Event Addis Media
9.08K subscribers
5.26K photos
5 videos
3 files
3.97K links
Connect with Addis Ababa's artistic community! Find out about art exhibitions, music events, workshops, and cultural experiences. Contact: @Tmanaye
Download Telegram
"አልፅፍም"መጽሐፍ ለንባብ በቃ

የአይዳ ታደሰ " አልፅፍም" የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ባሳለፍነው ቅዳሜ ለንባብ በቅቷል።

የግጥም መጽሐፉ በ140 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ200 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል በዓይናለም መጻሕፍት መደብር ውስጥም ይገኛል ተብሏል።

መጽሐፉ ታሪክን፣ ቁጭትን፣ ቁጣን፣ ተስፋ መሰነቅን፣ ተስፋ መቁረጥን፣ ምኞትን፣ ትዝብትን እና ምናባዊ ዳሰሳን የያዘ ሲሆን “ሰቆቃወ አይዳ” እና “ምናብና ትዝብት” በተሰኙ ንዑሰ ርዕሶች ተከፍሎ የቀረበ የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ነው።

አይዳ ታደሰ ከዓመታት በፊት ገጣሚያኑ በረከት በላይነህ ፣ አበባው መላኩ ፣ ቸርነት ወ/ገብርኤል እና ሌሎችም የተሳተፉበት "ቃል እና ቀለም" የተሰኘ ፊልም ለተመልካች ማድረሷ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"መስተዋድድ" የኪነጥበብ ምሽት ዛሬ ይካሄዳል

"መስተዋድድ" የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ግንቦት 14 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ ሜክሲኮ በሚገኘው ገነት ውስጥ ይካሄዳል።

በዕለቱም ገጣሚያኑ ሚካኤል ምናሴ ፣ ሂክማ ፋንቱ ፣ዘውድ አክሊል ከሚሎ ባንድ ጋር በመሆን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

በተጨማሪም ደራሲ ገብረክርስቶስ ደስታ፣ ሔኖክ ስዩም ፣ ሰመረ ባሪያው ፣መሐመድ ካሣ እና ካሣዬ ጨመዳ ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ሮፍናን ኑሪ የክብር የእንግዳ የሆነበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት ዛሬ ይካሄዳል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 14 2016 ዓ.ም ይካሄዳል።

በዕለቱ ሮፍናን ኑሪ "የአንድ ግጥም፣ የአንድ ወግ" የክብር እንግዳ ሆኖ  ይገኛል።

እንዲሁም ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ብለዋል አዘጋጆቹ ።

ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"የአዲስ አበባ ሰፈር ፣ እድር ፣ እና ግቢ" ውይይት

በዶ/ር አንተነህ ተስፋዬ የተዘጋጀው "ሰፈር፣ እድር እና ግቢ" የተሰኘው መጽሀፍ  የኢትዮጵያን የከተማ ኑሮ፣ ስፍራ የማበጀት እና የንድፍን ንድፈ ሀሳብ  የሚያሳይ መጽሀፍ ነው።

በዚህ በዶ/ር አንተነህ ተስፋዬ መጽሀፍ ሀሳብ ላይ ነገ ሐሙስ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 እስከ 10፡30 ድረስ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ዋናው ግቢ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ውስጥ ውይይት ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Event Addis Media
Photo
ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ በቅርቡ ለአድማጮች ያደረሰው "ቢሊሌ" ሙዚቃ ላይ የተጠቀሰችው "ቢሊሌ" ማናት ?

መህቡባ/ቢሊሌ

በኦሮሚያ ክልል በምትገኘው ጉማ እ.ኤ.አ. በ1820 ስትወለድ ቤተሰቦቿ "ቢሊሌ" የሚል ስም አውጥተውላት ነበር። ትርጉሙም "ቆንጆ" "የምታምር" እንደማለት ነው። መህቡባ ማለት ደግሞ በአረብኛ "ተወዳጇ" ማለት ነው።

መህቡባ እድሜዋ 15 ዓመት ሲሞላት እ.ኤ.አ. በ1835/36 በተነሳ የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት አባቷንና ስድስት ወንድሞቿን  አጣች። በ1837 በለጋነት እድሜዋ በእሳት ቃጠሎ ከወደመው የትውልድ መንደሯ በባሪያ ፈንጋዮች ተፈንግላ ከእህቷ ጋር ተቆራኝታ ወደ ጎንደር ከተወሰደች በኋላ ለሽያጭ ልትቀርብ በሱዳን ካርቱም አድርጋ ወደ ካይሮ አቀናች።

በ1837 የጀርመኑ ልዑል ኸርማን ፉርስት ቮን ፐክለር-ሙስካው ወደ ሰሜን አፍሪካ ጉዞ አድርጎ ነበር። በካይሮ ቆይታው የቱሪስቶች ተወዳጅ ስፍራ ወደሆነው የካይሮ የባሪያ ገበያ ቦታ ይሄዳል። በእዛም በባርነት ለሽያጭ በቀረበች አንዲት ጉብል የኦሮሞ ልጅ ውበት ይማረካል። ወዲያው ተደራድሮ ከገዛት በኋላ አገልጋዬ ናት በማለት ዋሽቶ ከእራሱ ጋር አብራው እንድትጓዝ አደረገ።

ልዑሉ በመህቡባ ፍቅር ተንበረከከ። ልዑሉና መህቡባ ወደ ፍልስጥኤም፣ ሶርያ እና ኢስታንቡል አብረው ተጉዘዋል። ልዑሉ ተፈጥሮ ለመህቡባ በለገሰቻት ሞገስና የአውሮፓውያንን ባህል ለመልመድ በምታሳየው ፍላጎት ተደምሞ ነበር። እሷም ባልጠበቀችው አዲስና ያልታሰበ ሁኔታ ደስተኛ ሆና ነበር።

አውሮፓ እንደደረሱ ለተወሰነ ጊዜ በቡዳፔስት ቆይታ አድርገው ነበር። በእዛም መህቡባ የቅዱስ ጥምቀት ስነስርዓት እከናውናለች። ልዑሉም መህቡባን ለተወሰነ ጊዜ በቪየና ወደሚገኝ ጥሩ ትምህርት ቤት አስገብቷት የትምህርት ቤቱን መነኩሴዎች አውሮፓዊ አኗኗርን እንዲያስተምሯት ነገራቸው። እሷም ተፈጥሮ በሰጠቻት ፀጋና ንቃት በትምህርቷ በመጎበዝ ሁሉንም አስደስታለች። የገባችበት ሁሉ አካባቢውን በፈገግታዋ ታደምቅ ነበር። ለቋንቋ የተሰጠች ስለነበረች ጣሊያንኛ በቶሎ ለመደች። አብረዋት ሊሆኑ የሚወዷትና በተፈጥሮ ገርና ደግ ነበረች።

ማህበረሰቡም የልዑሉንና የልዕልቷን ግንኙነት በቅንነት ተቀብሎ የመህቡባ አስደናቂ ውበት ያደንቅ ጀመረ። የቪየና ጣእም ሆነች፣ ጋዜጦችም ስለሷ አድንቀው ይፅፉ ነበር። የወሬ ሁሉ ማድመቂያም ሆነች። ወደ ንጉሱ ዙፋን በተወሰደች ጊዜም ይሁንታንና ግርማ ሞገስን አገኘች። ሁሉም ሰው ወደዳት።

ይሁን እንጂ መህቡባ ምግቡንና ቀዝቃዛውን የአውሮፓ አየር መልመድ አቃታት። በጊዜ ሂደትም በሳንባ ምች ተይዛ በፅኑ ታመመች።

ልዑሉ  መህቡባን ለሚንከባከበው ሃኪም ጥብቅ ክትትል እንዲያደርግላትና ስለ እርሷም እንዲያሳውቀው አዝዞት ለሥራ ወደ በርሊን ተጓዘ። ከሁለት ቀናት ቆይታ በኋላ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 27 ቀን 1840 የመህቡባ አገልጋይ የመህቡባን መኝታ ክፍል መጋረጃ ስትገልጥ መህቡባን ሞታ አገኘቻት። ብቻዋን ሞታ ተገኘች። በትልቁ አልጋ ላይ እንደ ትንሽ ምስል ትታይ ነበር። በአቅራቢያው በሚገኝ መካነ መቃብርም ተቀበረች። በመቃብሯም ላይ "መህቡባ" ብቻ የሚል ፅሁፍ ያለው ምልክት ተደረገላት። መካነ መቃብሯን በየአመቱ ሺህዎች ይጎበኙታል።

ልዑሉ ስለ መህቡባ ሞት ለጓደኛው በፃፈው ደብዳቤ "ሰው መውደድ እችላለሁ ብዬ ከማስበው በላይ ወድጃት ነበር። ሞቷም ጥልቅ ስቃይ ውስጥ ከትቶኛል። እርሷ ለእኔ ሁሉ ነገሬ ነበረች" በማለት መሪር ሃዘኑን ገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የአባቶች ቀን ልዩ ውድድር

ዘንድሮ በኢትዮጵያ ለ16ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ አባቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ልጆች ለአባታቸው ያላቸውን ክብርና ምስጋና በምን መልኩ እንደሚገልፁ የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ በመቅረጽ የሚካሄድ ነው።

ምስሎቹ እስከ ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በሚያገኙት የእይታና የላይክ መጠን ተመርጠው

1ኛ - ለሚወጣ የምስክር ወረቀት፣ ጋቢና ከውዱ አባብዬ ጋር በዮድ አቢሲኒያ ልዩ የምሳ ግብዣ፡፡

2ኛ - ለሚወጣ ጋቢና ከውዱ አባብዬ ጋር በዮድ አቢሲኒያ ልዩ የምሳ ግብዣ፡፡

እንዲሁም 3ኛ ለሚወጣ ከውዱ አባብዬ ጋር በዮድ አቢሲኒያ ልዩ የምሳ ግብዣ ላይ የሚታደሙ ይታደማሉ።

ተወዳዳሪዎች ቪዲዮዎቻቸውን ከታች በሚገኘው በኢትዮጵያ አባቶች ቀን በጎ አድራጎት ድርጅት ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅ መልዕክት መላኪያ ላይ ያስቀመጡ።

https://www.facebook.com/profile.php?id=100064190287928&mibextid=ZbWKwL
ፕሮግራሙ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በዮድ አቢሲያ የባህል አዳራሽ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይከናወናል።
ከዛሬ ጀምሮ የ12ኛው የበጎ ሰው ሽልማት የእጩዎች ጥቆማ መስጠት ይችላል ተብሏል።

ላለፉት 11 ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች ሽልማትና እውቅና ሲሰጥ የቆየው የበጎ ሰው የሽልማት ድርጅት ዘንድሮ ለ12ኛ ዙር ሽልማት እጩዎችን ለመቀበል የጊዜ ሰሌዳውን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም ከዛሬ ግንቦት 14  እስከ ሰኔ 14/2016ዓ.ም ድረስ የእጩዎች ጥቆማ እንደሚከናወን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቋል።

የበጎ ሰው ሽልማት እውቅና ከሚሰጣቸው ዘርፎች መካከል መምህርነት፣ መንግስታዊ ኃላፊነትን በአግባቡ የተወጡ አካላት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በጎ አድራጎት፣ ኪነጥበብ፣ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች ተካተውበታል።

ከዚህ ባለፈ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሆነው በባህር ማዶ የሚኖሩ ለሀገር በጎ ተግባር ላበረከቱ ግለሰቦችም ይሰጣል ተብሏል ።

በተገለፀው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ህዝቡ ለሽልማቶቹ ብቁ ናቸው የሚላቸውን አካላት በስልክ ቁጥር 0977232323  መምረጥ ይችላል ።ከዚህ ባለፈ በፖስታ ቁጥር 150035 ላይ መልዕክት  መላክ ይቻላል ተብሏል ።

ዘገባው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ነው

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የሐሙሰ መረጃዎች ደርሰዋል(የቻናሉ ስፔሻል )

እነሆ ተወዳጇ እና ተናፋቂዋ ሐሙስ ደረሰች

የሳምንቱ ኪናዊ መረጃዎች ቀጥለው ይቀርባሉ:-

ተከታዩን ሊንክ
https://rb.gy/0qui84 በመነካት ብቻ የቻናሉን ስፔሻል የሐሙስ መረጃዎችን በድረገጻችን በጥሩ አቀራረብ ማንበብ ትችላላችሁ።

ማሳሰቢያ: የኤቨንት አዲስ ድረገጽ መረጃዎችን በእርሶዎ ሚዲያ ሲጠቀሙ እባክዎ በተገቢው መንገድ ምንጭ ይጠቀሱ።

የEventAddis/ሁነት አዲስ ማህበራዊ ገፆቻችን:

Telegram:https://t.me/EventAddis1

Website: https://eventaddis.com

Facebook:https://facebook.com/groups/2009372275938661/

Facebook Page:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851&mibextid=ZbWKwL
የሳምንቱን የሙዚቃ ሰሞነኛ መረጃዎች ( በአጭሩ )

📍የድምጻዊ አንተነህ ምናሉ "አይዞን" የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ነገ አርብ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሙዚቃ ማሰራጫ መተግበሪያዎች በኩል ለአድማጮች ይደርሳል። የሙዚቃው ግጥም የሳሙኤል ሽፈራው ሲሆን ዜማውን ደግሞ ራሱ አንተነህ ምናሉ ሰርቶታል።  ድምጻዊ አንተነህ ምናሉ ከዚህ ቀደም "ዱንያ" እና "አንለይ" የተሰኙ ሙዚቃዎችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን ለአድማጮች አድርሷል።

📍የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "ይለያል "የተሰኘ የሙዚቃ ቪዲዮ ነገ አርብ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ይለቀቃል። የሙዚቃው ግጥም የወንድሰን ይሁብ ሲሆን ዜማው በብስራት ሱራፌል ተሰርቷል። የሙዚቃ ቪዲዮው ዳይሬክተር ወንድሰን ይሁብ ነው። ለምለም ኃ/ሚካኤል ባሳለፍነው ሳምንት "ማያዬ" የተሰኘ አልበም ለአድማጮች ማድረሷ ይታወሳል።

📍"አዲስ ጃዝ" የጃዝ ፌስቲቫል ከግንቦት 16 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል።ዝግጅቱ የሚካሄድበት ስፍራ አፍሪካን ጃዝ ቪሌጅ ሲሆን  አፍሪጎ ባንድ ከዩጋንዳ፣ ድምጻዊ ሴልሞር ቱኩድዚ ከዚምባብዌ፣ ማቲው ቴምቦ ከዛምቢያ በዕለቱ የሙዚቃ ስራቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።ከኢትዮጵያ ደግሞ ዳዊት ይፍሩ ፣ግርማ በየነ፣ ጆርጋ መስፍን፣ ያሆ ባህላዊ የሙዚቃ ባንድ፣ መሐሪ ብራዘርስና ዮሃና ሳህሌ በፌስቲቫሉ ስራቸውን እንደሚያቀርቡ ተነግሯል።በዚህ ፌስቲቫል የሙዚቀኛ ጆርጋ መስፍን "ከሁሉም የላቀው ደግ" አልበም ይመረቃል።

📍"ብርሃን ኮንሰርት" የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል። ገቢው ለሰበታ መርሐ የዓይነስውራን ት/ቤት እንዲውል  የተዘጋጀው "ብርሃን ኮንሰርት " የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 17 2016 ዓ.ም በግዮን ሆቴል እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የፐርፐዝ ብላክ " Invest in Poverty  Intiative" የተሰኘ አዲስ ዘመቻ የማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሄደ

ፐርፐዝ ብላክ በዛሬዉ ዕለት ሰዎች በየወሩ 100 እና ከዚያህ በላይ ብር የሚቆጥቡበት"Invest in Poverty  Intiative" የተሰኘ ዘመቻ  አስጀምሯል።

ፐርፐዝ ብላክ በዚህ ዘመቻ ተጠቃሚዎች በየወሩ ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ ገንዘብን በመቆጠብ ከፍ ያለ ትርፍ የሚያገኙበት አሰራር እንደሆነ አስታውቋል።

ተቋሙ በዚሁ መርሐግብር ላይ እንዳሳወቀዉ በአሁኑ ወቅት ካፒታሉ 2.4 ቢሊዮን ብር መድረሱን ነው። የፐርፐዝ ብላክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሃ እሸቱ(ዶ/ር) ሰዎች የሚያስቀምጡት ገንዘብ በዝግ ሂሳብ የሚቀመጥና ባሻቸዉ ጊዜ ወጪ የሚያደርጉበት መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ አዲስ አሰራር መሰረት ተቋሙ በቀጣዮቹ አምስት አመታት 100 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ማቀዱንም ይፋ አድርገዋል።

ቆጣቢዎች በተለመፈዉ የባንክ ቁጠባ ከሚያገኙት 7 በመቶ ወለድ በተሻለ በዚህ የቁጠባ ስርዓት 10 በመቶ ወለድ ተከፋይ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ከሕብረት ባንክ 19 በመቶ ወለድን ለተቋሙ የሚያቀርብ ሲሆን በጋራ ይሰራል ባሉት ስራም ፐርፐዝ ብላክ 9 በመቶ ድርሻ እንደሚያገኝ ጠቅሰዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የ"አኮፋዳ" ፕሮጀክት አካል የሆነው የፋይናንስ መረጃ ቋት ዛሬ በተካሄደ ሥነሥርዓት ይፋ ተደረገ

በኢትዮጵያ ለሚገኘው የፋይናንስ ዘርፍ አጠቃላይ መረጃ ፣ ምልከታና ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ያለምንም ክፍያ የሚያቀርብ ፈጠራ የታከለበት ፕላትፎርም ይፋ ተደረጓል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በተቀናጀ ሚዲያ፣ መረጃ አቅርቦትና ትንተና እንዲሁም ማማከር ከተሰማሩ ተጠቃሽ ድርጅቶች አንዱ የሆነው ሸጋ፣ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት  የኢትዮጵያ ፕላትፎርም መከፈቱን በዛሬው ዕለት ይፋ ያደርገው።

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተካታችነትን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሻሻል የሚያስችል አገልግሎት ማዕከል እንደሆነም ተገልጿል።

ይህ መረጃ ትንታኔና ምልከታን ይዞ ለየት ባለ መልኩ የመጣው ፕላትፎርም የፋይናንስ ተቋማትን፣ ውሳኔ ሰጪዎችን፣ የዘርፉ ባለ ድርሻዎችን እንዲሁም ተጠቃሚዎችን ሁሉ አቅም በማሳደግ፣ የኢትዮጵያን ዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍን ለመደገፍ ያለመ  ተብሏል።

ፕላትፎርሙ በሸጋ የበለፀገ ሲሆን፣ የሦስት ዓመት "አኮፋዳ" የተሰኘ ፕሮጀክት አካል ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ዓላማ የባለ ድርሻ አካላትን ዕውቀት በማዳበር፣ ለአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች የሚሆኑ አገልግሎቶችን መደገፍ፣ እንዲሁም በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ላይ ሰዎች ያላቸውን መተማመን በመገንባት የፋይናንስ ተካታችነትን ለማሻሻል ያለመ ነው፡፡

የፕላትፎርሙ ማብሰሪያ ሥነ ሥርዐት ዛሬ በሃያት ሬጀንሲ ሆቴል የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የዘርፉ ባለሙያዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት ተከናውኗል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የኢትዮጵያ አባቶች ቀን ተከበረ

የኢትዮጵያ አባቶች ቀን "ክብር ለአባትነት" በሚል ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ለ16ኛ ጊዜ ተከብሮ ውሏል።

ላለፉት አመታት በኢትዮጵያ የአባቶች ቀንን ግንቦት 15 ላይ ሲያከብር የቆየው የኢትዮጵያ አባቶች ቀን በጎ አድራጎት ድርጅት ዘንድሮ ለ16ኛ ጊዜ "ክብር ለአባትነት" በሚል ዕለቱን በዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ በልዩ ልዩ ሁነቶች አክብሮ ውሏል።

ከዚህ ቀደም በነበሩት ዓመታት ከቤተሰብ እስከ ሃገር በመልካም አባትነትና አበርክቶ የሚነሱ አባቶችን፤ የኢትዮጵያ አባቶች የክብር መገለጫ የሆነውን ጋቢ በመደረብ፣ ዝቅ ብሎ እግር በማጠብ፣ የዕውቅና ምስክር ወረቀት በመስጠትና ታሪካቸውን በመሰነድ ሲያመሰግን እና ሲያከብር ቆይቷል።

በዘንድሮው ዓመት የኢትዮጵያ አባቶች ቀንም ልጆች ለአባታቸው ያላቸውን ፍቅርና ክብር እንዲገልፁ ብሎም አባቴ የተለየ ታሪክ አለው የሚሉ ታሪካቸውን እንዲያጋሩ በማድረግ ለሁለት አባቶች ልዩ ዕውቅና እና የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል፤ የክብር ጋቢ የማልበስና እግር የማጠብ ስነ ስርዓትም ተከናውኗል።

ይህ የኢትዮጵያ አባቶች ቀን ኢትዮጵያውያን በራሳችን ወግና እሴት ብሎም የመከባበር ባህል መሰረት ኢትዮጵያዊ ቀለም ባለው መልኩ "ክብር ለአባትነት" በሚል ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ ግንቦት 15 በሃገር አቀፍ ደረጃ መከበር የጀመረ ሲሆን ዕለቱ የተመረጠበትም ምክንያት የጣልያን ወረሪ ኃይልን አድዋ ላይ መክተው ያሸነፉት አባቶቻችን በድል አድራጊነት ወደመናገሻ ከተማቸው የተመለሱበት በመሆኑ ብዙሃኑ አባቶች ከቤተሰብ ባሻገር ለሃገር መፅናት ላደረጉት ተግባር ምስጋና ለመስጠት በማሰብ ነው፡፡

በቀጣይ በተለያዩ ክልል ከተሞችም መከበሩን የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
አዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ታሰረ

የ"እብድት በህብረት" የአንድ ሰው ቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ እንደታሠረ ከቅርብ ምንጮች ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ሰምቷል።

የቴአትሩ አዘጋጅ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ በፖሊስ" ትፈልጋለህ" ተብሎ እንደተወሰደ እና በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

ከወራት በፊትም "እብድት በህብረት" ቴአትርን ለማሳየት ወደ እስራኤል ሀገር ለመጓዝ በዝግጅት ላይ የነበረውን አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙን ከአዲስ አበባ ኤርፖርት "ትፈልጋለህ" በሚል እንደወሰዱት እና እስካሁንም በእስር ላይ እንደሚገኝ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1