Excellent Ideas
632 subscribers
475 photos
68 videos
38 files
59 links
''THINK-LIKE-THERE-IS-NO-BOX''

For any Ideas,Comment and Opinion @AmenNc

Don't hesitate to contact us we need your ideas!!


Before Leaving The Channel Tell us our Problem/ ከቻናሉ ከመውጣቶ በፊት ችግራችንን ይንገሩን🙏 @AmenNc
Download Telegram
ዛሬ የሞባይል ዳታ የኢንተርኔት አገልግሎት ተለቋል
ይህም ማለት ሰፊው ህዝብ ኢንተርኔት ማግኘት ይችላል ማለት ነው።

ኢትዮጵያዊያን ዝቅተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት ካላቸው ሀገራት ውስጥ ቢመደቡም ከዛም ባለፈ በጣም ዝቅተኛ የኢንተርኔት አጠቃቀም ባህል ያለው ህዝብ እንዳላት ይነገራል። ጠቅላይ ሚንስትራችን ሲናገሩ እንደሰማነው አንድ ጥሩ Lecture ወይም ትምህርት ሰጪ ነገር ከማየት ይልቅ አንድ ስድብ ያለበትን ነገር ለማየት ብዙ መቶ ሺዎች ይሰለፋሉ በዛም በገዛ እጃችን አመጽን፣ ጥላቻንና የፀብን ሀሳብ ይሸምታሉ!

እኔ በግል አመለካከቴ ኢንተርኔት ተዘግቶ በመቆየቱ ብጎዳም ደስተኛ ከሆኑ ሰዎች መካከል ነኝ ምክንያቱም ለአብዛኛው ህዝብ ከጉዳቱ ይልቅ ጥቅሙ ስላመዘነ
ኢንተርኔት በመኖሩ ብሔር ከብሔር ከተጣላ ኢንተርኔት በመኖሩ ክብር የሰው ሕይወት እንዲሁ ወድቆ ከቀረ ኢንተርኔት በመኖሩ ሀገር ከፈረሰች ለምን ለዘለዓለሙ ኢንተርኔት ጥንቅር ብሎ አይቀርም!!

በአጠቃላይ ሀሳቤ እስከዛሬ ኢንተርኔትን ካለአግባብ በመጠቀማችን ከደረሰው ጉዳት ተምረን ከዚህ በኋላ ኢንተርኔትን ራስንና ሀገርን መርዞ ወደኋላ ለማስቀረት ሳይሆን አንድ እርምጃ ወደፊት ለማራመድ እንጠቀምበት!!

አመሰግናለሁ!

ምናልባት ይሄ መልዕክት ለሌሎች እንዲደርስ በቻልን መጠን ሼር በማድረግ እንድናደርስ በአክብሮት እጠይቃለሁ

@Excellentideas
@Excellentideas
ከላይ ባለው ምስል በምናየው የሩጫ ውድድር ላይ ከፊት ያለው ኬንያዊው አትሌት አቤል ሙታይ ውድድሩን ለመጨረስ ጥቂት ጫማ ርቀት ብቻ ሲቀረው ሩጫውን ማጠናቀቁን የሚያበስረው ምልክት ግራ አጋብቶት አሸነፍኩ ብሎ ቆሞ ነበር፡፡
ከኃላው በቅርብ ርቀት ሲከተለው የነበረው ስፔናዊው አትሌት ኢቫን ፈርናንዴዝ ኬንያዊው ለምን እንደቆመ ስለገባው ሩጫውን እንዲጨርስ በጩኸት ይነግረው ጀመረ ነገር ግን አቤል ሊሰማው አልቻለም በመጨረሻም አጠገቡ ሲደርስ ኬንያዊውን ወደፊት ገፍትሮ ውድድሩን እንዲያሸንፍ አደረገ።

ከውድድሩ በኃላ ኢቫን ከጋዜጠኛ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ይህን ተናገር:-

ጋዜጠኛ:- ለምን እንዲህ አደረግክ?
ኢቫን:- ህልሜ አንዳችን ስንደክም፣ስንሳሳት፣ወደኃላ ስንቀር... የምንተጋገዝበት ማኅበረሰብ እንዲኖረን ነው።👌

ጋዜጠኛ:- ታዲያ ኬንያውያን እንዲያሸንፍ ለምን ረዳኸው?
ኢቫን:- መጀመሪያውንም ውድድሩን ያሸነፈው እርሱ ነው👏

ጋዜጠኛ:- ግን አንተ አሸንፈህ የወርቅ ሜዳሊያውን መውሰድ ስትችል ወርቁን አሳልፈህ ሰጠኸው ለምን?
ኢቫን:- ጋዜጠኛውን እየተመለከተ ቀድሞ ያሸነፈውን ውድድር በትንሽ ስህተት ከሚያጣ መጠነኛ እርዳታ አድርጌለት ቢወስድ ከኔ የሚቀነስ ነገር ምንድን ነው? አሸንፌስ ቢሆን የዚህ ሜዳሊያ ክብር ምንድን ነው? የድሌስ ዋጋ ምንድን ነው? በጎ ስራን ያስተማረችኝ እናቴስ ይህን ስታይ ምን ትለኝ ነበር? ብሎ ተናገር

መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል፤ እኛስ ለልጆቻችን ምን አይነት እሴት እያስተላለፍን ነው?

@Excellentideas
@Excellentideas
#ውስጥህ ያለውን ጀግና አንቃው!!

ውስጥህ ተአምር መፍጠር የሚችል ሀይል አለ!! ሰው፣ሰፈር፣ጓደኛና ቤተሰብ የሰጠህ መታወቂያ ትክክል አይደለም። እዚህ ምድር ላይ ለምን የመጣህ ይመስልሀል ? ባጋጣሚ ?ወይስ ስለምታስፈልግ ? እዚህ ምድር ላይ ባንተ ብቻ የሚሰራ ስራ አለ። እመነኝ አለ። አንተ ብቻ ሌላ ማንም የማይሰራው ስራ በዉስጥህ አለ። ይህ የህይወት ትልቁ ስጦታ ነው። የሚያናደው አንተ ብቻ መስራት ያለብህን ስራ ባለመስራትህ የምትጎዳው አንተ ብቻ አይደለህም። ሌሎችንም ትጎዳለህ። ይህ የ universe አሰራር ነው። ሌሎች የሌለህን ይሰጡሃል እንተም በተራህ የሌላቸውን ትሰጣቸዋለህ። ለምሳሌ የያዝከው ሞባይል፣የለበስከው፣ጫማ፣የምትነዳው መኪና ሰዎች ላንተ ያበረከቱት ስጦታ ነው። አንተም በምላሹ የሌላቸውን ልትሰጣቸው ይገባል።
የምትኖርለት መኖር ካቃተህ የምትሞትለት አላማ አለ? ይህንን ሳልሰራማ አልሞትም የምትልለት አላማ ምንድን ነው? በምታደንቃቸው ሰዎች እና በአንተ ያለው ልዩነት ምንድን ነው? 24 ሰዓት ስለነሱ በመስማት እና በማውራት ጊዜህን በምታጠፋባቸው ሰዎች እና በአንተ ያለው ልዩነት ምንድነው? እውነቱን ልንገርህ እነሱ የተፈጠሩለትን አላማ አውቀውታል። ጉልበታቸውን፣ ዕውቀታቸውንና ጊዜያቸውን አላማቸው ላይ ብቻ ያጠፋሉ። አንተስ? ከጀርባቸው መከራ፣ ችግር፣ ትችትና ጠንክሮ መስራት አለ። ይህን ሁሉ ተቋቁመው ማለፋቸው ነው ዛሬ ላይ ያላቸውን ስም እና ዝና መገንባት የቻሉት። ስለሰው በመስማት እና በማውራት ዘመንህ እንዳያልቅ።ህይወት አጭር ናት ተጠቀምባት።
ኢትዮጵያ መወለድህ ፣ ድሃ ቤተሰብ ውስጥ መኖርህ ፣ ገንዘብ ስለሌለህ አይደለም እንደነሱ እንዳትሆን ያደረገህ ። እንደዛ የምታስብ ከሆነ ሞኝ ነህ። እንደነሱ እንዳትሆን ያደረገህ #ትጋት የሚባል መርህ ነው።
የምታነባቸው መጻሕፍትና የምታያቸው ፊልሞች ራዕይህን የሚያግዙ፣ ለስራ ፈጣሪነት inspire የሚያደርጉ፣ ለአዲስ አስተሳሰብ የሚጋብዙ፣ መንፈሳዊነትህን የሚያሳድጉ ይሁኑ። ይህን ስታደርግ ግን ከባድ ተግዳሮት ይገጥምሀል። ጓደኞችህ ሙድ ይይዙብሃል፣ ፋራ ይሉሃል አንተ ግን ሁለት ጣትህን ሁለት ጆሮህ ውስጥ ከተህ ወደ ፊት ቀጥል።
አስታውስ አንተ ዛሬ ያልሆንከው ነገ የምትሆነው፣ ዛሬ የማታወራው ነገ የምታወራው፣ ዛሬ የማትሰራው ነገ የምትስራው ነገር አለ። ታገል። ተፉለም። ድብን አድርገህ ተሳሳት። 7ቴ ብትወድቅ ለስምንተኛ ጊዜ ተነስ። ትላልቅ ሰዎች ያገኙትን መኪና፣ ገንዘብና ዝና በአንድ ጀምበር አላገኙትም።
እንደ ገና ዳቦ ከላይ እሳት ከታች እሳት ዘንቦባቸው ነው። ከህይወት ጋር ታግለው አሸንፈው ነው። የህይወትን መራራ ፅዋ ፉት ብለው ነው። አንተስ ለዚህ ዝግጁ ነህ? ለመሳሳት፣ ለመሰደብ፣ ፋራ ለመባል ዝግጁ ነህ? ትልቅ ለመሆን ትልልቅነት የሚገኝበትን መንገድ ለመሄድ መወሰን አለብህ። ሂደቱን (process) ጠልተህ ስኬቱን ወደህ አይሆንም። ሀላፊነት መውሰድ ከፈራህ ሕይወትህን በሙሉ follower ከመሆን ውጪ አስከታይ መሆን አትችልም። ደስ የሚለው ጊዜው ገና ነው። አሁን ብትጀምር ትጨርሳለህ። ዛሬ ወስን። የተሳካለት ዶክተር፣ የተሳካለት አርቲስት ፣ የተሳካለት ነጋዴ፣ የተሳካለት መንፈሳዊ ሰው፣ የተሳካለት ተማሪ፣ የተሳካለት ስፖርተኛ መሆን ትችላለህ። እመነኝ ትችላላ። ዋናው ነገር መትጋት ነው።

Eyob G/mariam

@Excellentideas
@Excellentideas
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው!!

እንዴት አንድ ሰውን በሀገሩ ሄደህ ትደበድባለህ የሀገራችን ስም በዓለም አደባባይ የዚህን ያህል መዋረድስ ይገባው ነበር?
እውነቱን ለመናገር ይሄ ሁሉ የአለመማርና የድህነት ውጤት ነው!

የሁሉም ብሔር ፖለቲከኞች እባካችሁ ፖለቲካውን በዕውቀት ላይ የተመሰረተና የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚሻ አድርጉት እንጂ ወደኋላ ተመልሳችሁ ቁልቁል አታውርዱን ሀገራችንንም አታሸማቋት!!

@Excellentideas
@Excellentideas
መማር በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። የተማረ ሰው ነገሮችን አስፍቶና በተሻለ ከፍታ የማየት ዕድሉ የበረታ ነው።

በእርግጥ መማር ስል አሁን በለመድነው አካሄድ ያለውን ብቻ አይደለም ውስጣችን ላይ ባለው ክህሎት ላይ ተመርኩዘን በትምህርት ማሳደግ የብልህ ምርጫ ነው። ለምሳሌ ሙዚቃ ከሆነ ተሰጥኦህ በልምድ ከምትጫወተው ሙዚቃ ይልቅ በትምህርት የምታጎለብተው አጨዋወት እጅግ የተሻለ ነው።
ሁሉም ነገር ራሱን የቻለ ሳይንስ ነው በዚህ በኩል የሀገራችን የትምህርት system በጣምምምም ደካማ ከመሆኑ የተነሳ ሳይንስ ሲባል ወደ አዕምሮአችን የሚመጣው Biology እና Chemistry ነው ነገርግን ሁሉም ነገር ሳይንስ ነው ስፖርት ብትል አርት ብትል ሳይንስ ናቸው።

እና ሀሳቤን ስጠቀልለው ውስጣችሁ ያለውን ተሰጥእ ወይም ክህሎት በትምህርት የማሳደግ ልምድ ቢኖረን መልካም ነው።

@Excellentideas
@Excellentideas
You can not change your past, but you can be a master of your future!

@Excellentideas
@Excellentideas
ሁሉ እንደ ሀይሌ ቢሆን

የ27 ሪከርዶች ባለቤት የሆነው እና ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ከፍ ያደረጋት ጀግናው ኢትዮጵያዊ ሀይሌ ገብረስላሴ በቅርቡ በሻሸመኔ እና ዝዋይ የደረሰበትን ጥቃት አስመልክቶ በሚዲያ ቀርቦ ሲናገር "ከኢትዮጵያ ውጪ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት የለኝም" ብሎ ነበር።

ምንም እንኳን በአንድ ቀን 300 ሚሊዮን የሚጠጋ ንብረት ቢወድምበትም በሁለቱም ድርጅቶቹ ለሚሰሩ ከ400 በላይ ለሆኑ ሰራተኞቹ የሁለት ወር ደሞዝ ግን መክፈል ችሏል።

"አንድ ሰው ማትረፍ ዓለምን እንደማትረፍ ነው" አይደል የሚባለው።

ዛሬ ደግሞ በሀገሩ ተስፋ ሳይቆርጥ በኤሌክትሪክ የምትሰራ መኪና በሀገር ውስጥ ገጣጥሞ ለገበያ አቅርቧል። እፍታውንም የሀገሪቱን የብልጽግና ጉዞ ለሚመሩት ጠሚ አስረክቧል።

ኢትዮጵያዊነት፣ ሀገር ወዳድነት በቃል ሳይሆን በተግባር ይሁን።

ዐቢይ ታደለ /ኪያ/

@Excellentideas
@Excellentideas
ሁቱትሲ፣_ከሩዋንዳው_የዘር_ማጥፋት_የተረፈች_ወጣት.pdf
1.8 MB
. ሁቱትሲ
ኢማኩዬሌ አሊባጊዛ
ትርጉም - መምህር ግርማ

በሩዋንዳ የነበረውን የዘር ጭፍጨፋ የሚያወሳና በዛ ሁኔታ ውስጥ ስላለፈች አንዲት ወጣት የሚተርክ ጥሩ መጽሐፍ

ተጋበዙልን!

@Excellentideas
@Excellentideas
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
😂😂😂
A Group of people who wants to destruct Ethiopia.

@Excellentideas
@Excellentideas
Simon_Sinek_Start_with_Why__How.pdf
1.4 MB
. START WITH WHY
Simon Sinek

How great leaders inspire everyone to take Action!

ከመጽሐፉ አንድ የምወድለት አባባል አለ
'' Everyone knows what to do
Everyone knows how to do
But the don't know why to do!''

ተጋበዙልን!

@Excellentideas
@Excellentideas
Almost everybody wants a better life!
The same way almost anyone who is massively overweight would like to lose weight and have a healthier body, only those who make a decision & then follow through with consistent action will have the results.

If you want a better life, or at least improve in a certain area of your life, make a decision to change, then put a strategy in place whereby you can take daily action to reach your goals.

@Excellentideas
@Excellentideas
#ድሮና_ዘንድሮ

* ፕሮግራማቸውን ማዳመጥ መጽሃፍ የማንበብ ያህል እውቀትን የሚያስጨብጥ

* ከጋዜጠኝነትም በላይ እንደ ትልቅ ቤተ መጻፍት የሚቆጠሩ

*የታሪክ ቤተ መዛግብት የትላንታችን ማሳያ መስታዎቶች

* የጋዜጠኝነት ስነ ምግባር ልኬቶች

#ጋዜጠኛ_መሃዛ_ብሩ እና #ጋዜጠኛ_ተፈሪ_አለሙ

የዋላው ከሌለ የለም የፊቱ

@Excellentideas
@Excellentideas
Spencer_Johnson_Who_Moved_My_Cheese__.pdf
1.8 MB
. Who Moved My Cheese
Dr. Spencer Johnson


One of the most successful business book ever.

አጭርና ጥሩ የቢዝነስ እንዲሁም ለማንኛውም ሰው ህይወቱን ለማስተካከል የሚረዳ መጽሐፍ

ተጋበዙልን!

@Excellentideas
@Excellentideas
A gift is meant to be given, open & enjoyed.

You are a gift to this world!

Don't stay wrapped up in a corner for the rest of your life.

@Excellentideas
@Excellentideas
በእጅ ያለ ወርቅ...
(በአሜን ዳንኤል)

ቀደምት እናት አባቶቻችን ይሄን ተረት ሲተርቱ በምን አጋጣሚ እንደሆነ ባላውቅም አሁን በሀገራችን ያለውን ነገር አይተው የተናገሩት በሚመስል ሁኔታ የዘመናችን ትውልድን ይወክለዋል ብዬ አስባለሁ።

ብዙዎቻችን በዉስጣችን ያለውን ውድ የሆነውን ተስጥኦ (Talent) ባለማወቃችን ምክንያት አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ተሰጥኦቸውን ላወቁ ሰዎች መጠቀሚያ ሆነን እየኖርን ነው በመልካምም ሆነ በክፉ ማለት ነው።

በእጃችን ያለውን ወርቅ ትተነው ለምን ድንጋይ እንይዝበታለን? ሕንፃ የሚገነባ አቅም በዉስጣችን አስቀምጠን ለምን በሌሎች ጥሪ ሕንፃ እናፈርስበታለን? ለዛውም ካለአንዳች ትርፍና ጥቅም ታዲያ ከዚህ በላይ መጠቀሚያነት አለ? ሰውየው ምግቡን ሲያበስል እኛን ለምን ማገዶ ያደርገናል?

ስለዚህ ለሁሉም መፍትሔው በውስጣችን ያለውን ወርቅ አውቀነው ከዛም ቆፍረን አውጥተነው ከራሳችን አልፈን ለሌሎች ጥቅም ፣ ዕረፍት እንዲሁም በረከት መሆን ነው ያኔ እኛም በራሳችን ጉዳይ ስለተጠመድን ሁሉም የራሱን ሲያበስል ራሱን ማገዶ አድርጎ ራሱ መስዋዕትነት ከፍሎ ይሆናል!!

አመሰግናለሁ🙏

@Excellentideas
@Excellentideas
Becoming A Leader - Monroe, Dr. Myles.pdf
696 KB
. BECOMING A LEADER
Dr. Myles Munroe


Discover the leader you were meant to be!
በጣም ጥሩ ለመሪነት የሚያዘጋጅ መጽሐፍ ነው።

ተጋበዙልን!

@Excellentideas
@Excellentideas