Excellent Ideas
632 subscribers
475 photos
68 videos
38 files
59 links
''THINK-LIKE-THERE-IS-NO-BOX''

For any Ideas,Comment and Opinion @AmenNc

Don't hesitate to contact us we need your ideas!!


Before Leaving The Channel Tell us our Problem/ ከቻናሉ ከመውጣቶ በፊት ችግራችንን ይንገሩን🙏 @AmenNc
Download Telegram
#Amazing_Fact_about_Ethiopia

Ethiopia adopted Christianity in the 4th century, making it one of the oldest Christian nations in the world.

Islam also appeared early in Ethiopia, during the time of Mohammed, when his followers fled persecution in Arabia and sought refuge in Ethiopia.

@Excellentideas
@Excellentideas
ብዙዎቻችን ጋር ያሰብነው ቦታ እንዳንደርስ እቅዳችን እንዳይሳካ ፍላጎታችን እንዳይሟላ ያረገ አንድ በሽታ አለ አልችልም የሚል!

አልችልም ሰነፍ ነው አዕምሮን ጨምቆ ይዞ አርፈህ ቁጭ በል ይልሀል

አልችልም ራስወዳድ ነው ሆድህን ብቻ እንድትሞላና ካንተ ዉጪ ለሌሎች እንዳትኖር አስሮ ይይዝሃል

አልችልም ስስታም ነው አንተ ውስጥ ያለና ለብዙዎች መፍትሔ የሚሆን ነገርን እንዳታወጣና እንዳታካፍል ያደርግሃል

አልችልም ጨለማ ነው ከፊትህ ያለውን ብሩህ ተስፋ እንዳታይ ያደርግሃል

አልችልም እስርቤት ነው አዕምሮህን ተጭኖ አሳምኖ ወደራዕይህ አንድ እርምጃ እንኳን እንዳትራመድ ያደርግሃል

አልችልም ፈሪ ነው ከዚህ ነገር ካለፍክ ያለህንም ነው የምታጣው እያለ ቁጭ ያደርግሃል

ስለዚህ ዛሬ ከአልችልም ቀንበር ራስህን አላቅ አንተ ላትችለው ወደአንተ ሕይወት የመጣ ነገር የለም! እንችላለን እናደርገዋለን እናሸንፋለን!!!
ተራ ፉከራ እንዳይመስላችሁ ማድረግ የምትችሉት ነገር ነው። በርቱ ዳይ አልችልም ብለኸው ወደ ነበረው ስራ!

አሜን ዳንኤል

@Excellentideas
@Excellentideas
እባብ በህይወት እያለ ጉንዳንን ይበላል፡፡
እባብ ሲሞት ጉንዳኖች ይበሉታል፡፡
ጊዜ በማንኛውም ሰዓት ይለወጣል
በህይወትህ የማንንም ዋጋ አታሳንስ ምን አልባት አንተ ሀይለኛ ትሆን ይሆናል ጊዜ ግን ካንተ የበለጠ ጉልበተኛ ነው
አስብ አንድ ዛፍ መቶ ሺ ክብሪቶችን ሲሰራ አንድ ክብሪት ግን መቶ ሺ ዛፎችን ታቃጥላለች፡፡አንድ መጥፎ ስራም ብዙ መልካም ነገሮችን ታጠፋለች፡፡ ዋናው ነገር በአስተሳሰብ መልካም ሁን ረጋ ብለህ አስብ ለሁሉም ጊዜ አለው
አትጨነቅ !

@Excellentideas
@Excellentideas
#Amazing_Fact_about_Ethiopia

Aksum, in Ethiopia, is famous as a claimant to the final resting place of the Ark of the Covenant, the chest containing the 10 commandments God gave to Moses, and the standing obelisk, which is 75 feet (23 m) high. With windows and doors, it looks like the world’s first skyscraper.

@Excellentideas
@Excellentideas
በጣም ያሳዝናል!!

ልብ ይሰብራል 💔 Heart breaking

በኦሮሞኛ የሙዚቃ ሥራዎቹ ታዋቂ የሆነው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ዛሬ ማምሻውን “ገላን ኮንደሚኒየም” ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በግምት ከምሽቱ 3፡30 ሰዓት ባልታወቁ ሰዎች መገደሉን ተሰምቷል።

የወንድማችን ሞት የእሱ ወይም የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ሞት ነው። እባካችሁ በእኛ የማይረባ ብሽሽቅ የሚረባውን የሰው ነፍስ አናጥፋ እባካችሁ እባካችሁ እባካችሁ🙏🙏🙏
ከዚህ በላይ ምን እንደምል አላውቅም

እግዚአብሔር ሀገራችንንና ህዝቦቿን ይጠብቅልን!

@Excellentideas
@Excellentideas
እንዴት Grief ማድረግ አንዳለብኝ አላውቅም፡፡ ጭራሽ ደግሞ የእሱን ሞት አሁንም ለራሳቸው የፖለቲካ ማስኬጃ የሚጠቀሙ ሰዎች ሳይ ዘገነነኝ፡፡ We are so vulnerable right now. We lost our son. Anyone can manipulate us easily. እባካችሁ ሀዘናችንን ስንገልጽ ሌላ የማንወጣው ችግሮች ውስጥ በማያስገባን ይልቁንም ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጣልን በሚችል መልኩ መሆን አለበት፡፡ ግድያ ብሄር የለውም፣ ግድያ ቋንቋ የለውም፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ እያወገዘው ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ የብሄር ግጭት ለማስነሳት እየሮጡ ያሉ ብዙ ናቸው፡፡ Don’t be victim of conspiracy theories. Please don’t fall in their trap, this is what they wanted in the first place eko. Be your brothers and Sisters Keeper!!

Hachalu Hundessa Rest in peace Brother!
Being an Ethiopian

@Excellentideas
@Excellentideas
“እኛ ዓባይን እንገድብ ብንል አቅሙ የለንም። የውጭ ወዳጅ አገራትን ደግሞ ‘ዓባይን ለመገደብ እንድንችል አግዙን’ ብለን ብንጠይቅ ግብጽን ላለማስቀየም ፈቃደኛ አይሆኑም። ቀጣዩ ትውልድ ግን በራሱ ንዋይ ይገነባዋል። ስለዚህ ጥናቱ በክብር ይቀመጥ!”

ይህንን ንግግር ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴ እንደተናገሩት በስፋት ይነገራል።

ይህ ትንቢታዊ የሚመስል ቃል ይፈጸም ዘንድ አፋፉ ላይ እንገኛለን። ተጋድሎው አሁንም ጠንካራ ነው፤ ግብጽ አሁንም በርካታ ወዳጆች ስላሏት በክፋት ስልቷ የግድቡ ነገር ህያው እንዳይሆን ምንም አይነት ዓለም አቀፍ ድጋፍና እንዳይደረግ ሌት ተቀን ታሴራለች! ነገር ግን ይህ ትውልድ በአንድነት ተባብሮ ከራሱ ባመነጨው ጥሪቱ ይህን ታላቅ ራዕይ እውን እያደረገ ይገኛል። ስራው ገና ሙሉ በሙሉ አላበቃም፣ ወደፊት የሚቀረውም መንገድ ገና ዳገታማ ሊሆን ይችላል። ለአሁኑ ግን ግድቡን በውሃ ለመሙላት ቁርጥ ሰዓት ላይ እንገኛለን!


@Excellentideas
@Excellentideas
Watch "ፖለቲካ ይሉት ተግባር እስከዚህ ድረስ ቁሻሻ ነው!! - ጌትነት እንየው
Watch "ፖለቲካ ይሉት ተግባር እስከዚህ ድረስ ቁሻሻ ነው!! - ጌትነት እንየው

እየሰማሁት የምሬን ተሰማኝ እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ እስቲ ስሙትና ለሌሎችም ሼር በማድረግ አጋሩት🙏

@Excellentideas
@Excellentideas

https://youtu.be/Tbvcjtsnr8c
እንኳን ደስ አለን!!!!

ዛሬ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እንዳበሰሩን የመጀመሪያው ዓመት የህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት በስኬት ተጠናቋል!!!

ግድቡ ከእንግዲህ በሁለት እግራችን ለመቆም እንደማይሳነን ወደከፍታው ለማቅናት የመታጠፊያ ነጥባችን መሆኑን ዓለም በትክክል ይረዳል!!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ለህዳሴው ግድብ ስኬት ከመዋጮ ጀምሮ በሙያቸው፣ በጉልበታቸውና በእውቀታቸው እንዲሁም በዓለም አቀፉ መድረክ በተደረገው ድርድር ለተሳተፉ አካላት እንዲሁም ለቀድሞዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

እኛም አመስግነናል!!!

@Excellentideas
@Excellentideas
ዛሬ የሞባይል ዳታ የኢንተርኔት አገልግሎት ተለቋል
ይህም ማለት ሰፊው ህዝብ ኢንተርኔት ማግኘት ይችላል ማለት ነው።

ኢትዮጵያዊያን ዝቅተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት ካላቸው ሀገራት ውስጥ ቢመደቡም ከዛም ባለፈ በጣም ዝቅተኛ የኢንተርኔት አጠቃቀም ባህል ያለው ህዝብ እንዳላት ይነገራል። ጠቅላይ ሚንስትራችን ሲናገሩ እንደሰማነው አንድ ጥሩ Lecture ወይም ትምህርት ሰጪ ነገር ከማየት ይልቅ አንድ ስድብ ያለበትን ነገር ለማየት ብዙ መቶ ሺዎች ይሰለፋሉ በዛም በገዛ እጃችን አመጽን፣ ጥላቻንና የፀብን ሀሳብ ይሸምታሉ!

እኔ በግል አመለካከቴ ኢንተርኔት ተዘግቶ በመቆየቱ ብጎዳም ደስተኛ ከሆኑ ሰዎች መካከል ነኝ ምክንያቱም ለአብዛኛው ህዝብ ከጉዳቱ ይልቅ ጥቅሙ ስላመዘነ
ኢንተርኔት በመኖሩ ብሔር ከብሔር ከተጣላ ኢንተርኔት በመኖሩ ክብር የሰው ሕይወት እንዲሁ ወድቆ ከቀረ ኢንተርኔት በመኖሩ ሀገር ከፈረሰች ለምን ለዘለዓለሙ ኢንተርኔት ጥንቅር ብሎ አይቀርም!!

በአጠቃላይ ሀሳቤ እስከዛሬ ኢንተርኔትን ካለአግባብ በመጠቀማችን ከደረሰው ጉዳት ተምረን ከዚህ በኋላ ኢንተርኔትን ራስንና ሀገርን መርዞ ወደኋላ ለማስቀረት ሳይሆን አንድ እርምጃ ወደፊት ለማራመድ እንጠቀምበት!!

አመሰግናለሁ!

ምናልባት ይሄ መልዕክት ለሌሎች እንዲደርስ በቻልን መጠን ሼር በማድረግ እንድናደርስ በአክብሮት እጠይቃለሁ

@Excellentideas
@Excellentideas
ከላይ ባለው ምስል በምናየው የሩጫ ውድድር ላይ ከፊት ያለው ኬንያዊው አትሌት አቤል ሙታይ ውድድሩን ለመጨረስ ጥቂት ጫማ ርቀት ብቻ ሲቀረው ሩጫውን ማጠናቀቁን የሚያበስረው ምልክት ግራ አጋብቶት አሸነፍኩ ብሎ ቆሞ ነበር፡፡
ከኃላው በቅርብ ርቀት ሲከተለው የነበረው ስፔናዊው አትሌት ኢቫን ፈርናንዴዝ ኬንያዊው ለምን እንደቆመ ስለገባው ሩጫውን እንዲጨርስ በጩኸት ይነግረው ጀመረ ነገር ግን አቤል ሊሰማው አልቻለም በመጨረሻም አጠገቡ ሲደርስ ኬንያዊውን ወደፊት ገፍትሮ ውድድሩን እንዲያሸንፍ አደረገ።

ከውድድሩ በኃላ ኢቫን ከጋዜጠኛ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ይህን ተናገር:-

ጋዜጠኛ:- ለምን እንዲህ አደረግክ?
ኢቫን:- ህልሜ አንዳችን ስንደክም፣ስንሳሳት፣ወደኃላ ስንቀር... የምንተጋገዝበት ማኅበረሰብ እንዲኖረን ነው።👌

ጋዜጠኛ:- ታዲያ ኬንያውያን እንዲያሸንፍ ለምን ረዳኸው?
ኢቫን:- መጀመሪያውንም ውድድሩን ያሸነፈው እርሱ ነው👏

ጋዜጠኛ:- ግን አንተ አሸንፈህ የወርቅ ሜዳሊያውን መውሰድ ስትችል ወርቁን አሳልፈህ ሰጠኸው ለምን?
ኢቫን:- ጋዜጠኛውን እየተመለከተ ቀድሞ ያሸነፈውን ውድድር በትንሽ ስህተት ከሚያጣ መጠነኛ እርዳታ አድርጌለት ቢወስድ ከኔ የሚቀነስ ነገር ምንድን ነው? አሸንፌስ ቢሆን የዚህ ሜዳሊያ ክብር ምንድን ነው? የድሌስ ዋጋ ምንድን ነው? በጎ ስራን ያስተማረችኝ እናቴስ ይህን ስታይ ምን ትለኝ ነበር? ብሎ ተናገር

መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል፤ እኛስ ለልጆቻችን ምን አይነት እሴት እያስተላለፍን ነው?

@Excellentideas
@Excellentideas
#ውስጥህ ያለውን ጀግና አንቃው!!

ውስጥህ ተአምር መፍጠር የሚችል ሀይል አለ!! ሰው፣ሰፈር፣ጓደኛና ቤተሰብ የሰጠህ መታወቂያ ትክክል አይደለም። እዚህ ምድር ላይ ለምን የመጣህ ይመስልሀል ? ባጋጣሚ ?ወይስ ስለምታስፈልግ ? እዚህ ምድር ላይ ባንተ ብቻ የሚሰራ ስራ አለ። እመነኝ አለ። አንተ ብቻ ሌላ ማንም የማይሰራው ስራ በዉስጥህ አለ። ይህ የህይወት ትልቁ ስጦታ ነው። የሚያናደው አንተ ብቻ መስራት ያለብህን ስራ ባለመስራትህ የምትጎዳው አንተ ብቻ አይደለህም። ሌሎችንም ትጎዳለህ። ይህ የ universe አሰራር ነው። ሌሎች የሌለህን ይሰጡሃል እንተም በተራህ የሌላቸውን ትሰጣቸዋለህ። ለምሳሌ የያዝከው ሞባይል፣የለበስከው፣ጫማ፣የምትነዳው መኪና ሰዎች ላንተ ያበረከቱት ስጦታ ነው። አንተም በምላሹ የሌላቸውን ልትሰጣቸው ይገባል።
የምትኖርለት መኖር ካቃተህ የምትሞትለት አላማ አለ? ይህንን ሳልሰራማ አልሞትም የምትልለት አላማ ምንድን ነው? በምታደንቃቸው ሰዎች እና በአንተ ያለው ልዩነት ምንድን ነው? 24 ሰዓት ስለነሱ በመስማት እና በማውራት ጊዜህን በምታጠፋባቸው ሰዎች እና በአንተ ያለው ልዩነት ምንድነው? እውነቱን ልንገርህ እነሱ የተፈጠሩለትን አላማ አውቀውታል። ጉልበታቸውን፣ ዕውቀታቸውንና ጊዜያቸውን አላማቸው ላይ ብቻ ያጠፋሉ። አንተስ? ከጀርባቸው መከራ፣ ችግር፣ ትችትና ጠንክሮ መስራት አለ። ይህን ሁሉ ተቋቁመው ማለፋቸው ነው ዛሬ ላይ ያላቸውን ስም እና ዝና መገንባት የቻሉት። ስለሰው በመስማት እና በማውራት ዘመንህ እንዳያልቅ።ህይወት አጭር ናት ተጠቀምባት።
ኢትዮጵያ መወለድህ ፣ ድሃ ቤተሰብ ውስጥ መኖርህ ፣ ገንዘብ ስለሌለህ አይደለም እንደነሱ እንዳትሆን ያደረገህ ። እንደዛ የምታስብ ከሆነ ሞኝ ነህ። እንደነሱ እንዳትሆን ያደረገህ #ትጋት የሚባል መርህ ነው።
የምታነባቸው መጻሕፍትና የምታያቸው ፊልሞች ራዕይህን የሚያግዙ፣ ለስራ ፈጣሪነት inspire የሚያደርጉ፣ ለአዲስ አስተሳሰብ የሚጋብዙ፣ መንፈሳዊነትህን የሚያሳድጉ ይሁኑ። ይህን ስታደርግ ግን ከባድ ተግዳሮት ይገጥምሀል። ጓደኞችህ ሙድ ይይዙብሃል፣ ፋራ ይሉሃል አንተ ግን ሁለት ጣትህን ሁለት ጆሮህ ውስጥ ከተህ ወደ ፊት ቀጥል።
አስታውስ አንተ ዛሬ ያልሆንከው ነገ የምትሆነው፣ ዛሬ የማታወራው ነገ የምታወራው፣ ዛሬ የማትሰራው ነገ የምትስራው ነገር አለ። ታገል። ተፉለም። ድብን አድርገህ ተሳሳት። 7ቴ ብትወድቅ ለስምንተኛ ጊዜ ተነስ። ትላልቅ ሰዎች ያገኙትን መኪና፣ ገንዘብና ዝና በአንድ ጀምበር አላገኙትም።
እንደ ገና ዳቦ ከላይ እሳት ከታች እሳት ዘንቦባቸው ነው። ከህይወት ጋር ታግለው አሸንፈው ነው። የህይወትን መራራ ፅዋ ፉት ብለው ነው። አንተስ ለዚህ ዝግጁ ነህ? ለመሳሳት፣ ለመሰደብ፣ ፋራ ለመባል ዝግጁ ነህ? ትልቅ ለመሆን ትልልቅነት የሚገኝበትን መንገድ ለመሄድ መወሰን አለብህ። ሂደቱን (process) ጠልተህ ስኬቱን ወደህ አይሆንም። ሀላፊነት መውሰድ ከፈራህ ሕይወትህን በሙሉ follower ከመሆን ውጪ አስከታይ መሆን አትችልም። ደስ የሚለው ጊዜው ገና ነው። አሁን ብትጀምር ትጨርሳለህ። ዛሬ ወስን። የተሳካለት ዶክተር፣ የተሳካለት አርቲስት ፣ የተሳካለት ነጋዴ፣ የተሳካለት መንፈሳዊ ሰው፣ የተሳካለት ተማሪ፣ የተሳካለት ስፖርተኛ መሆን ትችላለህ። እመነኝ ትችላላ። ዋናው ነገር መትጋት ነው።

Eyob G/mariam

@Excellentideas
@Excellentideas
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው!!

እንዴት አንድ ሰውን በሀገሩ ሄደህ ትደበድባለህ የሀገራችን ስም በዓለም አደባባይ የዚህን ያህል መዋረድስ ይገባው ነበር?
እውነቱን ለመናገር ይሄ ሁሉ የአለመማርና የድህነት ውጤት ነው!

የሁሉም ብሔር ፖለቲከኞች እባካችሁ ፖለቲካውን በዕውቀት ላይ የተመሰረተና የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚሻ አድርጉት እንጂ ወደኋላ ተመልሳችሁ ቁልቁል አታውርዱን ሀገራችንንም አታሸማቋት!!

@Excellentideas
@Excellentideas
መማር በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። የተማረ ሰው ነገሮችን አስፍቶና በተሻለ ከፍታ የማየት ዕድሉ የበረታ ነው።

በእርግጥ መማር ስል አሁን በለመድነው አካሄድ ያለውን ብቻ አይደለም ውስጣችን ላይ ባለው ክህሎት ላይ ተመርኩዘን በትምህርት ማሳደግ የብልህ ምርጫ ነው። ለምሳሌ ሙዚቃ ከሆነ ተሰጥኦህ በልምድ ከምትጫወተው ሙዚቃ ይልቅ በትምህርት የምታጎለብተው አጨዋወት እጅግ የተሻለ ነው።
ሁሉም ነገር ራሱን የቻለ ሳይንስ ነው በዚህ በኩል የሀገራችን የትምህርት system በጣምምምም ደካማ ከመሆኑ የተነሳ ሳይንስ ሲባል ወደ አዕምሮአችን የሚመጣው Biology እና Chemistry ነው ነገርግን ሁሉም ነገር ሳይንስ ነው ስፖርት ብትል አርት ብትል ሳይንስ ናቸው።

እና ሀሳቤን ስጠቀልለው ውስጣችሁ ያለውን ተሰጥእ ወይም ክህሎት በትምህርት የማሳደግ ልምድ ቢኖረን መልካም ነው።

@Excellentideas
@Excellentideas
You can not change your past, but you can be a master of your future!

@Excellentideas
@Excellentideas
ሁሉ እንደ ሀይሌ ቢሆን

የ27 ሪከርዶች ባለቤት የሆነው እና ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ከፍ ያደረጋት ጀግናው ኢትዮጵያዊ ሀይሌ ገብረስላሴ በቅርቡ በሻሸመኔ እና ዝዋይ የደረሰበትን ጥቃት አስመልክቶ በሚዲያ ቀርቦ ሲናገር "ከኢትዮጵያ ውጪ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት የለኝም" ብሎ ነበር።

ምንም እንኳን በአንድ ቀን 300 ሚሊዮን የሚጠጋ ንብረት ቢወድምበትም በሁለቱም ድርጅቶቹ ለሚሰሩ ከ400 በላይ ለሆኑ ሰራተኞቹ የሁለት ወር ደሞዝ ግን መክፈል ችሏል።

"አንድ ሰው ማትረፍ ዓለምን እንደማትረፍ ነው" አይደል የሚባለው።

ዛሬ ደግሞ በሀገሩ ተስፋ ሳይቆርጥ በኤሌክትሪክ የምትሰራ መኪና በሀገር ውስጥ ገጣጥሞ ለገበያ አቅርቧል። እፍታውንም የሀገሪቱን የብልጽግና ጉዞ ለሚመሩት ጠሚ አስረክቧል።

ኢትዮጵያዊነት፣ ሀገር ወዳድነት በቃል ሳይሆን በተግባር ይሁን።

ዐቢይ ታደለ /ኪያ/

@Excellentideas
@Excellentideas