"!!!የድምፅ አልባዎች ድምፅ(The Voice Of Voiceless)!!!"
2.9K subscribers
7.83K photos
1.82K videos
199 files
2.76K links
ወቅታዊ ሃይማኖታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ይዳሰሱበታል!
Download Telegram
የኦርቶዶክሳዊ ሀገሩ የት ነው?

ጥያቄው የጅል ጥያቄ ይመስላል አይደል? አዎ ነው። ግን መልሱ እንደ ገደል የራቀ ነው። የመጣልን አልያ የሚመስለንን መመለስ መልስ ስለማይኾን ነው። መልሱን ለማግኘት ተግባሩን መከተል አግባብ ነው። 

ኢትዮጵያ የኦርቶዶክሳዊነት ሃገር ናት። መሠረቷ የሕይወት ፍልስፍናዋ ተዋሕዶአዊነት ነው። ተከፍሎ ወይም ምንታዌነት የአውሮፓውያን የጥፋት ዘር በቅሎብን ነው። ሥጋና ነፍስን መነጣጠል፣ ሃይማኖትና ፓለቲካን ነጣጥሎ ማየት የኖረ ሳይኾን እንድንጠፋ የተዘራብን ነው። ሃገሩ የእኔ ነው። እኔ የዚኽ ሀገር ዜጋ ነኝ ካልክ በኋላ ፓለቲካው ግን አይመለከተኝም ካልኽ ደንቁረሃል ማለት ነው። ኑሮው መኖሪያው፣ መማሪያው ማምለኪያ ቦታው፣ ሥራው አይመለከተኝም ማለትኽ ነው። በጥቅሉ በገዛ እጅኽ ሃገሩን አስረክበሃል ማለት ነው። 

ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የኦርቶዶክሳዊ ሀገሩ የት ነው? ራሱ ኦርቶዶክሳዊው ስለ ሀገሩ የሚያስበው በጠላት የማሰቢያ መነጽርነት ነው። አንገቱ እየተቀላ በጥይት እየተደበደበ የሚሞተው ሃገርኽ አይደለም ቦታኽ አይደለኽም። ወራሪ ነኽ ሰፋሪ ነኽ እየተባለ ነው። ምድሪቱ ሀገሩቱ የእርሱ ኾና ሳለ በደምና አጥንት ቆጠራ መሬት ለክተው አንተ ከዚኽ ቦታ አይደለኽም ብለው ይገሉሃል። 

ይኽንን ይዘን የጀርባ ሥነ ልቡናዊ የጥፋት ውቅሩንም እንየው።

በኦርቶዶክሳዊ መረዳት ሀገሩ የተከፋፈለው በሃገረ ስብከት እንጂ በብሔር አይደለም። ለዚኽ ነው ሃገረ ስብከት የምንለው። ስለዚኽ ፓለቲካው ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ፣… ቢል ቤተ ክርስቲያን ይኽንን የምታውቀው በክልል ሳይኾን በሃገረ ስብከትነት ነው። ለስብከት የተከለለ ማለት ነው። አንድ ጳጳስ ለወንጌል ማዳረስ ይረዳው ዘንድ የተክልለለ ቦታ ወይም ሃገር ማለት ነው። ሃገረ ስብከት ዋና ዓላማው ለነስበክ ነው። 

ኾኖም ግን የጠላት ወጥመድ ውስጥ ገብተን በትውልድ ስፍራ ላይ ጳጳስ መመደብ ጀመርን። ጎንደሬ ጎንደር፣ ሸዌ ሸዋ፣ ኦሮሞ ኦሮሚያ፣ ትግሬ ትግራይ ላይ። ይኽ አጥንትና ደም ቆጣሪ የዳርዊን ትምህርት እንጂ የኦርቶዶክሳዊ ትምህርት አይደለም። ለእኛ ክህደት ጭምር ነው። 

የጎሳ አከላለል እውቀትም እውነትም የለውም። ትውልድን ሃገርን ከመበተን ውጭ ስሜትከመፍጠር ሌላ ሙያ የለውም። የተዋሐደውን በተነው። 
ዘጠኙ ቅዱሳን ኢትዮጵያ ሃገረ ስብከታቸው ናት። ለአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ኢትዮጵያ ሀገረ ስብከታቸው ናት። ከደምና አጥንት ጋር አይያያዘም። እጨጌ እንባቆም ደብረ ሊባኖስ ሃገረ ስብከታቸው ናት። ኹሉም ፍሬ አፈሩበት። 

የእኛ ጳጳሳት ወደ ሰፈራቸው የገቡት በምን ምክንያት ነው። ለስብከት ወይስ ለወንጀል መሸፈኛቸው? በደምና አጥንት ቆጠራ የተደበቁት ለስብከት ወይስ የፓለቲካ መስፈርት? 

ዛሬ ኦርቶዶክሳዊ ኢትዮጵያ ውስጥ ሀገር የለውም። መጤ ኾኗል። ወለጋ፣  ቤኒሻንጉል፣ ኦሮሚያ፣ ሐረር፣ ሶማሌ የሱ ሃገር አይደለም ተብሏል። ሃገረ ስብከት አለኝ የሚል ሲኖዶስ የሃገረ ስብከት ሉቀ ጳጳስ የስብከት ሃገሩን ወደ ጎሳ ክልል ሰጥቶ መንጎቹ ሲያልቁ ዝም ይላል። 
በወለጋ በአርሲ የሚያልቁት ካህናት ምእመና ሃገረ ስብከታቸው ነው።

ኦርቶዶክሳዊ የሚኖረው በስብከት ሃገሩ ነው። ለዚኽ ነው ቤተ ክርስቲያን በኖረበት የሚተክለው። ዛሬ ግን ካለበት እየተነቀለ እንደ በግ እየታረደ የሚኖረው። 

ይኽንን የሚያይ ጳጳስ ፣ ቄስ፣ ምእመናን ደግሞ በግድ የለሽነት እያዩ እየሰሙ ዝም ብለዋል። እንደ ሩቅ አካል ቆጥረዋቸዋል። ሕመማቸው አይሰማቸውም። ጳጳሱም የስብከት ሃገሩ ሳትኾን የሳንቲም ሃገሩ አድርጓታል። ወደ ስብከት ሃገራችን እንመለስ። ቋንቋ መግባቢያ እንጂ ሃገር አይደለም። በሃገር መሞት እንዲያበቃ ሃገር የነጠቀንን መታገል ብቸኛው ምርጫ ነው። እመኑ የሰው ልጅ የማይተርፍባት የእልቂት ሃገር ከፊታን አለች። መኝታው በዝቷል፣ መዝለሉ ለንግሥ መደለቁ፣ ሕንጻ ግንባታው ቆሞ ስለ ሕዝብ ማትረፍ ብቻ እናስብ። 

ንዋይ ካሳሁን
7
የጥቁር ናዚዎች ጭካኔ
😢2
የመነኮሳት ፍጅት በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በአጭሩ

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ፣ መነኮሳትና ካህናት አባቶች በብዛት የተገደሉባቸውና መከራ የተቀበሉባቸው በርካታ ዘመናት አልፈዋል። ከእነዚህም መካከል በታሪክ ጎልተው የሚታወሱት ዋነኞቹ የመነኮሳት ፍጅቶች የሚከተሉት ናቸው።

1) በግራኝ አሕመድ ዘመን በ16ኛው ክፍለ ዘመን ከ1529 እስከ 1543 ዓ.እ በነበረው ጦርነት ወቅት፣ በግራኝ በሚመራው ሠራዊት እንደ ደብረ ሊባኖስና መሰል ታሪካዊ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ወድመዋል። በወቅቱም በገዳማቱ ውስጥ የነበሩ በርካታ መነኮሳትና ሊቃውንት ለሃይማኖታቸው ሲሉ ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።

2) በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ዘመን የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት እልቂት የሚጠቀስ ታሪክ ነው። ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በመነኮሳት ላይ የተፈጸመው እጅግ ዘግናኝና የጅምላ ጭፍጨፋ ነው። ድርጊቱ የተፈጸመው ግንቦት 12 ቀን 1929 ዓ.ም ነበር። በጣሊያኑ እንደራሴ ግራዚያኒ በተወረወረበት የቦምብ ፍንዳታ ምክንያት ለመበቀል ባስተላለፈው ትእዛዝ መሠረት፣ በገዳሙ የነበሩ ብዙ መነኮሳት፣ ዲያቆናትና ንጹሐን ምእመናን በሠራዊቱ ተከበው በግፍ ተፈጅተዋል።

3) በቅርብ ዓመታት በመነኮሳት ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች መጥቀስ ይገባል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በንጹሐን መነኮሳት ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት እጅግ ዘግናኝ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል በሚገኘው በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ከአራት በላይ መነኮሳት በታጣቂዎች መገደላቸው ይታወሳል። በሌሎችም ቦታዎች ተመሳሳይ ጥቃቶች ደርሰዋል።

በምስሉ ላይ የሚታዩት የ85 ዓመቱ አዛውንት አባ አየለ አረጋ እና እማሆይ እስከዳር ገላው ይባላሉ። ሁለቱ መነኮሳት ከቀናት በፊት በወለጋ አካባቢ፣ ልክ እንደ ፋሺስት ጣሊያንና እንደ ግራኝ አሕመድ ሠራዊት ጨካኝ በሆኑ አረመኔዎች የተገደሉ ናቸው።

ዲ/ን ዬሴፍ ፍስሐ
5
Forwarded from Fantahun wakie ፋንታሁን ዋቄ (Fantahun ዋቄ)
ይህን የግፍ ቋት ተሸክሞ
👉 በዘር በቋንቋ የሚከፋፈል ክርስቲያን
👉 የጎሳ ጳጳስና ቄስ
👉 ክርስቲያን ፖለቲከኛና የሚዲያ ባለሙያ
👉 የህልውና ትግሉን ለግል ሥልጣን፣ ለገቢ፣ ለዝና፣ ለሴራ የሚጠቀምበት ሐሰተኛ ፋኖ
---- በምድርም በሰማይ የተረገመ ነው። ከነፍስ ገዳዮቹ እንደ አንዱ ነው።
😢3