Excellent Ideas
633 subscribers
475 photos
68 videos
38 files
59 links
''THINK-LIKE-THERE-IS-NO-BOX''

For any Ideas,Comment and Opinion @AmenNc

Don't hesitate to contact us we need your ideas!!


Before Leaving The Channel Tell us our Problem/ ከቻናሉ ከመውጣቶ በፊት ችግራችንን ይንገሩን🙏 @AmenNc
Download Telegram
Your biggest asset is your brain. Your mind controls your life, your confidence, your relationships, your purpose, your strengths, your success. Remember the Quality of your thoughts determines Quality of your life.

@Excellentideas
@Excellentideas
Be who you want to be, not what others want to see.
#beyourself

@Excellentideas
@Excellentideas
ሰው በሰውነቱ
የምግብ ቤት ባለቤት የሆነ ሰውየ :በደንበኞቹ መሀል ሲዘዋወር አንድ
ዝነኛ ጋዜጠኛ ይመለከታል። ወድያው ባለቤትየው አስተናጋጂቱን ጠርቶ ”
እዛ ጥግ ላይ የተቀመጠው ጋዜጠኛ ይታይሻል? ሂጅና የሚፈልገውን
እየጠየቅሽ ተንከባከቢው!! ወጥ ካነሰው ጨምሪለት!! እንዲያውም ለኔ
ራት ከተሰራው ዶሮ አንድ ቅልጥም ብትሰጪው ደስ ይለኛል። ሲያንሰው
ነው!! እንዴት ያለ የሰላ ጭንቅላት ያለው ሰው መሰለሽ!!! የስራ ጫና
የበዛበት ይመስላል። ደሞ ትንሽ እንደደበረው ፊቱ ያስታውቃል። እስቲ በኔ
ሂሳብ አንድ ብርጭቆ ወይን ቅጂለት ። ድብርቱን ያባርርለታል!!”
” የደበረው ዛሬ ከስራው ስለተጫረ ነው ! ምፅ!” አለች አስተናጋጂቱ።
“የምርሽን ነው?”
” አርሴማ ምስክሬ ናት ”
የምግብ ቤቱ ባለቤት ድምፁን ከረር አድርጎ እንዲህ አለ: “እንደሱ
አትይኝም ታድያ!! ይበለው!! እንደ ስራውማ ቢሆን ከቢሮው ብቻ ሳይሆን
ካገር መባረር ነበረበት!! ይሄ ቀዳዳ!! የሽንትቤት አገልግሎት አይሰጡም
እያለ ስንት ምግብ ቤቶችን በማዘጋጃቤት እንዲታሸጉ አድርጉዋል
መሰለሽ? ይሄ አሰልጥ!! በይ አጠገቡ ቁሚና ብርጭቆና ማንኪያውን ወደ
ቦርሳው እንዳይከት ባይነቁራኛ ተከታተይው።”
….
ሰውን በሰውነቱ መውደድ የሚባል ነገር በባህላችን ትርጉም አለው? ።
ብዙ ጊዜ:ለሰዎች ፍቅርና ርህራሄ ፍቅርና አክብሮት የምናሳየው
ይጠቅሙናል ብለን ካሰብን ነው። ምንም አያመጡም ብለን
የምናስባቸውን ሰዎች ማክበር ይቸግረናል። ምንም አይሰጡንም ብለን
የምናስባቸውን ሰዎች መውደድ ያቅተናል።
“እገሌ ሞተ አሉ የልቤ ወዳጅ
የሚያበላኝ ጮማ እሚያጠጣኝ ጠጅ”
ብላ ያለቀሰቺው ሴትዮ እንባ ያፈሰሰችው ለአቶ እገሌ አይደለም። ከአቶ
እገሌ ሞት ጋር አብሮ ለሚቀረው ጠጅ እና ጮማ ነው።
እና አንዳንዴ :በግል ጥቅም ስሌት ላይ ያልተመሰረተ የሰውም ሆነ ያገር
ፍቅር ይኖር ይሆን እላለሁ?
በባህላችን ሹመት አጥብቀን እንወዳለን ። ካቶ ሀዲስ አለማየሁ በቀር
ስልጣን በሰፌድ ቀርቦለት “ይለፈኝ” ያለ በታሪክ አላቅም። ሹመት
ባይደርሰን እንኩዋን : ልጆቻችንን “ተሾመ ” ነጋሲ : ሞቱማ ” እያልን
በመሰየም ጥማችንን እናስታግሳለን ። በሹም ፊት ሞገስ ለማግኘት
እድሚያችንን ክብራችንን አንዳንዴም ህይወታችንን እንገብራለን።
ለተሾመ ሰው ያለን አክብሮት ወደ አምልኮ የተጠጋ የሆነውን ያህል :
ለተሻረና ለተሸነፈ ሰው ርህራሄ አናቅም።
በታሪካችን: አንድ ሹም ከስልጣን ከወረደ ህይወቱን ያጣል። ህይወቱን
ባያጣ የሰውነት ክብሩን ያጣል። በምድር ላይ መኖሩን የሚያስጠላ
ውርደት ይጠግባል። በህይወት ተርፈው ስልጣን የለቀቁ አንዳንድ
ነገስታት በከተማ ከመኖር በገዳም መንነው መኖር የሚመርጡት ለዚህ
ይሆናል። ለምሳሌ እቴጌ ጣይቱ በስልጣን ላይ በነበሩ ጊዜ ” እቴጌ
ጣይቱ እቴጌ ብርሃን” እየተባሉ ይሞገሱ ነበር። ከስልጣን ከተወገዱ
በሗላ አድመኛው ጃንሜዳ ላይ ተሰብስቦ እንዳይሸጡ እንዳይለወጡ
አድርጎ ዘለፋቸው።
እናም እቴጌይቱ ሲያስከብራቸው የኖረው ወንበራቸው እንጂ ሰብእናቸው
አለመሆኑን ሲባንኑ-
” ከተቀመጥኩበት -ከስፍራየ ቢያጣኝ
“አንቱ ” ያለኝ ሁሉ -“አንቺ “ሊለኝ ቃጣኝ”
ብለው አንጎራጎሩ።
ተስፋ አንቁረጥ!! ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚገባውን ፍቅርና ክብር
የሚሰጡ ሰዎች ቁጥራቸው ይነስ እንጂ በየዘመኑ በየቦታው መኖራቸው
ያፅናናናል።
በድሮ ጊዜ ተደላ ጉዋሉ የተባለ ጌታ : አሉላ ተሰማ የተባለውን የስልጣን
ተፎካካሪውን ማርኮ ይዞ መንቆረር ገበያ ላይ አርባ ገረፈው። ግርፊያውን
ቆሞ እየተመለከተ ከሚዝናናው ገበያተኛ ማሃል – አንዲት ልበ-ብሩህ
ባላገር እንዲህ ብላ በግጥም ሀሳቡዋን ገለፀች።
“ከጮማው አልበላሁ ከጠጁም አልጠጣሁ
አላውቀው አያውቀኝ
አሉላ ተሰማ ቢቀጣ ጨነቀኝ”
ውለታ ሳይቆጥሩ: ሳይውቁን ሳናውቃቸው :የሚጨነቁልንን ያብዛልን!!

አለ / በ በዕውቀቱ ስዩም / እውነቱን ነው ።

እኔም እላለሁ ሰውን ከሚገባው በላይም መካብ፤ቢበድለን መውቀስም መናገርም መንታ ምላስ ያረገናልና ሁሉም በስራው እንጂ በጊዜያዊ ስልጣኑ መሆን የለበትም ብዬ አምናለሁ።ማንም ወደደም ጠላም ከፍ ያለው ዝቅ ሊል ዝቅ ያለው ከፍ ሊል የተፈጥሮ ግዴታ ነውና።

ነብዩ ሰለሞን ነኝ ሰላም አዳር

@Excellentideas
@Excellentideas
ስኬትን ፍለጋ

“ስኬትን ከፈለክ ስኬትን ዓላማህ አድርገህ አትያዝ፡፡ የምታምንበትንና የምትወደውን ነገር ከልብህ ስታደርግ ስኬት ራሱ ይመጣል” - David Frost

ለትክክለኛ አላማ መቆም ስኬትን ይቀድማል እንጂ ስኬት አላማን አይቀድምም፡፡ አንዳንድ ሰዎች፣ “ቢሳካልኝ ኖሮ ይህንና ያንን አደርግ ነበር” በማለት በገንዘብና በተለያዩ አቅጣጫዎች “ቢሳካላቸው” ሊያደርጉ ስለሚፈልጉት የወደፊት አላማ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ አንድ ማስታወስ ያለባቸው እውነታ ግን አንድን አላማ ይዘው መስራታቸው ወደ ስኬት እንደሚወስዳቸው ነው፡፡ በሌላ አባባል፣ ተሳካላቸው በመባል የሚታወቁ ሰዎች ለስኬት የኖሩ ሰዎች ሳይሆኑ ለአንድ አላማ በጽንአት የኖሩ ናቸው፤ ያንን ሲያደርጉ ስኬት ተከተላቸው፡፡

ለስኬት የሚኖር ሰው ስኬት ያጣ ሲመስለው ያቆማል፡፡ ለአላማ የሚኖር ሰው ግን ስኬት ያላገኘ ቢመስለውም እንኳ ጉዞውን ይቀጥላል፣ ምክንያቱም አላማ የተሰኘውን የስኬቶችን ሁሉ ስኬት በእጁ ጨብጧልና ነው፡፡ “የምትወደውንና መልካም የሆነውን ነገር አድርግ፣ ያንን የምታደርገውን ነገር ደግሞ ውደደው” የሚለው አባባል እውነት ነው፡፡ ስኬትን ፍለጋ ከአላማህ ውጪ የሆነን “ታላቅ” ነገር ከማድረግ፣ አላማን በመከተል አስቸጋሪ ጎዳና መጓዝ ይመረጣል፡፡

ዶ/ር ምህረት ደበበ

@Excellentideas
@Excellentideas
ለውጥ የለም ማለት ህይወት የለም ማለት ነው።
ከተደበቅንበት የሚያወጣን፣ ከመርጋት እና ከመሽተት እንደወንዝ ያለድንበር እንድንፈስ የሚያደርገን ባለውለታችን ለውጥ ነው።
ዛሬ እየኖርን ያለነው የትናንት ሃሳባችንን ነው!
የወደፊት ኑሮአችንን ለመለወጥ የዛሬውን ሃሳባችንን መለወጥ አለብን።


@Excellentideas
@Excellentideas
Forwarded from Smart me (Mysterious me)
Most of you want to change the world in the future, but why in the future. Can't you do it today, Yes you can. If you want do it do it today, if you want it, why not now. The future is already booked. This is your free time.
IT IS TIME
@smartme2
@smartme2
Success doesn't find you. You have to go out and get it!

@Excellentideas
@Excellentideas
የተቃውሞ ውበት

“ስኬታማ ሰው ማለት ሰዎች የሚወረውሩበትን የተቃውሞ ድንጋይ መሰረት ለመጣል የሚጠቀምበት ሰው ነው” - David Brinkley

የማይንቀሳቀስንና የማይሰራን ሰው ብዙም ተቃውሞ ሲገጥመው አይታይም፡፡ የሚያልምን፣ የሚሰራን፣ ለውጥን ለማምጣት የሚነሳሳንና ውጤትን የሚያስመዘግብን ሰው ግን ለመቃወም ሃሳብ ሰጪው ብዙ ነው፡፡ በሕይወትህ የመጀመሪያውን የስኬት ጣእም አጣጥመህ ሳትጨርስ የመጀመሪያውን የተቃውሞ ድንጋይ ወደ አንተ ሲወረወር ማየትህ የማይቀር ነው፡፡ ሆኖም፣ አንድ እውነታ መዘንጋት የለብህም፣ ለስኬታማነትህ መዋጮ የሚያደርጉት የሚደግፉህና የሚያደንቁህ ሰዎች ብቻ አይደሉም፤ የሚቃወሙህና የማይቀበሉህም ሰዎች ጭምር እንጂ፡፡ የሚጋፉህና የሚቃወሙህም ሰዎች በሕይወትህ ትልቅ ስፍራ እንዳላቸው መዘንጋት የለብህም፡፡

ሰው በተቀባይነት ውስጥ ይነሳሳል፣ በተቃውሞ ውስጥ ደግሞ ይጠነክራል፡፡

ተቃውሞ ራስህን ካለማቋረጥ እንድትመለከትና እንድትፈትሽ ያስታውስሃል፡፡ ተቃውሞ ነገ የተሻለ ስኬት በእጅህ ሲገባ ከተከፈለበት መስዋትነት አንጻር ለስኬቱ እንድትጠነቀቅ ይረዳሃል፡፡ ተቃውሞ ነገ የስኬት ከፍታ ላይ ስትደርስ ስኬቱን በጨዋነት እንድትይዘው የሚስችልህን ባህሪይ ይገነባልሃል፡፡ መለስ ብለህ ታሪክን አንብብና ለአለምም ሆነ ለሕብረተሰባችን መልካም ፈርን ቀድደው ያለፉ ሰዎችን ጎዳና አጢን፣ ምናልባት ለማመን የሚያስቸግርህን ውጣ ውረድና ተቃውሞ አሸንፈው እንዳለፉ ትደርስበታለህ ብዬ እጠረጥራለሁ፡፡

አየህ፣ ብዙ ሰዎች የሚቃወሙትን እንጂ የሚደግፉትን አያውቁም … የሚያፈርሱትን እንጂ የሚገነቡትን አያውቁም … የሚጠሉትን እንጂ የመወዱትን አያውቁትም፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ከላይ የተዘረዘሩትን አሉታዊ እርምጃዎች ከወሰዱና የተመኙትን አሉታዊ ውጤት ካገኙ በኋላ አዎንታዊ እቅድ ስለሌላቸው ሌላ የሚቃወሙትን፣ የሚያፈርሱትንና የሚጠሉትን ፍለጋ ይቅበዘበዛሉ፡፡ አንተ ግን ዝም ብለህ ዓላማህ ላይ አተኩር፡፡

@Excellentideas
@Excellentideas
Don't lose your imagination!!

@Excellentideas
@Excellentideas
Yes, major hurdles are disheartening, and they’re often unavoidable. But the way you engage with and think about problems directly influences your ability to solve them.
#EntrepreneurMindset
#motivation
#happiness
#lifestyle

@Excellentideas
@Excellentideas
ፆታህ ምንድን ነው?

ከላይ ያነሳሁትን ጥያቄ ስታዩት ምናልባት ''ያመዋል'' ወይም ''ምን ነካው?'' እንዳላችሁ አልጠራጠርም ነገርግን ''አደጉ'' ወደ አልናቸው ሀገራት ይሄን ጥያቄ ብንወስደው ለመመለስ ምናልባት ደቂቃዎች እንደሚፈጅባቸው እገምታለሁ።

አሁን ባገኘሁት መረጃ መሰረት በዓለም ላይ ከ52 በላይ ፆታዎች እንዳሉ ያመለክታል። ይሄን ስል ሌላ ተጨማሪ ፍጥረት መጥቶ ሳይሆን እኛ ወንድና ሴት በምንባለው ውስጥ ዘመን አመጣሽ ተመራማሪዎች የፈጠሯቸው ናቸው እናም በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ወላጆች የልጆቻቸውን ፆታ የመወሰን መብት የላቸውም።

በጣም ይገርማል እኛ ሀገር ቤተሰብ እንኳን ፆታህን ሃይማኖትህን፣ ብሔርህን ከዛም አልፎ ጓደኞችህን፣ አስተሳሰብህን፣ ወደፊት የምትሰራውን ስራ፣ ትዳርህን... የመወሰን መብት ያለን ባህልና ልምድ ሰጥቶታል። ምንም እንኳን ይሄን ባልደግፍምና ልጆች በራሳቸው ወይም ውስጣቸው በተቀመጠው ዓላማ ተቃኝተው ማደግ አለባቸው ብዬ ባምንም ሰው እግዚአብሔር የሰጠውን ስጦታ ላይ እስኪክድ ድረስ ወደ ''ማሰብ ማቆም'' መውረድ አለበት ብዬ አላምንም እንደውም በጣም እቃወመዋለሁ!!

ይሄ ሁሉ ግን በአንድ ሌሊት እንዳልመጣ ማወቅ አለባችሁ ለዘመናት በሳይንስ በትምህርት በፊልም (Specially Hollywood) እናም በተለያዩ መንገዶች ወደ አዕምሮአቸው ሲከቱ የቆዩትን ሀሳብ ዛሬ ዲሞክራሲን ሰበብ አርገው ማንነትን እስከሚያጠራጥር የሚደርስ ሰይጣናዊ ህግ ለማውጣት ብዙም አልተቸገሩም።

ወደ ሀሳቤ ስመጣ ዛሬም እኛ በልጆቻችን በወንድም እህቶቻችን በጓደኞቻችን የምንዘራው የጥላቻ፣ የመከፋፈል፣ የዘር፣ የጠባብነት አስተሳሰብ አሁን ካለንበት የባሰ ቀዉስ ውስጥ የሚያስገባን ከጊዜያት በኋላ ነው እንዲሁም ዛሬ የምንዘራው የአንድነት የእርቅ የፍቅር የሰላም ሐሳብ የሚገለጠው ከጊዜያት በኋላ ነው ስለዚህ ዓለም አንድ ወደ መሆን ወደ ሰውነት በሚታደግበት ጊዜ ጭራሽ ወደ ጠባብነት ወደ ትንሽነት መውረድ ያሳዝናል እናም ዛሬ ላይ የምንዘራው ክፉም ሆነ መልካም ዘር ከአሁኑ ትዉልድ በላይ ቀጣዩን ትውልድ ላይ ስለሚያፈራ እንጠንቀቅ!!!

በድንጋይ ፈንታ ዳቦ በዱላ ፈንታ እስኪብርቶ ብንሰጣቸው ዛሬ የምንደባደብበትን ጉዳይ ነገ እነሱ ቁጭ ብለው ተወያይተው ይፈቱታል።

አሜን ዳንኤል

@Excellentideas
@Excellentideas
@inspiringbooks_Cal_Newport_Deep_Work_Rules_for_focused_success.pdf
1.5 MB
. DEEP WORK
CAL NEWPORT

Author of so Good they can't ignore you

Rules for Focused success in a distracted world

🎖Amazon Best Book in Business & Leadership
🎖WallStreet Journal Business BestSeller

@Excellentideas
@Excellentideas
Yuo konw waht is Rael Reltionship?

I m gving yuo an exmpl : Jsut c tihs msg. Evrey splleing of tihs msg is wrnog. Bt sitll yuo can raed it wihtuot ayn mistake. if u wnat true Raleti0nship; jsut ignoer mistaeks of otheres..

And Understand Them.....!!

@Excellentideas
@Excellentideas
ከ 3 ወር በፊት በIntellegence Quotient (IQ) ምዘና ሀገራችን በጣም ዝቅተኛ በሆነ መልኩ 69 በማስመዝገብ ከ14 ሀገራት ብቻ ከፍ ብላ እንደተቀመጠች ፅፌ ነበር።

አሁን ባገኘሁት መረጃ መሰረት ወደታች ቁልቁል ወርዳ በጣም ዝቅተኛ አስተሳሰብ ካላቸው ሀገራት 2ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠናል። በጣም ያሳዝናል ነገሩ አንዳንዴም ሲያንሰን ነው ብዬ አስብና ነገርግን በጥቂቶች ድድብና 100 ሚሊዮን ህዝብ መጠቃለሉ ያናደኛል!
እናም እስቲ ያኔ ከ3 ወር በፊት የጻፍኳትን ፅሁፍ ደግሜ ልጋብዛችሁ እናም ለሌሎችም በማድረስ ተባበሩኝ🙏
ይኸው ወደ ጽሑፉ....

እኔ እንዲህ አምናለሁ ዓለም ላይ ካሉ ህዝቦች እንደ ኢትዮጵያዊ ብሩህ አዕምሮና ጥሩ የማሰብ ችሎታ ያለው ህዝብ አለ ብዬ አላስብም (ተራ ፉከራ ወይም ለማስተባበል አይደለም ይሄን ያልኩት) ታዲያ እንዲህ ብሩህ አዕምሮ ካለን ለምን መለስተኛ የአዕምሮ ችግር ካለባቸው ጋር ለምን ተመደብን???

አንድ በአንድ ሀገር ውስጥ ለረጅም ዘመናት የቆየ አንድ ግዙፍ ሀዉልት ነበር እናም ከረጅም ዓመታት በኋላ ይሄ ካለበት ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዘዋወር ተፈልጎ ለማንሳት ሲሞክሩ ለካ ሸክላ ኖሯል ይሰበራል በሚገርም ሁኔታ ግን ከተሰበረው ሀዉልት ውስጥ አንድ የሚያንፀባርቅ ነገር መታየት ጀመረ ሁሉም ደነገጡ ከዛም ያዩትን ነገር ሲያጣሩት ለካ ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተሰራ ሀውልት ነበር። በቀኝ ግዛት ጊዜ ጉልበታሞቹ ሀገራት ሀብታቸውን በመበዝበዝ ላይ ሳሉ ጥበበኛ አባቶች ይሄን ሀውልት ለማትረፍ ሲሉ በሸክላ ይለብጡታል።

ይሄን ታሪክ ያነሳሁበት ምክንያት እኛ ኢትዮጵያውያን ውስጣችን ብዙ ወርቅ አለ ነገርግን በተለያዩ የማያገቡን ፖለቲካዊ፣ማህበራዊና የተለያዩ ነገሮች ተሸፍኗል። ይሄን በውስጣችን ያለውን ትልቅ ሀብት ለማውጣት ከግርግር ወጥተን ራሳችንን ማየትና ማወቅ ያስፈልገናል።

አሁን እኛ ውስጥ ያለውን ወርቅ እንዳይታይ የለበጠውን ሸክላ የምናፈርስበት ጥሩ ከራስ ጋር የማሳለፊያ ጊዜ ያገኘን ይመስኛል ስለዚህ አሁን ካለው ፖለቲካ (ከፌስቡክ ፖለቲካ፣ ከሰፈር ፖለቲካ፣ ከወሬ ፖለቲካ...) ወጥተን ራሳችን ላይ እንስራ!
አትሳሳቱ! ትልቁና ትርፋማው Investment ራስ ላይ የሚደረግ Investment ነው።
ይሄ ሲሆን ብዙ ለዓለም መፍትሔ የሚሆኑ ሀሳቦች ፈጠራዎችና ግኝቶች ከእኛው መፍለቅ ይጀምራሉ!

ነገርግን አስተዉሉ Being Smart or Genius doesn't lead us to success but being wise in your time management

እወዳችኋለሁ

አሜን ዳንኤል

@Excellentideas
@Excellentideas
Fix your mind ~ Meditate, Read, Write, Be Mindful, Gratitude

Fix your body ~ Exercise, Water, Stretching, Sun, Relax

Fix your relationships ~ Trust, Give, Integrity, Honesty, Respect, Time, Space

Fix your wealth ~ Learn, Save, Invest, Growth, Value, Ethics, Simplicity

@Excellentideas
@Excellentideas
Millionaires set themselves apart by the skills they possess. These skills are too much that the average person can not realize or think that they can never achieve them all. That's what made millionaires super rich in the first place.

@Excellentideas
@Excellentideas
''ኤርትራ ውስጥ ብትወለድና እትብትህ እዛ ቢቀበር እትብትህን የበላው ምስጥ ግን ደቡብ ኢትዮጵያ ላለመድረሱ እርግጠኛ አትሁን። ጋምቤላ ተወለድ እትብትህን ጋምቤላ ውስጥ የበላው ምስጥ ግን አፋር ላለመድረሱ እርግጠኛ አትሁን። ለምን ከምስጡ ለመሻል አትሻም? ለምን ትጠባለህ?... ሰፊ አገር እያለህ ለምን ጠባብ ክልል አርገህ እንዲሆን ትመኛለህ?.... አህያ እንኳን ጋጣው ሲጠበዉ ይራገጣል። የማያሳፍርህ ነገር ቢኖር በኢትዮጵያዊነትህ ማመንህ ብቻ ነው በቃ!!''

🖋 ይስማዕከ ወርቁ

@Excellentideas
@Excellentideas
The Fixed mindset says, "Are you sure you can do it? Maybe you don't have the talent."

The Growth mindset answers, "I'm not sure I can do it now, but I think I can learn to with time and effort."

Fixed mindset: "What if you fail--you'll be a failure."

Growth mindset: "Most successful people had failures along the way."

@Excellentideas
@Excellentideas
ደግነት ማየት የተሳናቸው የሚያዩት መስማት የተሳናቸው የሚሰሙት ልዩ ቋንቋ ነው!

@Excellentideas
@Excellentideas
You’re braver than you believe, and stronger than you seem, and smarter than you think.

💡

Your mind will believe what you continuously tell it. So tell it that you’re smart, ambitious, cute and not afraid to go for it.

@Excellentideas
@Excellentideas