Excellent Ideas
633 subscribers
475 photos
68 videos
38 files
59 links
''THINK-LIKE-THERE-IS-NO-BOX''

For any Ideas,Comment and Opinion @AmenNc

Don't hesitate to contact us we need your ideas!!


Before Leaving The Channel Tell us our Problem/ ከቻናሉ ከመውጣቶ በፊት ችግራችንን ይንገሩን🙏 @AmenNc
Download Telegram
ጳጉሜ 1
የይቅርታ ቀን


እንዴት ደስ ይላል! በሀገር አቀፍ ደረጃ የታወጀ ይቅር የመባባል ቀን። ዓመቱን ሙሉ በብዙ ነገር ውስጥ ላሳለፈ ሰው እስቲ በዓመቱ መጨረሻ ውስጥህ ያለውን ቂም፣ ሀዘን፣ ጥላቻ.... አራግፈን በንፁህ ልብና አዕምሮ ወደ ቀጣዩ ዓመት ተሻገር ከማለት በላይ ምን የምሥራች አለ!

በርግጥ በይቅርታ ሕይወት ለመኖር ቀንም ቀጠሮም አያሻውም ነገርግን ሀገር የይቅርታን ቀን አውጃ ይሄን ትልቅ ዕድል ስትሰጠን ደግሞ በዘመናት ውስጥ ብዙም የማናየው ልምድ ነውና ይበል የሚያሰኝ ነው።

እንግዲህ ከእንቅልፋችን ከነቃንባት ሰዓት ጀምሮ በተለያየ አጋጣሚ ያስቀየምናቸውን ያስቀየሙንን ሁሉ ዛሬ ስልካችንን በማንሳት የይቅርታንና የፍቅርን ቃል በሙሉ ወደ ጆሮአቸው እንልካለን። ሌላው ደግሞ በዙሪያችን ያሉ የተቀያየሙ ሰዎችን የምናስታርቅበት ሰላም የምናወርድበት ልዩ ቀን እንዲሆን እመኛለሁ።

አምናለሁ በዚህ ቀን ብዙ ትዳሮች እንደሚመለሱ፣ ቤተሰብ እንደገና እንሚሰባሰብ፣ የረጅም ጊዜ ደመኞች ዛሬ በይቅርታ ወንድማማች እንደሚሆኑ፣ ብዙ ወዳጆች ወደ ቀድሞ ፍቅራቸው እንደሚመለሱ.... መልካሙን ሁሉ ያሰማን!

ይሄን አስገራሚ ቀንን ላልሰሙ ላላወቁ ሁሉ ሼር በማድረግ እናድርስ!

@Excellentideas
@Excellentideas
Hatred is filled with negative energy. And it won't take us anywhere. Forgiveness radiates positive energy, which reveals itself through hope, faith, love and compassion. Forgiveness will transforms our lives in a positive way. For cynics and those who trade in stereotypes, there is no better place than being in vacuum. Forgive, inspire hope, and love even your haters.

አንዳንድ ጊዜ ጥሩ ወዳጅ የምናገኘው ከይቅርታ በኋላ ነው። ይቅርታ ሰው አዕምሮ ላይ ያስቀመጥነውን መጥፎ ፋይል መደምሰሻ ማፅጃ ነው።
ዮናታን አክሊሉ እንዳለው ''ይቅርታ አልረሳውም ግን አላነሳውም ማለት አይደለም! ይቅርታ ማለት Shift + Delete ነው! Recycle binህ ውስጥ ምንም አለማስቀመጥ ነዉ።''

Happy Sunday!

@Excellentideas
@Excellentideas
If we keep putting off what we really want to do, we are never going to get anywhere!
Stop procrastinating and just go do it.

@Excellentideas
@Excellentideas
Working hard for something we don't care about is called Stress.
Working hard for something we love is called Passion!

🤵Simon Sinek

@Excellentideas
@Excellentideas
Dear all subscribers
The use of this channel ( t.me/newestinventions ) is to share information about the newest inventions, to the whole world. You are lucky you're in this channel, because there are many other people who don't even know that phones exist, because there is no one to tell them. But you can share this channel right now and be the reason others will find out more about the newest inventions of the world.
You can't just sit there and hopping the world will change. We have to make differences now. It is time for the world to grow people diserve to know, so be the reason for its growth and share
አንተ ብቻ አደለህም በህይወት ውስጥ ደክሞህ እሚያውቀው…አንተ ብቻ አደለህም እምታዝነው እና እሚከፋህ…አንተ ብቻ አደለህም ብዙ ነገር ፈልገህ ያጣህው…ሁሉም ሰው የራሱ ፈተና አለው…ማሸነፍ እሚገባው ጦርነት ሁሉም አለው…
የአንተን መንገድ ከሌሎች ጋር አታወዳድር…የአንተን ስኬት በሌሎች ሚዛን አትለካ…የአንተን ደስታ ሌሎች ውስጥ አትፈልግ…አንተን ከ አንተ ጋር ብቻ አወዳድር…ከትላንትህ የተሻለ ለመሆን ሞክር…ከሌሎች ተማር ግን እነሱን ለመሆን አትሞክር…አንተ መሆን ያለብህ እንደራስህ ነው…

ህልምህን እስከምታሳካው ድረስ ለህልምህ ታገል።

@Excellentideas
@Excellentideas
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎥Video

ጠ/ሚ አብይ አህመድ የትራፊክ ፓሊስ ልብስ በመልበስ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ሲያስተላልፉ!!

@Excellentideas
@Excellentideas
You're tired of several failures?
He has failed for 1009 times and now look at him.
#dailyinvestment #business #company
#motivation #startup
#successful

@Excellentideas
@Excellentideas
Events in Addis Ababa and 🇪🇹Ethiopia. 💻Technology, Competitions,conference scholarshipships, trainings,💡Art, 🎵Music,📷Photography, 🔮Poetry,🎛Concert.
#ከእኛ_ጋር_ቤተሰብ_ሲሆኑ
⌨️የ sci- Tech መረጃዎች እናTips
🏅🏆🎁ሽልማት ያላቸው ውድድሮች
🎤ወቅታዊ መረጃዎች
📚✍️ የተለያዮ ዝግጅቶች
#ብቻ_ይቀላቀሉን ዘርፈ ብዙ የሆኑ ማራኪ ጉዳዮችን ያገኛሉ።
Submit events on the bot below

👉👉 @presenteventsbot 👈👈

https://t.me/presentevents
#መለስ_ብሎ_ማየት
ሁለት አይነት ሰዎችን እየተመለከትኩኝ ነው፥ በድንግዝግዝ የሚኖሩ አልያም ተደብቀው የሚኖሩ። ምን ለማለት ፈልጌ ነው?
#2012ኑሮህ ምን ይመስላል?
#ተደብቀህ ነው የኖርከው ውይስ በድንግዝግዝ ነው የኖርከው?
#ምን አሳካህ?
#ምን ስህተት ሰራክ ምን ተማርክበት?
ማለት መጠየቅ አለብህ። በግሪሳ አስተሳሰብ ከተሸበብክ እመነኝ ወይ ተደብቀህ ነው ያለኸው አልያም ድንግዝግዝ ውስጥ ነህ።
2013 ያንኑ ህይወት ልትደግመው ትፈልጋለህ ወይስ የመጣው ይምጣ ብለህ ከራስህ ጋር ተጋፍጠህ ከሰራኸው ጥላ ሰብረህ ለመውጣት አስበሃል?
መለስ ብልህ ተመልከት፥ እስከመቼ የነከሌ ሀሳብ ማገዶ ትሆናለህ? እስከመቼ ይጠቀሙሃል? እስከመቼ እነከሌ ኮከቦቹ አንተ አጨብጫቢያቸው ሁነህ ትቀራለህ?
#ላንቺም ነው፥ እስከመቼ በነሱ ፕሮፋይል ፒክቸር ትኖሪያለሽ? መቼ ነው አንቺስ ፕሮፋይል ፒክቸር ሚያደርጉሽ? እስከመቼ ነው አርቴፊሻል የሆነው ማንነትሽ ብቻ የሚታየው? መቼ ነው ያንቺን ውበት ምናደንቀው?
ያንቺስ ጊዜ መቼ ነው?
#ላንተም ነው፥ በቃ ብለህ ውጣ። ልብህን ተከተል። ሳልኖርበት አልመክርህም፥ ሳላደርገው አድርግ አልልህም። በቃ አንተ ጋር ያለው ትልቅ ነው። እነሱ ሀብታም ከሆኑ አንተን ተጠቅመው ሀብቱ ያለው አንተ ጋር ነው። ውጣ አትፍራ።
2013 ብዙ አዳዲስ ድርጅት ያላችሁ ሰዎችን እጠብቃለው። ብዙ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን እጠብቃለው። 2013 ብዙ ሴት እህቶቻችን የሴትነትን ክብር ይመልሳሉ፥ መልካም እናቶች፣ ሚስቶች እና መሪዎች እናያለን።
መለስ ብሎ መመልከት ምርጫ አይደለም። ከጫጫታው ውጣ፥ ግዜ ውሰድ፥ ራስህን አድስ። አድርገው።
#መልካም_አዲስ_ዓመት

ስለሺ ሳልስ ኡመር

@Excellentideas
@Excellentideas
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኃይሌ💪💪💪
An example of consistency
A Role Model for all of Ethiopians

@Excellentideas
@Excellentideas
እንኳን አደረሳችሁ!

አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የጤና ፣ የስኬት ፣ ያሰባችሁት ሁሉ የሚሳካበት እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።

2013 ዓ/ም በሀገራችን ክፉ የማንሰማበት ፣ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ መፍትሄ አግኝቶ የቀደመው ህይወታቸን የምንመለስበት አድንነታችን የሚጠነክርበት ይሁንልን።

ዓመቱ እናቶች የማያለቅሱበት ፣ አባቶች ማያዝኑበት ፣ ወጣቶች በሀገራቸው ጉዳይ ብሩህ ተስፋ የሚያዩበት ዓመት ያድርግለን።

መልካም አዲስ አመት!

@Excellentideas
@Excellentideas
We will open the Book.
Its pages are Blank.
We are going to put words on them by ourselves.
its first chapter is New Year Day

ተጀምሯል!!!
የደግነት ዓመት ይሁንልን!
Happy New Year.


@Excellentideas
@Excellentideas
አዲሱ ዘመን ፦ በግ ሳይሆን ብሄርተኝነትን፣የምንሰዋበት

፦ዳቦ ሳይሆን ዘረኝነትን፣..........የምንደፋበት፤

፦ጠላ ሳይሆን ጥላቻን፣............እንትፍ የምንልበት፤

፦ጠጅ ሳይሆን ጠመንጃን፣.......የምንጥልበት፤

፦ልብስ ሳይሆን ልባችንን፣.........የምቀይርበት፤

፦ቄጠማን ሳይሆን ቂምን፣........
መሬት ላይ ጎዝጉዘን የምንረግጥበት፤

፦ዘመንን ብቻ ሳይሆን ህሊናችንን፣.....የምንለውጥበት፤

ዘመን ያድርግልን።

@Excellentideas
@Excellentideas
የቤተሰባቸውን የእርሻ መሬት ወርሰው በጋራ የሚሰሩ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ፡፡ አንድኛው ትዳር መስርቶ ትልቅ ቤተሰብ ሲኖረው ሁለተኛው ግን ብቻውን ነበር የሚኖረው፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን ወንድማማቾቹ ከቤተሰባቸው የወረሱትን ሀብትና ንብረት በመከፋፈል በየግላቸው ለመስራት ይስማማሉ፡፡ ያለውንም ሀብት እኩል ተከፋፍለው የየግላቸው ኑሮ ይጀምራሉ፡፡

ወድያውኑ ግን ብቻውን የሚኖረው ወንድሙ ከራሱ ጋር መነጋገር ይጀምራል “ያለውን ሀብትና ትርፍ እኩል መከፋፈላችን አግባብ አልነበረም፡፡ እኔ ብቻየን ነው የምኖረው የሚያስፈልገኝ ነገር ጣም ትንሽ ነው፡፡ እርሱ ግን ብዙ የቤተሰብ ሀላፊነት አለበት” በማለት ያስባል፡፡

እናም በጎተራው ካለው እህል አንድ ጆንያ የሚሆነውን ሁል ግዜ ማታ ማታ እየተደበቀ ወንድሙ ጎተራ ውስጥ ማስገባት ይጀምራል፡፡

በተመሳሳይ ግዜ ሚስትና ልጆች ያሉት ወንድምም በተመሳሳይ ሁኔታ ያስባል “ይህንን ሀብት እኩል መካፈል አልነበረብንም፡፡ እኔኮ ትዳር አለኝ፡፡ሚስቴና ልጆቼ ሁል ግዜ ከጎኔ በመሆናቸው ወደፊት በደንብ ይንከባከቡኛል፡፡ ወንድሜ ግን ብቸኛ ነው፡፡ ወደፊት አጠገቡ ሆኖ የሚንከባከበው እንኳ የለውም” ሲል ያስባል፡፡ እርሱም እንደዚያኘው ወንድም በጎተራ ካለው እህል አንድ ጆንያ የሚሆነውን ሁል ግዜ ማታ ማታ እየተደበቀ ወንድሙ ጎተራ ውስጥ ማስገባት ይጀምራል፡፡

ወንድማማቾቹ በዚህ ሁኔታ ለብዙ ግዜ ኖሩ፡፡

ከብዙ ግዜ ብኋላ ግን ሁለቱንም አንድ ነገር ያስገርማቸው ጀመር፡፡
በጎተራቸው ውስጥ ያለው እህል መጠን እየቀነሰ አለመሄዱ ግራ ያጋባቸዋል፡፡

ሁለቱም የገጠማቸውን ያልተለመደ ነገር ለመመርመር በየግላቸው እየጣሩ ሳለ ከእለታት አንድ ቀን ሌሊት ላይ የተለመደውን ተግባራቸውን ለመፈጸም እህል የተሞላበት ከረጢት እንደተሸከሙ በድንገት ተገናኙ፡፡

ምንም አይነት ቃላት ሳይለዋወጡ ሸክማቸውን መሬት ላይ በመጣል በፍቅር ተቃቅፈው አለቀሱ፡፡

ራስ ወዳድነትን አስወግዶ ለሌላው መኖር ይሉታል ይሄ ነው፡፡
ምን ተማራችሁ ከነዚህ ወንድማማቾች?

@Excellentideas
@Excellentideas
2013 Better Year, Better Personality🙏

@Excellentideas
@Excellentideas
ዛሬ በማህበራዊ ገፅ ላይ ካዝናኑኝ ከዛ ባለፈ ደሞ ትልቅ ትምህርት ካገኘሁባቸው ምስሎች አንዱ ነው።

ሜም የሚባለው የቀልድ አይነት በሀገራችን አሁን ተለምዷል በሚገርም ሁኔታ ከትልቅ እስከ ትንሽ ይከታተለዋል እኔም እሱን በማየት በትንሹም ብዝናናም በየትኛውም ሁኔታ በሰው ስብዕና (Personality) የአካል ወይም የአቅም ሁኔታ የሚቀለዱ ቀልዶች ተቃዋሚ ነኝ ይሄን ሀሳብ ሌላ ጊዜ በደንብ አነሳዋለው ነገርግን ከላይ ካለው ምስል አንድ ቁም ነገር ተማርኩ ሜም የሚሰራባቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ በጣም ስኬታማ፣ ባለሀብቶች፣ ታዋቂዎች ናቸው ሜም ስለሚሰሩት ምንም መረጃ የለኝም ግን በእንዲህ አይነት ቀልድ ላይ የምትሳተፉ ሁሉ ስርዓት ያለውን ቀልድ እየቀለዳችሁ ግን ከነዚህ ስኬታማ ሰዎች ትምህርትን ብትወስዱ ከኢንተርቪያቸው የሚቀለድበትን ነገር ከማውጣት በፊት ለህይወታችሁ የሚጠቅማችሁን እንድትወስዱ እንደ አንድ ትንሽ ወንድማችሁ ምክሬን አስተላልፋለሁ!

አመሰግናለሁ🙏

@Excellentideas
@Excellentideas
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ያደረጉንን አሸዋ ላይ ያደረጉልንን አለት ላይ እንፃፈው!

አስገራሚ ንግግር
ተጋበዙልን!

@Excellentideas
@Excellentideas
የሰው ልጅ ሲፈልግ ተዓምረኛ ካልፈለገ ደግሞ ሰበበኛ ነው!
ዳዊት ድሪምስ

@Excellentideas
@Excellentideas