ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
243K subscribers
289 photos
1 video
16 files
239 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_አርባ_ስምንት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ድንገት የሞተሩ ድምጽ ተለወጠ፤ሁሉም ተሳፋሪ የሆነውን ሁሉ ባለማወቁ በፍርሃት ረጭ አለ፡፡ አይሮፕላኑ ተንቀጠቀጠና ወደ ታች መውረድ ጀመረ፡

አራቱም ሞተሮች በአንድ ጊዜ ሲጠፉ የኤዲም ዕጣ ፈንታ አብሮ ተዘጋ።

ችግር ከመከሰቱ በፊት ሃሳቡን ቢለውጥ ኖሮ ይሄ ችግር አይመጣም፡፡
ሃሳቡ በውጥን ላይ ብቻ ቢቀር አይሮፕላኑ ሰላማዊ መንገዱን ይጓዝ ነበር
አሁን ግን ምንም ሆነ ምን ችግሩ ዓይኑን አፍጥጦ ጥርሱን አግጦ መጥቷል፡፡ ከዚህ በኋላ እንደተሳፋሪ መብረር ካልሆነ በስተቀር የበረራ መሀንዲስ መሆን አይችልም፡፡ አልቆለታል። በንዴት ስህተት እንዳይሰራ
መጠንቀቅ አለበት፡ ይህን ዕቅድ በርጋት መከወን አለበት፡፡ ከዚያ በኋላ
ህይወቱን ያመሰቃቀሉበት ርጉሞች ላይ ይዘምታል።

አይሮፕላኑ በድንገት ባህር ላይ ማረፍ ሊገደድ ነው: ሚስቱን ያገቱበት ወሮበሎች አይሮፕላኑ ላይ ይወጡና ፍራንክ ጎርዲኖን ያስፈታሉ፡ ከዚያ በኋላ የሚሆነው አይታወቅም:፡ ካሮል አን ደህና ስለመሆኗ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ ወሮበሎቹ ወደ አይሮፕላኑ ሲመጡ የጠረፍ ጠባቂ
ፖሊሶች አደጋ ይጥሉባቸው ይሆናል፡፡ ኤዲ በዚህ ስራ ውስጥ ለፈጸመው እስር ቤት ይወረወር ይሆናል፡፡ እሱ እጣ ፈንታው ሆኖ እዚህ ውስጥ በመግባቱ ነው
ለእስር  የሚበቃው።ካሮል አንን በደህና እጁ እንዳስገባ ሌላ የሚፈልገው ነገር የለም::

የአይሮፕላኑ ሞተሮች ቀጥ ካሉ ከአፍታ በኋላ የካፒቴን ቤከር ድምጽ በጆሮ ማዳመጫው መጣና ‹‹ምንድነው ነገሩ?›› ሲል ጠየቀ፡፡

ኤዲ በድንጋጤ አፉ ስለደረቀበት ከመናገሩ በፊት ሁለት ጊዜ ምራቁን ዋጥ አደረገ ‹‹ገና አላወቅሁትም›› አለና  መለሰ፤ ነገር ግን መልሱን ያውቃል፡ ሞተሮቹ መስራት ያቆሙት ነዳጅ ስላለቀ ነው፡፡ እሱ ነው ነዳጅ
ወደ ሞተሮቹ እንዳይደርስ ሆን ብሎ ያደረገው። አይሮፕላኑ ስድስት የነዳጅ
ታንከሮች ያሉት ሲሆን ነዳጅ ወደ ሞተሮቹ የሚያደርሰው ክንፉ ላይ ባሉት
ታንከሮች አማካይነት ነው፡፡ ወደ ሞተሮቹ ነዳጅ
የሚያመጡትን ፓምፖች ሆን ብሎ እንዳይሰሩ አድርጓቸዋል፡፡ ሌላ ኢንጂነር
ቢያየው ሆን ብሎ እንዳይሰሩ እንደተደረጉ ያውቅበታል፡

ረዳት ኢንጂነሩ ሚኪ ፊን ተራው ባይደርስም ድንገት ሊመጣ ይችላል ብሎ ተጨንቋል፡ ነገር ግን ሚኪ እንቅልፉን እየለጠጠ ይሆናል ይህን ጊዜ፡
በረራው ረጅም ጊዜ የሚወስድ በሚሆንበት ጊዜ ከስራ ውጭ ያሉ
የአይሮፕላኑ ሰራተኞች ይተኛሉ፡

ሼዲያክ ላይ ሁለት ጊዜ አስፈሪ የፖሊስ ምርመራዎች ነበሩ፡
የመጀመሪያው ፖሊሶች አይሮፕላኑ ላይ የተሳፈረውን የፍራንኪ ጎርዲኖ
ግብረ አበር ስም ማወቃቸውን ገልጸው ነበር፡፡ ኤዲ ሉተርን ማለታቸውን
ገምቷል በዚህም ምክንያት ሉተር  አልቆለታል ብሎ  ካሮል አንን የሚያስለቅቅበትን ሌላ ስልት ማውጠንጠን ጀምሮ ነበር፡፡ በኋላ ደግሞ
ፖሊሶቹ ሄሪ ቫንዴርፖስትን እንደሚፈልጉ ሲገልጹ ኤዲ ጮቤ ረገጠ፡፡ከድንጋጤው መለስ ሲል ከሃብታም ቤተሰብ የተወለደ የሚመስለው ቫንዴርፖስት ለምን በሀሰት ፓስፖርት እንደሚጓዝ ገርሞታል፡የፖሊሶችን ትኩረት ከሉተር ወደ ራሱ እንዲዞር በማድረጉ ቫንዴርፖስትን በሆዱ እግዚአብሔር ይስጥህ  ብሎታል፡።
ፖሊሶችም በምርመራው  ብዙም ሳይገፉበት ርግፍ አድርገው ተዉት፡ ስለዚህ ሉተር ተረዳና በዕቅዱ መሰረት እነ ኤዲ የጀመሩትን ሊያከናውኑ ተነሱ፡፡
የፖሊሶችን

ለካፒቴን ቤከር ግን የተፈጸመው ሁሉ ጥርጣሬን የሚቀሰቅስ ሆኖበታል፡፡ ኤዲ ገና ከድንጋጤው ሳያገግም አንድ ድንገተኛ ሃሳብ ይዞ ብቅ አለ፡፡ አይሮፕላኑ ላይ ጎርዲኖ
ተባባሪ አለው ማለት እሱን ነጻ ለማውጣት የተዘጋጀ ሰው አለ ሲል ደመደመ፡፡ ስለዚህ ጎርዲኖን ከአይሮፕላኑ ላይ ማስወረድ ፈለገ፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የኤዲ እቅድ ውሃ በላው ማለት ነው፡፡

ህግ እንዳይከበር በማድረጉ በህግ እንደሚጠይቀው የኤፍ.ቢ.አዩ ኦሊስ ፊልድ ካፒቴን ቤከር ላይ ዝቶ ነበር፡፡ በመጨረሻ ካፒቴኑ ኒውዮርክ ለሚገኘው ለፓን አሜሪካን አየር መንገድ መስሪያ ቤት ስልክ ደውሎ ለችግሩ መፍትሄ እንዲሰጡ ነገራቸው፡፡ አየር መንገዱም ጎርዲኖ በአይሮፕላኑ
መጓዙን እንዲቀጥል ሲፈቅድለት ኤዲም በእፎይታ ተነፈሰ፡፡

ሼዲያክ ላይ አንድ አስደሳች መልዕክት ደረሰው፡፡ የመጣው የኮድ
መልዕክት ከጓደኛው ስቲቭ አፕል ባይ መሆኑ አያጠራጥርም፡ መልዕክቱም አንድ የባህር ኃይል ጀልባ አይሮፕላኑ የሚያርፍበት አካባቢ ጥበቃ እያደረገ መሆኑንና እንዳይታወቅ ከእይታ ውጭ ሆኖ ወደ አይሮፕላኑ የሚጠጋ ማንኛውንም ጀልባ ለመምታት የተዘጋጀ መሆኑን ይገልጻል፡

ይሄ ለኤዲ ትልቅ ነገር ነው፡፡ በኋላ ወሮበሎቹ ከህግ እንደማያመልጡ
ማረጋገጫ ቢሰጠውም ዕቅዱ ግን ያለምንም እንከን ባሰበው መልኩ
እንዲጠናቀቅ እንቅፋት እንዳይፈጠር ምኞቱ ነው፡፡
ካፒቴን ቤከር ወደ ኤዲ መጣ፡፡ ኤዲ እጁ እየተንቀጠቀጠ ለሞተሩ ነዳጅ የሚመግበውን ፓምፕ ከፈተውና ‹‹ታንከሩ ባዶ ስለሆነ ሞተሩ አልነሳ አለ›› አለው::

‹‹ለምን?›› ሲል ካፒቴኑ ተቆጣ፡፡

ኤዲ መልስ አልነበረውም፡፡
የአይሮፕላኑ መሳሪያዎች በመጠባበቂያ ነዳጅና በመጋቢ ቧንቧዎቹ
መካከል የነዳጅ እንቅስቃሴ ወይም ግፊት መኖሩን አያሳዩም፡ ፓይለቶቹ ጋ
ግን የነዳጅ ሁኔታን የሚያሳዩ የነዳጅ መቆጣጠሪያዎች አሉ ካፒቴኑ ሁሉንም በየተራ አየና ‹‹ምንም ነዳጅ የለም›› አለ፡፡ ‹‹በክንፉ ላይ ባለው
ታንከር ውስጥ ምን ያህል ነዳጅ አለን?›› ሲል ጠየቀ፡፡
‹‹ትንሽ ነው የቀረው - የተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ብቻ የሚያስኬድ››
‹‹እንዴት ነው ይህን ያላስተዋልከው?›› ሲል ጠየቀ በቁጣ፡

‹‹እኔ ፓምፕ እያደረገ ነው የመሰለኝ›› አለ ኤዲ በተቆራረጠ ድምጽ
ይህ መልስ ግን ካፒቴኑን አላጠገበውም፡፡

‹‹ሶስቱም ፓምፖች እንዴት ባንድ ጊዜ ስራ ሊያቆሙ እንደቻሉ አልገባኝም›› አለ ካፒቴኑ።

‹‹ቶሎ ባህር ላይ ካላረፍን የቀረው ነዳጅ ተንጠፍጥፎ አይሮፕላኑ ሊወድቅ ይችላል›› አለ ኤዲ፡፡

‹‹ባህር ላይ ልናርፍ ስለሆነ ሁላችሁም ተዘጋጁ›› አለ ቤከር፡፡ ጣቱንም ኤዲ ላይ እያወዛወዘ ‹‹አንተ አታስፈልገኝም አላምንህም›› አለው፡

ኤዲ ሞቱን ተመኘ፡፡ ካፒቴኑ ላይ ክህደት ለመፈጸም በቂ ምክንያት እንዳለው ቢያውቅም የፈጸመውን ድርጊት አልወደደውም፡ ህይወቱን በሙሉ
ሃቀኛ ሆኖ ነው የኖረው:: አጭበርባሪዎችንና አታላዮችን አጥብቆ ይጠላ
ነበር፡፡ አሁን ግን የሚጠላውን ነገር ለማድረግ ተገዷል፡
ካፒቴኑ ናቪጌተሩ ጋ በመሄድ ቻርቱ ላይ ዓይኑን ተከለ፡፡ ናቪጌተሩ ጃክ
አሽፎርድ ኤዲን በግርምታ ገረመመውና ‹‹አሁን ያለነው እዚህ ላይ ነው››
ብሎ ቻርቱ ላይ በመጠቆም ለካፒቴኑ አሳየው፡፡

የኤዲ ዕቅድ ሊሳካ የሚችለው አይሮፕላኑ እሱ ባሰበው ቦታ ከወረደ
ነው፡፡ ወሮበሎቹ እዚህ ቦታ ላይ ነው የሚጠብቁት፡፡ ነገር ግን ድንገት
የሚፈጠር ነገር ካለ ከታሰበው ውጭ ሊደረግ ይችላል፡፡ ካፒቴኑ ሌላ ቦታ
ከመረጠ ግን ኤዲ እሱ ያለው ቦታ የተሻለ ስለሆነ እዚያ ማረፍ እንዳለበት
ካፒቴኑን ማሳሰቡ አይቀርም፡፡ ካፒቴኑ ሊጠረጥር ቢችልም እዚህ ቦታ ከማረፍ የተሻለ ነገር እንደሌለ በሎጂክ መቀበል ይኖርበታል፡ ሌላ ቦታ
እንዲያርፍ የሚያደርግ ከሆነ ግን ትክክል የማይሆነው እሱ ነው፡፡ ስለዚህ የእሱ ጣልቃ ገብነት አያስፈልግም ማለት ነው፡፡ ትንሽ ቆየና ‹‹እዚህ ጋ ነው የምናርፈው›› አለ ካፒቴኑ፡
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_አርባ_ስምንት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

የሰው ልጅ ውስጡ ሲጨልምበት እና የመጨረሻ ተስፋው መቁረጥ ላይ ሲደርስ ብስጭቱን የሚያራግፍበት ወይም የሚያላክክበት ሶስት አካላት አሉ…መንግስት፤እግዚያሔር እና እናት ፡፡
የመንግስት እንዝለለው…እግዚያብሄርን ግን ሲከፋን ለምን ፈጠርከኝ….? ብለን እንጠይቀዋለን……መፈጠር ትፈጊያለሽ ወይስ ይቅርብሽ ብለህ ምርጫ ሳትሰጠኝ ለምን ፈጠርከኝ…….?እሺ ይሁን ካለፍላጎቴ ከፈጠርከኝሽ በኋላ ለምን እንደፍላጎቴ ልታኖረኝ አልቻልክም.?  ወይም ብትችል እንኳን ለምን አልፈለክም….? ብለን እንጠይቀዋለን…

እሱ በፍቃዱ እኛን መፍጠሩ እና እንደ እኛ ፍቃድ ሳይሆን እንደእራሱ ፍላጎትም የህይወት ጅረታችን  የሚፈስበትን መስመር ማስመሩ ስህተት አይመስልም...የሰው ልጅም ሲበሳጭ ፤ተስፋ ሲቆርጥና ሲማረር ለምን ….?ብለን እሱን መጠየቃችንም ስህተት አይደለም….የእግዚያብሄር ዋናው ጥቅም የህይወት ሸክማችንን ከብዶን ስንንገዳገድ ከመውደቅ ታድጎ እንዲያግዘን  እና የተሰበረ ተስፋችን እንዲጠግንልን የተንኮታኮተ ሞራላችን እንዲያክምልን ነው….ስለዚህ በከፋን ጊዜ ልንነጫነጭበት የግድ ነው…መነጫነጫችንም ክፋት የለውም፡፡
ከእግዜር ቀጥሎ በዚህ ጉዳይ የፈረደባት እናት ነች …አራት አመት ሆነን አርባ አመት ሁላችንም ውስጣችን ጨልሞ ነጋችንን ማለም ድክም ሲለን ወደ እናታችን ጉያ ሮጠን መሸጎጥ የመጀመሪያ ተግባራችን ነው፡፡ 

…እናታችንን በቅርብ አግኝተን የተመኘነውን ማድረግ ባንችል እንኳን ‹‹….እማዬ ለምን ወለድሺኝ….? ››ብለን ባትሰማንም ማማረራችን አይቀርም….በማማረሩ ውስጥ ምስጋና አለው…ለህልውናችን መሰረቷ ሰው ለመሆናችን ዋናዋ ምክንያቷ  እሷ ለመሆኗ እየተናገርን ለዛም እውቅና እየሰጠናት ነው…
አሁን እነኬድሮን ያሉት ደሎመና ነው…ትውልድ ሀገሯ፡፡ያሉት ሳር ቤት ውስጥ ግድግዳውን ተደግፎ በተሰራ እና ግዙፍ አጎዛ በተነጠፈበት ትልቅ መደብ ላይ ፤ ንስሯን ከጉያዋ አድርጋ እናቷ እግሯ ላይ ተኝታ እንባዋን እያንጠባጠበች ነው….አሁን ካሉበት የሳር ቤት ፊት ለፊት ባለአራት ክፍል ቢላ ቤት ቢኖራትም እናቷ ግን አትወደውም…በቃ አስገዳጅ ሆኖባት እንግዳ ካልመጣባት በስተቀር ውሎዋ እዛች ሳር ቤት ውስጥ ነው…ምግቡ እዛው ይሰራል እዛው ብና ይፈላል….እዛው ጋደም ይባላል…

‹‹ገራኮ ማል ታቴ….?››(ሆዴ ምን ሆንሽ….?)ትጠይቃለች እናቷ
ድምጽ ያላጀበውን እንባዋን ከማፍሰስ ውጭ መልስ ልትሰጣት አልቻለችም….እርግጥ ሊሆን ያለውን ነገር ለእሷ ልትነግራት እና ልትሰናበታት  ነው የመጣችው …ግን እንዲህ በቃላሉ ቃላት ከአንደበቷ ልታወጣ አልተቻላትም፡፡

‹‹ሆማ ኢንታኔ ሀርሜ ኮ..ነገኡማ ›( ….ምንም አልሆንኩ እናቴ…ደህና ነኝ)

‹‹ቀሮ ቲያ .ኢንሶቢን ….? ››(የእኔ ብልጥ አትዋሺኝ….?)

‹‹እማ ጨንቆኛል..በጣም ጨንቆኛል..መልሼ ወደሆድሽ ሁሉ መግባት አምሮኛል››

‹‹እኮ ንገሪኝ …እኔ እናትሽ እያለሁ ለማን ይድላው ብለሽ ትጨነቂያለሽ……?ደግሞ ባንቺ ጭንቀት አያምርም..አንቺ እኮ ለተጨነቀው ሁሉ መፍትሄ ስትሰጪ እንጂ ስትጨነቂ  አያምርብሽም››

‹‹እማ አሁን የገጠመኝ ግን ከባድ ችግር  ነው››

‹‹እኮ ምንድነው….?››

‹‹ልሄድ ነው››

ፈገግ አለች እናቷ‹‹እንቺ እኮ ገና ከልጅነትሽ ጡት ሳትጥይ ጀመሮ እንደሄድሽ ነው….ያንቺ መሄድ ምን አዲስ  ነገር ኖሮት ነው
ሊያስጨንቅሽ የቻለው…….?አይዞሽ ልጄ ንስርሽ ከጎንሽ እስካለ የትም ብትሄጂ ምንም ሀሳብ አይገባኝም..በዛ ላይ የእኔ የእናትሽ ፀሎት እና የአባትሽ መንፈስ በየሄድሽበት ሁሉ ይከተልሻል… ይጠብቅሻል፡፡››

‹‹ሀርሜ…ንስሬ አብሮኝ አይሄድም ….››

ባለማመን አፍጥጣ አየችት..ምክንያቱም ንስሯ ለአንድም ቀን ቢሆን ከእሷ የተለየበትን አጋጣሚ እናቷ አታስታውስም..እንደውም እናቷ ሁለት መንታ ልጇች አሉኝ ብላ ነው የምታወራው…ያው እንደሚታወቀው እናቷ በምትኖርበት አካባቢ በጣም የተከበረችና ሰው ሁሉ የሚፈራት  ነች‹‹….አረ ከዳቢሎስ የተወለደች ልጅ አለቻት …አንድ ነገር ብለን ብናስከፋ በልጇ ታስጠፋናለች….አታዩም እንዴ ልጇ እኮ አቅፋ የምትኖረውን ንስር ዳቢሎሱ አባቷ ነው የላከላት›› እያሉ በማንሾካሾክ እንደሚያሟት ታውቃለች……በዛም ምክንያት ሳይወዱ በግዳቸው ይፈሯታል..ስለሚፈሯትም በጣም ያከብሯታል….ግን ይህን ንስሯን የላከላት አባቷ መሆኑን ትጠራጠራለች እንጂ እርግጠኛ አይደለችም እንዴ….….?

‹‹ለምን ልጄ…?ለምንድነው አብሮሽ የማይሄደው….?››

‹‹የምሄድበት ቦታ እሱን ይዤ መሄድ አይፈቀድልኝም….ቢፈቀድልኝ እሱ አዛ መኖር አይችልም…. አየሩ አይስማማውም…››

ከተጋደመችበት ጭኖ ላይ ገፍትራ አስነሳቻትና እንድትቀመጥ አድርጋ ፊት ለፊት አፍጥጣ እያየቻት‹‹እንዴ ቅሪያ…እንዴት እሱን ጥለሽ መሄድ ታስቢያለሽ…….?የህይወት ጉዳይ  ቢሆን እንኳን ማድረግ የለብሽም..እሱን ጥለሽ ሄድሽ ማለት እኔንም አሳዝነሽ ሄድሽ ማለት ነው…በዕድሜሽ ለመጀመሪያ ጊዜ አዝንብሻለሁ››

‹‹ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው›ይሏችኋል ይሄ ነው..ከእሷ  ባሰች……በጣም ከባዱን ነገር ጭራሽ የበለጠ ጠጣር አደረገችባት፡፡

‹‹ሀርሜ ወዴት እንደምሄድ እኮ አልገባሽም….?››

‹‹ወደ የትም ይሁን አልኩሽ እኮ ..ንስርሽን ጥለሽ የትም መሄድ አትቺይም›› አለችና..ከእቅፌ ንስሬን መንጭቃ ወስዳ ጉያዋ ውስጥ ወሸቀችው…እሱም እጥፍጥፍ ብሎ ተሸጎጠላት፡፡

አፈረጠችው‹‹አባዬ ጋር ነው የምሄደው››
በእድሜዋ ሙሉ እናቷ በዚህ መጠን ስትደነግጥ አጋጥሞት አያውቅም..ሰው እንዴት እየታየ የሰውነት ቀለሙ እየተቀየረ ይሄዳል..?እንዴት እያያችሁት ደም ስሮቹ እየተወጣጠሩ እና ለእይታ ግልጽ እየሆኑ ይታያል….?ሰው እንዴት በሚያግለበልብ ሙቀት ውስጥ ሆኖ የአንታሪቲካ በረዶ ውስጥ እንደጣሉት ጥርሶቹ እርስ በርሳቸው ይንገጫገጫሉ….መልሰው ቃላት ለመለዋወጥ አያሌ ደቂቃዎች ነው ያሳለፈት…..

‹‹እንዴት አድረገሽ ነው የምትሄጂው….?››

‹‹ወገኖቹ ከስድስት ቀን በኃላ መጥተው ይወስዱኝል››

‹‹እሱስ ይመጣል….?››ጉጉት ባሰቃየው እይታ እያየች ጠየቀቻት
‹‹አይ እሱ እንዲመጣ የሚፈቅዱለት አይመስለኝ››

‹‹እሱስ ትክክል ነሽ…ግን እነሱስ እንደሚመጡ በምን አወቅሽ….?››

የሆነውን ሁሉ አስረዳቻት..ቀስ በቀስ በድንጋጤ ወይቦ የነበረው ፊቷ በደስታ እየደመቀ እና እየፈካ መጣ

‹‹እማ እየሳቅሽ እኮ ነው…….?››በገረሜታ ጠየቀቻት ..እያለቀሰችም እየሳቀችም መሆኗ ገርሞት

‹‹አዎ..በጣም ደስ ብሎኝ ነው››

‹‹እንዴ!! እንዴት ደስ ይልሻል..….?ከሄድኩ እኮ አልመለስም››

‹‹አውቃለሁ…ታውቂያለሽ አይደል ትናፍቂኛለሽ …. በጣም ነው የምወድሽ …ግን ወደአባትሽ ነው የምትሄጂው..ደግሞ በአንቺ ዕድሜ ሙሉ ለብቻዬ ተሸክሜው የኖርኩትን እወነቴን ዛሬ አንቺ አረጋገጥሺልኛል… እንዳልተሳሳትኩ አንቺ ልጄ ምስክር ነሽ…እንቡጥ ልጃገረድ ሆኜ ከሌላ አለም የመጣ ሰው መሰል ፍጡር አፍቅሬ እንደነበረ ….ወደእሱ የመኖሬያ አለምም ለአንድ ቀን ወስዶኝ እንደነበረ…የወለድኳት ልጅ አባትም እሱ እንደሆነ ለዘመድም ለጓደኞቼም ሳወራ ነበር የኖርኩት..ግን አውቃለሁ አንድም ሰው አምኖኝ አያውቅም ነበር…እንደውም ነካ እንደሚያደርግኝ ነው የሚስቡት…ዛሬ እወነቴን እንደነበርና ዕድሜዬን ሙሉ ያፈቀርኩት ፍቅር የእውነት እንደነበር አንቺም ተገንዝበኛል…በህይወቴ ሙሉ ከዚህ በላይ ምንም የሚያስደስተኝ ነገር ሊፈጠር