ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
243K subscribers
290 photos
1 video
16 files
240 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_አርባ_አራት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


አይሮፕላኑ ወደ ማረፊያው ሼዲያክ ቤይ ለማረፍ እየወረደ እያለ ሄሪ የሌዲ ኦክሰንፎርድን ጌጣ ጌጦች መስረቅ ወይም አለመስረቅ ሃሳቡን እልባት ለመስጠት ተቸግሯል፡ ጌጡን ለመስረቅ የነበረው ጉጉት በማርጋሬት
ምክንያት ቀንሷል፡ ቦስተን ይዟት ሄዶ ቤት ተከራይቶ እየኖሩና ራሷን እንድትችል እየረዳት በ ይበልጥ ከእሷ ጋር ሊላመድ ይፈልጋል፡ ደስታዋ ያስደስተዋል፡ ቀለል ያለ ኑሮ ለመኖር ያላትን ጉጉት ይጋራል፡

እናቷን ከዘረፈ ግን ይህ ሁሉ ያከትመለታል፡፡
በአንጻሩ ኒውዮርክ ከመድረሳቸው በፊት የመጨረሻ ማረፊያቸው ከተማ ሼዲያክ ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ ቶሎ መወሰን አለበት፡ ሻንጣ   ክፍሉም የመግባት የመጨረሻ ዕድሉ ይሄ ብቻ ነው፡

ማርጋሬትንም ዕንቁውንም በእጁ ማድረግ የሚችልበትን መንገድ እያሰበ ነው፡ በመጀመሪያ ዕንቁው ቢጠፋ እሱ የሰረቀ መሆኑን ታውቅ ይሆን? ሌዲኦክፎርድ  ዕንቁው መጥፋቱን የሚያውቁት ኒውዮርክ ከደረሱ በኋላ
ልዶርፍ አስቶሪያ ሆቴል ውስጥ ሻንጣቸውን ሲከፍቱ ነው: ዕንቁው 'የጠፋው አይሮፕላኑ ውስጥ፣ በፊት ወይም በኋላ መሆን አለመሆኑን ማንም
አያውቅም፡፡ ማርጋሬት ሄሪ ሌባ መሆኑን ስለምታውቅ እሱ ነው የሰረቀው
ብላ ትጠረጥር ይሆናል። እኔ አልሰረቅሁም ቢላት ታምነዋለች? ታምነው
ይሆናል።

ከዚህ በኋላስ? እሱ ባንክ ውስጥ አንድ መቶ ሺ ዶላር ወሽቆ በድህነት ይኖራሉ! በዚህ አይነት ብዙ ዓመት ሊገፉ አይችሉም፡፡ ወደ እንግሊዝ አገር ትመለስና ሴት ወታደሮችን ትቀላቀላለች፡ ሄሪ ደግሞ ካናዳ ሄዶ የአየር
ኃይል ፓይለት ይሆናል፡፡ ጦርነቱ ሲያበቃ ገንዘቡን ከባንክ ያወጣና መኖሪያ
ቤት ይገዛል፧ እሷም አሜሪካ ትመጣና አብረው መኖር ይጀምራሉ፤ አብረው
ሲኖሩም ይህን ሁሉ ገንዘብ ከየት እንዳመጣ ትጠይቀዋለች።
የሆነውን ሁሉ ወዲያው ወይም ቆይቶ ይነግራት ይሆናል፡ በኋላ ቢነግራት ነው ግን የሚሻለው፡፡

አይሮፕላኑ ሼዲያክ ላይ ሲያርፍ ሁሉም ሲወጡ እሱ የሚቆይበትን ምክንያት መንገር አለበት፡፡ አመመኝ ቢላት አብሬህ እሆናለሁ የምትለው በመሆኑ ሁሉም ነገር ተበላሸ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከሰዎቹ ጋር ወጥታ
መሄዷን ማረጋገጥ አለበት፡
ሄሪ ማርጋሬትን አሻግሮ ያያታል፡፡ የመቀመጫ ቀበቶዋን እያጠበቀች
ነው፡ በዓይነ ህሊናው ደግሞ ራቁቷን ሆና አጎጠጎጤዋ ፈጦ ወጥቶ እና እግሮቿ ከፈት ብለው ብልቷ ዙሪያ ያከፈከፈው ጸጉር ይታየዋል፡፡ ይችን
የመሰለች ቆንጆ ለዕንቁ መለወጡ ጅል የሆነ አያስመስለውም? ታዲያ

እነዚህን ዕንቁዎች መተው ማለት ዘወትር የሚመኘውን የባለጸጋ ኑሮ ሊያደርግ ያሰበውን ነገር ነገራት እንበል፡፡ የናትሽን ዕንቁ ብሰርቅ ምን ይመስልሻል? ቢላት ጥሩ ሃሳብ ነው፤ ይቺ አሮጊት እነዚህ ዕንቁዎች
አይገቧትም ብላ እንደማትመልስለት  ያውቃል፡ በፖለቲካ  አመለካከቷ ተራማጅ  በመሆኗ በፍትሃዊ ክፍፍል ታምናለች፡፡ ይሄ ደግሞ በጽንለ ሃሳብ ደረጃ ነው፡፡ ሄሪ እናትና አባቷ ያላቸውን አንድ ዕንቁ ቢወስድባቸው በጣም በጣም ትበሳጫለች በዚህም ምክንያት ለእሱ ያላት ፍቅር ሁሉ ይተናል።

ይህን በአዕምሮው ሲያሰላስል ከእሷ ጋር ዓይን ላይን ግጥም አሉና
ፈገግ አለች፡ እሱም በእፍረት ፈገግ አለና ፊቱን ወደ መስኮቱ አዞረ፡፥

አይሮፕላኑ ባህር ዳርቻው ላይ ለማረፍ ዝቅ እያለ ነው። ዙሪያዋን የተበታተኑ መንደሮች የተገጠገጡ ሲሆን ከመንደሮቹ ጀርባ የእርሻ ቦታ ይታያል፡ ወደ ማረፊያቸው እየተጠጉ ሲመጡ በመንደሮቹ መሃል እንደ እባብ እየተሹለከለከ እስከ ወደቡ የተዘረጋው የባቡር ሃዲድ ከሩቅ ተለይቶ
ይታያል በባህሩ ዳርቻ ላይ በርካታ መርከቦችና አንድ የአየር በራሪ ጀልባ መልህቃቸውን ጥለዋል።ከወደቡ በስተምስራቅ እዚህም እዛም የበጋ መዝኔኛ
ቤቶች ፈንጠቅጠቅ ያሉበት አሸዋማ የባህር ዳርቻ ይታያል፡ ሄሪ እንደዚህ
ያለ የበጋ መዝናኛ ቤት እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ ይህንንማ በእጄ ካላስገባሁ
ሞቻለሁ! ሀብታም እሆናለሁ› ሲል በሆዱ ተመኘ፡፡

አይሮፕላኑ ባህሩ ዳርቻ ላይ በሰላም አረፈ፡ ሄሪ አሁን ተረጋግቷል፡ በአይሮፕላን መብረርንም ተላምዷል፡
‹‹ስንት ሰዓት ነው?›› ሲል ሄሪ ፔርሲን ጠየቀው፡
‹‹ብአገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ አምስት ሰዓት ነው፡፡ አንድ ሰዓት ዘግይተን ነው የደረስነው››

‹‹ሼዲያክ ላይ ስንት ሰአት እንቆያለን?››

‹‹አንድ ሰዓት››

ሄሪ ማርጋሬት ቀድማ እንድትሄድና ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደሚከተላት
ይነግራታል እሷም ካንተ ጋር እቆያለሁ ብላ እንደማታስቸግር ገምቷል፡፡
አንድ አስተናጋጅ የአይሮፕላኑን በር ሲከፍት ተሳፋሪዎች ልብሶቻቸውን
ደረቡ: የኦክስንፎርድ ቤተሰብ ከአይሮፕላን ለመውጣት ተነሳ፡፡ እስካሁን
አፉን ለጉሞ የቀረው ክላይቭ መምበሪም ከመቀመጫው ተነሳ፡
ማርጋሬትን ‹‹አንቺ ሂጂና እኔ እከተልሻለሁ›› አላትና ወደ መጸዳጃ ቤት ሄደ።

ሰው እስኪወጣ የሆነ ነገር ልስራ ብሎ ጸጉሩን አበጣጠረ እጁንም ታጠበ፡፡ አንድ የአይሮፕላኑ ሰራተኛ በደረጃው ወርዶ አልፎ ሲሄድ አየ፡፡
ሰዓቱን አየና ተጨማሪ ሁለት ደቂቃ ለመጠበቅ ወስነ፡፡ሁሉም ወጥተው እንደሆነ ለማየት ዙሪያ ገባውን አማተረ፡፡ ቦትውድ ላይ ሁሉም አሸልበው  ነበር
አሁን ግን ብዙዎቹ እግሮቻቸውን ለማፍታታተና ንጹህ አየር ለመቀበል እየወጡ ነው፡፡ ኦሊስ ፊልድና እስረኛው እስካሁን ሲያደርጉ እንደነበረው አይሮፕላኑ ላይ ይቆያሉ፡፡
መምበሪ ፍራንኪን እንዲጠብቅ የተመደበ ከሆነ ከአይሮፕላኑ ወጥቶ መሄዱ እንግዳ ነገር ነው፡፡ ሄሪን አሁንም ግርምት ውስጥ የከተተው ሙሉ ልብስ የለበሰው ሰው ነው።
ቲም ሉተር።

የጽዳት ሰራተኞች ወዲያውኑ እየተግተለተሉ መምጣታቸው አይቀርም
ብሎ ጆሮውን ቀስሮ አዳመጠ፡፡ በበሩ በኩል የሚመጣ ድምጽ የለም፡፡ በሩን ትንሽ ከፈት አደረገና አየ፡ ምንም ነገር አለመኖሩን አረጋገጠና ኮቴ ሳያሰማ ወጣ።

ከወጣበት በር ትይዩ ኩሽና ያለ ሲሆን ሰው የለበትም፡፡ ወደ ሌላው የአይሮፕላኑ ክፍልም ዘው ሲል የሰው ዘር አይታይም ወደ ሳሎኑ ሲገባ መጥረጊያ የያዘች ሴት ጀርባዋን ሰጥታው ቆማለች፡፡ ደረጃውን ወጣ፡፡
Lያለምንም መጠራጠር ኮቴ ሳያሰማ ደረጃውን ቀስ ብሎ ወጣ፡፡ ደረጃው መጠምዘዣ ላይ ሲደርስ ቆም አለና ዓይኑን ወረወረ፡ ማንም የለም ወደፊት ሊሄድ ሲል አንድ ሰው ደረጃው ስር ሲሄድ አየና ከመቅጽበት
ኮሪደሩ ላይ ልጥፍ ብሎ ዓይኑን አጮልቆ ሲያይ ባለፈው ጊዜ ሻንጣ
ሲበረብር ያየው ሚኪ ፊን ነው፡፡ ሰውየው የበረራ መሃንዲሱ ቦታ ሲደርስ
ዞር ብሎ አየ፡፡ ሄሪ በዚህ ጊዜ እንዳይታይ ግድግዳው ላይ ልጥፍ አለና አዳመጠ፡ ይሄ ሰው የት ነው የሚሄደው? ሲል መልስ
የሌለው ጥያቄ ጠየቀ የሰውየው ኮቴ እየራቀ ሲሄድ ጸጥታ ሰፈነ፡፡

በደረጃው ወጣ፡፡ ደረጃውን ወጥቶ እንደጨረሰ አሻግሮ ሲመለከት ሰው የለም፡ በቀጥታ ያመራው ወደ ሻንጣዎቹ መቀመጫ ክፍል ነው፡፡ እዚያም ገብቶ በሩን ቀስ ብሎ ዘጋና ትንፋሹን በረጅሙ ለቀቀው፡፡
ሻንጣዎቹን ሲቃኝ አንድ ትልቅ ሳጥን ላይ ዓይኑ ተተከለ፡፡የሌዲ ኦክሰንፎርድ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ጠጋ ብሎ ሲያይ ኦክሰንፎርድ የሚል ስም ተለጥፎበታል፡፡
📕ታምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_አርባ_አራት

#ተከታታይ ልቦለድ

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

እየሄደች ነው… ልታናግረው…፡፡ ለምን እሱን ማናገር እንደፈለገች አታውቅም፡፡ ምን አልባት ዳግመኛ አጠገቡ ልትቆምና ያንን ወንዳወንድ ቁመናው እና ቆንጅዬ ባሪያ የሆነ መልኩን በቅርበት ለማየት ፈልጋ ሊሆን ይችላል….ናፍቋትም ሊሆን ይችላል፡፡ 

ንስሯ የት እዳለ በነገራት መሰረት ቀጥታ ቤቱ ነው የሄደችው..የውጩን የጊቢ በር መጥሪያ ስትጫን ዘበኛው ነበር የከፈተላት…‹‹ከመላኩ ጋ ቀጠሮ ነበረኝ ቤት እየጠበኩሽ ነው ብሎ ደውሎልኝ ነበር..?››ብላ ቀላመደች… ዘበኛው ያልተለመደ ነገር ሆኖበት .. ግራ እንደመጋባት አለና በመጠኑ ካቅማማ በኃላ እንድትገባ  ፈቀደላት…
ቀጥታ ቤተኛ እንደሆነ ሰው የተንጣለለውን ግቢ ሰንጥቃ ባለአንድ ፎቅ ከሆነው ዘመናዊ መኖሪያ ቤት  በረንዳው ላይ ደረሰች… የሳሎኑን በር ገፋ ስታደርገው ተከፈተ…የቀኝ እግሯን አስቀድማ ግራዋን አስከትላ ወደውስጥ ከገባች በኃላ  ወደኃላ ዞሯ በራፉን አንኳኳችው…
‹ከገቡ በኃላ ማንኳኳት ከገደሉ በኃላ ማዘን አይነት አይደለም እንዴ…..?››እራሷው በራሷ ነው የጠየቀችው
መላኩ የሳሎኑ መአከላዊ ስፍራ ላይ  ካለችበት ወደውስጥ 4 ወይም 5 ሜትር ያህል ርቆ በመገረም አፍጥጦ እያያት ነበር….
ማንኳኳቷን ስትቀጥል

‹‹አቤት››የሚል ድምጽ አሰማ

‹‹መግባት ይቻላል..?››

‹‹ገብተሻል እኮ ››

‹‹እሺ ካልክ›› ብላ ቀጥታ የሳሎኑን በር መልሳ ዘግታ ወደእሱ አቅጣጫ አመራች ….በተገተረበት ስለማንነቷ በመመራመር ይመስለል ፈዞ እንደቆመ በስሩ አልፋ ልክ እንደቤተኛ ሶፋው ላይ ዘና ብላ ተቀመጠች….መጣና ከፊት ለፊቷ ተቀመጠ

‹‹አውቅሻለሁ ልበል..?››

‹‹እኔን የመሰለች ቆንጆ ልጅ እንዴት ልትረሳ ትችላለህ..?››

‹‹ማለት..?››

‹‹ጎበዝ የዋና ተማሪህ ነበርኩ ብዬ ነዋ››

…ድንገት እንደበራለት ሰው በመደነቅ ‹‹እንዴ አንቺ እብድ ..እቤቴን ደግሞ ማን አሳየሽ..?›› አለት ‹‹ቀላል ሰው  አይደለሁም ብዬህ ነበርኮ..?››

‹‹አረባክሽ.. ፉከራሽን እኮ አየነው..እኔማ አንተን ማሳሳት ካቀተኝ እንጠለጠላለው ብለሽ ስለነበረ..በቃ ይቺ ልጅ አልሆንላት ሲል እራሷን አጥፍትለች ማለት ነው..ምን አይነት ለቃሏ ታማኝ ልጅ ነች ብዬ ሳደንቅሽ ነበር የሰነበትኩት፤ለካ ዝም ብለሽ ጉረኛ ነገር ነሽ..?››

‹‹አንተን ማውጣት አቅቶኝ ሳይሆን አሳዝነኸኝ ነው የተውኩህ ››

ግድግዳውን ሰንጥቆ በመውጣት ውጭ ድረስ ለመሰማት ኃይል ባለው አይነት አንቧራቂ ሳቅ ሳቀ‹‹አሳዘንኩሽ…..?ቀልደኛ ነሽ››

‹‹ቀልድ አይደለም…የዛን ቀን የሄደክው ከፍቅረኛህ ጋር ወደሆቴል አልነበር…..?ስለ ጋብቻ ስታወሩ አልነበር....?እንድታገባህ ስትለምናት አልነበር…..?እሷ መጋባቱ ቀርቶባችሁ እስክትሞት ድረስ የቀራትን ህይወት እንደዚሁ እንድታሳልፉ ስትለምንህ አልነበር…..?ከመሞቷ በፊት ካላገባችህ እና መጽናኝ የሚሆን ልጅም ካልወለደችልህ በሞተች ቀን አብረሀት እንደምትሞት እየነገርካት ስትላቀሱ አልነበር……..?››

ይሄንን ስትነግረው እነዛ የኮከብ ክፋይ የሚመስሉ  ደማቅ አይኖቹን ከወዲህ ወዲያ በመገረም እያሽከረከራቸው ነበር…..

‹‹አንቺ ክፍል ውስጥ ተደብቀሽ ስታዳምጪኝ ነበር እንዴ..?››በንዴት ጡንቻው ውጥርጥር ሲልና … ልነቃት አልነቃት እያለ ከውስጡ ጋር ሙግት እንደገተመ ከሁኔታው ያስታውቃል….

‹‹አይደለም …ክፍል ውስጥ አልነበርኩም…ግን በአካል ባይሆንም ክፍል ውስጥ ገብቼ  እናንተን ምታዘብበት ሌላ ዘዴ ነበረኝ››

‹‹ምን ..?ካሜራ ..?››
‹‹አይደለም…ምንነቱን ቀስ ብዬ ነግርሀለሁ…አሁን ወደመጣሁበት ጉዳይ እንግባ››

‹‹ወደመጣሁበት ጉዳይ .. ..?በይ ሳትዋረጄ በመጣሽበት እግርሽ ሹልክ ብለሽ ቤቴን ለቀሽ ውጪ..››ከመቀመጨው ቀድሞ ተነሳ…

‹‹ሁለተኛ እንኳን እቤቴ እኔ ባለሁበት አካባቢ  በድንገት ባገኝሽ እወነቴን ነው አጠፋሻለሁ…ሲጥ አድርጌ ነው የምገልሽ….››

ዘና ብላ እንደተቀመጠች መልስ መመለሷን ቀጠለች  ‹‹ዝም ብለህ አትፎክር…በቁጣ እያንቧረቁ መናገር እና ፊትን ማጨማደድ የምትለውን አይነት ጭካኔ እንዲኖርህ አያግዝህም››

‹‹ምን ማለት ነው..?››

‹‹እንኳን እኔን ምንህም  ላይ ያልደረስኩትን ልጅ ይቅርና ሰላምን እንኳን እንደዛ በድላህ ፍቅህን ረግጣ የገዛ ወንድምህን በማግባት ስታወድምህ   ለህግ አሳልፎ ከመስጠት ውጭ ምንም ልታደርጋት  አቅም አላገኘህም፡፡››
ተንደርድሮ ወደእሷ ቀረበና  ተንበርክኮ አንገቷን በማነቅ እያረገፈገፋ‹‹ማነሽ …....?አንቺን ማነው የላከብኝ....?ማነው ንገሪኝ..?››

‹‹ማንም …ምን አልባት የምታመልከው አምላክ ሊታረቅህ ፈልጎ ይሆናል…ምን አልባት እስዛሬ የፀለይከው ፀሎት አምላክ መንበር ደርሶ መልስ የማግኛህ ጊዜ ደርሶም ሊሆን ይችላል…››
፣እጁን ከአንገቷ ላይ መንጭቃ በማላቀቅ ገፈተረችውና …ዝርፍጥ ብሎ ወለሉ ላይ በቂጡ ቁጭ አለ …እዛው ባለበት አፍጦ እሷን ከማየት በስተቀር ለመነሳት አልሞከረም

‹‹ሰሚራን ባድንልህ ምን  ታደርግልኛለህ..?››

‹‹ምን  እየቀባጠርሽ ነው…...?ደግሞ በእሷ ልትቀልጂብኝ ነው..?››

‹‹አይደለም ..ካዳንኩልህ ምን ታደርግልኝለህ..?››

‹‹ቅጠል አሽተሸ በመቀባት የምታድኚው ቁስል… ምች መድሀኒት ወይንም ጅንጅብል ጨቅጭቀሽ ከሻይ ጋር አፍልቶ በመጋት  የምታድኚው  ጉንፋን በሽታ  ያመማት መሰለሽ  እንዴ..?››
‹‹አውቃለሁ…ለአመታት በጭንቅላቷ ቆይቶ የነበረው ጥይት እና የጭንቅላት እጢ ተከትሎ…….››
አላስጨረሳትም ‹‹…በፈጠረሽ ማን ነሽ ?ምንድነው ምትፈልጊው....?ይሄን ሁሉ ገበናችኝን ስንት አመት ብትሰልይን ነው ማወቅ የቻልሺው..?››

ጥያቄውን ችላ በማለት  የራሷን ጥያቄ ደግማ ጠየቀችው

‹‹ካዳንኩልህ ምን ታርግልኛለህ..?››

‹‹ እኮ እንዴት ነው የምታዲኚያት…..?የጀርመንና አሜሪካ ጠበብቶች ያቃታቸውን አንቺ እንዴት ብለሽ..?››

‹‹እኔ የተለየ መንፈሳዊ ስጦታ አለኝ …››

‹‹አላምንሽም››

‹‹እንድታምነኝ…አንድ አንተ ብቻ የምታውቀው ታሪክ ልንገርህ…እንደውም ለምን ዛሬ ያየኸውን ህልም አልነግረህም ..…››

ንገሪኝም ተይው ማለት አቅቶት በግራ መጋባት ስሜት እየዋለለ ዝም ብሎ እንዳፈጠጠባት ፈዞ ቀረ…

ጣና ሀይቅ መሀል ላይ ያለች ትንሽ ደሴት ትመስልሀለች….እሷን ከብዙ የሀገሪቷ ሀብታሞች ጋር ተወዳደረህ በጫረታ በማሸነፍ ትገዛና …በጣም ውብ የሆነ በባህላዊ መንገድ እጽብ ድንቅ ተደርጎ የታነፀ ቤት ትሰራበታለህ…በዛች ደሴት ላይ አንተ ከሰራሀት ቤት ውጭ ምንም አይነት ሌላ ቤት የለም፤ደሴቱ ሙሉውን በቡና ተክል፣በሙዝ፣በብርቱካን፣በመንደሪን፣በአፕል እና  በመሰሰሉት የሚበሉ ፍራፍሬዋች የተሞላች ነች…አዕዋፍት እና የዱር እንስሳትም  ከደኑ ጋር ስመም ፈጥረው ተፈጥሮን አድምቀው እና በተፈጥሮም ደምቅው የሚኖርበት ቦታ በመሆኑ ልዩ ድስታ ተሰምቶህ ይሄንን ስጦታ ላዘጋጀህላት ለሰሚራ ትሰጣታለህ…

‹‹ሰሚርዬ ቀሪ ህይወትሽን ምንም እንኳን አጭር ብትሆንም በደስታ የተሞላች እድትሆን ፈልጋለሁ…በዛ ላይ እዚህ ከእኔ እና ከተፈጥሮ ውጭ ምንም አይነት የሰው ልጅ ወደ ሌለበትና ወደማይኖርበት ቦታ ሳመጣሽ ቀሪ ዘመንሽን የብቻዬ ብቻ እንድትሆኚ በመፈለግ እና በመሰሰት ነው…ይቺ ስፍራ የእኔ እና የአንቺ ገነት ነች››ትላታለህ፡