Excellent Ideas
633 subscribers
475 photos
68 videos
38 files
59 links
''THINK-LIKE-THERE-IS-NO-BOX''

For any Ideas,Comment and Opinion @AmenNc

Don't hesitate to contact us we need your ideas!!


Before Leaving The Channel Tell us our Problem/ ከቻናሉ ከመውጣቶ በፊት ችግራችንን ይንገሩን🙏 @AmenNc
Download Telegram
@inspiringbooks_Michael_Hyatt_Your_Best_Year_Ever_A_5_Step_Plan.epub
15 MB
. YOUR BEST YEAR EVER
MICHAEL HYATT

''A simple program backed by the best modern research to reach your dreams''

@Excellentideas
@Excellentideas
የስኬታማዎችና የስኬተ-ቢሶች ልዩነት

በአንድ ዘርፍ አቅጣጫ ስኬታማ ሰዎች ስኬታማ ከሆኑበት ምክንያቶች አንዱ ስኬተ-ቢሶቹ አንዳንድ ጊዜ የሚያደርጉትን ነገር እነሱ ሁልጊዜ በማድረጋቸው ምክንያት ነው፡፡ እኔና አንተ አንዳንድ ጊዜ እንሮጥ ይሆናል፣ ይህ የአንዳንድ ጊዜ ሩጫችን ግን በሩጫ ውድድር ስኬታማ አያደርገንም፡፡ እነዛኞቹ ግን በየቀኑ በመሮጣቸው ምክንያት በሩጫው መስክ ወደስኬታማነት አልፈው ይሄዳሉ፡፡

አንዳንደ ጊዜ በሚያነቡትና ዘወት በሚያነቡት ሰዎች መካከል፣ አንዳንድ ጊዜ በሚሞክሩትና ዘወትር አዳዲስ ነገር ከመሞከር በማያርፉት መካከል፣ አንዳንድ ጊዜ ለጤንነታቸው በሚጠነቀቁትና ዘወትር በሚጠነቀቁት መካከል፣ ከፍቅረኛቸው ጋር አንዳንድ ጊዜ በሚወያዩትና ውይይወትን የዘወትር ልምምዳቸው ባደረጉ ሰዎች መካከል . . . ያለው ልዩነት አንዳንድ ጊዜ ከማድረግ የሚመጣ ደካማ ውጤትና ዘወትር ከማድረግ የሚመጣ ብርቱ ውጤት ነው፡፡

ስኬታማ ለመሆን የመትፈልግበትን የሕይወትህን መስክ በሚገባ አጢነውና ተግባሮችህን ምን ያህል እየደጋገምካቸው እንደምታደርጋቸው አስበው፡፡ ሳትሰለች በምትደጋግማቸው ነገሮች ላይ ስኬታማ ነህ ወይም ስኬታማ መሆንህ አይቀርም፡፡ አንዳንድ ጊዜ በምታደርጋቸው ነገሮች ላይ ደግሞ ስኬተ-ቢስ ሆነህና ዘወትር፣ “ለምን?” እያልክ እንደጠየክ ትኖራህ፡፡

ዶ/ር ኢዮብ ማሞ

@Excellentideas
@Excellentideas
"Communication is a Skill that you can Learn. If you are Willing to Work at it. You can Rapidly Improve the Quality of Every Part of Your Life."
Have a peaceful night😊

@Excellentideas
@Excellentideas
Don't be afraid...💯

@Excellentideas
@Excellentideas
Thought Of The Day:
"Almost every Successful Person Begins with Two Beliefs... The Future can be Better than the Present & 'I HAVE THE POWER' to Make it So."

@Excellentideas
@Excellentideas
My Favorite Quote

የቻሉ ያግዙናል ፤ ያልቻሉ ይተውናል ያልገባቸው ይተቹናል ፤ ያልፈለጉን ይቃወሙናል ፤ እኛ ግን ወገባችንን ጠበቅ አድርገን የጀመርነውን ጨርሰን ሪቫን እንቆርጣለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፡፡

ጠ/ሚ አብይ አህመድ

@Excellentideas
@Excellentideas
👆👆👆💯💯

@Excellentideas
@Excellentideas
Fun Fact

እጅግ አስደናቂና የማይታመን የ መንትያ ወንድማማቾች ታሪክ

እነዚህ ከላይ በምስል የምትመለከቱዋቸው መንትያዎች በ 1940 የተወለዱ ሲሆን እናታቸው ማሳደግ ስለማትችል በ ማደጎ መልክ ለተለያዩ አሳዳጊ ቤተሰቦች ትሰጣቸዋለች፡፡ እናም እኚህ መንትያዎች ተለያይተው ለ 30 አመታት ሳይተዋወቁ ያድጋሉ ከዛም በ 1979 መልሰው ይገናኛሉ ፡፡ እናም በሚገናኙበት ሰአት ሂወታቸው ሲጣራ እጅጉኑ ለማመን የሚከብድ መመሳሰል ተገኝቶባቸዋል
👉ሁለቱም ስማቸው james ይባላል
👉ሁለቱም toy የተባለ ውሻ ነበራቸው
👉ሁለቱም ሂሳብ ይወዱ ነበር
👉ሁለቱም spelling ይጠሉ ነበር
👉ሁለቱም ስራቸው ፖሊስነት ነበር
👉ሁለቱም የመጀመርያ ሚስታቸው linda ትባል ነበር
👉ሁለቱም ወንድ ልጅ ነበራቸው
👉ሁለቱም ልጃቸውን Alen ብለው ነው የጠሩት
👉ሁለቱም የመጀመርያ ሚስታቸውን ፈተው ነበር
👉ሁለቱም ደግመው አግብተዋልም
👉ሁለቱም ያገቡት ሚስት betty ነው ስማቸው
ይሄ ከሚያመሳስላቸው ነገር ጥቂቱ ነው፡፡

ምንጭ : http://all-that-is-interesting.com/jim-twins

@Excellentideas
@Excellentideas
Your biggest asset is your brain. Your mind controls your life, your confidence, your relationships, your purpose, your strengths, your success. Remember the Quality of your thoughts determines Quality of your life.

@Excellentideas
@Excellentideas
Be who you want to be, not what others want to see.
#beyourself

@Excellentideas
@Excellentideas
ሰው በሰውነቱ
የምግብ ቤት ባለቤት የሆነ ሰውየ :በደንበኞቹ መሀል ሲዘዋወር አንድ
ዝነኛ ጋዜጠኛ ይመለከታል። ወድያው ባለቤትየው አስተናጋጂቱን ጠርቶ ”
እዛ ጥግ ላይ የተቀመጠው ጋዜጠኛ ይታይሻል? ሂጅና የሚፈልገውን
እየጠየቅሽ ተንከባከቢው!! ወጥ ካነሰው ጨምሪለት!! እንዲያውም ለኔ
ራት ከተሰራው ዶሮ አንድ ቅልጥም ብትሰጪው ደስ ይለኛል። ሲያንሰው
ነው!! እንዴት ያለ የሰላ ጭንቅላት ያለው ሰው መሰለሽ!!! የስራ ጫና
የበዛበት ይመስላል። ደሞ ትንሽ እንደደበረው ፊቱ ያስታውቃል። እስቲ በኔ
ሂሳብ አንድ ብርጭቆ ወይን ቅጂለት ። ድብርቱን ያባርርለታል!!”
” የደበረው ዛሬ ከስራው ስለተጫረ ነው ! ምፅ!” አለች አስተናጋጂቱ።
“የምርሽን ነው?”
” አርሴማ ምስክሬ ናት ”
የምግብ ቤቱ ባለቤት ድምፁን ከረር አድርጎ እንዲህ አለ: “እንደሱ
አትይኝም ታድያ!! ይበለው!! እንደ ስራውማ ቢሆን ከቢሮው ብቻ ሳይሆን
ካገር መባረር ነበረበት!! ይሄ ቀዳዳ!! የሽንትቤት አገልግሎት አይሰጡም
እያለ ስንት ምግብ ቤቶችን በማዘጋጃቤት እንዲታሸጉ አድርጉዋል
መሰለሽ? ይሄ አሰልጥ!! በይ አጠገቡ ቁሚና ብርጭቆና ማንኪያውን ወደ
ቦርሳው እንዳይከት ባይነቁራኛ ተከታተይው።”
….
ሰውን በሰውነቱ መውደድ የሚባል ነገር በባህላችን ትርጉም አለው? ።
ብዙ ጊዜ:ለሰዎች ፍቅርና ርህራሄ ፍቅርና አክብሮት የምናሳየው
ይጠቅሙናል ብለን ካሰብን ነው። ምንም አያመጡም ብለን
የምናስባቸውን ሰዎች ማክበር ይቸግረናል። ምንም አይሰጡንም ብለን
የምናስባቸውን ሰዎች መውደድ ያቅተናል።
“እገሌ ሞተ አሉ የልቤ ወዳጅ
የሚያበላኝ ጮማ እሚያጠጣኝ ጠጅ”
ብላ ያለቀሰቺው ሴትዮ እንባ ያፈሰሰችው ለአቶ እገሌ አይደለም። ከአቶ
እገሌ ሞት ጋር አብሮ ለሚቀረው ጠጅ እና ጮማ ነው።
እና አንዳንዴ :በግል ጥቅም ስሌት ላይ ያልተመሰረተ የሰውም ሆነ ያገር
ፍቅር ይኖር ይሆን እላለሁ?
በባህላችን ሹመት አጥብቀን እንወዳለን ። ካቶ ሀዲስ አለማየሁ በቀር
ስልጣን በሰፌድ ቀርቦለት “ይለፈኝ” ያለ በታሪክ አላቅም። ሹመት
ባይደርሰን እንኩዋን : ልጆቻችንን “ተሾመ ” ነጋሲ : ሞቱማ ” እያልን
በመሰየም ጥማችንን እናስታግሳለን ። በሹም ፊት ሞገስ ለማግኘት
እድሚያችንን ክብራችንን አንዳንዴም ህይወታችንን እንገብራለን።
ለተሾመ ሰው ያለን አክብሮት ወደ አምልኮ የተጠጋ የሆነውን ያህል :
ለተሻረና ለተሸነፈ ሰው ርህራሄ አናቅም።
በታሪካችን: አንድ ሹም ከስልጣን ከወረደ ህይወቱን ያጣል። ህይወቱን
ባያጣ የሰውነት ክብሩን ያጣል። በምድር ላይ መኖሩን የሚያስጠላ
ውርደት ይጠግባል። በህይወት ተርፈው ስልጣን የለቀቁ አንዳንድ
ነገስታት በከተማ ከመኖር በገዳም መንነው መኖር የሚመርጡት ለዚህ
ይሆናል። ለምሳሌ እቴጌ ጣይቱ በስልጣን ላይ በነበሩ ጊዜ ” እቴጌ
ጣይቱ እቴጌ ብርሃን” እየተባሉ ይሞገሱ ነበር። ከስልጣን ከተወገዱ
በሗላ አድመኛው ጃንሜዳ ላይ ተሰብስቦ እንዳይሸጡ እንዳይለወጡ
አድርጎ ዘለፋቸው።
እናም እቴጌይቱ ሲያስከብራቸው የኖረው ወንበራቸው እንጂ ሰብእናቸው
አለመሆኑን ሲባንኑ-
” ከተቀመጥኩበት -ከስፍራየ ቢያጣኝ
“አንቱ ” ያለኝ ሁሉ -“አንቺ “ሊለኝ ቃጣኝ”
ብለው አንጎራጎሩ።
ተስፋ አንቁረጥ!! ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚገባውን ፍቅርና ክብር
የሚሰጡ ሰዎች ቁጥራቸው ይነስ እንጂ በየዘመኑ በየቦታው መኖራቸው
ያፅናናናል።
በድሮ ጊዜ ተደላ ጉዋሉ የተባለ ጌታ : አሉላ ተሰማ የተባለውን የስልጣን
ተፎካካሪውን ማርኮ ይዞ መንቆረር ገበያ ላይ አርባ ገረፈው። ግርፊያውን
ቆሞ እየተመለከተ ከሚዝናናው ገበያተኛ ማሃል – አንዲት ልበ-ብሩህ
ባላገር እንዲህ ብላ በግጥም ሀሳቡዋን ገለፀች።
“ከጮማው አልበላሁ ከጠጁም አልጠጣሁ
አላውቀው አያውቀኝ
አሉላ ተሰማ ቢቀጣ ጨነቀኝ”
ውለታ ሳይቆጥሩ: ሳይውቁን ሳናውቃቸው :የሚጨነቁልንን ያብዛልን!!

አለ / በ በዕውቀቱ ስዩም / እውነቱን ነው ።

እኔም እላለሁ ሰውን ከሚገባው በላይም መካብ፤ቢበድለን መውቀስም መናገርም መንታ ምላስ ያረገናልና ሁሉም በስራው እንጂ በጊዜያዊ ስልጣኑ መሆን የለበትም ብዬ አምናለሁ።ማንም ወደደም ጠላም ከፍ ያለው ዝቅ ሊል ዝቅ ያለው ከፍ ሊል የተፈጥሮ ግዴታ ነውና።

ነብዩ ሰለሞን ነኝ ሰላም አዳር

@Excellentideas
@Excellentideas
ስኬትን ፍለጋ

“ስኬትን ከፈለክ ስኬትን ዓላማህ አድርገህ አትያዝ፡፡ የምታምንበትንና የምትወደውን ነገር ከልብህ ስታደርግ ስኬት ራሱ ይመጣል” - David Frost

ለትክክለኛ አላማ መቆም ስኬትን ይቀድማል እንጂ ስኬት አላማን አይቀድምም፡፡ አንዳንድ ሰዎች፣ “ቢሳካልኝ ኖሮ ይህንና ያንን አደርግ ነበር” በማለት በገንዘብና በተለያዩ አቅጣጫዎች “ቢሳካላቸው” ሊያደርጉ ስለሚፈልጉት የወደፊት አላማ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ አንድ ማስታወስ ያለባቸው እውነታ ግን አንድን አላማ ይዘው መስራታቸው ወደ ስኬት እንደሚወስዳቸው ነው፡፡ በሌላ አባባል፣ ተሳካላቸው በመባል የሚታወቁ ሰዎች ለስኬት የኖሩ ሰዎች ሳይሆኑ ለአንድ አላማ በጽንአት የኖሩ ናቸው፤ ያንን ሲያደርጉ ስኬት ተከተላቸው፡፡

ለስኬት የሚኖር ሰው ስኬት ያጣ ሲመስለው ያቆማል፡፡ ለአላማ የሚኖር ሰው ግን ስኬት ያላገኘ ቢመስለውም እንኳ ጉዞውን ይቀጥላል፣ ምክንያቱም አላማ የተሰኘውን የስኬቶችን ሁሉ ስኬት በእጁ ጨብጧልና ነው፡፡ “የምትወደውንና መልካም የሆነውን ነገር አድርግ፣ ያንን የምታደርገውን ነገር ደግሞ ውደደው” የሚለው አባባል እውነት ነው፡፡ ስኬትን ፍለጋ ከአላማህ ውጪ የሆነን “ታላቅ” ነገር ከማድረግ፣ አላማን በመከተል አስቸጋሪ ጎዳና መጓዝ ይመረጣል፡፡

ዶ/ር ምህረት ደበበ

@Excellentideas
@Excellentideas
ለውጥ የለም ማለት ህይወት የለም ማለት ነው።
ከተደበቅንበት የሚያወጣን፣ ከመርጋት እና ከመሽተት እንደወንዝ ያለድንበር እንድንፈስ የሚያደርገን ባለውለታችን ለውጥ ነው።
ዛሬ እየኖርን ያለነው የትናንት ሃሳባችንን ነው!
የወደፊት ኑሮአችንን ለመለወጥ የዛሬውን ሃሳባችንን መለወጥ አለብን።


@Excellentideas
@Excellentideas
Forwarded from Smart me (Mysterious me)
Most of you want to change the world in the future, but why in the future. Can't you do it today, Yes you can. If you want do it do it today, if you want it, why not now. The future is already booked. This is your free time.
IT IS TIME
@smartme2
@smartme2
Success doesn't find you. You have to go out and get it!

@Excellentideas
@Excellentideas
የተቃውሞ ውበት

“ስኬታማ ሰው ማለት ሰዎች የሚወረውሩበትን የተቃውሞ ድንጋይ መሰረት ለመጣል የሚጠቀምበት ሰው ነው” - David Brinkley

የማይንቀሳቀስንና የማይሰራን ሰው ብዙም ተቃውሞ ሲገጥመው አይታይም፡፡ የሚያልምን፣ የሚሰራን፣ ለውጥን ለማምጣት የሚነሳሳንና ውጤትን የሚያስመዘግብን ሰው ግን ለመቃወም ሃሳብ ሰጪው ብዙ ነው፡፡ በሕይወትህ የመጀመሪያውን የስኬት ጣእም አጣጥመህ ሳትጨርስ የመጀመሪያውን የተቃውሞ ድንጋይ ወደ አንተ ሲወረወር ማየትህ የማይቀር ነው፡፡ ሆኖም፣ አንድ እውነታ መዘንጋት የለብህም፣ ለስኬታማነትህ መዋጮ የሚያደርጉት የሚደግፉህና የሚያደንቁህ ሰዎች ብቻ አይደሉም፤ የሚቃወሙህና የማይቀበሉህም ሰዎች ጭምር እንጂ፡፡ የሚጋፉህና የሚቃወሙህም ሰዎች በሕይወትህ ትልቅ ስፍራ እንዳላቸው መዘንጋት የለብህም፡፡

ሰው በተቀባይነት ውስጥ ይነሳሳል፣ በተቃውሞ ውስጥ ደግሞ ይጠነክራል፡፡

ተቃውሞ ራስህን ካለማቋረጥ እንድትመለከትና እንድትፈትሽ ያስታውስሃል፡፡ ተቃውሞ ነገ የተሻለ ስኬት በእጅህ ሲገባ ከተከፈለበት መስዋትነት አንጻር ለስኬቱ እንድትጠነቀቅ ይረዳሃል፡፡ ተቃውሞ ነገ የስኬት ከፍታ ላይ ስትደርስ ስኬቱን በጨዋነት እንድትይዘው የሚስችልህን ባህሪይ ይገነባልሃል፡፡ መለስ ብለህ ታሪክን አንብብና ለአለምም ሆነ ለሕብረተሰባችን መልካም ፈርን ቀድደው ያለፉ ሰዎችን ጎዳና አጢን፣ ምናልባት ለማመን የሚያስቸግርህን ውጣ ውረድና ተቃውሞ አሸንፈው እንዳለፉ ትደርስበታለህ ብዬ እጠረጥራለሁ፡፡

አየህ፣ ብዙ ሰዎች የሚቃወሙትን እንጂ የሚደግፉትን አያውቁም … የሚያፈርሱትን እንጂ የሚገነቡትን አያውቁም … የሚጠሉትን እንጂ የመወዱትን አያውቁትም፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ከላይ የተዘረዘሩትን አሉታዊ እርምጃዎች ከወሰዱና የተመኙትን አሉታዊ ውጤት ካገኙ በኋላ አዎንታዊ እቅድ ስለሌላቸው ሌላ የሚቃወሙትን፣ የሚያፈርሱትንና የሚጠሉትን ፍለጋ ይቅበዘበዛሉ፡፡ አንተ ግን ዝም ብለህ ዓላማህ ላይ አተኩር፡፡

@Excellentideas
@Excellentideas
Don't lose your imagination!!

@Excellentideas
@Excellentideas
Yes, major hurdles are disheartening, and they’re often unavoidable. But the way you engage with and think about problems directly influences your ability to solve them.
#EntrepreneurMindset
#motivation
#happiness
#lifestyle

@Excellentideas
@Excellentideas
ፆታህ ምንድን ነው?

ከላይ ያነሳሁትን ጥያቄ ስታዩት ምናልባት ''ያመዋል'' ወይም ''ምን ነካው?'' እንዳላችሁ አልጠራጠርም ነገርግን ''አደጉ'' ወደ አልናቸው ሀገራት ይሄን ጥያቄ ብንወስደው ለመመለስ ምናልባት ደቂቃዎች እንደሚፈጅባቸው እገምታለሁ።

አሁን ባገኘሁት መረጃ መሰረት በዓለም ላይ ከ52 በላይ ፆታዎች እንዳሉ ያመለክታል። ይሄን ስል ሌላ ተጨማሪ ፍጥረት መጥቶ ሳይሆን እኛ ወንድና ሴት በምንባለው ውስጥ ዘመን አመጣሽ ተመራማሪዎች የፈጠሯቸው ናቸው እናም በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ወላጆች የልጆቻቸውን ፆታ የመወሰን መብት የላቸውም።

በጣም ይገርማል እኛ ሀገር ቤተሰብ እንኳን ፆታህን ሃይማኖትህን፣ ብሔርህን ከዛም አልፎ ጓደኞችህን፣ አስተሳሰብህን፣ ወደፊት የምትሰራውን ስራ፣ ትዳርህን... የመወሰን መብት ያለን ባህልና ልምድ ሰጥቶታል። ምንም እንኳን ይሄን ባልደግፍምና ልጆች በራሳቸው ወይም ውስጣቸው በተቀመጠው ዓላማ ተቃኝተው ማደግ አለባቸው ብዬ ባምንም ሰው እግዚአብሔር የሰጠውን ስጦታ ላይ እስኪክድ ድረስ ወደ ''ማሰብ ማቆም'' መውረድ አለበት ብዬ አላምንም እንደውም በጣም እቃወመዋለሁ!!

ይሄ ሁሉ ግን በአንድ ሌሊት እንዳልመጣ ማወቅ አለባችሁ ለዘመናት በሳይንስ በትምህርት በፊልም (Specially Hollywood) እናም በተለያዩ መንገዶች ወደ አዕምሮአቸው ሲከቱ የቆዩትን ሀሳብ ዛሬ ዲሞክራሲን ሰበብ አርገው ማንነትን እስከሚያጠራጥር የሚደርስ ሰይጣናዊ ህግ ለማውጣት ብዙም አልተቸገሩም።

ወደ ሀሳቤ ስመጣ ዛሬም እኛ በልጆቻችን በወንድም እህቶቻችን በጓደኞቻችን የምንዘራው የጥላቻ፣ የመከፋፈል፣ የዘር፣ የጠባብነት አስተሳሰብ አሁን ካለንበት የባሰ ቀዉስ ውስጥ የሚያስገባን ከጊዜያት በኋላ ነው እንዲሁም ዛሬ የምንዘራው የአንድነት የእርቅ የፍቅር የሰላም ሐሳብ የሚገለጠው ከጊዜያት በኋላ ነው ስለዚህ ዓለም አንድ ወደ መሆን ወደ ሰውነት በሚታደግበት ጊዜ ጭራሽ ወደ ጠባብነት ወደ ትንሽነት መውረድ ያሳዝናል እናም ዛሬ ላይ የምንዘራው ክፉም ሆነ መልካም ዘር ከአሁኑ ትዉልድ በላይ ቀጣዩን ትውልድ ላይ ስለሚያፈራ እንጠንቀቅ!!!

በድንጋይ ፈንታ ዳቦ በዱላ ፈንታ እስኪብርቶ ብንሰጣቸው ዛሬ የምንደባደብበትን ጉዳይ ነገ እነሱ ቁጭ ብለው ተወያይተው ይፈቱታል።

አሜን ዳንኤል

@Excellentideas
@Excellentideas
@inspiringbooks_Cal_Newport_Deep_Work_Rules_for_focused_success.pdf
1.5 MB
. DEEP WORK
CAL NEWPORT

Author of so Good they can't ignore you

Rules for Focused success in a distracted world

🎖Amazon Best Book in Business & Leadership
🎖WallStreet Journal Business BestSeller

@Excellentideas
@Excellentideas