Event Addis Media
9.09K subscribers
5.26K photos
5 videos
3 files
3.97K links
Connect with Addis Ababa's artistic community! Find out about art exhibitions, music events, workshops, and cultural experiences. Contact: @Tmanaye
Download Telegram
ለአባቶች ቀን ልዩ ውድድር ተዘጋጀ

ላለፉት 15 አመታት የኢትዮጵያ የአባቶች ቀንን በየዓመቱ ሲያከብር የቆየው ኢትዮጵያ አባቶች ቀን በጎ አድራጎት ድርጅት ዘንድሮም ለ16ኛ ጊዜ የኢትዮጵያ የአባቶች ቀንን ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በልዩ ሁኔታ ለማክበር ተዘጋጅቷል።

የበጎ አድራጎት ድርጅቱ በዘንድሮው የኢትዮጵያ አባቶች ቀን በተለየ መልኩ ልጆች ለአባታቸው ስሜትና ፍቅራቸውን በመግለፅ የሚሳተፉበት ውድድርም አዘጋጅቷል፡፡

ውድድሩም ለደጉ አባብዬ ያላችሁን ክብርና ምስጋና በምን መልኩ እንደምትገልፁ የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ በመቅረጽና "በኢትዮጵያ አባቶች ቀን በጎ አድራጎት ድርጅት" ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅ መልዕክት መላኪያ ላይ በማስቀመጥ የሚከናወን ነው።

በዚህም የሚላኩ ቪዲዮዎች በተቋሙ ገፆች ላይ ተለጥፈው እስከ ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በሚያገኙት የእይታና የላይክ መጠን ተመርጠው

1ኛ ለሚወጣ የምስክር ወረቀት፣ ጋቢና ከውዱ አባብዬ ጋር በዮድ አቢሲኒያ ልዩ የምሳ ግብዣ፡፡

2ኛ ለሚወጣ ጋቢና ከውዱ አባብዬ ጋር በዮድ አቢሲኒያ ልዩ የምሳ ግብዣ፡፡

እንዲሁም 3ኛ ለሚወጣ ከውዱ አባብዬ ጋር በዮድ አቢሲኒያ ልዩ የምሳ ግብዣ ላይ የሚታደሙ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ታሪካዊ ፎቶና ምስል በመላክ መወዳደር ትችላላችሁ ተብላችኋል።

በአባቶች ቀን ለአባቶቻችሁ ፍቅራችሁን እና ክብራችሁን ለመግለፅ አስባችሁ ነገር ግን አቅማችሁ የማይፈቅድላችሁ፤
እንዲሁም "አባቴ ፍፁም የተለየ ሊነገር የሚገባው ታሪክ አለው" የምትሉ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጻቸው በውስጥ መስመር መልዕክታችሁን ማስቀመጥ ትችላላችሁ።

ድርጅቱ የተመረጠ ታሪክ ያላቸውን አባቶች ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በዮድ አቢሲያ የባህል አዳራሽ ለአባቶቻችሁ ተገቢውን ክብርና ምስጋና ይሰጣል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ነጻ የቤተመዘክር( ሙዚየም ) ጉብኝት

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀንን ዘንድሮ  በሀገራችን  ለ22ኛ ግዜ «ሙዚየሞች ለትምህርት እና ምርምር»  "Museum for Education and Research" በሚል መሪ ቃል ያከብራል::

ዛሬ ግንቦት 10 2016 ዓ.ም ሁሉም ነዋሪ ያለምንም  ክፍያ በነፃ እየመጣ እንዲጎበኝ ይጋብዛል።

የሙዚየሙ አድራሻ:- መስቀል አደበባይ ከአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በስተቀኝ በኩል።

ምንጭ። አዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የአብርሆት ቤተመጽሀፍት ከ18 ዓመት በላይ በሆናቸው ወጣቶች የተሰሩ የሰው ሰራሽ  አስተውሎት ዘርፍ  ውጤቶችን  በሞሮኮ ራባት በሚካሄድ ኤግዚቢሽን ላይ ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ፡፡

23 ታዳጊዎችን ያካተተ ቡድን ለሮቦ ፌስት ውድድር ወደ አሜሪካን ማቅናቱ  የሚታወስ ነው፡፡

ይህ በከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንዲሁም በአብርሆት ቤተመጽሀፍት እና በአቡጊዳ ሮቦቲክስ ማእከል በተደረገ ስምምነት ወደ አሜሪካ ያቀናው  የታዳጊዎች ቡድን በሚቺጋን ሎውረንስ ዩኑቨርስቲ በተካሄደ ውድድር በሶስት የሮቦ ፌስት የውድድር ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ ከግብጽ እና ጋና ውጪ አፍሪካንም ጭምር ወክለው እንደተሳተፉ የተናገሩት ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ ያደረጉት የአብርሆት ቤተመጽሀፍትና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዳይሬክተር ኢንጂነር ውባየሁ ማሞ በቴክኖሎጂ ሰለጠኑ ከሚባሉ አገራት ጋር የነበረው ፉክክር በስተመጨረሻ ድል የተቀዳጀንበትም ነው ብለዋል፡፡

በሰው ሰራሽ የአስተውሎት ዘርፍ የአብርሆት ቤተመጽሀፍት ከጎግል ኩባንያ ጋር በመተባባር እየሰራ ነው ያሉት ኢንጂነር ውባየሁ ከ18 ዓመት በላይ የሆናቸው ወጣቶች ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ የሮቦቲክ ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በእንግሊዝና በሞሮኮ ራባት በሚካሄድ ኤግዚቢሽን ላይ ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጋቸውንም አንስተዋል፡፡

በጥንቃቄ ታይተው ተፈትሸው ለውድድር የሚቀረቡት የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተማሪዎች ያለአስተማሪ እውቀት መገብየት እንዲችሉ የሚያግዝ፤የነፍሰጡር እናቶችን የእርግዝና ክትትል ጊዜን የሚከታተል እንዲሁም አሰሪና ሰራተኛን ማገናኘት የሚችሉ መተግበሪያዎች ናቸው ያሉት ኢንጂነር ውባየሁ በሁለት ሳምንት ጊዜም ለህዝብ ይፋ ይደረጋሉ ብለዋል፡፡

Via AMN

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
እሺ ሚዲያ እና የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በጋር ለመስራት ተፈራረሙ 

እሺ ሚዲያ እና የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን የፕሮሞሽን እና የኮምኒኬሽን ስራዎችን በጋር ለመስራት ዛሬ ግንቦት 10 2016 ዓ.ም ተፈራርመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በአሁን ወቅት አሥር የሚደርሱ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች በማስተዳደር ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ኮርፖሬሽኑ እነዚህን የሕዝብ መዝናኛና ፓርኮችን በማልማትና በማስተዋወቅ በከተማዎ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን አቀፍ ልማትና ገፅታ የመገንባት ስራ አንድ አካል በማድረግ ሰፊ የህብረተሰብ ንቅናቄ  መድረክ ለማዘጋጀት አቅዷል፡፡

በዚህ የማነቃቂያ መድረክ መዝናኛ ቦታዎቹና ፓርኮቹን በሚሊዮን በሚቆጠሩ ነዋሪዎች እንዲጎበኙ እንዲሁም የንግዱ ማህበረሰብም ፓርኮቹን ለሕብረተሰብ አገልግሎት ለሚውሉ ተግባራት እንዲያለሙ ለማነቃቃት ብሎም ከፓርኮቹ የተሻለ ገቢ በማመንጨት ከተማ አስተዳደሩ ለወጠናቸው የልማት ተግባራትን እንዲደግፉ የማስቻል ዓላማ ተይዟል ተብሏል።

በዚህ የማነቃቂያ መርሐግብር ላይ የሰርግና ልደት ትዝታዎች የፎቶግራፍ አውደርዕይ፣ የዲፕሎማቶች እና አምባሳደሮች እንዲሁም የሚዲያ ባለሞያዎች ጉብኝት ፣ የሰርከስ ትርዒት ፣ የልጆች ጨዋታ ዝግጅቶችን ጨምሮ በርካታ መሰናዶዎች እንደተዘጋጀ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ፋና ላምሮት እና ብሌን ዮሴፍ ተለያዩ

ለዓመታት በፋና ቴሌቪዥን እየተላለፈ በሚገኘው በ"ፋና ላምሮት" የድምጻዊውን ውድድር ላይ በመሐል ዳኝነት ስትዳኝ የቆየችው የሙዚቃ ባለሞያው ብሌን ዮሴፍ ከፋና ላምሮት ጋር የነበራትን ቆይታ መጨረሷን በማህበራዊ ትስስር ገጿ አስታውቃለች።

ብሌን ዮሴፍ በማህበራዊ ትስስር ገጿ"የፋና ላምሮት የዳኝነት ቆይታዬን ጨርሻለሁ።ሲያበረታኝ የነበረዉ ልብን የሚያሞቅ ፍቅራችሁ እንደነበር ታዉቁ ይሆን እግዚአብሔር ያክብርልኝ እወዳችኋለሁ" ብላለች።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የታሪክ ተመራማሪ ፣ ደራሲ ፣ግራፊክስ ዲዛይነርና ሠዓሊ በሁሉም አለበል በሙያዋ ላበረከተችው በርካታ ስራዎች የምስጋና ዝግጅት ተከናወነ

ደራሲ፣ገጣሚ፣ሠዓሊ እና በጎ ፍቃደኛ በሁሉም አለበል ለስራቻቸው ስራዎች ዛሬ ግንቦት 10 2016 ዓ.ም በፈንድቃ ባህል ማዕከል በተዘጋጀ የምስጋና ሥነሥርዓት ላይ በወዳጆቿ ተመስግናለች።

ደራሲ በሁሉም አለበል "የተዳፈነው ታሪክ :ራስ ጉግሣ ወሌ" ፣ "ታሪክን በቅኔ" ፣ የተዋጡ ድምጾች ፣ውስብስብ ውሎዎች ፣ሣምራዊ ፣የሸንበቶ ባህር የተሰኙ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሳለች።

"ኢትዮጵያዊ ሀገሩ የት ነው?" ፣ "የተቆለፈበት ቁልፍ" ፣ "ወድቆ የተገኘ ሀገር " ፣"ናፍቆት" የተሰኙ መጻሕፍትን ጨምሮ ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ መጻሕፍት የሽፋን ገፅ (Cover) ሰርታለች።

በዚህ የምስጋና ሥነሥርዓቱ ላይ ዶ/ር ፀደይ ወንድሙ ስለ በሁሉም አለበል የታሪክ መጻሕፍት ዳሰሳ አቅርባለች።

ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ አርቲስት ደሳለኝ ኃይሉ ፣ ደራሲና የፊልም ባለሞያ እስከዳር ግርማይ ፣ ገጣሚ ይታገሱ ጌትነት ዶ/ር ተዋበች ቢሻው ፣ ዘላለም አለበል እና ሌሎችም ስለደራሲ ለሁሉም አለበል  ንግግር አድርገዋል።

በጉንጉን ባንድ ታጅበው ድምጻዊ ኤልያስ ተባባል ፣ ገጣሚ ሰለሞን ሳህለ የሙዚቃ እና ግጥም ስራዎችን አቅርበዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ አዲስ አልበም

የድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ አዲስ አልበም እንደተጠናቀቀ እና በቅርቡ ለአድማጮች እንደሚቀርብ ድምጻዊው በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ ከዚህ ቀደም "አንተ ጎዳና" እና "ናፍቆት እና ፍቅር"የተሰኙ የሙዚቃ አልበሞችን ለአድማጮች ማድረሱ ይታወሳል።

ለብዙ ፈጣን የኪነጥበብ መረጃዎች ይህን የቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ:

https://t.me/EventAddis1
"ብርሃን ኮንሰርት" የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል

ገቢው ለሰበታ መርሐ የዓይነስውራን ት/ቤት እንዲውል የተዘጋጀው "ብርሃን ኮንሰርት " የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 17 2016 ዓ.ም በግዮን ሆቴል እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት ላይ ድምጻዊያኑ አብዱ ኪያር ፣ ቀመር የሱፍ ፣ ይርዳው ጤና ፣ባልከው አለሙ፣ ኃይማኖት ግርማና ሌሎችም የሙዚቃ ስራዎችን ያቀርባሉ ተብሏል።

የኮንሰርቱ መግቢያ መደበኛ መግቢያ 500 ሲሆን ቪአይፒ 1500 ብር እንደሆነ ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
በእይታ ላይ ያሉ የሥዕል አውደርዕዮች

📍የሠዓሊ ሳምሶን ከበደ የሥዕል ስራዎች የቀረቡበት "ወይን ጠጅ" የሥዕል አውደርዕይ ከግንቦት 5 2016 ዓ.ም  ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ እይታ ይገኛል። ይህ የሥዕል አወድርዕይ እስከ ግንቦት 19 2016 ዓ.ም ይቆያል ተብሏል።

📍የሠዓሊ ሱራፌል አማረ “ድፍድፍ ” የተሰኘው የሥነጥበብ አውደርዕይ ከግንቦት 9 2016 ዓ.ም ጀምሮ ቦሌ ዓለም ሲኒማ ጀርባ በሚገኘው አትሞስፌር ጋለሪ ውስጥ በእይታ ላይ ይገኛል።ይህ አውደርዕይ እስከ ግንቦት 22 2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"ማማ በሰማይ" ስድስተኛ ዕትም ለንባብ በቃ

በህይወት ተፈራ "Tower in the sky" በሚል በእንግሊዝኛ ተጽፎ በጌታነህ አንተነህ "ማማ በሰማይ" በሚል የተተረጎመው መጽሐፍ ስድስተኛው እትም ከሰሞኑ ለአንባቢያን ቀርቧል።

"ማማ በሰማይ" መጽሐፍ በ1965 ዓም የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርስቲን በ18 አመቷ ተቀላቅላ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጣች ጉብል የሐረሯ ልጅ “ ሕይወት ተፈራ ” እና ስለ ሪቮሉሽነሪው ጌታቸው ማሩ በኢሕአፓ ድርጅት ውስጥ ያላቸውን ፓለቲካዊ ሚና እና የፍቅር ሕይወታቸውን የሚተርክ  መጽሐፍ ነው፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የመጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ "37 አልፋ ገ3" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ በሚቀጥለው ሳምንት ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።

መጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው " [37 አልፋ 73] በሚቀጥለው ሳምንት ለአንባብያን ይቀርባል።"

ስለ ይዘቱም "ቀደምት ሊቃውንት የተጠበቡበት ጥበብ እጆ ይደርሳል። ከጽርሐ አርያም እስከ DNA፤ ከኢዮር እስከ አሚኖ አሲድ፤ ከአድማስ እስከ ፔርዮዲክ ቴብል፤ ከመላእክት ስም እስከ ኖኅ መርከብ ሙሉ ዕውቀት ይዟል።" ብለዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
የዓለማየሁ ደመቀ "ዮቶር 2" መጽሐፍ ለንባብ በቃ

የደራሲ ዓለማየሁ ደመቀ " ዮቶር 2" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ  ግንቦት 12 2016 ዓ.ም ለንባብ በቅቷል።

በ207 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ በ450 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።

የመጽሐፉ መታሰቢያነትም ለአንጋፋው የሙዚቃ አቀናባሪ አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ የተሰጠ ሲሆን ደራሲው በመግቢያው "ለታላቁ የኢትዮጵያ ሙዚቃ አድባር ፣እኔንም ሆነ የጥበቡን ቤተሰቦች በሥራዎችህ ውስጥ ላስተማርከን ፣ በግንባርም ለመገብከን ዕውቀት እናመሰግናለን" በማለት ምስጋናውን አቅርቧል።

መጽሐፉ ጃፋር መጻሕፍት መደብርን ጨምሮ በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል።

ከዚህ ቀደም በደራሲ አለማየሁ ደመቀ የተጻፈው "ዮቶር ኮባላይ ካህን" 14ተኛ ዕትም መጽሐፍ በድጋሚ ለአንባቢያን መቅረቡ ይታወሳል።

በተጨማሪም አለማየሁ ደመቀ ለበርካታ ድምጻዊያን የግጥም እና ዜማ ስራዎችን ሰርቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"አልፅፍም"መጽሐፍ ለንባብ በቃ

የአይዳ ታደሰ " አልፅፍም" የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ባሳለፍነው ቅዳሜ ለንባብ በቅቷል።

የግጥም መጽሐፉ በ140 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ200 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል በዓይናለም መጻሕፍት መደብር ውስጥም ይገኛል ተብሏል።

መጽሐፉ ታሪክን፣ ቁጭትን፣ ቁጣን፣ ተስፋ መሰነቅን፣ ተስፋ መቁረጥን፣ ምኞትን፣ ትዝብትን እና ምናባዊ ዳሰሳን የያዘ ሲሆን “ሰቆቃወ አይዳ” እና “ምናብና ትዝብት” በተሰኙ ንዑሰ ርዕሶች ተከፍሎ የቀረበ የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ነው።

አይዳ ታደሰ ከዓመታት በፊት ገጣሚያኑ በረከት በላይነህ ፣ አበባው መላኩ ፣ ቸርነት ወ/ገብርኤል እና ሌሎችም የተሳተፉበት "ቃል እና ቀለም" የተሰኘ ፊልም ለተመልካች ማድረሷ ይታወሳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"መስተዋድድ" የኪነጥበብ ምሽት ዛሬ ይካሄዳል

"መስተዋድድ" የኪነጥበብ ዝግጅት ዛሬ ግንቦት 14 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ጀምሮ ሜክሲኮ በሚገኘው ገነት ውስጥ ይካሄዳል።

በዕለቱም ገጣሚያኑ ሚካኤል ምናሴ ፣ ሂክማ ፋንቱ ፣ዘውድ አክሊል ከሚሎ ባንድ ጋር በመሆን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

በተጨማሪም ደራሲ ገብረክርስቶስ ደስታ፣ ሔኖክ ስዩም ፣ ሰመረ ባሪያው ፣መሐመድ ካሣ እና ካሣዬ ጨመዳ ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ሮፍናን ኑሪ የክብር የእንግዳ የሆነበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት ዛሬ ይካሄዳል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 14 2016 ዓ.ም ይካሄዳል።

በዕለቱ ሮፍናን ኑሪ "የአንድ ግጥም፣ የአንድ ወግ" የክብር እንግዳ ሆኖ  ይገኛል።

እንዲሁም ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ብለዋል አዘጋጆቹ ።

ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
"የአዲስ አበባ ሰፈር ፣ እድር ፣ እና ግቢ" ውይይት

በዶ/ር አንተነህ ተስፋዬ የተዘጋጀው "ሰፈር፣ እድር እና ግቢ" የተሰኘው መጽሀፍ  የኢትዮጵያን የከተማ ኑሮ፣ ስፍራ የማበጀት እና የንድፍን ንድፈ ሀሳብ  የሚያሳይ መጽሀፍ ነው።

በዚህ በዶ/ር አንተነህ ተስፋዬ መጽሀፍ ሀሳብ ላይ ነገ ሐሙስ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 እስከ 10፡30 ድረስ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ዋናው ግቢ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ውስጥ ውይይት ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Event Addis Media
Photo
ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ በቅርቡ ለአድማጮች ያደረሰው "ቢሊሌ" ሙዚቃ ላይ የተጠቀሰችው "ቢሊሌ" ማናት ?

መህቡባ/ቢሊሌ

በኦሮሚያ ክልል በምትገኘው ጉማ እ.ኤ.አ. በ1820 ስትወለድ ቤተሰቦቿ "ቢሊሌ" የሚል ስም አውጥተውላት ነበር። ትርጉሙም "ቆንጆ" "የምታምር" እንደማለት ነው። መህቡባ ማለት ደግሞ በአረብኛ "ተወዳጇ" ማለት ነው።

መህቡባ እድሜዋ 15 ዓመት ሲሞላት እ.ኤ.አ. በ1835/36 በተነሳ የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት አባቷንና ስድስት ወንድሞቿን  አጣች። በ1837 በለጋነት እድሜዋ በእሳት ቃጠሎ ከወደመው የትውልድ መንደሯ በባሪያ ፈንጋዮች ተፈንግላ ከእህቷ ጋር ተቆራኝታ ወደ ጎንደር ከተወሰደች በኋላ ለሽያጭ ልትቀርብ በሱዳን ካርቱም አድርጋ ወደ ካይሮ አቀናች።

በ1837 የጀርመኑ ልዑል ኸርማን ፉርስት ቮን ፐክለር-ሙስካው ወደ ሰሜን አፍሪካ ጉዞ አድርጎ ነበር። በካይሮ ቆይታው የቱሪስቶች ተወዳጅ ስፍራ ወደሆነው የካይሮ የባሪያ ገበያ ቦታ ይሄዳል። በእዛም በባርነት ለሽያጭ በቀረበች አንዲት ጉብል የኦሮሞ ልጅ ውበት ይማረካል። ወዲያው ተደራድሮ ከገዛት በኋላ አገልጋዬ ናት በማለት ዋሽቶ ከእራሱ ጋር አብራው እንድትጓዝ አደረገ።

ልዑሉ በመህቡባ ፍቅር ተንበረከከ። ልዑሉና መህቡባ ወደ ፍልስጥኤም፣ ሶርያ እና ኢስታንቡል አብረው ተጉዘዋል። ልዑሉ ተፈጥሮ ለመህቡባ በለገሰቻት ሞገስና የአውሮፓውያንን ባህል ለመልመድ በምታሳየው ፍላጎት ተደምሞ ነበር። እሷም ባልጠበቀችው አዲስና ያልታሰበ ሁኔታ ደስተኛ ሆና ነበር።

አውሮፓ እንደደረሱ ለተወሰነ ጊዜ በቡዳፔስት ቆይታ አድርገው ነበር። በእዛም መህቡባ የቅዱስ ጥምቀት ስነስርዓት እከናውናለች። ልዑሉም መህቡባን ለተወሰነ ጊዜ በቪየና ወደሚገኝ ጥሩ ትምህርት ቤት አስገብቷት የትምህርት ቤቱን መነኩሴዎች አውሮፓዊ አኗኗርን እንዲያስተምሯት ነገራቸው። እሷም ተፈጥሮ በሰጠቻት ፀጋና ንቃት በትምህርቷ በመጎበዝ ሁሉንም አስደስታለች። የገባችበት ሁሉ አካባቢውን በፈገግታዋ ታደምቅ ነበር። ለቋንቋ የተሰጠች ስለነበረች ጣሊያንኛ በቶሎ ለመደች። አብረዋት ሊሆኑ የሚወዷትና በተፈጥሮ ገርና ደግ ነበረች።

ማህበረሰቡም የልዑሉንና የልዕልቷን ግንኙነት በቅንነት ተቀብሎ የመህቡባ አስደናቂ ውበት ያደንቅ ጀመረ። የቪየና ጣእም ሆነች፣ ጋዜጦችም ስለሷ አድንቀው ይፅፉ ነበር። የወሬ ሁሉ ማድመቂያም ሆነች። ወደ ንጉሱ ዙፋን በተወሰደች ጊዜም ይሁንታንና ግርማ ሞገስን አገኘች። ሁሉም ሰው ወደዳት።

ይሁን እንጂ መህቡባ ምግቡንና ቀዝቃዛውን የአውሮፓ አየር መልመድ አቃታት። በጊዜ ሂደትም በሳንባ ምች ተይዛ በፅኑ ታመመች።

ልዑሉ  መህቡባን ለሚንከባከበው ሃኪም ጥብቅ ክትትል እንዲያደርግላትና ስለ እርሷም እንዲያሳውቀው አዝዞት ለሥራ ወደ በርሊን ተጓዘ። ከሁለት ቀናት ቆይታ በኋላ እ.ኤ.አ ኦክቶበር 27 ቀን 1840 የመህቡባ አገልጋይ የመህቡባን መኝታ ክፍል መጋረጃ ስትገልጥ መህቡባን ሞታ አገኘቻት። ብቻዋን ሞታ ተገኘች። በትልቁ አልጋ ላይ እንደ ትንሽ ምስል ትታይ ነበር። በአቅራቢያው በሚገኝ መካነ መቃብርም ተቀበረች። በመቃብሯም ላይ "መህቡባ" ብቻ የሚል ፅሁፍ ያለው ምልክት ተደረገላት። መካነ መቃብሯን በየአመቱ ሺህዎች ይጎበኙታል።

ልዑሉ ስለ መህቡባ ሞት ለጓደኛው በፃፈው ደብዳቤ "ሰው መውደድ እችላለሁ ብዬ ከማስበው በላይ ወድጃት ነበር። ሞቷም ጥልቅ ስቃይ ውስጥ ከትቶኛል። እርሷ ለእኔ ሁሉ ነገሬ ነበረች" በማለት መሪር ሃዘኑን ገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1