Event Addis Media
9.23K subscribers
6.38K photos
17 videos
5 files
4.97K links
Connect with Addis artistic community!

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
Event Addis Media
Photo
🔶አደይ ኮንቴምፖራሪ የጥበብ ሽልማት ተካሄደ

በኢትዮጵያ የኮንቴምፖራሪ ጥበብን ለማበረታታትና ለባለሙያዎች ዕውቅና ለመስጠት የተዘጋጀው "አደይ ኮንቴምፖራሪ የጥበብ ሽልማት" የመጀመሪያ ዙር የሽልማት ሥነ ሥርዓት ፤ ጥቅምት 7 2019 ዓ፣ም በዓድዋ ድል መታሠቢያ ሙዚየም ተካሄደ።

በ19 ዘርፎች ለጥበብ ባለሙያዎች እውቅና ተሰጥቷል።ከዋናው የሽልማት ዝግጅት በተጨማሪም የሥዕል ዐውድርዕይ፤ የሰርከስ ትርዒት፤የፋሽን ሾውን ጨምሮ የተለያዩ ትርዒቶች ለታዳሚያን ቀረበዋል።

የመጀመሪያው “አደይ ኮንቴምፖራሪ አርት አዋርድ” የሽልማት ሥነ-ሥርዓት አሸናፊዎች እና የህይወት ዘመን ተሸላሚዎች ሙሉ ዝርዝር

👉በምርጥ የሙዚቃ አቀናባሪነት አሸናፊ -ዲጄ ደስ

👉በምርጥ የሴት ዘፋኝ ዘርፍ አሸናፊ -ሳሌሚያ

👉በምርጥ የወንድ ዘፋኝ ዘርፍ አሸናፊ -ሳሞን ዜማስ

👉 በምርጥ ዲጄ ዘርፍ አሸናፊ -ዲጄ ቲተም

👉በምርጥ ባለራዕይ ሙዚቀኛ ተሸላሚ -ሃዲንቆ

2 በኮቴንፖራሪ ቪዧል አርት/ ዕይታ ጥበብ ዘርፍ (3 ንዑስ ዘርፎች)

👉በምርጥ ሰዓሊ ዘርፍ አሸናፊ - እያዩ ገነት

👉በምርጥ ቀራፂ ዘርፍ አሸናፊ - ተፈሪ መኮንን

👉በምርጥ ራዕይ ሽልማት አሸናፊ - ያቡ አርትስ

3)በኮንቴምፖራሪ ሰርከስ ዘርፍ (በ 5 ንዑስ ዘርፎች)

👉በምርጥ ሰርክስ ዳይሬክተር ዘርፍ አሸናፊ -ፍፁም መሳይ

👉በምርጥ ሰርከስ አሰልጣኝ ዘርፍ አሸናፊ -በሃይሉ ዮሴፍ

👉ምርጥ ሴት ሰርከስ ትርዒት አቅራቢ ዘርፍ አሸናፊ -ቤተልሔም ዳዊት

👉ምርጥ ወንድ ሰርከስ አቅሪቢ ዘርፍ -ዳግም አይተንህ

👉የሰርከስ ዘርፍ የህይወት ዘመን ተሸላሚ -አወቀ እምሩ

4. በኮንቴምፖራሪ ፋሽን ዘርፍ (በ4 ንዑስ ዘርፎች)

👉በምርጥ ባለራዕይ ሞዴል ተሸላሚ - ሩት ይርጋለም

👉በምርጥ ሴት ሞዴል ዘርፍ አሸናፊ -ሰላማዊት ፅሩይ

👉በምርጥ ወንድ ሞዴል ዘርፍ አሸናፊ -ዘላለም ተድላ

👉በምርጥ ዲዛይነር ዘርፍ አሸናፊ - ፍቅርተ አዲስ

5 )በኮንቴምፖራሪ ዳንስ ዘርፍ (በ5 ንዑስ ዘርፎች)

👉በምርጥ ዳንስ ኬሮግራፈር ዘርፍ አሸናፊ -ሲሳይ ተካልኝ (ሲስኮ)

👉በምርጥ ሴት ተወዛዋዥ ዘርፍ አሸናፊ -መቅደስ ደሳለኝ
በምርጥ ወንድ ተወዛዋዥ ዘርፍ አሸናፊ - ኤልያስ ሽኩር (ኤርሚ ላስታ)
👉የዳንስ ዘርፍ የህይወት ዘመን ተሸላሚ - ታደሰ ወርቁ

👉ምርጥ ባለራዕይ ኬሮግራፊ ተሸላሚ -ልጅ ተመስገን መለሰ

6 ) በኮንቴምፖራሪ አጭር ፊልም ዘርፍ

በምርጥ አጭር ፊልም ዘርፍ አሸናፊ -ሲሳይ መለሰ

7. የአደይ ኮንቴምፖራሪ አርት አዋርድ የህይወት ዘመን ተሸላሚዎች

👉ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን

👉የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

👉መርሄ ተውኔት ጋሽ አባተ መኩርያ
❤9
🔶"ምስጠት - The Listening Room"

የሥነ-ጽሑፍ፣ የሙዚቃ እና የኪነ-ጥበብ አፍቃሪያንን የሚያገናኝ "ምስጠት - The Listening Room" የተሰኘ አዲስ መድረክ ተዘጋጅቷል።

በዚህ ዝግጅት ላይ ማሎ ተጋባዥ እንግዳ ሲሆን መካኒሳ ሲዶ ሕንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው ጃዝ ኮፊ ጥቅምት 11 2019 ዓ.ም ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ ይካሄዳል።

የመግቢያ ዋጋው 400 ብር መሆኑ ተገልጿል።

ለተጨማሪው:
Telegram: https://t.me/EventAddis1

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
❤6
Forwarded from Kelemat Ads
✅እንግሊዝኛን በቀላሉ እና በራስ መተማመን ለመናገር ዝግጁ ነዎት?

✅የ Yimaru አፕሊኬሽንን በማውረድ ዛሬውኑ ልምምድ ይጀምሩ፦
👇: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.yimaru.lms.app
መልካም የትምህርት ጊዜ! ✨

እንግሊዘኛ መማር ከፈለጉ ይህ ቻናል ለእርስዎ ነዉ!
❤2
🔶የማዲንጎ አፈወርቅ አዲስ አልበም

ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በሕይወት እያለ ሲሠራቸው የቆያቸውና ያላጠናቀቃቸው ያልተሰሙ የሙዚቃ ስብስቦች የያዘው አዲስ አልበም ይፋ የሚሆንበት ቀን መታወቁ ተገለጸ።

“አሻራ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ አልበም በድምፃዊው ልጅ በዲቦራ ማዲንጎ አማካኝነት ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ የፊታችን ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም በተለያዩ የሙዚቃ ማሰራጫ መተግበሪያዎች በኩል ለአድማጮች እንደሚደርስ ታውቋል።

ለተጨማሪው:
Telegram: https://t.me/EventAddis1

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
❤18🔥5
🔶የአበባ ደሳለኝ አዲስ አልበም ደርሷል

የዘጠናዎቹ ተወዳጅ ድምፃዊት የሆነችው አበባ ደሳለኝ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊታቀርብ መሆኑን ኤቨንት አዲስ ሚዲያ ሰምቷል።

አበባ ደሳለኝ ከ13 ዓመታት የሙዚቃ አልበም እረፍት በኋላ የምታወጣው ይህ አልበም "መርቁኝ"  የተሰኘ ስያሜ ወጥቶለታል።

ለተጨማሪው:
Telegram: https://t.me/EventAddis1

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
❤24👏4
🔶 ማህሙድ አህመድ በሕይወት አለ

"ምን ቢያረጋችሁ ነው? አባቴ በሕይወት እያለ ሞተ እያላችሁ የምታወሩት?" የድምጻዊ ማሕሙድ ልጅ ሀብቱ

የአንጋፋው ድምፃዊ ማሕሙድ አሕመድ ልጅ ሀብቱ ማሕሙድ ፤ "ማሕመድ አህመድ አረፈ" በሚል በማኀበራዊ ሚዲያ ገጾች በዛሬው ዕለት ሲሰራጭ የቆየው መረጃ ሙሉ በሙሉ ሐሰት መሆኑን አስታወቀ።

ኤቨንት አዲስ ሚዲያ እንደተመለከተው ሀብቱ ማህሙድ ባስተላለፈው መልዕክት "አንዳንድ የፌስቡኩ ፔጆች እና ቲክቶከሮች አባቴን ከዚህ አለም ተለየ እያሉ በውሸት እየዘገቡ ነው ያሉት። እና ይሄ በጣም በጣም አስነዋሪ ድርጊት ነው። ምን ቢያረጋችሁ ነው  አባቴ በህይወት እያለ ሞተ እያላችሁ የምታወሩት? አባቴ በህይወት አለ" ብሏል።

አባቱ ድምፃዊ ማህሙድ አሕመድ በሕይወት የሚገኝና በሙሉ ጤንነት ላይ ያለ መሆኑን አረጋግጦ፣ መሰል የሐሰት ወሬዎችን የሚያሰራጩ አካላትን ድርጊት "አስነዋሪ" ሲል ኮንኖታል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአንጋፋው ድምፃዊ ያለውን ፍቅርና አክብሮት ያወሳው ሀብቱ፤ ህብረተሰቡ ያልተረጋገጡና ሐሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ገጾችን ሪፖርት በማድረግ የሐሰት መረጃ ስርጭትን እንዲከላከል ጥሪ አቅርቧል።

አንጋፋው ድምፃዊ ማሕሙድ አሕመድ ትላንት ረቡዕ ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባሕል ማዕከል በተካሄደውና ለታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ በተዘጋጀው ጥበባዊ መርሃ-ግብር ላይ በክብር እንግድነት ተገኝቶ እንደነበር ይታወሳል።

ለተጨማሪው:
Telegram: https://t.me/EventAddis1

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
❤26👍3😢2
🔶ሰላም አዲስ ክሪዬቲቭ ሀብ ተመረቀ

በአዲስ አበባ በሚገኘው ታሪካዊው የነርሰስ ናልባንዲያን መኖሪያ ቤት የተቋቋመው ሰላም አዲስ ክሪዬቲቭ ሀብ ተመርቋል።

በዝግጅቱ ላይ የስዊድን አምባሳደር፣ የኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ዘርፍ የሚመለከታቸው አካላትና የነርሰስ ናልባንዲያን ልጅ ተገኝተዋል።

በአሁኑ ወቅት “The Creative Nexus: Space, Rights, and Sustainability in Ethiopia” በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የፈጠራ ሥራዎች የሚከናወኑበት ቦታ፣ የአርቲስቶች መብትና የዘርፉ ዘላቂነት ላይ ውይይት እየተደረገ ነው። ዝግጅቱ በፓን አፍሪካ የአርቲስቶች ነፃነት ኔትወርክ (PANAF) ትብብር እየተካሄደ ነው።

የፕሮግራሙ ቀጣይ ክፍል የቴዎድሮስ መኮንን (Teddy Mak) አልበም ምርቃት ሲሆን፣ ይህም የሥነ-ጥበብና የሙዚቃ ዝግጅቱን ያስቀጥላል።

ለተጨማሪው:
Telegram: https://t.me/EventAddis1

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
❤5👍1
🔶የትግራይ ቴሌቪዥን

በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ታግዶ የነበረዉ “የትግራይ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ” የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ የትግራይ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በሚል አዲስ ስያሜ በባለሥልጣኑ የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ በዛሬው ዕለት ተሰጥቶታል።

ባልስልጣኑ በተመሳሳይ «ድምጺ ወያነ ትግራይ ሬድዮና ቴሌቪዥን»ን፣ የክልሉን ሰላም እና የህዝብ ድምፅ በመሆን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት በማሰብ «ማእዶት ብሮድካስቲንግ አገልግሎት» በሚል አዲስ ስያሜ የብሮድካስት ፈቃድ ሰጥቶታል።

ለተጨማሪው:
Telegram: https://t.me/EventAddis1

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
😁5👎2
🔶የዘሪቱ ከበደ መጽሐፍ ድጋሚ ታተመ

የዘሪቱ ከበደ “ከልጅነት እስከ ልጁነት”የተሰኘዉ መፀሀፍ በድጋሚ ለህትመት በቅቷል።

መጽሐፉ በጃፋር መጽሐፍት መደብር ይገኛል።

ለተጨማሪው:
Telegram: https://t.me/EventAddis1

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
❤14😁10🔥2👎1🙏1
"የአእምሮ ጤና ጉዳይ እኔንም ያገባኛል"

የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ወር የዘንድሮው ዓለም አቀፍ መሪ ቃል “የተኖሩ ልምዶች መደመጥ፡ ትክክለኛ ድምጾች፣ ትክክለኛ ለውጥ” የሚል ሲሆን፣ በሃገራችን ደግሞ “የኔ አበርከቶ” በሚል መሪ ቃል በመታሰብ ላይ ይገኛል።

ይህ መሪ ቃል የተመረጠበት ዋና ምክንያት በዓለም ላይ ያሉ የአእምሮ ህመም እና ተያያዥ ችግሮችን ማንኛውም ግለሰብ ሊገነዘብ፣ መፍትሔ ሊሆን እንደሚችል በአጽኖት ለማስገንዘብ እና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የመፍትሔው አካል የማድረግን አስፈላጊነት ለማጽናት መሆኑ ታውቋል።

በአእምሮ ጤንነት ጥበቃ ላይ በመስራት የሚታወቀው ሃሺም ኮንሰልታንሲ ይህንኑ ዓለም አቀፍ ወር በማስመልከት የሚካሄዱ ታላላቅ ሁነቶችን ይፋ አድርጓል።

ድርጅቱ ጥቅምት 28 እና 29 ቀን 2019 ዓ.ም. በፒኮክ ፕላዛ የተለያዩ ትምህርታዊ ይዘት ያላቸውን የግንዛቤ ማሳደጊያ፣ የልምድ ልውውጥ እና የመዝናኛ ዝግጅቶችን እንደሚያቀርብ አስታውቋል።

በነዚህ መርሃ-ግብሮች ላይ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች፣ የጤና ባለሙያዎች እና አርቲስቶች እንደሚገኙና ዝግጅቱ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በቀጥታ እና በድህረ ሁነቶች እንደሚሰራጭ ተገልጿል።

ለተጨማሪው:
Telegram: https://t.me/EventAddis1

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
❤10🔥3
🔶«አመፀኛ ነፍሶች» መጽሐፍ ማክሰኞ ይመረቃል

«አሌፋት» የግጥም ስብስብ እና «ጥቁር ሽታ» የአጫጭር ልቦለድ ስብስብ ሥራዎቹ በሚታወቀው ደራሲ መሐመድ ነስሩ (ሶፎኒያስ አቢስ) የተዘጋጀው «አመፀኛ ነፍሶች» የተሰኘው ሦስተኛው የአጫጭር ልቦለድ ስብስብ መጽሐፍ ሊመረቅ ነው።

መጽሐፉ በመጪው ማክሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኘው በወመዘክር (የብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ባለሥልጣን) አዳራሽ በድምቀት እንደሚመረቅ ታውቋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ደራሲና መምህር ኃይለመለኮት መዋዕል፣ ገጣሚ ዋሲሁን በላይ፣ ደራሲ ሕይወት እምሻው፣ ገጣሚ ረድኤት ተረፈ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ደራሲና ገጣሚ ታገል ሰይፉ፣ ገጣሚ ይታገሱ ጌትነት፣ ዶ/ር አበባ የሺጥላ እና እጸገነት ላቀውን ጨምሮ በርካታ የጥበብ ሰዎች ሥራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ተገልጿል።

ለተጨማሪው:
Telegram: https://t.me/EventAddis1

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
❤3👌2🔥1
🔶 በረከት በላይነህ አዲስ የቲቪ ሾው ሊጀምር ነው

በገጣሚነቱ፣ «እያዩ ፈንገስ» በተሰኘው ቴአትር ደራሲነቱ እንዲሁም በፍትሕ መጽሔት ላይ «ዋጋዬ ለገሠ» በሚለው የብዕር ስሙ በሚጽፋቸው የፖለቲካና ማኅበራዊ ትንታኔዎች የሚታወቀው በረከት በላይነህ በፋና ቴሌቪዥን አዲስ የቴሌቪዥን ዝግጅት ሊጀምር መሆኑ ታወቀ።

ደራሲና ጋዜጠኛ በረከት በላይነህ ሊጀምረው ያሰበው «ወቅታሪካዊ» የተሰኘው ይህ አዲስ ዝግጅት፤ ወቅታዊ ኩነቶችን ከታሪካዊ ዳራዎች ጋር አቆራኝቶ የሚያቀርብ የቴሌቪዥን ፕሮግራም እንደሆነ ተገልጿል።

ለተጨማሪው:
Telegram: https://t.me/EventAddis1

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
❤17🥰7👏5👍4😁4
ለአርቲስት አብርሃም ቀናው ድጋፍ ልዩ ዝግጅት

አርቲስት አብርሃም ቀናው ራሱ የሚተውንበት «አትጥሪኝ» የተሰኘ አዲስ የቴአትር ተውኔት ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም ረቡዕ ከቀኑ 11:30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በልዩ ሁኔታ ለተመልካች እንደሚቀርብ ተገለጸ።

ይህ የቴአትር መድረክ አርቲስቱን ለማገዝና አብሮነታቸውን ለማሳየት ለሚፈልጉ አድናቂዎቹና ጥበብ ወዳዶች የተዘጋጀ ሲሆን፤ የመደበኛ መግቢያ ዋጋው 200 (ሁለት መቶ) ብር መሆኑ ታውቋል።

በተጨማሪም የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ባስተላለፉት ጥሪ፤ የቪ.አይ.ፒ (VIP) መግቢያ ለማግኘት የሚፈልጉ ተመልካቾች አርቲስት አብርሃም ቀናውን ለማገዝ የቻሉትን ያህል የገንዘብ መጠን «1000308114671» በተባለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ሂሳብ ቁጥሩ ገቢ በማድረግ እና የከፈሉበትን ደረሰኝ በማሳየት የቴአትሩ ታዳሚ መሆን እንደሚችሉ አስታውቀዋል።

ታዳሚያዎች ገንዘብ በሚያስተላልፉበት ወቅት በምክንያት (Reason) ቦታ ላይ «አትጥሪኝ ቴአትር» የሚል እንዲጽፉ ተመላክቷል።
ስለ ዝግጅቱ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትም በስልክ ቁጥር 0901103400 ደውሎ መጠየቅ እንደሚቻል ተገልጿል።

ለተጨማሪው:

Telegram: https://t.me/EventAddis1

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
❤8👏5
ጋዜጠኛ በርናባስ ተስፋዬ አህጉራዊ ሽልማትን አሸነፈ

በስፑትኒክ አፍሪካ ኮረስፖንደንት እና የፕሮግራም አዘጋጅ የሆነው ኢትዮጵያዊው የብሮድካስት ጋዜጠኛ በርናባስ ተስፋዬ የ«Unstoppable African Journalist of the Year 2026» ታላቅ አህጉራዊ እውቅና ማግኘቱ ተነግሯል።

በናይሮቢ ኬንያ በተካሄደው የመጀመሪያው ‘ዘ አንስቶፔብል አፍሪካ አዋርድስ 2026’ አህጉራዊ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ጋዜጠኛ በርናባስ ተስፋዬ ኢትዮጵያን ወክሎ ተሸልሟል።

በርናባስ በስፑትኒክ አፍሪካ እንደ ፕሮፌሰር ፒ.ኤል.ኦ. ሉሙምባ ካሉ ታዋቂ ፓን-አፍሪካኒስቶች ጋር ባካሄዳቸው ጥልቅ ውይይቶች፣ የአፍሪካን የራሷን ታሪክ በራሷ አንደበት የመተረክ፣ የኢኮኖሚ ውህደትና የእድገት አጀንዳዎችን በስፋት በማንሳቱም የላቀ እውቅና ማግኘቱ ተመልክቷል።

በ20 የተለያዩ የሥራ ዘርፎች ከፍተኛ አህጉራዊ ተጽዕኖ የፈጠሩ አፍሪካውያንን ለማበረታታትና እውነተኛ የስኬት ታሪኮችን ለመዘከር በተዘጋጀው በዚህ መድረክ፤ ኢትዮጵያ በጋዜጠኝነት ከተመዘገበው ድል በተጨማሪ በዲፕሎማሲ፣ በሴቶችና ማኅበረሰብ ተጽዕኖ እንዲሁም በአቪዬሽን ዘርፎች በዕጩነት መቅረቧ ይታወሳል።

ለተጨማሪው:

Telegram: https://t.me/EventAddis1

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
❤21🔥5👍2
🔶ሪፖርተር ጋዜጣ ላልተወሰነ ጊዜ ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሴንተር ኃ.የተ.የግል ማህበር ስር በሚታተሙት ሪፖርተር አማርኛ፣ ዘ ሪፖርተር እንግሊዝኛ ጋዜጦች እና በኢትዮጵያን ሪፖርተር የዲጂታል ፕላትፎርሞች ላይ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እግድ መጣሉን አስታወቀ።

ውሳኔው ከጥቅምት 23 ቀን ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሚጸና ሲሆን፣ ተቋሙ ከማንኛውም የህትመት እና የስርጭት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ ተደርጓል።

ባለስልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 1238/2013 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ላለፈው አንድ ዓመት ባደረገው የይዘት ክትትል፣ መገናኛ ብዙኃኑ ተደጋጋሚ የህግ እና የሙያ ስነ-ምግባር ጥሰቶችን መፈጸሙን አረጋግጫለሁ ብሏል።

ከተጠቀሱት ጥሰቶች መካከል ከሀገር ብሔራዊ ጥቅም ጋር የሚጻረሩ ይዘቶችን ማሰራጨት፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ርዕሰ ጉዳዮችን በማጮህ በህብረተሰቡ ዘንድ ብዥታ መፍጠር፣ እንዲሁም በውጭ ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝም እና ዲፕሎማሲ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የተዛቡ መረጃዎችን ማሰራጨት ይገኙበታል።

በተጨማሪም ተቋሙ ሚዛናዊነት የጎደላቸው እና የሀገርን ገጽታ የሚያጠለሹ ዘገባዎችን ሲያቀርብ መቆየቱ ተገልጻል።

ባለስልጣኑ ባለፉት ጊዜያት ከሚዲያው ባለቤቶች እና ዋና አዘጋጆች ጋር ውይይት በማድረግ እንዲሁም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ለማስተካከል መሞከሩን ቢገልፅም፣ በይዘቶች ላይ ምንም አይነት መሻሻል ባለመታየቱ የእግድ ውሳኔውን ለማስተላለፍ መገደዱን አስታውቋል።

በዚህ ወሳኔ ላይ ከሪፖርተር በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👎10😁6😢5❤4💔1🖕1
🔶"ምስጠት - The Listening Room"

የሥነ-ጽሑፍ፣ የሙዚቃ እና የኪነ-ጥበብ አፍቃሪያንን የሚያገናኝ "ምስጠት - The Listening Room" የተሰኘ አዲስ መድረክ ተዘጋጅቷል።

በዚህ  ዝግጅት ላይ ዘ ኦብዘርቨር ተጋባዥ እንግዳ ሲሆን መካኒሳ ሲዶ ሕንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው ጃዝ ኮፊ ጥቅምት 25 2019 ዓ.ም ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ ይካሄዳል።

የመግቢያ ዋጋው 400 ብር መሆኑ ተገልጿል።

ለተጨማሪው:
Telegram: https://t.me/EventAddis1

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
❤3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔶የሕይወት እምሻው አዲስ መጽሐፍ

ደራሲ ሕይወት እምሻው 90 ታሪኮችን የያዘውን አዲስ መጽሐፏን ልታስመርቅ ነው

በኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ መጽሐፍ 90 ታሪኮችን ያካተተው የደራሲ ሕይወት እምሻው አዲስ መጽሐፍ፣ «ቀብር እና ማስካራ»፣ ቅዳሜ ሕዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም. ገበያ ላይ ይውላል።

የመጽሐፉ የሽያጭ መጀመሪያና የፊርማ ሥነ ሥርዓት ቅዳሜ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም. ለገሃር በሚገኘው ጃዕፈር መጽሐፍት መደብር ከቀኑ 8:00 እስከ 11:00 ሰዓት ይከናወናል። አንባቢያን ደራሲዋን በአካል የሚያገኙበትና የተፈረመበትን መጽሐፍ የሚያገኙበት ዕድልም ይሆናል።

«ቀብር እና ማስካራ» የሕይወት እምሻውን ሰባተኛ መጽሐፍ ሲሆን፣ በአንድ ጥራዝ ውስጥ 90 ታሪኮችን በማካተት በኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ልዩ ስፍራ የሚይዝ ሥራ ነው ተብሏል። ደራሲዋ "ይህ መጽሐፌ ከአማርኛ ቋንቋ እና ስነፅሁፍ ጋር ደጋግሜ በፍቅር እንድወድቅ ላደረገኝ ደራሲ አዳም ረታ የተበረከተ ነው" ብላለች።

ሕይወት እምሻው ከዚህ በፊት ለአንባቢያን ያበረከተቻቸው ስድስት መጽሐፍት በአንባቢያን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኙ ሲሆን ባርቾ፣ ፍቅፋቂ፣ ማታ ማታ፣ለእርቃን ሩብ ጉዳይ፣ የቡና ቁርስና፣ ዥዋዥዌ ይሰኛሉ።

ለተጨማሪው:
Telegram: https://t.me/EventAddis1

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
❤13🔥5👍4👎1
🔶እሱባለው ይታየው ከአልበሙ በፊት

ድምፃዊ እሱባለው ይታየው (የሺ)፤ በቅርቡ ከሚወጣው አዲስ አልበሙ መካከል «ለየቱ ጊዜ ነው?» የተሰኘውን ነጠላ ዜማ በቪዲዮ ክሊፕ አጠናቆ ለሕዝብ ሊያደርስ መሆኑ ተገለጸ።

የግጥም እና የዜማ ባለቤትነቱ የራሱ የድምፃዊው እሱባለው ሲሆን፣ ሙዚቃውን ሚካኤል ሃይሉ አቀናብሮታል፤ ማስተሪንጉን ደግሞ ኪሩቤል ተስፋዬ አከናውኖታል።

ይህ አዲስ ነጠላ ዜማ የፊታችን ዓርብ በድምፃዊው በራሱ ኦፊሴላዊ የዩቲዩብ ቻናል ላይ እንደሚለቀቅ ታውቋል።

ለተጨማሪው:

Telegram: https://t.me/EventAddis1

Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
❤24