Excellent Ideas
633 subscribers
475 photos
68 videos
38 files
59 links
''THINK-LIKE-THERE-IS-NO-BOX''

For any Ideas,Comment and Opinion @AmenNc

Don't hesitate to contact us we need your ideas!!


Before Leaving The Channel Tell us our Problem/ ከቻናሉ ከመውጣቶ በፊት ችግራችንን ይንገሩን🙏 @AmenNc
Download Telegram
Battlefield-of-the-Mind-Meyer.pdf
3.7 MB
. Battlefield of the Mind
Joyce Meyer


- Winning the battle in your Mind
-The One-Million Copy Bestseller

@Excellentideas
@Excellentideas
“I will study and prepare myself, and someday my chance will come.” Abraham Lincoln

Have a nice Day😊👍

@Excellentideas
@Excellentideas
#አመስጋኞች_እንሁን!!
(ዘሪሁን ግርማ)

"እንዲረግልን ከምንፈልገው ይልቅ የተደረገልን ይበልጣል። አመስጋኞች እንሁን።

ይህ ቢኖረኝ ደስተኛና አመስጋኝ እሆናለሁ! ያኛው ሲጨመር ደግሞ የምስጋና ፕሮግራም አዘጋጃለሁ! አመስጋኝ የምሆነው ብዙው ነገር ሲሳካልኝ ነው! ብለው የሚያስቡ ሰዎች ያልተረዱት ነገር፣ አሁን ባላቸው ነገር ደስተኛና አመስጋኝ ካልሆኑ ነገም ብዙ ነገር ቢሆኖራቸውም አያመሰግኑም። ያለን ነገር ከሚሰጠን ነገር ይበልጣልና አመስጋኞች እንሁን።

አመስጋኝነት የምናዳብረው ነው። ብዙ ሰው ለማጉረምረም ምክንያቱን ይቆጥራል ያ እንደዚህ ሆነ፤ ይህ እንደዚህ ሆነ አገራችን እንዲህ ናት እነ እንትናም ከድተውኛል፤ ምንም ገንዘብም የለኝም ወዘተ እያልን እንቆጥራለን። አመስጋኝ ሰው ስላለው ጥቂት ነገር ጭምር ያመሰግናል። ማጉረምረምና፤ ሐዘን፣ የበዛ ምኖትና፣ ባለን አለመርካት አመስጋኝ እንዳንሆን ያደርገናል።

"ከከበቡን ጥቂት ቸግሮች ይልቅ እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት ምክንያት ይበዛል።"

አመስጋኝነት የደስታ ምንጭ ነው። ሰዎች ስላረጉልን ጥቂት ነገር አመስጋኝ ልንሆን ይገባል። ስላቀበሉን እቃ፤ ስላሳዩን መንገድ፣ ስለሳዩን ቅንነት፣ ጥቃቅን ስለሆኑ ድርጊቶቻቸው ጭምር ሰዎችን ማመስገን መልመድ አለብን። በህይወት ስላለን፤ አገር አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለች እኛ ግን በህይወት መኖራችን የምስጋናችን መጀመሪያ ነው። ጠዋት ስንነሳ የምናየው ቀን፤ ማሰብ መቻላችን፤ መብላት መቻላችን፣ ያለን ጤንነት ሁሉ የምስጋናችን ምንጭ መሆን ይችላሉ። አመስጋኝነት የደስታ ምንጭ ነው።

"ያለን ካልገባን አመስጋኞች አንሆንም"

@Excellentideas
@Excellentideas
ሁሌ ሳነበው ልቤን የሚነካኝና ውስጤ ያለውን የደግነት ስጦታ እንዳስበው የሚያደርገኝ ታሪክ

የ10 አመት ህጻን ልጅ ኪሱ ላይ ጥቂት ሳንቲሞችን ይዞ አንድ አነስተኛ ካፌ ቤት ጎራ አለ ሰው ጥቅጥቅ ብሏል ከህጻንነቱ የተነሳ ማንም ትኩረት አልሰጠውም ትንንሽ አይኖቹን ከርተት አድርጎ አንድ ክፍት ወንበር አገኘና ሄዶ ቁጭ አለ።

ምን ፈለክ........ አስተናጋጇ በቁጣ እና በንቀት
ልጁ፦ እ..እ...እእ አይስክሬም አለ??
አስተናጋጅ፦ብር ይዘሀል?.....ገልመጥ አድርጋ ጠየቀችው
ህጻኑም ስንት ነው??? አላት
አስተናጋጅ፦ብር ከ ስሙኒ ነው ስትለው ወድያው ኪሶቹ ውስጥ ያለውን ሳንቲሞች አውጥቶ መቁጠር ጀመረ አንድ ብር ከ ሀያ አምስት ሳንቲም ነው የያዘው "ቶሎ በል ባክህ ሌላ ስንት የምታዘዘው ሰው አለ አንተ፦ ሳንቲም ትቆጥራለህ ብላ አመናጨቀችው ህጻኑም ሳንቲሞቹን ቆጥሮ፦ እሺ ኬክ ስንት ነው አላት??..
፦አንድ ብር በቁጣ አለችው
፦ኬክ ብሎ እጆቹን ዘርግቶ ሳንቲሞቹን
ሰጣት ስትቆጥረው አንድ ብር ነው ኬኩን ውርውር አድርጋለት ሄደች ህጻኑም በልቶ ጨርሶ ወጣ አስተናጋጅዋም የበላበትን እቃ ለማንሳት እቃውን ስታነሳ ከ ሳህኑ ስር ሀያ አምስት ሳንቲም አስቀምጦላት ነበር ስታይ ደነገጠች ወድያው እንባዋ ዱብ ዱብ ማለት ጀመረ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች የሚወደውን እና የሚፈልገውን አይስክሬም ብር ከ ሀያ አምስት ከፍሎ ከበላ ለአስተናጋጁዋ የሚሰጣት ነገር ስላልነበረው ያልፈለገውን ኬክ በአንድ ብር በልቶ ስሙኒውን ለሷ ቲፕ አስቀምጦላት ሄደ ትንሹ ልጅ ትንሹዋን ስጋው አሸንፎ ክብርንና ርህራሄ
መስጠት በትህትና ላላስተናገደችው አስተናጋጅ ትህትና አስተማራት።

@Excellentideas
@Excellentideas
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አመሰግናለሁ🙏

የሰው እገዛ አስፈላጊ ነው ምንም የምትናገረው ብዙ ጥሩ ነገር ቢኖር አምኖ የሚሰማህ ካላገኘህ ዋጋ የለውም። የሚሰማህ ሰው ማግኘት ደግሞ ትልቁ ስኬት ይመስለኛል።

አንዳንዶች እንደቀልድ ጀምረው ጥሩ ደረጃ ይደርሳሉ አንዳንዶች ደግሞ በዓላማ እኔ እንደቀልድ አልከፈትኩትም እግረ መንገድም አልከፈትኩትም ስራ ፈትቼም አይደለም የከፈትኩት ትልቅ ስራ ለመስራትም እንጂ!

ትልቁን ስራ ለመስራት ስዘጋጅ አብሮነታችሁን ያሳያችሁኝ ወድ ተከታታዮቼ በጣም ለማሰግናችሁ እወዳለሁ። ሁልጊዜ ነገሮች ሊያደክሙኝ ሲፈልጉ ምንም እየጠቀምክ አይደለም የሚል ድምፅ ማንሾካሾክ ሲጀምር የእናንተ አነቃቂና ተስፋ ሰጪ አስተያየት ተመልሼ ኃይሌን አድሼ እንድሰራ ይረዱኛል!

ለሁላችሁም እግዘብሔር ያክብርልኝ እያልኩ አሁንም የትኛውንም አይነት አስተያየት ቢኖራችሁ @AmenNc ላይ አስተያየት እንድሰጡኝ እጠይቃለሁ። ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር አድርጉልኝ!

በድጋሚ አመሰግናለሁ!🙏

@Excellentideas
@Excellentideas
Dear all subscribers
Most of you have been asking, what is the use of this channel? Why do we waste time on it? Well you're not wasting your time on this channel, because this channel will apreciatte and encourage you to forfill your dreams. And sometimes we even give you advices and new information. So what are you waiting for if you didn't then JOIN and SHARE
t.me/smartme2
ጳጉሜ 1
የይቅርታ ቀን


እንዴት ደስ ይላል! በሀገር አቀፍ ደረጃ የታወጀ ይቅር የመባባል ቀን። ዓመቱን ሙሉ በብዙ ነገር ውስጥ ላሳለፈ ሰው እስቲ በዓመቱ መጨረሻ ውስጥህ ያለውን ቂም፣ ሀዘን፣ ጥላቻ.... አራግፈን በንፁህ ልብና አዕምሮ ወደ ቀጣዩ ዓመት ተሻገር ከማለት በላይ ምን የምሥራች አለ!

በርግጥ በይቅርታ ሕይወት ለመኖር ቀንም ቀጠሮም አያሻውም ነገርግን ሀገር የይቅርታን ቀን አውጃ ይሄን ትልቅ ዕድል ስትሰጠን ደግሞ በዘመናት ውስጥ ብዙም የማናየው ልምድ ነውና ይበል የሚያሰኝ ነው።

እንግዲህ ከእንቅልፋችን ከነቃንባት ሰዓት ጀምሮ በተለያየ አጋጣሚ ያስቀየምናቸውን ያስቀየሙንን ሁሉ ዛሬ ስልካችንን በማንሳት የይቅርታንና የፍቅርን ቃል በሙሉ ወደ ጆሮአቸው እንልካለን። ሌላው ደግሞ በዙሪያችን ያሉ የተቀያየሙ ሰዎችን የምናስታርቅበት ሰላም የምናወርድበት ልዩ ቀን እንዲሆን እመኛለሁ።

አምናለሁ በዚህ ቀን ብዙ ትዳሮች እንደሚመለሱ፣ ቤተሰብ እንደገና እንሚሰባሰብ፣ የረጅም ጊዜ ደመኞች ዛሬ በይቅርታ ወንድማማች እንደሚሆኑ፣ ብዙ ወዳጆች ወደ ቀድሞ ፍቅራቸው እንደሚመለሱ.... መልካሙን ሁሉ ያሰማን!

ይሄን አስገራሚ ቀንን ላልሰሙ ላላወቁ ሁሉ ሼር በማድረግ እናድርስ!

@Excellentideas
@Excellentideas
Hatred is filled with negative energy. And it won't take us anywhere. Forgiveness radiates positive energy, which reveals itself through hope, faith, love and compassion. Forgiveness will transforms our lives in a positive way. For cynics and those who trade in stereotypes, there is no better place than being in vacuum. Forgive, inspire hope, and love even your haters.

አንዳንድ ጊዜ ጥሩ ወዳጅ የምናገኘው ከይቅርታ በኋላ ነው። ይቅርታ ሰው አዕምሮ ላይ ያስቀመጥነውን መጥፎ ፋይል መደምሰሻ ማፅጃ ነው።
ዮናታን አክሊሉ እንዳለው ''ይቅርታ አልረሳውም ግን አላነሳውም ማለት አይደለም! ይቅርታ ማለት Shift + Delete ነው! Recycle binህ ውስጥ ምንም አለማስቀመጥ ነዉ።''

Happy Sunday!

@Excellentideas
@Excellentideas
If we keep putting off what we really want to do, we are never going to get anywhere!
Stop procrastinating and just go do it.

@Excellentideas
@Excellentideas
Working hard for something we don't care about is called Stress.
Working hard for something we love is called Passion!

🤵Simon Sinek

@Excellentideas
@Excellentideas
Dear all subscribers
The use of this channel ( t.me/newestinventions ) is to share information about the newest inventions, to the whole world. You are lucky you're in this channel, because there are many other people who don't even know that phones exist, because there is no one to tell them. But you can share this channel right now and be the reason others will find out more about the newest inventions of the world.
You can't just sit there and hopping the world will change. We have to make differences now. It is time for the world to grow people diserve to know, so be the reason for its growth and share
አንተ ብቻ አደለህም በህይወት ውስጥ ደክሞህ እሚያውቀው…አንተ ብቻ አደለህም እምታዝነው እና እሚከፋህ…አንተ ብቻ አደለህም ብዙ ነገር ፈልገህ ያጣህው…ሁሉም ሰው የራሱ ፈተና አለው…ማሸነፍ እሚገባው ጦርነት ሁሉም አለው…
የአንተን መንገድ ከሌሎች ጋር አታወዳድር…የአንተን ስኬት በሌሎች ሚዛን አትለካ…የአንተን ደስታ ሌሎች ውስጥ አትፈልግ…አንተን ከ አንተ ጋር ብቻ አወዳድር…ከትላንትህ የተሻለ ለመሆን ሞክር…ከሌሎች ተማር ግን እነሱን ለመሆን አትሞክር…አንተ መሆን ያለብህ እንደራስህ ነው…

ህልምህን እስከምታሳካው ድረስ ለህልምህ ታገል።

@Excellentideas
@Excellentideas
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🎥Video

ጠ/ሚ አብይ አህመድ የትራፊክ ፓሊስ ልብስ በመልበስ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ሲያስተላልፉ!!

@Excellentideas
@Excellentideas
You're tired of several failures?
He has failed for 1009 times and now look at him.
#dailyinvestment #business #company
#motivation #startup
#successful

@Excellentideas
@Excellentideas
Events in Addis Ababa and 🇪🇹Ethiopia. 💻Technology, Competitions,conference scholarshipships, trainings,💡Art, 🎵Music,📷Photography, 🔮Poetry,🎛Concert.
#ከእኛ_ጋር_ቤተሰብ_ሲሆኑ
⌨️የ sci- Tech መረጃዎች እናTips
🏅🏆🎁ሽልማት ያላቸው ውድድሮች
🎤ወቅታዊ መረጃዎች
📚✍️ የተለያዮ ዝግጅቶች
#ብቻ_ይቀላቀሉን ዘርፈ ብዙ የሆኑ ማራኪ ጉዳዮችን ያገኛሉ።
Submit events on the bot below

👉👉 @presenteventsbot 👈👈

https://t.me/presentevents
#መለስ_ብሎ_ማየት
ሁለት አይነት ሰዎችን እየተመለከትኩኝ ነው፥ በድንግዝግዝ የሚኖሩ አልያም ተደብቀው የሚኖሩ። ምን ለማለት ፈልጌ ነው?
#2012ኑሮህ ምን ይመስላል?
#ተደብቀህ ነው የኖርከው ውይስ በድንግዝግዝ ነው የኖርከው?
#ምን አሳካህ?
#ምን ስህተት ሰራክ ምን ተማርክበት?
ማለት መጠየቅ አለብህ። በግሪሳ አስተሳሰብ ከተሸበብክ እመነኝ ወይ ተደብቀህ ነው ያለኸው አልያም ድንግዝግዝ ውስጥ ነህ።
2013 ያንኑ ህይወት ልትደግመው ትፈልጋለህ ወይስ የመጣው ይምጣ ብለህ ከራስህ ጋር ተጋፍጠህ ከሰራኸው ጥላ ሰብረህ ለመውጣት አስበሃል?
መለስ ብልህ ተመልከት፥ እስከመቼ የነከሌ ሀሳብ ማገዶ ትሆናለህ? እስከመቼ ይጠቀሙሃል? እስከመቼ እነከሌ ኮከቦቹ አንተ አጨብጫቢያቸው ሁነህ ትቀራለህ?
#ላንቺም ነው፥ እስከመቼ በነሱ ፕሮፋይል ፒክቸር ትኖሪያለሽ? መቼ ነው አንቺስ ፕሮፋይል ፒክቸር ሚያደርጉሽ? እስከመቼ ነው አርቴፊሻል የሆነው ማንነትሽ ብቻ የሚታየው? መቼ ነው ያንቺን ውበት ምናደንቀው?
ያንቺስ ጊዜ መቼ ነው?
#ላንተም ነው፥ በቃ ብለህ ውጣ። ልብህን ተከተል። ሳልኖርበት አልመክርህም፥ ሳላደርገው አድርግ አልልህም። በቃ አንተ ጋር ያለው ትልቅ ነው። እነሱ ሀብታም ከሆኑ አንተን ተጠቅመው ሀብቱ ያለው አንተ ጋር ነው። ውጣ አትፍራ።
2013 ብዙ አዳዲስ ድርጅት ያላችሁ ሰዎችን እጠብቃለው። ብዙ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን እጠብቃለው። 2013 ብዙ ሴት እህቶቻችን የሴትነትን ክብር ይመልሳሉ፥ መልካም እናቶች፣ ሚስቶች እና መሪዎች እናያለን።
መለስ ብሎ መመልከት ምርጫ አይደለም። ከጫጫታው ውጣ፥ ግዜ ውሰድ፥ ራስህን አድስ። አድርገው።
#መልካም_አዲስ_ዓመት

ስለሺ ሳልስ ኡመር

@Excellentideas
@Excellentideas
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኃይሌ💪💪💪
An example of consistency
A Role Model for all of Ethiopians

@Excellentideas
@Excellentideas
እንኳን አደረሳችሁ!

አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የጤና ፣ የስኬት ፣ ያሰባችሁት ሁሉ የሚሳካበት እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።

2013 ዓ/ም በሀገራችን ክፉ የማንሰማበት ፣ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ መፍትሄ አግኝቶ የቀደመው ህይወታቸን የምንመለስበት አድንነታችን የሚጠነክርበት ይሁንልን።

ዓመቱ እናቶች የማያለቅሱበት ፣ አባቶች ማያዝኑበት ፣ ወጣቶች በሀገራቸው ጉዳይ ብሩህ ተስፋ የሚያዩበት ዓመት ያድርግለን።

መልካም አዲስ አመት!

@Excellentideas
@Excellentideas