ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
215K subscribers
284 photos
1 video
16 files
220 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
‹‹በቃ አልቅሰሽ ቅበሪኝ….ከዛ በኃላ ሞተ የእያንዳንዱ ሰው ዕጣ ፋንታ መሆኑን አምነሽ ተቀበይና ወደ ህይወትሽ ተመለሺ…የራስሺኝ ሰው ፈልገሽ ኑሮሽን  ኑሪ….የእኔ በድን ታቅፈሽ እዚህ ቤት ባሳለፍሽው ስድስት ቀናት ውስጥ ስራ ላይ ብትሆኚ ኖሮ ሰንት ነፍስ  እንደምታታርፊ አስበሽዋል….… ?ስንት ያንቺን ክትትል የሚፈልጉ ህመምተኞችን እርግፍ አድረግሽ በመተውሽ  በያሉበት ምን ያህል እየተሰቃዩ እንደሆኑ ታውቂያለሽ….…?ያባትሽን መንፈስ ለዘላለም ለማስደሰት እውነታውን ተቀብለሽ  ፈገግ በይ ..በእኔ ስም የአዛውንቶችን ጤንነት ተንከባከቢ…እኔን እያሰብሽ ሞያሽን በጥንቃቄ እና በታማኝነት ስሪ..እያንዳንዱ ሰው ባንቺ እጅ ታከሞ በመዳኑ ተደስቶ ፈገግ ሲል  እኔም ባለሁበት  ፈገግ እንዳልኩ በማሰብ ውስጥሽ ሀሴት ታድርግ….›.

‹‹አዎ አባ እውነትህን ነው..እንዳልከው አደርጋለሁ››

‹‹ስለዚህ ተስማምተናል››

‹‹አዎ አባ ..ተስማምተናል››

‹‹በቃ ደህና ሁኚ ልሄድ ነው

‹‹አባ ከመሄድህ በፊት ››

‹‹እሺ ምንድነው…?››

‹‹ግን ገነት ነው ምትገባው አይደል…?››

‹‹አይ ልጄ..መች ሄድኩና አውቀዋለሁ ..ግን ምንም አይት ፍራቻ እየተሰማኝ አይደለም….እረፍትና እፎይታ ነው ዙሪያዬን የከበበኝ….የሚታየኝ  አንፀባራቂ ብርሀን እንጂ ፅልመት አይደለም….እና ፈጥኜ የመሄድ ፍላጎት ነው ያለኝ…ባከሽ ልጄ እንድዘገይ አታድርጊኝ..››

‹‹እሺ አባ ..አንድ የመጨረሻ ጥያቄ››

‹‹ምን ልጄ…?››

‹‹እማዬን ታገኛታለህ…?››

‹‹አዎ ልጄ ተስፍ አደርጋለሁ..በጣም መቸኮሌ አንድም ለዛ ይመስለኛል››

‹‹እንደምወዳትና በጣምም እንደናፈቀቺኝ ንገርልኝ››

‹‹እሺ ነገርልሻለሁ››
ደግሞ ቀኔ ደርሶ ወደእናንተ  ስመጣ ከእናንተ ጋር አብሬያችሁ መኖር ነው የምፈልገው››

‹‹እሺ ልጄ  እንዳልሽ…ደህና ሁኚልኝ…››

‹‹እሺ አባ ደህና ሁን››

     ይቀጥላል።

#ክፍል 57,,እንዲለቀቀ 👍(20) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
የሆነው…›› ስትል እራሷን ጠየቀች፡ለመሄጃ 3 ደቂቃ ቀረው….ንስሩ ከነበረበት ጉቶ ጥቅልል ብሎ በመንሸራተት  መሬት ላይ ተዘረረ..እናቷም እሷም በደቂቃ ውስጥ ስሩ ደረሱ..አገላበጡት…ከአይኖቹ ደም እየፈሰሰ ነው…‹‹ወይኔ እማ ቅጠሉ….. ቅጠሉ ነው..መርዝ ነው የተጠቀመው..እማ ምን እናድርግ…?››የማሰቢያ ጊዜ ሳያገኙ ግቢያችን በሰማያዊ ብርሀን ተሞላ…ቀና ስትል በሰማይ ላይ ዲስክ መሳይ መንኮራኩር ብርሀን እየረጨች ሰማየ ሰማያትን በመሰንጠቅ እነሱ  ወዳሉበት አቅጣጫ እየወረደች ነው….መጡ ማለት ነው…መጡ መሰለኝ….ወይኔ ንስሬ….

  ተፈፀመ

#በአዲስ ታሪክ እንመለሳል‼️ ከተመቻችሁ 👍👍

ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📍አንዳንዴ ምን ሆነሀል ስትባል የማትመልሰው ብዙ መሆን አለ። ለመናገር የማይመች ለመተው የማይቀል ብዙ ስሜት አለ ..ለአንተ የከበደ ለሌላው የቀለለ ነገር አለ ።

💡እንዴ ይሄ እኮ ቀላል ነው ይሄ እኮ አያስጨንቅም በሚባል ቃል የሚሸነፍ ለአንተ/አንቺ ግን የከበደ ስሜት አለ ።
ምን ሆነሀል ስትባል ምንም ብለክ የምታልፈው ውስጥህ ብቻ የምታንሸራሽረው እያዳመጥክ የምትታመምበት ። ከባድ ስሜት አለ ከባድ.......

✔️ምናልባት የምትፈልገው ስፍራ ላይ አልተቀመጥክ ወይንም የምትመኘውን ነገር አላገኘህ ይሆናል፣ ቢሆንም ተስፋ አትቁረጥ ፣ ተስፋ የመኖር ምክንያት ነውና፣

እየኖርን ነው አይደል? በሰው ሳይሆን በፈጣሪ!!
ትላንት የኖርነው ህይወት በነበር ይተካል፣
ሰዎችም ኖረው ነበሩ ይባላሉ፣
ፈጣሪን ግን ነበር ብለን አናወራውም ፤ ያለና የሚኖር ፣ በዛሬያችን ,በነጋችን አልፎም በዘላለም ውስጥ ኗሪ ነው ።
" የትላንት ነበሮቻችን በእሱ መኖር ተረስተዋል"

እናም  ወዳጄ

✔️አትድከም ፣ አትዘን ። ማንያውቃል ሸክምህ ህመምህ ሁሉ ተራግፎ ሌላ ሰው ሆነህ ትነሳ ይሆናል። ያለን ፈጣሪ እንኳን በአንድ ሙሉ ቀንና ሌሊት፣ በቅጽበት ጊዜ ዉስጥም ብዙ ተዓምር ይሠራል።

💡ንፋስ የማይወዘዉዘው ዛፍ የለም። ችግር ፣ ፈተና ፣ ሀሳብ ወስዶ የማይመልሰው ሰዉም የለም። እንዲህም ሆኖ የማይወድቅ ዛፍ አለ። በፈተና የሚፀና የሚበረታ ሰዉም አለ። ዐሳብህ ጉልበትህ ሥሮችህ ታክቶዋቸው በደከሙ ጊዜ ልብህ ብቻ ፈጣሪን ይዞ ይበርታ።


🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ግዜ 🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
💚ህይወት ከእናንተ ትጠብቃለች!

ዶ/ር ቪክቶር ፍራንክል (Dr. Victor Frankl) ይባላል። በ20ኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ኦስትሪያዊ ታዋቂ ኒዎሮሎጂስት (Neurologist) እና ሳይኮሎጂስት (psychologist) ነው። በህይወትና የህይወትን ትርጉም በማግኘት ዙሪያ በሚያነሳቸው ሀሳቦችና አስተምህሮዎች ይታወቃል። በአንድ ወቅትም እንዲህ ብሎ ነበር፦ "ለምን እንደሚኖሩ ለማያውቁና ከህይወት ምንም ለማይጠብቁ ሰዎች ህይወት በእራሷ ከእነርሱ ሌላ ነገር እነደምትጠብ ማሳወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።" የህይወት አላማችሁን ፍለጋ ብዙ ዋጋ ብትከፍሉም ላታገኙት ትችላላችሁ፣ ለዘመናት ስታደርጉት የነበራችሁት ነገር የሆነ ጊዜ ስትነቁ ትርጉም አልባ ሊሆንባችሁ ይችላል፣ ከዚህም በላይ ከእራሳችሁና ከህይወታችሁ ምንም የተሻለ እሴትን መጨመር የሚችል ነገር መጠበቅ ታቆሙ ይሆናል። ነገር ግን ይሔንን አስተውሉ። እናንተ በሰውኛ አዕምሮ አስባችሁ፣ አውጥታችሁ አውርዳችሁ ደክሟችሁና ሰልችታችሁ ያላገኛችሁት የህይወት ትርጉም ዝም ብላችሁ ስትኖሩና እያንዳንዱን ሃላፊነታችሁን ስትወጡ በሒደት ወደ እናንተ ይመጣል። እናንተ የምትኖሩት ህይወት አለ፣ ህይወት ደግሞ እንድትኖሯት የምትፈልግበት መንገድ አለ።

አዎ! ህይወት ከእናንተ ትጠብቃለች! እናንተ በህይወታችሁ ውስጥ ትርጉምን እንደምትፈለጉ ሁሉ ህይወታችሁም ከእናንተ አንድ የተለየና የእናንተ መገለጫ የሆነ ልዩ ነገር ትጠብቃለች። የህይወት አላማን ለማግኘት መውጣት መውረድ፣ እራስን ማታገልና ማስጨነቅ አያስፈልግም። አንዳንድ ክስተቶች እራሳቸው ፍሰት አላቸው፣ ሲጨመቁ ከሚያወጡት መልካም ነገር ይልቅ እንዲሁ በራሳቸው ሲፈሱና በኡደታቸው ሲጓዙ የሚያመጡት ውጤት ይበልጥ ትርጉም ይሰጣል። የትኛውም ትልቅ ነገር መነሻው ትንሽ ነው። "ህይወት ትርጉም አልሰጥ አለችኝ" ከማለት ይልቅ "ህይወት ከእኔ ምን ትጠብቃለች?" ብሎ መጠየቅ ብዙ የተደበቁ አቅማችንን እንድናወጣ ያግዘናል። በየትኛውም ዘርፍ ሊሆን ይችላል፣ በምንም ስራ ውስጥ ሊሆን ይችላል በእኛና በእኛ ብቻ መሞላት የሚችል ክፍተት አለ። ተምረን፣ አውቀን፣ ተረድተንና አስተውለን ወይም በተፈጥሮ በተሰጠን የተለየ ክህሎት ይህንን ክፍተት መሙላት አንችላለን። ዓለማችን በችግር የተሞላች ነች፣ ወረድ ስንል አህጉራችን ውስጥ የችግር መዓት አለ፣ ከዛም ወረድ ስንል ሀገራችን ውስጥ ብዙ ያልተፈቱ እንቆቅልሾች አሉ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከምታየውና ከምትሰማው ችግርና ክፍተት ውስጥ ለአንተ የትኛው ጎልቶ ይታይሃል? የትኛውን ለመቅረፍ የቀረብክ ይመስልሃል? በየትኛው ላይ ብትሰማራ ነፍስህ የምትረካ ይመስልሃል? ትንሽ ጊዜ አስብ፣ ለተወሰነ ጊዜ አቅድ፣ በቀጣይ ግን ቀጥታ ትግበራውን ጀምር። ብዙ ሰው የማያየውን ነገር ማየት ስትችል ብቻ ከሰዎች የተለየ አዲስ ነገር ማከናወን ትችላለህ። ህይወትን በዓላማ መኖር ውስጥ እይታ፣ ዝግጁነት፣ ቆራጥነትና የተግባር ሰው መሆን በጣም አስፈላጊዎች  ጥበቦች ናቸው። እይታህ የምትሔድበትን አቅጣጫ ያጠራልሃል፣ ዝገጁነት በማንኛው ሰዓት ወደ ተግባር እንድትገባ ያደርግሃል፣ ቆራጥነት ከሃሳብ በላይ ተግባር ላይ እንድታተኩር ያደርግሃል፣ የተግባር ሰው መሆን ደግሞ በውድቀትና በስህተት ውስጥ አያሳለፍና እያስተማረ ለላቀው ውጤት ያበቃሃል። ቀላል፣ የተረጋጋና ትርጉም ያለው ህይወት ለመኖር እንቅስቃሴዎችህን ሁሉ ትግል አታድርገው። የዓለምን ክፍተት ፈልግ፣ ከፍላጎትህ ጋር አቆራኘው፣ እርሱን ለመሙላትም እንቅስቃሴህን ጀምር


🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
“ደሃ እያለሁ ለምን የድህነቴን ምንጭ አላጣራም?”
*
በ10ሺ ዶላር የተገዛ የወርቅ ጫማ ፣በአልማዝ የተለበጠና 100ሺ ዶላር የተገዛ ሮሌክስ ሰዓት፣ 200ሺ ዶላር ያወጣ ሜርሴዲዝ ቤንዝ ካሉት በርካታ የቅንጦት እቃዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ይህ ሰው የደቡብ ሱዳን ዜጋ ሲሆን በአንድ ወቅት የሀብቱን ምንጭ መንገግስት ለማጣራት ሲሞክር ሀብቱን ሰብስቦ ከሀገሩ አመለጠ፡፡

ታዲያ ይሄን ለምን እንዳደረገ ሲጠየቅ የመለሰው መልስ ሳቅን የሚያጭር ነበር፡፡

የመለሰው መልስ እንዲህ የሚል ነበር…“ደሃ እያለሁ ለምን መንግስት የድህነቴን ምንጭ አላጣራም?”

የአነጋጋሪውን ቢሊየነር ታሪክ በተከታዩ ቪዲዮ ይመልከቱት…

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

  መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
ለውብ ቀን

ከዛ በላይ ናችሁ!

ማንም ምንም ይበላችሁ እናንተ ከዛ በላይ ናችሁ፣ ማንም ሰራችሁን ያጣጥል ስራችሁ ግን ከማንም ስራ በላይ ነው፣ ማንም በኑሯችሁ ይፈር ኑሯችሁ ግን ከማንም ኑሮ በላይ ነው፣ ማንም ከፊታችሁ ቆሞ እንደማትችሉ ይንገራችሁ አቅማችሁ ግን ከንግግሩ በላይ ነው። ከውጪ የሚመጣው ጫና ይቅርና በውስጣችሁ እንኳን የሚመላለሰው የገዛ ሃሳባችሁ ከእናንተ በላይ አይደለም። እራሳችሁን በጥራት የምትመለከቱባት የግል መነፅር አላችሁ፣ ለእራሳችሁ የምትሰጡት ቦታ አላችሁ። ውድድራችሁ ከሰዎች ንግግር ወይም ከውስጥ ጩሀታችሁ ጋር ሳይሆን ለእራሳችሁ ከሰጣችሁት ቦታ ጋር እንደሆነ አስተውሉ። ብለሃትንና ጥበብን ትምህርት ቤት ገብታችሁ አትማሩም። እውቀትን ታወሩት ይሆናል ጥበብና ብለሃት ግን በየቀኑ የምትኖሯቸው ናቸው። ጥበበኞች የማይጠቅማቸውን ንግግር አይሰሙም፣ ብልሆች ከጩሀት በላይ በሳል ንግግር ይገዛቸዋል። በየጊዜው ይማራሉ፣ እራሳቸውን በእውቀት መሰረት ላይ ያንፃሉ፣ መንፈሳቸው ጠንካራ ነው፣ ልብና አዕምሯቸው ቅርብ ለቅርብ ናቸው፣ ስለራሳቸው ሚዛናዊ ሀሳብን በማሰብ ይታወቃሉ፣ በእራሳቸው ያምናሉ ከእራሳቸው ጋር ስለሚያወሩት እያንዳንዱ ነገር በሚገባ ይጠነቀቃሉ።

አዎ! እናንተ ከዛ በላይ ናችሁ! ሳትኖሩ ከሚወራባችሁ፣ በጆሯችሁ ከሰማችሁት፣ አዕምሯችሁ ደጋግሞ ከሚነግራችሁ አሉታዊ ማንነት በላይ ናችሁ። ህይወታችሁ በመዳፋችሁ ነች። የትኛውንም ወደ አዕምሯችሁ የሚገባውን አሉታዊ ሀሳብ የማገድ መብት አላችሁ፣ የትኛውንም በአዕምሯችሁ ውስጥ የሚመላለሰውን መጥፎ ሀሳብ ጠራርጎ የማውጣት አቅሙ አላችሁ። የሰዎችን ሀሳብ በማሳደድ አትጠመዱ፣ ስለሚወራባችሁ ነገር ብዙ አትጨነቁ። "ሰዎች ስለእኔ ምን አሉ ሳይሆን እኔ ስለእራሴ ምን እላለሁ?" ብላችሁ ጠይቁ። በማንኛውም ሰዓት በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ እራሳችሁን ልታገኙ ትችላላችሁ፣ በየትኛውም ሰዓት ያልጠበቃችሁት ስፍራ ልትገኙ ትችላላችሁ። ይህም ሁኔታ የህይወታችሁ አንድ አካል እንጂ የህይወታችሁ መጨረሻ እንዳልሆነ አስተውሉ። ሁሉም ነገር በፍጥነት ይቀየራል፣ የትኛውም ከባድ ስሜት እንደ ንፋስ ያልፋል። በተፈጥሮ የደስታችን ጊዜ አጭር የመከራችን ወቅት ግን ረጅም እንደሆነ ልናስብ እንችላለን። ነገር ግን ልዩነቱን ያመጣው አስተሳሰባችን እንጂ በእርግጥም የጊዜው ርዝመት ተለያይቶ አይደለም።

አዎ! ጀግናዬ..! ከየትኞቹም ከባድ ሁኔታዎችህ በላይ ስለመሆንህ አትጠራጠር። የሚሆነው ይሆናል፣ የሚቀረው ይቀራል፣ የምትባለውን ትባላለህ፣ የሚሰጥህ ስም ይሰጥሃል በስተመጨረሻ ግን ህይወት በእራሷ አቅጣጫ ስትቀጥል ትመለከታለህ። አንተ ተስፋ ቆርጠህ ካልቆምክ ምንም የሚቆም የህይወት ፍሰት የለም። ብዙዎች ሰዎችን ሰምተው ባሉበት ቆመው ቀርተዋል፣ ብዙዎች ለራሳቸው በሰጡት መጥፎ ስም ምክንያት ህይወታቸውን ፈተና አድርገውታል። የምትሰማውም ሆነ የምታየው ነገር ሁሉ እውነት እንደሆነ መቀበል አቁም። እውነት የእምነት ቅጂ ነው። ጉዳዩ የሚያወራው ወይም የሚያሳይህ ሰው ሳይሆን የእራስህ አቀባበል ነው። ሀሳብ ሰውን ይገነባል፣ ሀሳብ ሰውን ያፈራርሳል። ማንም የማይገባበት የግል ዓለም እንዳለህ እወቅ። ያንተ ዓለም ያንተ ብቻ ነው። ከማንም ዓለም አያንስም ከማንም ዓለም አይበልጥም። በልብህ ያኖርከውን ያንኑ እምነት በገሃድ አውጥቶ ያሳይሃል። የግል ዓለምህን ጠብቅ። የማንም ሀሳብ ገብቶ እንዳይረብሸው ተጠንቀቅለት። በህይወት አጋጣሚ ከተገኘህበት ሁኔታ የተሻለ ስፍራ እንደምታደርሰው ቃል ግባለት።

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

#መልካም ቀን

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
ለውብ ቀናችን

👍ከዚህ ይበልጣል!

አንዳንድ ሃሳቦች ሃሳብ ብቻ ናቸው፤ አንዳንዶችም ቅዠት ሊሆኑ ይችላሉ። ደጋግመህ ታስበዋለህ ነገር ግን ልታደርገው አትሞክርም፤ ደጋግሞ ይታይሃል፣ ይመጣብሃል ነገር ግን በእውን ልታየው አልቻልክም። ጀርባህ ብዙ ታሪክ፣ ኋላህ ብዙ እንቆቅልሽ፣ ብዙ ሸክም ይኖራል። በምንም ተዓምር በእንቆቅልሽ ማንነት፣ ባልተፈታ ታሪክ ታጅበህ ወደፊት መጓዝ፣ ሃሳብህን መኖር፣ እቅድህን መፈፀም፣ ህልምህን መኖር ሊቀልህ አይችልም። ምንም እንኳን መጠኑና አይነቱ ቢለያይም ሁሉም ሰው በህይወት አጋጣሚ በህመም ውስጥ ያልፋል፤ በስቃይ ይፈተናል፤ በግል አጣብቂኝ ውስጥ ይወድቃል፤ ደፋ ቀና ይላል፣ ይታገላል። የተደላደለ ህይወት ለማግኘት ብዙ ርቀት መጓዝ ይኖርበታል፤ ብዙ መሰናክሎችን ማለፍ ይጠበቅበታል፤ መወጣት የማይፈልገውን ሃላፊነት መወጣት ይጠበቅበታል።

አዎ! ጀግናዬ..! ሃላፊነትህ ቢልቅም፣ ተጠያቂነትህ ቢበዛም፣ ችግሮችህ ቢወሳሰቡም ህይወትህ ግን ከዚህ ይበልጣል፤ መቆየትህ ከዚህ ሁሉ ይልቃል። የሚሆኑ የማይመስሉ ታሪኮች ሊከሰቱ ይችላሉ፣ አጣብቂኞቹ ሊደራረቡ ይችላሉ፣ ፍላጎትና አሁናዊው አቅምህ ሊለያዩ ይችላሉ፣ ምኞትህና የጀመርከው መንገድም ሊራራቁ ይችላሉ። ነገር ግን በዚህ መሃልም ቢሆን መዳረሻህ አንድና አንድ ነው፤ በአዎንታዊነት ዘርፍ ከፍ ማለት፤ ጠቃሚ፣ ችግር ፈቺና አንተ የመጣህበት ከባድ መንገድ ላይ ያሉ ሰዎችን ማብቃት፣ መደገፍና አቅጣጫውን መጠቆም። የሆነው ቢሆንም የሚበልጠው ላይ ማተኮር ይኖርብሃል፤ እውነታውን ተቀብሎ መቆም ሳይሆን ወደፊት መጓዝ፣ መሰናክሎችን ተሻግሮ የተሻለውን ህይወት መፍጠር ይጠበቅብሃል።

አዎ! በጊዜ ብዛት የተገለጡ፣ ጊዜ ወዳንተ ያመጣቸው ጉዳዮች ፈቺው ጊዜያቸው ነው፤ የሚያቀላቸው እራሱ አምጪው አምላክ ነው። ፅናትህ እስከ ጥግ ሲሆን እንቆቅልሾችህ ይፈታሉ፤ ትዕግስትህ ሲበዛ የላቀውን ብለሃት ትጎናፀፋለህ። በደረሰብህ ጉዳይ ፈጥነህ ብይን አትስጥ፤ እራስህ ላይ ለመፍረድ፣ ማንነትህን ለመተቸት፣ መንገድህን ለማንቋሸሽ አትቸኩል። ሁሉም ሰው የተመረጠለት መንገድ በእርሱ በመራጩ በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክልና እንከን አልባ ነው። ሁኔታህን መቃወም፣ ገጠመኞችህን መተቸት፣ በመጣህበት መንገድ ማፈር ከአምላክህ መቃረን፣ ፈጣሪህን መተቸትና በስራው ማፈር እንደሆነ እወቅ። መሰራት ባለብህ መንገድ ትሰራለህ፤ ብቁ መሆን በሚገባህ አቅጣጫ ብቁ ትሆናለህ። ዋናው ስቃይና ውድቀትህ ሳይሆን ዳግም መነሳትና የፈለክበት ስፍራ መድረስህ ነው።

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

#መልካም ቀን💚💛

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
🌍የዚህ ዓለም እውነታዎች!

ውሾች እና ድመቶች አልጋ ላይ እንዲዘሉ እየፈቀድን ድሆች ግን የግቢያችን ድንጋይ ላይ እንዲቀመጡ አንፈቅድም፡፡

የሰው ዋጋው እየቀነሰ የዶሮ እና የእህል ዋጋ እየጨመረ ሲመጣ በርትተህ ጸልይ፤ ጤናማ አካሄድ አይደለምና፡፡

የውሻ ቡችላ በዋጋ እየተሸጠ ሰውን ግን በነጻ የሚፈልገው ሲታጣ ዘመኑ መክፋቱን እወቀው፡፡

ስለብርቅዬ እንስሳት ብዙዎች እያለቀሱ ይናገራሉ። በምግብ እጥረት ስለሚሞቱት ሕጻናት ግን ቃል አይናገሩም፡፡

ስለ ጠፈር ሳይንስ ብዙ ይወራል (ይሰራል)። የምድር ኑሮ ግን ሲተራመስና ሲጎሳቆል ያስተዋለ የለም፡፡

የወደቁ የታዋቂ ሰዎች ሐውልቶች መልሶ ለመትከል ገንዘብ ይሰበሰባል፤ በየጎዳናው ዳር ስለወደቁት ምስኪን ሕጻናት ግን ምንም አይባልም፡፡

በዚች ምድር ሚሊዮኖች ቤት ሳይኖራቸው በሚልዮን ብሮች እስር ቤቶች ይገነባሉ፡፡

ስለ አየር መበከል ዓለም በሙሉ ይጮሃል። ስለሰው ልጆች ስነ ምግባር መመረዝ ግን ማንም ምንም አይልም፡፡
ሰዎች ሆይ! ... ከዚህ አፍ እና ልብ ከተለያዩበት ትያትረኛ ማንነታችን ፈጥነን እንውጣ ፡፡

☞ ሰዎች ሆይ! ... የሚቀድመውን ብናስቀድም የማይተወን ፈጣሪ ይከተለን ነበር ..።

‌‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎
🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

#መልካም ምሽት💚💛

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
#ቋሚ ነገር የለም

እራሳችሁን ብዙ አታስጨንቁ፣ ያሰብኩት ሁሉ ለምን አልሆነም ብላችሁ ከራሳችሁ ጋር አትጣሉ፣ ከአቅማችሁ በላይ እየታገላችሁ ራሳችሁን አታድክሙ። ሁሉም ነገር በጊዜ እንደሚቀየር አስተውሉ። ተጨነቃችሁ ተጠበባችሁ፣ አወጣችሁ አወረዳችሁ፣ እራሳችሁን ጎዳችሁ አልጎዳችሁ በስተመጨረሻ ነገሮች ሁሉ መቀየራቸው አይቀርም። ስንት ዋጋ የከፈላችሁለት፣ ደጋግማችሁ በይቅርባይነት የጠገናችሁት፣ ለረጅም ጊዜ የተንከባከባችሁት የፍቅር ህይወታችሁ የኋላኋላ እንቅልፍ ሲያሳጣችሁ፣ ከልክ በላይ ሲያስጨንቃችሁና ለከፋ ችግርም ሲያጋልጣችሁ ዝም ብላችሁ አትመልከቱ። የትኛውም ሀሳብ ስልጣን ሰጥታችሁት እንጂ በእናንተ ላይ ምንም አይነት ስልጣን የለውም፣ ሊኖረውም አይችልም። ቅዱስ መፅሐፍ ይህን ይላል፦ "ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንዳች ክንድ የሚጨምር ማነው?" ስለተጨነቅን የሚስተካከል ነገር ቢኖር መልካም ነበር ነገር ግን የለም፤ ስለተዋከብንና ስለተጣደፍን በፍጥነት የሚሳካ ነገር ቢኖረን ጥሩ ነበር ነገር ግን የለም። ሁሉም በሰዓቱ ይቀየራል፣ ሁሉም በጊዜ በእጃችን ይገባል። የእኛ ድርሻ በተቻለ አቅም ነፃ ሆኖ መኖር ነው።

አዎ! ምንም ቋሚ ነገር የለም፣ አንዳች ዘላለም እንደነበር የሚኖር ነገር የለም። ጥቂት የማይባል ሰው ለአንዲት ነፍሱ ብሎ እራሱ የከፋ አደጋ ውስጥ ይጥላል፣ የማያውቀውን ዓለም ናፍቆ ለሞት እራሱን ያጋልጣል፣ የነገሮችን መቀየር መታስ አቅቶት የገዛ ዓለሙን በጨለማ ይሞላል። ዛሬ ላይሆን ይችላል፣ አሁን የታሰበው ነገር ላይሳካ ይችላል፣ በዚህ ሰዓት የተፈለገው ለውጥ ላይመጣ ይችላል ነገር ግን አሁን አልሆነም ማለት ነገም አይሆንም ማለት አይደለም። እስካልቸኮላችሁ ድረስ አይናችሁ እያየ ብዙ ነገር ሲቀየር ትመለከታላችሁ። ለከፋው የህገወጥ ስደት፣ ማንነትን ለሚገድለው መጥፎ ሱስ፣ አንገት ለሚያስደፋው የበታችነትና ፍረሃት እራሳችሁን አሳልፋችሁ አትስጡ። ነፍስን ሸጦ የሚኖር ህይወት የለም። አስቡት ምናልባትም እናንተ ዛሬ እራሳችሁን የሰዋችሁለት ህይወት ውስጥ እናንተ አትኖሩም ይሆናል። እራስን ከማጣት የከፋ ወድቀት የትም የለም። ሰው ሆኖ ሰውነትን መርሳት፣ የተከበሩ ሆኖ እንደ ርካሽ መናኛ መታየት፣ ብርቱ ሆኖ እነተልፈሰፈሱ መኖር የምርም ቅስም ሰባሪና ተስፋ አስቆራጭ ነው። ነገር ግን ነገ ሌላ ቀን ነው። ዛሬ ያቀረቀረው አንገት ነገ ቀና ይላል፣ ዛሬ የተሰበረ ልብ ነገ ይጠቀናል።

አዎ! ጀግናዬ..! ምንም የሚቀየር ነገር የለም ብለህ ቶሎ ተስፋ አትቁረጥ። ታጋሽ ሰው በረዶ ውሃ ሲሆን ያያል። በነገሮች ጊዜያዊነት የሚያምን ሰውም ከክፉው ቀን ማግስት መልካሙን ቀን ለማየት ይበቃል። ፅኑ ልብ የማይሻገረው የህይወት ፈተና የለም፣ በአምላኩ ስራ የሚያምን ሰው በየትኛውም ውድቅ አይሰበርም። ማግኘትና ማጣት፣ ማትረፍና መክሰር፣ መውደቅና መነሳት የህይወት ተቃራኒ ገፆች ናቸው። ለረጅም ጊዜ ሲያተርፍ የኖረ ነጋዴ የሆነ ጊዜ ሊከስር ይችላል፣ እንዲሁ ደጋግሞ ሲከስር የነበረ ነጋዴም አንድ ቀን ከኪሳራው በላይ የሚያተርፍበት ቀን ይመጣለታል። ለብዙዎች ሀብታም መሆን ከባድ አይደለም፣ ሀብታም ሆኖ መቆየት ግን እጅግ ፈታኝ ነው። ምክንያቱም ምንም ቋሚ ነገር የለም። ምን እንዴትና መቼ መቀየር እንደሚችል አይታወቅም። በጊዜያዊ ስሜት አትረበሽ፣ በወቅታዊ ደረጃህ አትከፋ፣ አሁን ስለሆነብህ የከፋ ነገር ከልክ በላይ አትጨነቅ። ምንም ቋሚ ነገር በሌለበት ዓለም የእኔ ህይወት አይቀየርም ብለህ በፍፁም በራስህና በፈጣሪህ ተስፋ እንዳትቆርጥ።

#ውብ ምሽት ይሁንልን💚💛❤️

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
አንድ ዘፋኝ እና መምህር ጎረቤት ሆነው ይኖሩ ነበር

👇🏾

ከእለታት በአንዱ ቀን ዘፋኙ ወደ መምህሩ መጥቶ "ድንገት እግር ጥሎኝ ጎረቤቴ ቤት ስገባ ስለአንተ መጥፎ ነገር ሲወራ ሰማሁኝ:: ምን አይነት መጥፎ መምህር እንደሆንክ እና ልነግርህ የማልችላቸው ሌሎች አፀያፊ ነገሮች ሲይወሩ ነበር:: ይህ ጎረቤትህ ጠላትህ ነው" ሲል ይነግረዋል

መምህሩ በረጅሙ ተንፍሶ "አዎ ጠላቴ ነው" ብሎ ዝም አለ

**

በሌላ ቀን አርቲስቱ በድጋሚ ወደ መምህሩ መጥቶ "ዛሬ ደግሞ ሌላኛው ጎረቤቴ ግሮሰሪው ውስጥ ከሰዎች ጋር ሆኖ ስለ አንተ ባህርይ መጥፎ ሲያወራ ደረስኩኝ: የማይለው ነገር የለም በቃ:: ይህ ሰውዬ ጠላትህ ነው" ሲል ይነግረዋል

መምህሩም "አዎን ጠላቴ ነው: እስካሁን ሁለት ጠላቶች አሉኝ ማለት ነው" ሲል ይመልስለታል

**

በሌላ ቀን ደግሞ "መምህር ሆይ የዛሬውስ ይባስ! ጭራሽ የአንተ ወዳጅ የሆነ ሰው ስለአንተ ክፋት ሲያወራ ሰምቼ አላስቻለኝምና ልነግርህ መጣሁኝ:: ይህ ወዳጅህ ጠላትህ ነው:: ሶስት ጠላቶች አሉህ ማለት ነው" ሲል ይነግረዋል

መምህሩም ቀበል አድርጎ "ሶስት ጠላት ብቻ አይደለም ያለኝ: አራት ናቸው"

"እንዴ መምህር ሶስት እኮ ነው እኔ የነገርኩህ"

መምህሩ መለሰለት

👇🏾

"ራስህን መቁጠር ረስተሃል: አንተ አራተኛ ጠላቴ ነህ:: በቦታው ተገኝተህ ስለ እኔ አንዳችም አልተከራከርክም: የምታውቀኝን ያህል እንኳን ስሜን በክፉ እንዳይነሳ አላደረግክም:: እንደውም ከእነርሱ ይልቅ አንተ ጠላቴ ነህ"

ለምታውቁት እና ለምትወዱት ሰው ዘብ ቁሙ !!❤️🙌🏼


#ውብ ምሽት ይሁንልን💚💛❤️

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄