Excellent Ideas
633 subscribers
475 photos
68 videos
38 files
59 links
''THINK-LIKE-THERE-IS-NO-BOX''

For any Ideas,Comment and Opinion @AmenNc

Don't hesitate to contact us we need your ideas!!


Before Leaving The Channel Tell us our Problem/ ከቻናሉ ከመውጣቶ በፊት ችግራችንን ይንገሩን🙏 @AmenNc
Download Telegram
Millionaires set themselves apart by the skills they possess. These skills are too much that the average person can not realize or think that they can never achieve them all. That's what made millionaires super rich in the first place.

@Excellentideas
@Excellentideas
''ኤርትራ ውስጥ ብትወለድና እትብትህ እዛ ቢቀበር እትብትህን የበላው ምስጥ ግን ደቡብ ኢትዮጵያ ላለመድረሱ እርግጠኛ አትሁን። ጋምቤላ ተወለድ እትብትህን ጋምቤላ ውስጥ የበላው ምስጥ ግን አፋር ላለመድረሱ እርግጠኛ አትሁን። ለምን ከምስጡ ለመሻል አትሻም? ለምን ትጠባለህ?... ሰፊ አገር እያለህ ለምን ጠባብ ክልል አርገህ እንዲሆን ትመኛለህ?.... አህያ እንኳን ጋጣው ሲጠበዉ ይራገጣል። የማያሳፍርህ ነገር ቢኖር በኢትዮጵያዊነትህ ማመንህ ብቻ ነው በቃ!!''

🖋 ይስማዕከ ወርቁ

@Excellentideas
@Excellentideas
The Fixed mindset says, "Are you sure you can do it? Maybe you don't have the talent."

The Growth mindset answers, "I'm not sure I can do it now, but I think I can learn to with time and effort."

Fixed mindset: "What if you fail--you'll be a failure."

Growth mindset: "Most successful people had failures along the way."

@Excellentideas
@Excellentideas
ደግነት ማየት የተሳናቸው የሚያዩት መስማት የተሳናቸው የሚሰሙት ልዩ ቋንቋ ነው!

@Excellentideas
@Excellentideas
You’re braver than you believe, and stronger than you seem, and smarter than you think.

💡

Your mind will believe what you continuously tell it. So tell it that you’re smart, ambitious, cute and not afraid to go for it.

@Excellentideas
@Excellentideas
አንድ የ78 ዓመት አባት እራሳቸውን ስተው ወደሆስፒታል ይወሰዳሉ ። ለ24 ሰዓት የሚያቆያቸው የመተንፈሻ ኦክስጅን ተሰጣቸው ። ከጥቂት ግዜ በኃላ ተሻላቸውና ዶክተሩ የተጠቀሙበትን ሂሳብ የ500 ዶላር ደረሰኝ ሰጣቸው ። እኝህ አባትም የተሰጣቸውን ደረሰኝ በተመለከቱ ግዜ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ ። ዶክተሩም ስለ ገንዘቡ ማልቀስ አይገባዎትም በአንድ ግዜም ባይሆን ቀስ እያሉ መክፈል እንደሚችሉ ነገራቸው ። ሆኖም እኝህ አባት " እኔ የማለቅሰው ስለዚህ ገንዘብ አደለም ገንዘቡን በሙሉ የመክፈል አቅም አለኝ ፤ የማለቅሰው 24 ሰኣት ለተነፈስኩበት ኦክስጅን 500 ዶላር ልከፍል በመሆኑ ነው ፤ ነገር ግን ላለፋት 78 አመታት የእግዚአብሔርን ንፁህ አየር በነፃ ስተነፍስ ኖሬያለው ለእነዚ ሁሉ ግዜያት መክፈል ቢኖርብኝ ምን ያህል የእግዚአብሔር እዳ እንዳለብኝ መገመት ትችላለህ ?? " በማለት መለሱለት።

በዚህች ጥቂት ጊዜያት እንኳን በማስክ መሄድ እንደኔ የመረረው ካለ ምንያህል ፈጣሪ እንደሚወደን በነፃነት እንድንተነፍስ በሰጠን ንፁህ አየር መረዳት እንችላለን!

በሁሉ አመስግኑ🙏

@Excellentideas
@Excellentideas
'HAKUNA MATATA'

We often see this word in different contexts but we do not know its meaning in it. When I read Hakuna Matata's philosophy, I shared it because the message inspired and encouraged me

The word is an East African Swahili word from the movie The Lion king, which means 'Don't worry'

Timon and Pumba are the two characters of The Lion King who told Simba to enjoy life no matter how tough it gets do not expect anything from anyone do whatever you heart says. hence, Hakuna Matata means no worries philosophy discover yourself freely and don't worry about the past as dwelling over the past only ruins the present and future. the song Wherein the characters of the movie describe Hakuna Matata's definition and the meaning is quite funny and cheery songs.
The philosophy behind the phrase Hakuna Matata Can really transform your life. All you need to understand what hakuna matata stands for

Not only in movies, we can also apply this phrase everywhere in our lives. Like, what if someone says, you are bad at this… and you just say “Hakuna Matata!” This was just an example of no worries philosophy, you can apply it anywhere you In the Bible also, Paul wrote: “Do not be anxious over anything. If something or someone troubles you, just say Hakuna Matata. As simple as that!

@Excellentideas
@Excellentideas
'HAKUNA MATATA' (Translated)

ብዙ ጊዜ ይሄን ቃል በተለያየ አጋጣሚ እናየዋለን ግን ውስጥ ትርጉሙን አናውቅም። እኔም የHakuna Matataን ፍልስፍና ባነበብኩ መልዕክቱ ስላነቃኝና ስላበረታታኝ አካፈልኳቹ....

ቃሉ The Lion king ከተሰኘ ፊልም ላይ የተወሰደ የምስራቅ አፍሪካ የስዋሂሊ ቃል ሲሆን ትርጉሙም 'በምንም አትጨነቁ' ይሰኛል።

The Lion King በተሰኘው ፊልም ላይ Timonና Pumba የተሰኙ ገፀባሕርያት ሲምባ ለተሰኘው መሪ ገፀ ባህሪ ''ምንም አይነት ነገር ቢገጥመው በህይወቱ መደሰት እንዳለበትና ከማንም ምንም ሳይጠብቅ ልቡ ያለውን ብቻ እንዲያደርግ'' ያስተምሩታል እናም 'Hakuna Matata' የሚለውን ቃል ይጠቀሙበት ነበር ይህ ቃል ነው አሁን ራሱን ወደ ቻለ 'በምንም እንዳትጨነቅ' ወደሚል ፍልስፍና የመጣው ይህም ፍልስፍና...

''ራስህን ወይም ውስጥህ ያለውን አቅም ፈልግ፣ ላለፈው ነገር አትጨነቅ ምክንያቱም የአሁኑንና የወደፊት ህይወትህን ስለሚጎዳብህ'' ይላል።

'Hakuna Matata' ከሚለው ቃል በስተጀርባ ያለው ቅን ሀሳብ በርግጥ ህይወታችንን መቀየር የሚችል ነው። እኛ መረዳት ያለብን የቃሉን ፍሬ ሀሳብ ነው።

ከፊልሙ ባለፈ በህይወታችን ዉስጥ ልንተረጉመው የሚገባ ቃል ነው ብዬ አምናለሁ በመጽሐፍ ቅዱስም ጳዉሎስ 'በአንዳች አትጨነቁ' በሚል አስቀምጦታል። ምንም አይነት ችግር ሲገጥማችሁ Just Say 'Hakuna Matata' - የአሁኑም ችግር እንዳለፈው ቀላል ነው!!!

@Excellentideas
@Excellentideas
You were born in poverty, that is not your fault.
You die in poverty, that is absolutely your fault.

በድህነት ውስጥ መወለድህ የአንተ ጥፋት አይደለም
በድህነት ውስጥ መሞት ግን ሙሉ በሙሉ የአንተ ጥፋት ነው!!

@Excellentideas
@Excellentideas
Channel photo updated
ኑሮ ቢገፋኝ ፥ የማልወድቅለት
የጊዜ ሞገድ ፥ ያላደቀቀኝ
የመከራ ዶፍ ፥ ያልነቀነቀኝ
ለሙሾ ሲያጩኝ ፥ ቅኔ የምቀኝ
በግራ ሲሉኝ ፥ የምገኝ በቀኝ
ግትር ጠላቴን ፥ ባጭር አንካሴ
ራስ ምታቴን ፥ በዳማከሴ
ነቅዬ ምጥል
ነገር በነገር ፥ የማብጠለጥል
በጠላቴ ፊት ፥ ቀንድ የማበቅል
ልክ እንደዋልያ ፥ ተራራ መራጭ
ልክ እንዳሞራ ፥ ብርንዶ ቆራጭ
እንደመሀረብ ፥ ቤቴን በኪሴ
እንደንቅሳት ፥ ተስፋን በጥርሴ
ይዤ የምዞር
ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ። 😎

አቤል ጎሳዬ

@Excellentideas
@Excellentideas
Change begins from your MIND
ለውጥ ከአዕምሮህ ነው የሚጀምረው


ሁላችንም ማለት ይቻላል ብንችል መቀየር የምንፈልጋቸው ብዙ ነገሮች አሉን። ከራሳችን ጀምሮ በቤት ውስጥ በሰፈር በአከባቢ እያለ እስከ ዓለም ድረስ ይሄ መለወጥ የምንለው ብዙ ነገር እንዳለ እርግጠኛ ነኝ። ይሄ የሆነበት ምክንያት ለውጥ ውስጣችን ያለና የተቀመጠ ነገር ስለሆነ ነው ነገር ግን ይሄን በውስጣችን ያለውን ያለውን የለውጥ ፍላጎት በጊዜ ሂደት ውስጥ አዳፍነነው ቋሚ ወይም ለውጥን መቀበል የሚከብደው ሰው እንሆናለን።

ብዙዎቻችን ያለንበትን ቦታ ወይም ሁኔታ ስለለመድነው ከዛ መንቀሳቀስ አንፈልግም ወይ እንፈራለን። ለምሳሌ ብዙዎቻችን የምንኖርበትን ቤት እንዲቀየር እንፈልጋለን ግን መለወጥ አንፈልግም ምክንያቱም ለምደነዋል ሲቀጥል የምንበላውን የምግብ አይነት እንኳን መቀየር ይከብደናል (ለዛ ነው አሜሪካና አውሮፓም ሄደው እንጀራ ከኢትዮጵያ የሚያስጭኑት) በአጠቃላይ የኑሮ ዘይቤያችንን መቀየር ከባድ መስሎ ይታየናል።

ይኸውላችሁ ለውጥ የሚጀምረው ከአዕምሮህ ነው! አዕምሮህን ሳትቀይር ቤትህን ኑሮህን አትቀይርም። አዕምሮህን ከለመደው ህይወት ዛሬ አነቃንቀው አዲስ ህይወትን ፈላጊ አድረገው! ነገን በአዲስ ተስፋና እምነት እንዲጠብቅ ንገረው! ያኔ ህይወትህን ለመለወጥ መነሳት ትጀምራለህ ያለህበት ቦታ አንተን እንደማይመጥንህ ይገባሃል ለመለወጥ መስራትና አንድ እርምጃ መራመድ ትጀምራለህ!
ዛሬም ደግመዋለው 1000 ኪሜ. ለመጓዝ ዛሬ አንዷን እርምጃ ተራመድ!!!

እናም በጊዜው ቋንቋ ሀሳቤን ስጠቀልለው የለውጡ አመራር ያለው አዕምሮ ውስጥ ነው😉

አመሰግናለሁ
አሜን ዳንኤል

@Excellentideas
@Excellentideas
@inspiringbooks_Buffett_Warren_Liberman_Nic_McGill_Craig_Being_Warren.epub
1 MB
. BEING WARREN BUFFET
NIC LIBERMAN


Life Lesson from a cheerful Billionaire.

◾️Little is known about what really makes Warren Buffett, the business magnate, investor and philanthropist, so extraordinarily successful🎖.

@Excellentideas
@Excellentideas
Its like a new Sunrise of Hope, Prosperity, Happiness.
Its like a new Beginning of Thoughts, Words, Actions.
Its like a new Day of Energy, Strength, Ideas.
Have a fruitful day ahead.. 🤗👍

@Excellentideas
@Excellentideas
እኔ👉 ከአማራነት
👉ከትግሬነት
👉ከኦሮሞነት
እበልጣለሁ
ሰው👉 ከቋንቋ, ከሀገር, ከባህል,ከሀይማኖት ይበልጣል ።

@Excellentideas
@Excellentideas
Battlefield-of-the-Mind-Meyer.pdf
3.7 MB
. Battlefield of the Mind
Joyce Meyer


- Winning the battle in your Mind
-The One-Million Copy Bestseller

@Excellentideas
@Excellentideas
“I will study and prepare myself, and someday my chance will come.” Abraham Lincoln

Have a nice Day😊👍

@Excellentideas
@Excellentideas
#አመስጋኞች_እንሁን!!
(ዘሪሁን ግርማ)

"እንዲረግልን ከምንፈልገው ይልቅ የተደረገልን ይበልጣል። አመስጋኞች እንሁን።

ይህ ቢኖረኝ ደስተኛና አመስጋኝ እሆናለሁ! ያኛው ሲጨመር ደግሞ የምስጋና ፕሮግራም አዘጋጃለሁ! አመስጋኝ የምሆነው ብዙው ነገር ሲሳካልኝ ነው! ብለው የሚያስቡ ሰዎች ያልተረዱት ነገር፣ አሁን ባላቸው ነገር ደስተኛና አመስጋኝ ካልሆኑ ነገም ብዙ ነገር ቢሆኖራቸውም አያመሰግኑም። ያለን ነገር ከሚሰጠን ነገር ይበልጣልና አመስጋኞች እንሁን።

አመስጋኝነት የምናዳብረው ነው። ብዙ ሰው ለማጉረምረም ምክንያቱን ይቆጥራል ያ እንደዚህ ሆነ፤ ይህ እንደዚህ ሆነ አገራችን እንዲህ ናት እነ እንትናም ከድተውኛል፤ ምንም ገንዘብም የለኝም ወዘተ እያልን እንቆጥራለን። አመስጋኝ ሰው ስላለው ጥቂት ነገር ጭምር ያመሰግናል። ማጉረምረምና፤ ሐዘን፣ የበዛ ምኖትና፣ ባለን አለመርካት አመስጋኝ እንዳንሆን ያደርገናል።

"ከከበቡን ጥቂት ቸግሮች ይልቅ እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት ምክንያት ይበዛል።"

አመስጋኝነት የደስታ ምንጭ ነው። ሰዎች ስላረጉልን ጥቂት ነገር አመስጋኝ ልንሆን ይገባል። ስላቀበሉን እቃ፤ ስላሳዩን መንገድ፣ ስለሳዩን ቅንነት፣ ጥቃቅን ስለሆኑ ድርጊቶቻቸው ጭምር ሰዎችን ማመስገን መልመድ አለብን። በህይወት ስላለን፤ አገር አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለች እኛ ግን በህይወት መኖራችን የምስጋናችን መጀመሪያ ነው። ጠዋት ስንነሳ የምናየው ቀን፤ ማሰብ መቻላችን፤ መብላት መቻላችን፣ ያለን ጤንነት ሁሉ የምስጋናችን ምንጭ መሆን ይችላሉ። አመስጋኝነት የደስታ ምንጭ ነው።

"ያለን ካልገባን አመስጋኞች አንሆንም"

@Excellentideas
@Excellentideas