙሉ ያመለክሽው ልጅ… ስንት ቀን እና ሌት የናፈቃሽው እና በትዝታው የተሰቃየሽለት ልጅ -ማን ነበር ስምሽ ሲልሽ…..….?

በውስጥሽ  የሚፈጥረው ስሜት ግማሽ ህልውናሽ  የመደምሰስ አይነት ነው …..እመኚኝ በጣም ነው የሚያመው …እሷ ግን ለእኔ የስሜት መጎዳት ቁብ ሳይኖራት፤.መልሴንም ለመስማት ትግስት አጥታ ወደትዕዛዞ ተሸጋገረች

‹‹ካላስቸገርኩህ የሆነ ቦታ ትወስደኛለህ…….?››

‹‹የፈለግሺው ባታ …ተዘጋጂና ነይ መኪና ውስጥ እጠብቅሻለሁ››ብዬ ወደላዳዬ ፊቴን አዞርኩ‹‹አይ ላዳህን ወደግቢው አስገባት እና አቁማት.. በእኔ መኪና ነው የምንሄደው፤ ከከተማ ወጣ ማለት ነው የፈለግኩት…..››አለቺኝ፡
ግራ ግብት እንዳለኝ ወደኃላዬ ተመለስኩና ላዳዬ ውስጥ ስገባ እሷ ደግሞ የውጩን በራፍ ከፈተችልኝ…ወደ ጊቢ ውሰጥ አስገባኋትና ሚጢጢ ላዳዬን  ግዙፍ የእሷ ላንድኩሩዘር መኪና ጎን አቆምኳትና ሞተሩን አጥፍቼ ወጣሁ… በሩን ዘግቼ ቆምኩ..
‹‹እሷ ወደሳሎን ተመልሳ እየገባች ነበር…ደግሞ የሰውነቷ ቅርፅ ከቁመቷ ጋር ያለው ምጣኔ እንዴት አባቱ ያምር ነበር መሰለሽ…..5 ደቂቃ ሳትቆይ ተመልሳ ወጣችና የሳሎኑን በራፍ መቆለፍ ጀመረች ….በእጇ ካንጠለጠለችው ቦርሳ በስተቀር ምንም  የያዘችውም ሆነ የቀየረችው ነገር አልነበረም… እንደነበረችው ነው ተመልሳ የመጣችው..ዝንጥንጥ ብላ የምትመጣ መስሎኝ ነበር..ግን በለበሰችው ቱታ ሱሪ እና ቲሸረት ነው አሁንም ያለችው..ስሬ እንደደረሰች ከቦርሳዋ ውስጥ ቁልፍ አወጣችና ወረወረችልኝ …በአየር ላይ ቀለብኩና ወደመኪናዋ ተንቀሳቀስኩ…..ሞተሩን እስነስቼ ከግቢሁ ከወጣሁ በኋላ አቁሜ ጠበቅኳት… የውጩውን በራፍ  በመዝጋት እና በመቆለፍ መጣችና ጋቢና  በመግባት ከጎኔ ትቀመጣለች ብዬ ስጠብቅ  የኃላውን በራፍ ከፍታ ገባች……››

‹‹ምነው እዚህ አይሻልሽም….?›› ልላት ነበር ..ግን አንደበቴን ማላቀቅ አልቻልኩም…በእስፖኪዬ ወደኃላ ተመለከትኳት ….ግማሽ እሷነቷ ሞቶ ግማሽ እሷነቷ ብቻ በህይወት እና በሞት መካከል ያለ ይመስላል..ልክ እኔ  ለመሞት ወደሀገሬ ልግባ ብዬ በወሰንኩበት በዛ ጭለማ ጊዜ የነበርኩበትን ሁኔታ አስታወሰችኝ ….

‹‹ሰላም ወዴት ነው የምንሄደው..….?››ብዬ ጠየቅኳት

‹‹አቤት›› አለችኝ እንደመባነን ብላ
‹‹ወዴት ልንዳው ነው ያልኩሽ….?››

‹‹ወደ ፈለከው…. ግን ከከተማ ውጭ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይሁን እንጂ ወደየትም ይሁን …..››
‹‹እሺ››
‹‹ግን ስሜን መቼ ነው የነገርኩህ….….?ሰላም ብለህ የጠራህኝ መሰለኝ….?››

‹‹ነግረሺኝ አይደለም…››

‹‹እና እንዴት  አወቅከው…..….?››

‹‹አውቄውም አይደለም…ሰላም ማለት ለእድሜ ልኬ ያፈቀርኳት..አሁንም ድረስ የማፈቅራት ከህጻንነቴ ጀምሮ የማውቃት ፤መቼም ልረሳት የማልችላት  ልጅ ስም ነው…እና ያው ፍቅሯ ጅል አደርርጎኛል መሰለኝ ብዙ ሴቶችን ሰላም ብዬ መጥራት እወዳለሁ…››አልኳት….ሽሙጤ ሳይገባት….ፈገግ አለችና‹‹ ይገርማል እንደአጋጣሚ የእኔም ስም ሰላም ነው››አለችኝ 

‹‹አውቃለሁ››

‹‹ማለት›….?›››መልሶ  ግር ብሏት

‹‹በመልክም በጣም ትመሳሰላላችሁ ልልሽ ፈልጌ ነው››
ዝም አለች….በጦር ኃይሎች አድርገን በ18 ማዞሪያ ታጥፈን በአንቦ መስመር አሸዋ ሜዳን አቆርጠን ወደቡራዬ ተጓዝን…እሷ እውነትም እንዳለችው ወደየትም ብነዳው ግድ ያላት አትመስልም ነበር..አይኗን በመኪናው መስታወት ወደውጭ ልካ በየመንገዱ ዳር ያለውን ትዕይንት ምታይ ትመስላለች ….ግን አታይም እሳቤዋም እይታዋም ከውስጧ ጋር እንደሆነ ያስታውቃል…ብራዩንም አለፍን ፣እኔም አላቆምኩም እሷም አቁም አላለችኝ…ግን ጊንጪ ልንደርስ ኪሎ ሜትሮች ሲቀረን  የሆነ ለጥ ያለ ሜዳ ጋር ስንደርስ…..‹‹ይቅርታ ማን ነበር ስምህ...….?››ስትል ከሳዕታት ዝምታ በኃላ አብሻቂ ጥያቄ ለሁለተኛ ጊዜ ጠየቀችኝ….