Excellent Ideas
632 subscribers
475 photos
68 videos
38 files
59 links
''THINK-LIKE-THERE-IS-NO-BOX''

For any Ideas,Comment and Opinion @AmenNc

Don't hesitate to contact us we need your ideas!!


Before Leaving The Channel Tell us our Problem/ ከቻናሉ ከመውጣቶ በፊት ችግራችንን ይንገሩን🙏 @AmenNc
Download Telegram
#Did_You_Know . Did you know that "A dogs heart beats 40 times a minute faster than yours." @Excellentideas @Excellentideas
በአንድ ወቅት ቻርሊ ቻፕሊን በመድረክ ላይ አንድን ቀልድ ተናገረ።ሁሉም ሳቁ፤ እራሱን ቀልድ ለሁለተኛ ጊዜ ደገመው የተወሰኑት ሳቁ ፤ ለሶስተኛ ጊዜ ራሱን ቀልድ ደገመው የዚህን ጊዜ ግን አንድም የሳቀ ሰው አልነበረም።

የዚህን ጊዜ አንድ ድንቅ ንግግር ተናገረ:-
"ለተመሳሳይ ቀልድ ደጋግመህ አትስቅም! ታዲያ ተመሳሳይ ለሆነና ለሚያስጨንቅህ ነገር ለምን ደጋግመህ ታለቅሳለህ?"
ያለፈን ነገር ደጋግመህ እያነሳህ ማልቀስህ እምባህን ማባከን መቆዘምህም የፊትህን ውበት ማርገፍ ነው።
ሳያልፍ በፊህ ታገል ካለፈ በኃላ ግን አትጨነቅ! @Excellentideas @Excellentideas
#Did_You_Know . Did you know that "Most people blink about 17,000 times a day." @Excellentideas @Excellentideas
ለሀሳብ የምንሰጠው ዋጋ ለቁስ ከምንሰጠው ዋጋ ሊበልጥ ይገባዋል።
የሰው ውበቱ ውብ ሀሳቡ ነው። የሰው ጥራቱ የጠራ ሀሳቡ ነው። የሰው ጤናው ጤነኛ ሀሳቡ ነው። የሰው ሀብቱ ሀብታም ሀሳቡ ነው። ሰው ሀሳቡ ነውና።
አብዛኛው ማህበረሰባችን ከዚህ የልዕቀት ሰፈር አታገኙትም። ማቴርያሊስት ነውና። የአንድን ሰው ማንነት ለመግለፅ ጥሩ አዕምሮ አለው ከማለት ይልቅ ቀይ፥ ጥቁር፥ አጭር፥ ረጅም፥ ወንድ፥ ሴት፥ ሀብታም፥ ድሀ ወዘተርፈ ማለት ይቀናናል።
መለኪያችን የወረደ ነው። ለዚህ ይመስለኛል ውጭውና ውስጡ ያልገጠመ ሰው ማህበረሰባችን ዘንድ የተትረፈረፈው።
ሀሳባዊያን የተሻለ ስብዕና ባለቤት ናቸው። @Excellentideas @Excellentideas
እንኳን #ለደመራና_ለመስቀል_በዓል አደረሳችሁ።

መልካም በዓል እንዲሆን እንመኛለን በዓሉን ሀገር ውስጥም ከውጭም ሆናችሁ ለምታከብሩ በሙሉ፣ ከExcellent Ideas

Happy Meskel!

Best wishes to all those celebrating #Meskel, in #Ethiopia and abroad, from @Excellentideas
👏You gain strength, courage and confidence by every experience in which you really stop to look fear in the face. You are able to say to yourself, 'I have lived through this horror. I can take the next thing that comes along.' You must do the thing you think you cannot do.

@Excellentideas @Excellentideas
#Did_You_Know Did you know that "About 10% of the world's population is left-handed." @Excellentideas @Excellentideas
"ቀናችንን በአንዳች መልካም ነገር እንጀምር! በጨለማው ድቅድቅነት ከማጉረምረም ይልቅ ብርሀን ለመፈንጠቅ ሻማ እንለኩስ!"
-
ቶማስ አልቫ ኢድሰን በ65 ዓመቱ ፋብሪካው እና ጥሪቱ በእሳት ጋየ። ኢንሹራንስ ወይም ምትክ የሚያገኝበት ሁናቴ ላይ አልነበረም።
ሰዎች ያብዳል ብለው ሲጠብቁ ፈገግ አለና፦
"እግዚአብሔር ይመስገን ያለፉ ስህተቶቻችን ጭምር ዶጋመድ ሆነዋል፤ አዲስ ነገርን እንጀምራለን።"
በሚል ፅኑ እምነት ተነስቶ በርካታ ፈጠራዎችን ለዓለም አበረከተ። ከእነዚህም መሀከል አንዱ የኤሌክትሪክ ብርሀን ነው።
-
ትላንት ተመልሶ አይመጣም፤ በትላንት ውስጥ ከታዩ ስህተቶች ትምህርት ወስደን፤ የሚታረሙትን በማስተካከል፤ የማይታረሙትን በማስወገድ ወደፊት እንወነጨፋለን።
በእኛ ብርቱ ጸሎትና ጠንካራ ትጋት፤ በፈጣሪ ምኅረት ለሁላችንም መልካም ዘመን ይሁንልን።
-
ፈጣሪ ሰው አድርጎ ፈጥሮናልና ሰው እንሁን፤ ትልቁ ስህተት አውሬ የማይፈፅመውን ገቢር እያደረጉ 'ሰው ነኝ" ብሎ መውሰድ ነው። ሰው መሆን ለተፈጠሩበት ዓላማ መኖር ነው።

መምህር ታዬ ቦጋለ
@Excellentideas @Excellentideas
Small Minds Discuss People Average Minds Discuss Events Great Minds Discuss IDEAS
@Excellentideas @Excellentideas
በማህበራዊ ሚዲያ አግኝቼ ከወደድኩትና እንደራሴ የተረጎምኩት ጽሑፍ

1. ዕድሜያችሁ 30 ከመሆኑ በፊት አግቡ
ስትዘጋጁ
2. ከብዙ ገንዘብ ጋር ጡረታ ውጡ
ከብዙ መልካም ትዝታ ጋር
3. ሀብታም ሁኑ
ደስተኛ
4. ከቆንጆ ሰዉ ጋር በፍቅር ወደቁ
ከአስተዋይ
5. ባገኛችሁት ገንዘብና ዝና ቤተሰባችሁን አስደስቱ
ባገኛችሁት ሰላምና እርካታ
6. ብዙ ጓደኛ ይኑርህ
ትክክለኛ
7. አብራችሁ መኖር የምትችሉትን ሰው ፈልጉ
ካለእሱ መኖር የማትችሉትን

@Excellentideas
@Excellentideas
Not always, but usually 😊
@Excellentideas
@Excellentideas
ሰዎች ከናቁሽ ጥፋቱ የአንቺ ነው፡፡
+
ለራስሽ የምትሰጪው ዋጋ ከፍ ካላለ
የሚያገኝሽ ሰው ሁሉ ዝቅ ያደርግሻል፡፡
+
ራስሽን ካልወደድሽ ከቶ እንዴት ሰው ይወድሻል?
+
ሰዎች እንዲወዱሽ የውሸት ታሪክ አትፍጠሪ፡፡ያልሆንሽውን ለመሆን አትሞክሪ፡፡ትኩረት ለመሳብ አትኳኳይ፡፡ፎቶሽን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ አስር ጊዜ አትለጥፊ፡፡
+
ይህንን ባደረግሽ ቁጥር ባዶነት እየተሰማሽ ይሄዳል፡፡የሰዎች ሀሳብ ባርያ ትሆኛለሽ፡፡የስሜትሽ ሪሞት ኮንትሮል በእነሱ እጅ ይሆናል፡፡መጥፎ ነገር ካሉሽ ስሜትሽ ይወድቃል፡፡ላይክ፣ ትኩረትና አድናቆት ሲነፈጉሽ አብዝተሽ ትከፊያለሽ፡፡
+
እውነተኛ በራስ መተማመን የሚፈልቀው ከራስሽ ውስጥ ነው፡፡አንቺ አንቺን ከልብ የምታደንቂ ከሆነ በሰዎች አለመደነቅ አትችይም፡፡ራስሽ ላይ አተኩሪ፡፡ለራስሽ ታማኝ ሁኚ፡፡የምታደርጊው ለሰው ሳይሆን ለራስሽ ይሁን፡፡
+
ማውራት ፡ ዝም ማለት ፡ ሽክ ማለት ፡ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ መፖሰት ፡ መዝናናት ፡ ውድ ነገር መግዛትም ሆነ ሌላም ነገር ለሂሊናሽ ምቾት ከሰጠው ያለፍርሃት አድሮጊው፡፡ሰው ምን ይለኛል ብለሽ አትጨነቂ፡፡
+
ዳሩ ግን ሰው የሚጎዳ ነገር በፍጹም አታድርጊ፡፡ለመጥፎ ሰዎች ሳይቀር መልካምነ ሁኚ፡፡ራስሸን የሚጠሏትን የምትወድ ውብ ሴት አድርጊያት፡፡ሲንቁሽም አክብርያቸው፡፡ሲሰድቡሽም መርቅያቸው፡፡
+
የአንቺ ድርጊት የሚናገረው ስለአንቺ እንጂ ስለእነሱ አይደለም፡፡በመጥፎ ሰዎች ምክንያት ጥሩነትሽ አይቁም፡፡መጥፎ ሰው መሆን የሚጎዳው ራስሽን ነው፡፡
+
በራስ መንገድ መኖር እውነትን መኖር ነው፡፡ይህ በማንኛውም ሁኔታ ራስን የመሆን ወኔን ይፈልጋል፡፡ መጀመርያ በጣም ይፈትንሻል፡፡በብዙ ሰዎች ምልከታ እብድ ያስብልሻል፡፡ግን በጊዜ ሂደት የውስጥሽ ሰላም ሲያበራ ሁሉም ይመኝሻል፡፡ድሮ ብልመና ያጣሽው ትኩረት ወደ አንቺ አቅጣጫ ይፈሳል፡፡ሁሉም አብሮሽ ለመሆን ይገፋል፡፡አንቺ ግን ሁሌም ከአንቺ ጋር ሁኚ::
+
ወደ ራስሽ ተመለሺ፡፡መስተዋቱ ላይ የምትመለክችያትን ልጅ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ውደጃት፡፡ከእነ ስህተቷ እቀፊያት፡፡ከእነጥፋቷ ሳሚያት፡፡በሙሉ ልብሽ አብረሻት ሁኚ::
+
# share! @Excellentideas @Excellentideas
Every Test in life makes us

Bitter or Better.

Every Problem comes to

Make Us or Break Us.

Choice is ours,

Whether Become Victim or Victor.

@Excellentideas @Excellentideas
Forwarded from Zerihun G Girma
"እያንዳንዱ ሐሳብ ዘር ነው" በዘሪሁን ግርማ የሚጻፉ ጹሑፎችን ለማግኘት "የዘር ሐሳብ" የተሰኘውን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ። አዳዲስ ጽሑፎችን ያገኛሉ።
https://t.me/theideaofs
Losers are those whose words are bigger than actions. Winners are those whose actions are bigger than words.
Have a blessed day 😊 🙏 @Excellentideas @Excellentideas
📍 አጉል ተናጋሪ ነው ካሉህ እነሱ መናገር የማይደፍሩትን አንተ እያልክላቸው ነውና ደስ ይበልህ
📍 አጉል ታማኝ ነኝ ይላል ካሉህ እንዳያታሉ አርገሀቸዋልና ኩራ!
📍 ምነው ፈጠን ፈጠን አለ ካሉህ ከነሱ ቀድመህ ሄደሀልና በራስህ ተደነቅ
📍 እዩኝ እዩኝ አበዛ ካሉህ ባለህበት ቦታ ንቁ ተሳታፊ ነህና በርታ

የነሱ የትችት ድንጋይ ሞኙን ይፈነክተዋል ጠቢቡ ግን ድንጋዩን እየተቀበለ ቤቱን ይሰራበታል
እናንተ የትኛው ናቸሁ? ጠቢቡ ግንበኛ ወይስ ሞኙ ወሬ ሰሚ?

አንተ ውስጥህ ንፁህ ከሆነና በቅን ልብ ከሰራህ ለሰው ትችት መልስ አትስጥ ስራህ መልስ ይስጥ፤ ስራህ መልስ የሚሰጥ ከሆነ ደግሞ አይደለም 1 ሰው 100 ሚሊየን ሰው ቢተችህ ስራህ ያሳፍራቸዋል!!

አድናቆትንም፣ ትችትንም፣ ምክርንም በእኩል ስሜት ተቀበል ከዛ እንደ ጠቢቡ ግንበኛ ቤትህን ስራበት!!

@Excellentideas
@Excellentideas
ሮበርት ብሩስ የእንግሊዝ ንጉሥ ነበር ፡፡ የእሱ ጦር በሌላ የእንግሊዝ ንጉስ ቀዳማዊ ኤድዋርድ ላይ ደጋግሞ ተሸነፈ ፡፡ ለ ‹ስድስት ጊዜ) ተሸንፎ ፣ ተስፋውን ሁሉ አጣ ፡፡ አንድ ቀን በተደበቀበት ቦታ ቁጭ ብሎ የደረሰበትን መጥፎ አጋጣሚ እያሰላሰለ ነበር ፡፡ ድንገት አንዲት ሸረሪት ድሯን ለማጠናቀቅ በሸረሪት ክርዋ ጣራውን ለመድረስ ስትሞክር አስተዋለ ፡፡ ሸረሪቷ ደጋግማ ሞከረች። ፤ ግን በእያንዳንዱ ጊዜ ወደቀች ፡፡ በሸረሪቷ የተደረጉ ስድስት ሙከራዎች አንድ በአንድ ከሽፈዋል ፡፡ ግን አሁንም ትግሉን አልተወችም። ሙከራዋን ቀጠለች ፡፡ ብሩስ ሸረሪቱን በከፍተኛ ፍላጎት ተመልክተው ሰባተኛው ሙከራ እንደተሳካ አየ ፡፡ የሸረሪቷ ጽናት ብሩስን አበረታተው ፡፡ የተስፋ ጨረር አየ ፡፡ በአዲስ ተስፋ ተሞልቶ የተበተነ ኃይሉን በአንድ ላይ በማሰባሰብ ጠላቶቹን በታደሰ ኃይል እንደገና ገጠማቸው ፡፡ በዚህ ጊዜ ጠላቶቹን በማሸነፍ ተሳካለት ፡፡

@Excellentideas
@Excellentideas