ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
243K subscribers
290 photos
1 video
16 files
240 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ናንሲ ሌኔሃን ከማታውቀው ሰው ጋር አንድ ክፍል ውስጥ መተኛቷ
ሰላም ሳይነሳት አልቀረም:

ምንም እንኳን ክፍሉ የሙሽሮች ክፍል ቢሆንም አልጋዎቹ ተደራራቢ ናቸው፡፡ በሩ ክፍት እንዲሆን ቢፈልጉም በወጀቡ ምክንያት በሩ እየተወረወረ
ይዘጋል፡፡ ስለዚህ አስሬ ሲዘጋ እየተነሱ ከመክፈት ይልቅ አንድ ጊዜ ዘግቶ
መተዉ የሰውን ትኩረት አይስብም:፡

ናንሲ በጊዜ ላለመተኛት ብዙ ጥራለች። በዋናው ሳሎን ሄዳ ለመቀመጥ
ብትፈልግም ወንዶች ብቻ ናቸው የተሰባሰቡት፡፡ ቦታው በሲጋራ ጭስ ታፍኗል፧ በዊስኪ ሽታ ታውዷል፡ በተጨማሪም የካርታ ተጫዋቾች ስድብና
ጫጫታ ጆሮ ይሰነጥቃል፤ ቦታው ለሴት ልጅ የሚሆን አይደለም፤ ስለዚህ
‹መተኛት ሳይሻል አይቀርም› ብላ ወደ መኝታ ክፍሏ ሄደች።

ስለዚህ መርቪንና ናንሲ መብራቱን አጠፉና በየአልጋቸው ላይ ሰፈሩ።
ናንሲ ዓይኖቿን ብትጨፍንም እንቅልፍ በአይኗ hልዞር አለ፡፡ ወጣቱ ሄሪ ማርክስ ያመጣላት አንድ መለኪያ ዊስኪ እንኳን ለመተኛት የረዳት ነገር
የለም፡ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ቢሆንም በዓይኗ እንቅልፍ አልኳል ብሏል፡

መርቪንም እንቅልፍ እንዳልያዘው አውቃለች፡ የላይኛው ቆጥ ላይ
ሰፍሮ ይገላበጣል፡፡ እንደ ሌሎች መኝታዎች የሙሽሮቹ አልጋዎች በመጋረጃ የተሸፈኑ ባለመሆናቸው ላለመታየት ያላት ምርጫ መብራቱን ማጥፋት ነው፡፡

እንቅልፍ አልመጣላት ሲል ማርጋሬት ኦክሰንፎርድ በሀሳቧ መጣች ማርጋሬት በጣም ወጣት፣ የኑሮ ውጣ ውረድ የማይገባትና ወደፊት
ስለሚገጥማት ነገር ቅንጣት ታህል የማታውቅ ልጅ ናት። ከማርጋሬት
በጥርጣሬ የተሞላ ፊት ላይ ያነበበችው ግን ከፍተኛ ነፃ የመሆን ስሜት ነው፡፡ ይህ ደግሞ እሷ ወጣት በነበረችበት ጊዜ የገጠማት አይነት ችግር ነው፡፡ ናንሲም በዚያ ወቅት ከወላጆቿ ጋር አተካራ ውስጥ ገብታ ነበር፧
በተለይ ከእናቷ ጋር፡ እናቷ የተከበረ የቦስተን ቤተሰብ ልጅ እንድታገባ
ብትፈልግም እሷ ግን ገና አስራ ስድስት አመት ሲሞላት ሾን ሌኔሃን
ከሚባል የህክምና ትምህርት ከተማረ ከአባቷ ፋብሪካ ውስጥ ከሚሰራ ካቦ ልጅ ጋር ፍቅር ጀመረች፡፡ እናትዬው ናንሲ ይህን ልጅ እንዳታገባው ልጁ ከሌሎች ሴቶች ጋር እንደሚማግጥ፣ እናት አባቱን ከፍ ዝቅ እያደረገ
እንደሚሳደብና በየጊዜው እንደሚያመው ሀሜት ብታስወራም ናንሲ ግን
የሚነዛውን ሀሜት እንዳልሰማች በማሳለፍ ሾንን አግብታ እስከ ዕለተ ሞቷ ድረስ አብራው ኖራለች፡፡

ማርጋሬት የእሷን ያህል ጥንካሬ ያላት ልጅ አትመስልም፡፡ ከአባቷ ጋር
ካልተስማማች ከቤታቸው መውጣት ትችላለች፡፡ ይቺ ልጅ በየጊዜው ችግር
እያነሳች እንዳታላዝንና ራሷን ለመቻል እንድትጥር የሚመክራት ሰው ያስፈልጋታል፡ እኔ በእሷ እድሜ የሁለት ህጻናት እናት ነበርኩ› አለች በሃሳቧ፡

ስለዚህ ማርጋሬት ራሷን እንድትችል ጠበቅ ያለ ምክር ለግሳታለች እሷም ቃሏን በመጠበቅ ስራ ልትሰጣት ተስፋ አድርጋለች፡፡

ይሄ ሁሉ ደግሞ የሚወሰነው ከወንድሟ ጋር ባላት ጠብ የሀይል
ሚዛኑን በጨበጠው በአጭበርባሪው ሽማግሌ በዳኒ ሪሌይ ነው፡፡ ናንሲ
እንደገና ወደ ጭንቀቷ ተመለሰች፡፡ ጠበቃዋ ማክ ዳኒ ሪሌይን ይኸኔ
አግኝቶት ይሆን? ከአገኘውስ ስለቀድሞው ወንጀሉ ሲነግረው ምን አለ? ይህ ሁሉ ሴራ እሱ ላይ ግፊት ለማድረግ የተጠነሰሰ መሆኑን ጠርጥሮ ይሆን?›
እነዚህን ገና ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች ስታወጣ ስታወርድ እንቅልፍ አጥታ
አልጋዋ ላይ ትገላበጣለች፡፡

የሚቀጥለው የአይሮፕላኑ ማረፊያ ቦትውድ ከተማ ነው፡፡ ኒውፋውንድ ስትደርስ ማክጋ ስልክ ደውላ ታረጋግጣለች፡፡በዚያ ጊዜ ሁሉ ነገር ይለይለታል፡

አይሮፕላኑ ሲንዘፈዘፍና ሲንገጫገጭ ናንሲ መላ አካልዋ ተረበሸ፡፡አሁን ደግሞ ብሶበታል፡ በአይሮፕላን በተደጋጋሚ ብትሄድም ከዚህ ቀደም
እንዲህ አይነት ሁኔታ ገጥሟት አያውቅም፡፡ ግዙፉ አይሮፕላን በንፋሱና
በወጀቡ ሲወዛወዝ ስጋት ገብቷት ተወርውራ እንዳትወድቅ የአልጋውን ብረት አጥብቃ ያዘች፡፡ ባሏ ከሞተ ወዲህ ብዙ ችግር ገጥሟታል፤ ‹አሁን ጉልበቴ
በርታ በርታ› ማለት አለበት፤ ነገር ግን የአይሮፕላኑ መንዘፍዘፍ ክንፎቹን
ይገነጥል፣ ሞተሩን ሰብሮ ይጥለው ይሆን?› እያለች መፍራቷ አልቀረም፡፡
ፍርሃቷን ይቋቋምላት ይመስል ትራሷን በጥርሷ ነክሳ ያዘች፡፡ ድንገት
አይሮፕላኑ ቁልቁል ወረደ፡፡ ቁልቁል መውረዱ እንዲቆም በእጅጉ ብትመኝም
መውረዱን ቀጥሏል፡ ይህ ሁኔታ ክፉኛ አስደነገጣት፡፡ ከዚያም ዘጭ አለና
ቀጥ ብሎ መብረር ጀመረ፡
መርቪን እጁን ሰዶ ትከሻዋን ያዝ አደረገና ‹‹ንፋሱ የፈጠረው ወጀብ ነው አይሮፕላኑን እንዲህ የሚያደርገው›› አለ ‹‹ከዚህ የባሰ ሁኔታ እኔ ብዙ
ገጥሞኛል፤ አይዞሽ አትፍሪ›› ሲል አጽናናት፡፡

እጁን በእጇ ፈልጋ አጥብቃ ያዝ አደረገችው፡፡ ከአልጋው ወረደና እሷ አልጋ ጫፍ ላይ ቁጭ ብሎ ፀጉሯን ይደባብስ ገባ፡፡ አሁንም ፍርሃቷ ሙሉ በሙሉ ባይለቃትም አይሮፕላኑ ሲወዛወዝ መርቪን ያዝ ስላደረጋት በመጠኑ
ቀለል አላት፡፡

ምን ያህል ጊዜ እንደተያያዙ አላወቀችም:: ትንሽ ቆይቶ ወጀቡ ተነሳ፡፡በደምብ ስትረጋጋ የመርቪንን እጅ
ለቀቅ አደረገችው፡፡ ምን ማለት እንዳለባት አላወቀችም።

ናንሲ መብራቱን አበራችና ከአልጋዋ ውስጥ ወጣች፡፡ ከላይ የሆነ ልብስ ደረብ አደረገችና መስታወቱ ፊት ቁጭ አለች፡፡ ሁልጊዜም
ጭንቀት ሲይዛት እንደምታደርገው ፀጉሯን አበጠረች፡፡ በጭንቀቷ ጊዜ የመርቪንን እጅ መያዟ አሳፈራት፡ በዚያ ጊዜ ክብሯን ሸጣ እጁን ለጥቂት ጊዜ በመያዟ በሆዷ
ብታመሰግነውም አሁን ፍርሃቷ ሲለቃት ግን ነገሩ አስፈራት፡፡ እሱም ስሜቷን በመረዳት እፍረቷ እንዲለቃት ብሎ ለጊዜው ክፍሉን ለቆላት ወጣ፡፡

መርቪን ትንሽ ቆይቶ ጠርሙስ ብራንዲ ከሁለት መለኪያ ጋር አመጣና
መጠጡን ቀድቶ አንዱን ሰጣት፡፡ አይሮፕላኑ ትንሽ ይወዛወዝ ስለነበር
በአንድ እጇ መለኪያውን በሌላ እጇ ደግሞ የአልጋውን ብረት ይዛለች:
የለበሰው አስቂኝ ልብስ ባያስቃት ኖሮ ድንጋጤው ቶሎ አይለቃትም አስቂኝ ቢሆንም ልክ ሱፍ ለብሶ
እንደሚንጎራደድ ሁሉ ምንም አልመሰለውም፡፡ ሰው ሞኝ ነው ቢለው ግድ
የለውም፡፡ ልበ ሙሉነቱ አስደስቷታል፡፡

ብራንዲዋን ስትጨልጥ በሰራ አካላቷ ሙቀት ስለፈጠረላት ደጋግማ
ተጎነጨች፡፡

መርቪን ወሬ ለመጀመር ብሎ ‹‹እዚያ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ የሆነ
እንግዳ ነገር አየሁ›› አለ ‹‹እኔ ወደ መታጠቢያ ክፍል ስገባ አንድ በድንጋጤ
ቀልቡ የተገፈፈ ተሳፋሪ ሲወጣ አየሁ፡፡ የመታጠቢያ ክፍሉ መስኮት ተሰብሯል የበረራ መሀንዲሱ ደግሞ ጥፋት ሲፈጸም የተያዘ ሰው መስሎ እዚያ ቆሟል፡፡ መስኮቱ የተሰበረው ከአይሮፕላኑ ውጭ ተወርውሮ በገባ
የበረዶ ቋጥኝ መሆኑን ሊታመን የማይችል ታሪክ ነገረኝ፡፡ እኔ ግን ሁለ±
ሲደባደቡ እንደነበር መገመት አላቃተኝም፡፡››

ናንሲ እዚያ እጅ ለእጅ ተያይዘው ከሚቀመጡ ታሪክ ስለነገራት በሆዷ
መርቪንን አመሰገነችው፡፡ ‹‹የትኛው የበረራ መሀንዲስ?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹እንደ እኔ ቁመቱ ሎጋ የሆነና ፀጉሩ ቃጫ የመሰለ መልከ መልካም ወጣት››
‹‹መሀንዲሱን አወቅሁት፤ ተሳፋሪውስ ማን ነው?››
‹‹ስሙን አላውቀውም፤ ነጋዴ ይመስላል፤ አመድማ ሱፍ ልብስ የለበሰው ሰውዬ ነው›› አለና መርቪን ተነስቶ ብራንዲ ብርጭቆዋ ውስጥ
ጨመረላት፡፡
​​📕ተአምረተ_ኬድሮነ

#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ቀጥታ  ለፖሊስ ሄዳ ነገሩን  ማመልከት ፈለገች…ግን በዚህ ሀሳብ  ብዙም አልገፋችበትም.. ሰዎቹን  እንዳየቻቸው ገንዘብን እንደወረቀት የሚበትኑ ናቸው..ስለዚህ ለፖሊስ እንዳመለከተች በሆነ መንገድ ቢደርሱበት በሽተኛውን  በሌላ መንገድ አስወግደው ለእሷም እንደማይመለሱላት እርግጠኛ ነች፡፡አንድ ዜጋ እንዲህ አይነት ፈታኝ  የደህንነት ስጋት አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት ወቅት  በሀገሩ ህግ  መተማመን ካቃተውና ፍትህ በጥቂት ገንዘብ እና በትውውቅ በቀላሉ እንደሚጠመዘዝ እያሰበ እና  እያመነ ሲሄድ  አደጋ አለው… ምክንያቱም እንዲህ አይነተ ተመሳሳይ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ  የሚሸሽበት መደበቂያ ይጠፋዋል፡፡

ሰሚራም የዚህ ጥርጣሬ ተጠቂ ስለሆነች ፖሊስን አምና የዚህን አይነት ከባድ ጉዳይ ይዛ ወደፖሊስ መሄድ አልደፈረችም….ከዛ ይልቅ  በራሷ ነገሩን በሚስጥር ለመወጣት ወሰነች..እራሷንም ከአደጋ ከልላ ይሙት በቃ የተወሰነበትን ሰው ለማዳን…፡፡

እንደዛ በመወሰኗ በወቅቱ እራሷንም አስገርሟት ነበር…የገዛ ዘመዶቹ እና  የራሴ የሚላቸው ሰዎች መኖሩን ሳይፈልጉ እሷ ለምን ተጨነቀችለት..ሰው ስለሆነ ብቻ ወይስ ሰባዊነቷ አሸንፎት…..….?
መቼስ ነርስ እንደመሆኗ መጠን በየቀኑ የሞት መንደር ውላ የሞት መንድር  ውስጥ የምታድር ሰው ነች…ሞት ያንን  ያህል የሰው ልጅ የመጨረሻው ክስረት እንዳልሆነ ትገነዘባለች ታምናለችም....፡፡ከሞት ወዲህ ማዶ የሰው ልጅ በመኖሩ ውስጥ የሚያስተናግዳቸው ብዙ ክስረቶች አሉ… ሰውን ከመኖር በታች ከመሞትም በታች የሚያደርጉ የስብዕና ዝቅጠቶች ……
ምን አልባት ይሙት በቃ የተፈረደበት ወጣት ከሞት ተርፎ በገዛ ሰዎቹ የደረሰበትን ክህደት አውቆ   ስብርብር ከማለት ስለእነሱ ምንም ሳያውቅ እንዳፈቀራቸው እና እንዳመናቸው ቢሞት ይሻለው ይሆናል…
መሰል ነገሮችን  በአዕምሮዋ ውስጥ በማጉላላት ለሳዕታት ብትብሰለስልም ይሙት በቃ የተወሰነበትን እና በኮማ ውስጥ የሚገኘውን መላኩን በቃ የራሱ ጉዳይ ብላ ችላ ልትለው አልቻለችም…ስሜቷ ጠቅላላ ይሄንን ልጅ አድኝው የሚል ነበር…
እርግጥ በሰዎች ሀሰብ  ተስማምታ  የታማሚውን  ህይወት እንዲያልፍ ማድረግ ለእሷ ከሱቅ መስቲካ ገዝቶ እንደማኘክ ቀላል ነገር ነው….ያንን ቀላል ነገር በማድረጓም የተሰጣትና  ቼክ እና የሚጨምርላት ቦነስም ህይወቷን ተአምራዊ በሆነ ቅጽበት እንደሚቀይርላት ታውቃለች….የምትወዳቸውን ሽቶዎች ለማርከፍከፍ፤ከደሞዞ የመግዛት አቅም እጅግ የራቁ ብራንድ ቀሚስ እና ጫማዎችን እየቀያየሩ ለመድመቅ…. ቢኖረኝ ብላ እንደህልም የምትመኘውን  መኪና ገዝታ  ለማሽከርከረር…ጠቅላላ የኑሮ ዘይቤዋን  ፍጥነት ይቀይርላት ነበር…
ግን ‹‹ይሄ ሁሉ ቁሳቁስ እና  ድምቀት  በቀሪው ህይወቴ ውስጥ ደስተኛ ሆኜ  እንድኖር ያደርገኛል ወይ ... ….?››ብላ ስትጠይቅ ዝግንን ነበር ያላት ..በየቀኑ ከጣረ ሞት ጋር ግብ ግብ ስትገጥም ታያት…እንኳን በዚህ አይነት ሁኔታ  አቅዳና   ተከፍሏት ግድያ  ፈፅማ ይቅርና  እሷ ቀጥታ የምትከታተለው በሽኛተኛ ህይወት እንደአጋጣሚ ሆኖ እጆ ላይ ሲያልፍ ..‹‹ማድረግ ሲገባኝ ያላደረኩለት ነገር ይኖር  ይሆን እንዴ….….?›› 
‹‹እንደዚህ አይነት መድሀኒት ቢሰጠው ይድን ይሆን… ….?››እያለች መሰል ጥያቄዎችን  እራሷን በመጠቅ መብሰልሰል እና መፀፀት የሁል ጊዜ  ስቃዮ  ነው…እና ይሙት በቃ የተወሰነበትን ወጣት  በሽተኛ  ልታተርፈወ ወሰነች….እራሷን አደጋ ላይ ሳትጥል እሱን ከገዳዮቹ ማዳን…ግን እንዴት አድርጋ….….?

     ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 39,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄