Excellent Ideas
632 subscribers
475 photos
68 videos
38 files
59 links
''THINK-LIKE-THERE-IS-NO-BOX''

For any Ideas,Comment and Opinion @AmenNc

Don't hesitate to contact us we need your ideas!!


Before Leaving The Channel Tell us our Problem/ ከቻናሉ ከመውጣቶ በፊት ችግራችንን ይንገሩን🙏 @AmenNc
Download Telegram
በድጋሜ

ሰውን ሰው ያደረገው ምን ይመስላችኃል? ከአንድ መጽሐፍ ያነበብኩትን ላጋራችሁ፡፡ "ሰውን ሰው ያደረገው ሥራ አይደለም፤ አህያም ይሰራል፡፡ ሰውን ሰው ያደረገው ንግግር አይደለም፤ በቀቀንም ይናገራል፡፡ ሰውን ሰው ያደረገው መኖር መቻሉ አይደለም፤ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እየኖረ ነው፡፡ ሰውን ሰው ያደረገው ብልሐት አይደለም፤ ዶልፊንም ብልህ ነው፡፡ ሰውን ሰው ያደረገው ስለ ነገ ማሰቡ አይደለም፤ ጉንዳኖችም ስለ መጭወው ክረምት ያስባሉ፡፡ ሰውን ሰው ያደረገው ለዓላማ መፈጠሩ ነው፡፡" ይላል

@Excellentideas
@Excellentideas
#Did_You_Know

Did you know that "The Nile River in Africa is the longest river (6,825 kilometers) of the earth."

@Excellentideas
@Excellentideas
Know what you want,

Why you want it, and

What you're going to do about it.

@Excellentideas
@Excellentideas
#Did_You_Know

Did you know that "The brain uses more than 25% of the oxygen used by the human body."

@Excellentideas
@Excellentideas
Be a positive influence to those around you!

@Excellentideas
@Excellentideas
⚡️ • • አመስጋኝ እንሁን • • ⚡️

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሰው በአንድ ተራራ አጠገብ ሲያልፍ ተንሸራትቶ ወንዝ ይገባል። ከውኃው ጋር ሲታገል ቆይቶ ሞት አፋፍ ላይ ሲቃረብ፣ ሃይማኖት ባለፈበት ያላለፈው ሰው ወደ ፈጣሪው ጮኸ። "አምላኬ ሆይ!… እባክህን ከሞት አድነኝ ካዳንከኝ ከዛሬ ጀምሮ እጸልያለሁ! ትዕዛዛትህንም እፈጽማለሁ!…" እያለ ጮኸ። በዚህ ጊዜ ከወንዙ ዳርቻ ያለ አንድ የዛፍ ሥር አጋጠመውና ለቀም አድርጎ፣ "አምላክ ሆይ ግዴለም አትቸገር" አለ።

⚡️ገና ይህን ተናግሮ ሳይጨርስ ግን የጨበጠው ግንድ ተሰብሮ ተመልሶ ወንዙ ውስጥ ገባ። ተደናግጦ፣ "ምነው አምላክ ሆይ ቀልድ አታውቅም አንዴ?" አለ ይባላል።

⚡️ይህች ትንሽ ቀልድ የአእምሯችንን አሠራር ቁልጭ አድርጋ ታሳየናለች፡፡ ሁላችንም ፈጣሪያችንን የምናስታውሰው በመከራችን እንጂ በደስታችን ቀን አይደለም። ወደ ቤተ ክርስቲያን ወይም መስጊድ የምንሄደው መቼ ነው? ጤነኞችና ደስተኞች በሆንበት ሰዓት? አይደለም፥ ችግር ወይም መከራ(በሽታ) ሲደርስብን ብቻ ነው። በሕይወታችን ውስጥ ሃብት ኖሮንም ብዙም ደስተኞች አይደለንም፡፡ ድሆች ስንሆን ደግሞ ችግራችንና ስቃያችን የበረታ ይሆናል። ጤነኞች ስንሆን ጤነኞች በመሆናችን አምላክን አናመሰግንም። ስንታመም ግን፣ ሕይወታችንንና በአጠቃላይ መኖራችንን እንረግማለን። አንዳንዶቻችን እንደውም ያሉንን መልካም ነገሮች ሁሉ ለመራገም ትንሽ የራስ ምታት ትበቃናለች። ለማመስገን ጊዜ እንሰጥ፥ አሁኑኑ እናመስግን። ስናመሰግን የሌለን ነገር ይጨምርልናልና። .@Excellentideas @Excellentideas
#Did_You_Know . Did you know that "A dogs heart beats 40 times a minute faster than yours." @Excellentideas @Excellentideas
በአንድ ወቅት ቻርሊ ቻፕሊን በመድረክ ላይ አንድን ቀልድ ተናገረ።ሁሉም ሳቁ፤ እራሱን ቀልድ ለሁለተኛ ጊዜ ደገመው የተወሰኑት ሳቁ ፤ ለሶስተኛ ጊዜ ራሱን ቀልድ ደገመው የዚህን ጊዜ ግን አንድም የሳቀ ሰው አልነበረም።

የዚህን ጊዜ አንድ ድንቅ ንግግር ተናገረ:-
"ለተመሳሳይ ቀልድ ደጋግመህ አትስቅም! ታዲያ ተመሳሳይ ለሆነና ለሚያስጨንቅህ ነገር ለምን ደጋግመህ ታለቅሳለህ?"
ያለፈን ነገር ደጋግመህ እያነሳህ ማልቀስህ እምባህን ማባከን መቆዘምህም የፊትህን ውበት ማርገፍ ነው።
ሳያልፍ በፊህ ታገል ካለፈ በኃላ ግን አትጨነቅ! @Excellentideas @Excellentideas
#Did_You_Know . Did you know that "Most people blink about 17,000 times a day." @Excellentideas @Excellentideas
ለሀሳብ የምንሰጠው ዋጋ ለቁስ ከምንሰጠው ዋጋ ሊበልጥ ይገባዋል።
የሰው ውበቱ ውብ ሀሳቡ ነው። የሰው ጥራቱ የጠራ ሀሳቡ ነው። የሰው ጤናው ጤነኛ ሀሳቡ ነው። የሰው ሀብቱ ሀብታም ሀሳቡ ነው። ሰው ሀሳቡ ነውና።
አብዛኛው ማህበረሰባችን ከዚህ የልዕቀት ሰፈር አታገኙትም። ማቴርያሊስት ነውና። የአንድን ሰው ማንነት ለመግለፅ ጥሩ አዕምሮ አለው ከማለት ይልቅ ቀይ፥ ጥቁር፥ አጭር፥ ረጅም፥ ወንድ፥ ሴት፥ ሀብታም፥ ድሀ ወዘተርፈ ማለት ይቀናናል።
መለኪያችን የወረደ ነው። ለዚህ ይመስለኛል ውጭውና ውስጡ ያልገጠመ ሰው ማህበረሰባችን ዘንድ የተትረፈረፈው።
ሀሳባዊያን የተሻለ ስብዕና ባለቤት ናቸው። @Excellentideas @Excellentideas
እንኳን #ለደመራና_ለመስቀል_በዓል አደረሳችሁ።

መልካም በዓል እንዲሆን እንመኛለን በዓሉን ሀገር ውስጥም ከውጭም ሆናችሁ ለምታከብሩ በሙሉ፣ ከExcellent Ideas

Happy Meskel!

Best wishes to all those celebrating #Meskel, in #Ethiopia and abroad, from @Excellentideas
👏You gain strength, courage and confidence by every experience in which you really stop to look fear in the face. You are able to say to yourself, 'I have lived through this horror. I can take the next thing that comes along.' You must do the thing you think you cannot do.

@Excellentideas @Excellentideas
#Did_You_Know Did you know that "About 10% of the world's population is left-handed." @Excellentideas @Excellentideas
"ቀናችንን በአንዳች መልካም ነገር እንጀምር! በጨለማው ድቅድቅነት ከማጉረምረም ይልቅ ብርሀን ለመፈንጠቅ ሻማ እንለኩስ!"
-
ቶማስ አልቫ ኢድሰን በ65 ዓመቱ ፋብሪካው እና ጥሪቱ በእሳት ጋየ። ኢንሹራንስ ወይም ምትክ የሚያገኝበት ሁናቴ ላይ አልነበረም።
ሰዎች ያብዳል ብለው ሲጠብቁ ፈገግ አለና፦
"እግዚአብሔር ይመስገን ያለፉ ስህተቶቻችን ጭምር ዶጋመድ ሆነዋል፤ አዲስ ነገርን እንጀምራለን።"
በሚል ፅኑ እምነት ተነስቶ በርካታ ፈጠራዎችን ለዓለም አበረከተ። ከእነዚህም መሀከል አንዱ የኤሌክትሪክ ብርሀን ነው።
-
ትላንት ተመልሶ አይመጣም፤ በትላንት ውስጥ ከታዩ ስህተቶች ትምህርት ወስደን፤ የሚታረሙትን በማስተካከል፤ የማይታረሙትን በማስወገድ ወደፊት እንወነጨፋለን።
በእኛ ብርቱ ጸሎትና ጠንካራ ትጋት፤ በፈጣሪ ምኅረት ለሁላችንም መልካም ዘመን ይሁንልን።
-
ፈጣሪ ሰው አድርጎ ፈጥሮናልና ሰው እንሁን፤ ትልቁ ስህተት አውሬ የማይፈፅመውን ገቢር እያደረጉ 'ሰው ነኝ" ብሎ መውሰድ ነው። ሰው መሆን ለተፈጠሩበት ዓላማ መኖር ነው።

መምህር ታዬ ቦጋለ
@Excellentideas @Excellentideas
Small Minds Discuss People Average Minds Discuss Events Great Minds Discuss IDEAS
@Excellentideas @Excellentideas
በማህበራዊ ሚዲያ አግኝቼ ከወደድኩትና እንደራሴ የተረጎምኩት ጽሑፍ

1. ዕድሜያችሁ 30 ከመሆኑ በፊት አግቡ
ስትዘጋጁ
2. ከብዙ ገንዘብ ጋር ጡረታ ውጡ
ከብዙ መልካም ትዝታ ጋር
3. ሀብታም ሁኑ
ደስተኛ
4. ከቆንጆ ሰዉ ጋር በፍቅር ወደቁ
ከአስተዋይ
5. ባገኛችሁት ገንዘብና ዝና ቤተሰባችሁን አስደስቱ
ባገኛችሁት ሰላምና እርካታ
6. ብዙ ጓደኛ ይኑርህ
ትክክለኛ
7. አብራችሁ መኖር የምትችሉትን ሰው ፈልጉ
ካለእሱ መኖር የማትችሉትን

@Excellentideas
@Excellentideas
Not always, but usually 😊
@Excellentideas
@Excellentideas
ሰዎች ከናቁሽ ጥፋቱ የአንቺ ነው፡፡
+
ለራስሽ የምትሰጪው ዋጋ ከፍ ካላለ
የሚያገኝሽ ሰው ሁሉ ዝቅ ያደርግሻል፡፡
+
ራስሽን ካልወደድሽ ከቶ እንዴት ሰው ይወድሻል?
+
ሰዎች እንዲወዱሽ የውሸት ታሪክ አትፍጠሪ፡፡ያልሆንሽውን ለመሆን አትሞክሪ፡፡ትኩረት ለመሳብ አትኳኳይ፡፡ፎቶሽን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ አስር ጊዜ አትለጥፊ፡፡
+
ይህንን ባደረግሽ ቁጥር ባዶነት እየተሰማሽ ይሄዳል፡፡የሰዎች ሀሳብ ባርያ ትሆኛለሽ፡፡የስሜትሽ ሪሞት ኮንትሮል በእነሱ እጅ ይሆናል፡፡መጥፎ ነገር ካሉሽ ስሜትሽ ይወድቃል፡፡ላይክ፣ ትኩረትና አድናቆት ሲነፈጉሽ አብዝተሽ ትከፊያለሽ፡፡
+
እውነተኛ በራስ መተማመን የሚፈልቀው ከራስሽ ውስጥ ነው፡፡አንቺ አንቺን ከልብ የምታደንቂ ከሆነ በሰዎች አለመደነቅ አትችይም፡፡ራስሽ ላይ አተኩሪ፡፡ለራስሽ ታማኝ ሁኚ፡፡የምታደርጊው ለሰው ሳይሆን ለራስሽ ይሁን፡፡
+
ማውራት ፡ ዝም ማለት ፡ ሽክ ማለት ፡ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ መፖሰት ፡ መዝናናት ፡ ውድ ነገር መግዛትም ሆነ ሌላም ነገር ለሂሊናሽ ምቾት ከሰጠው ያለፍርሃት አድሮጊው፡፡ሰው ምን ይለኛል ብለሽ አትጨነቂ፡፡
+
ዳሩ ግን ሰው የሚጎዳ ነገር በፍጹም አታድርጊ፡፡ለመጥፎ ሰዎች ሳይቀር መልካምነ ሁኚ፡፡ራስሸን የሚጠሏትን የምትወድ ውብ ሴት አድርጊያት፡፡ሲንቁሽም አክብርያቸው፡፡ሲሰድቡሽም መርቅያቸው፡፡
+
የአንቺ ድርጊት የሚናገረው ስለአንቺ እንጂ ስለእነሱ አይደለም፡፡በመጥፎ ሰዎች ምክንያት ጥሩነትሽ አይቁም፡፡መጥፎ ሰው መሆን የሚጎዳው ራስሽን ነው፡፡
+
በራስ መንገድ መኖር እውነትን መኖር ነው፡፡ይህ በማንኛውም ሁኔታ ራስን የመሆን ወኔን ይፈልጋል፡፡ መጀመርያ በጣም ይፈትንሻል፡፡በብዙ ሰዎች ምልከታ እብድ ያስብልሻል፡፡ግን በጊዜ ሂደት የውስጥሽ ሰላም ሲያበራ ሁሉም ይመኝሻል፡፡ድሮ ብልመና ያጣሽው ትኩረት ወደ አንቺ አቅጣጫ ይፈሳል፡፡ሁሉም አብሮሽ ለመሆን ይገፋል፡፡አንቺ ግን ሁሌም ከአንቺ ጋር ሁኚ::
+
ወደ ራስሽ ተመለሺ፡፡መስተዋቱ ላይ የምትመለክችያትን ልጅ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ውደጃት፡፡ከእነ ስህተቷ እቀፊያት፡፡ከእነጥፋቷ ሳሚያት፡፡በሙሉ ልብሽ አብረሻት ሁኚ::
+
# share! @Excellentideas @Excellentideas
Every Test in life makes us

Bitter or Better.

Every Problem comes to

Make Us or Break Us.

Choice is ours,

Whether Become Victim or Victor.

@Excellentideas @Excellentideas