Event Addis Media
9.32K subscribers
6.35K photos
16 videos
5 files
4.95K links
Connect with Addis artistic community!

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
🔶ሀሰተኛው ሞትና የቀብር ሥነ-ሥርዓት

በቻይና ሁናን ግዛት ሰክሮ በማሽከርከሩ የሚጠብቀውን የሕግ ተጠያቂነት ለማምለጥ የሐሰት ሞትና የቀብር ሥነ-ሥርዓት ያዘጋጀው ወጣት በቁጥጥር ሥር ዋለ።

ሲ የተባለው ግለሰብ የሕግ ተጠያቂነትን ለማምለጥ ሲል ከቤተሰቡ ጋር በመተባበር የሐሰት የቀብር ሥነ-ሥርዓት መፈጸሙን ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

ግለሰቡ ቀደም ሲል ያለ መንጃ ፈቃድ በስካር በማሽከርከር ሁለት ጊዜ የተያዘ ሲሆን፣ ለሦስተኛ ጊዜ በተመሳሳይ ጥፋት በመያዙ ምክንያት የሚጠብቀውን የእስራት ቅጣት በመፍራት በዋስ ከተለቀቀ በኋላ ከሀገር ለማምለጥ አቅዷል።

በመቀጠልም  ሲ እና ቤተሰቦቹ አስቀድመው የሬሳ ሣጥን በመግዛት ዕቅዳቸውን መተግበር ጀምረዋል።

ፖሊስ እንዳወጣው መረጃ፤ አቶ ሲ በመድኃኒት መጠን ማለፍ ምክንያት እንደሞተ ለማስመሰል ባዶ የመድኃኒት ብልቃጦችን በቤቱ በመበተን፣ እስትንፋስን የመያዝ ልምምድ በማድረግና የሰውነት ሙቀትን የሚቀንሱ መሣሪያዎችን በመጠቀም የሐሰት ሞቱን አስመስሏል።

የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ በተካሄደበት ዕለትም እናቱና አያቱ የሲ ፊት በመድኃኒቱ ምክንያት ተበላሽቷል የሚል ምክንያት በመስጠት ፊቱን በጨርቅ ሸፍነው ቀብሩን ፈጽመዋል። የቀብሩ ሥነ-ሥርዓት በሚከናወንበት ወቅት ግን ግለሰቡ ወደ ሌላ ግዛት በማምለጥ ላይ ነበር።

የፖሊስ አባላት ድራማውን በቀላሉ ሊደርሱበት የቻሉት የሬሳ ሣጥኑ ግለሰቡ ከመሞቱ በፊት በመገዛቱ፣ የሕክምና እርዳታ ወይም ፖሊስ ባለመጠራቱ፣ የሞት ምስክር ወረቀት ባለመኖሩና የክትትል ካሜራዎች እንዲሁም የባንክ እንቅስቃሴዎች ግለሰቡ በሕይወት መኖሩን በማረጋገጣቸው ነበር።

በክትትሉም ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ውሎ የ5 ወራት የእስራት ቅጣትና የ20 ሺህ ዩዋን የገንዘብ መቀጮ ተጥሉበታል።

©️ቻናል ዋን

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁13❤2😱1💯1
🔶ዓለም አቀፉ የወጣቶች ቀን በድምቀት ተከበረ

​"የወጣቶች ቀን፣ የበጎ ፈቃደኝነት እና የተለያዩ  እድሎች” በሚል መሪ ቃል በብሪቲሽ ካውንስል አዳራሽ የተዘጋጀው የ2026 ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።

​በ'ስዊት ላይፍ ፎር ኦል' (Sweet Life For All) ዋና አዘጋጅነት፣ ከብሪቲሽ ካውንስል፣ ከኢትዮጵያ የብሪታንያ ኤምባሲ እና ከቲኤች group (TH Group) ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ታዳጊ ተማሪዎች  ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

መድረኩ ወጣቶች የሚማሩበት፣ የሚወያዩበት፣ ትስስር የሚፈጥሩበት እና ተስፋ የሚያንፁበት አጋጣሚን ፈጥሯል።

​በበዓሉ አከባበር ላይ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት ቢሮ፣ ከብሪቲሽ ካውንስል እንዲሁም ከብሪቲሽ ኤምባሲ የተወከሉ እንግዶች እንዲሁም የሲቪል ማህበራት መሪዎች የተገኙ ሲሆን፣ የወጣቶች ድምፅ የፕሮግራሙ ዋና ማዕከል ሆኖ ውሏል።

​በወጣቶች የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ዙሪያ ያተኮረ አሳታፊ እና አበረታች ውይይት ተካሂዷል።በስደት እና ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ተደርጓል።

​በወጣቶች የተዘጋጁ ኤግዚቢሽኖች የቀረቡ ሲሆን፣ አወንታዊ የሥራ ትስስሮችም ተፈጥረዋል።​ይህ መድረክ ወጣቶች ማህበረሰባቸውን የማገልገል እና ለማህበራዊ ችግሮች መፍትሔ የማፍለቅ ከፍተኛ አቅም እንዳላቸው በተግባር ያሳየ እንደነበር ተገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😁8❤2
Forwarded from Kelemat Ads
. የቻናል ጥቆማ

የህይወት እይታዎን ማሻሻል ከፈለጉ ይህ ቦታ ለእርስዎ ነዉ፤ ይቀላቀሉ !

@Seidendre

የሚያጋጥሙንን ክስተቶች መወሰን እና መቆጣጠር ባንችልም ስሜታችንን እና አፀፋችንን መቆጣጠር ግን በእጃችን ነዉ።

Rise Daily — Where great minds are built through daily discipline !

📌 Join: @SeidEndre
🚀Share:
@SeidEndre
👎4💯4❤1
🔶አሻም ቲቪ በፍርድ ቤት ክርክር ተሸነፈ

አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ የሰራተኞቹን የ4 ወር ያልተከፈለ ደሞዝ ሳይከፍል ተቋሙን መዝጋቱን ተከትሎ፣ የቀድሞ ሰራተኞቹ ባቀረቡት ክስ ፍርድ ቤት የሰራተኞቹን አሸናፊነት የሚገልፅ ውሳኔ አስተላልፏል።

​ሰራተኞቹ መብታቸውን ለማስከበር ላለፉት 6 ወራት በፍርድ ቤት በጽናት ሲከራከሩ የቆዩ ሲሆን፣ ፍርድ ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረትም ተቋሙ ለሠራተኞቹ ያልከፈላቸውን ደሞዝ እና ተያያዥ ጥቅማጥቅሞች እንዲከፍል የሚያስገድድ ውሳኔ ወስኗል።

​ይህ ውሳኔ በሚዲያ ዘርፉ ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎችን የሰራተኞችን መብትና ጥቅም ለማስከበር ትልቅ ማሳያ የሚሆን ሲሆን፣ ተቋማት የፋይናንስ ፈተና ቢገጥማቸው እንኳ የህግና የውል ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ግልፅ መልእክት አስተላልፏል።
​
​ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤21👍7
🔶የቅዳሜ ገበያ ባዛር ጥሪ

ዚ አርባን ሴንተር (The Urban Center) በቅርቡ በሚያዘጋጀው "ቅዳሜ ገበያ" በተሰኘው የባዛር መርሃ ግብር ላይ ምርትና አገልግሎታቸውን ማቅረብና መሸጥ የሚፈልጉ ባለሙያዎችና ነጋዴዎች እንዲመዘገቡ ጥሪ አቀረበ።

በዚህ ባዛር ላይ በእጅ የተሰሩ የጥበብ ስራዎች፣ የፋሽንና የጌጣጌጥ ውጤቶች፣ የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች፣ የውበትና የጤና መጠበቂያዎች፣ የቤት ውስጥ ጌጣጌጦች እንዲሁም መጻሕፍት፣ ስዕሎች፣ እፅዋትና የጽሕፈት መሣሪያዎችን የሚያቀርቡ አካላት መሳተፍ ይችላሉ።

ለአንድ ሙሉ ቀን የጠረጴዛ ኪራይ ክፍያ 3,000 ብር ሲሆን፣ ፍላጎቱ ያላቸው ተሳታፊዎች እስከ ሰኞ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም (August 24) ድረስ መመዝገብ እንደሚችሉ ታውቋል።

ፍላጎት ያላቸው ነጋዴዎችና አቅራቢዎች
https://forms.gle/mwcJSuxg55pGpHjr8
በሚለው የማመልከቻ ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ።
❤5😁1
🔶በመኰንን ሸገኔ ስም ሽልማት ሊሰጥ ነው

በርካታ ተማሪዎችን ባፈሩት ፣ ከ 50 አመት በፊት ሕይወታቸው ባለፈው በመምህር መኮንን ሸገኔ ስም ሽልማት ሊሰጥ ነው።

የአርአያ ሰው ሽልማት  ፋውንዴሽን ፕሬዚዳንት ዲያቆን ፍሬው ሰይፉ ለተወዳጅ ሚድያ እንደተናገሩት በየዓመቱ በሚሰጠው የአርአያ ሰው ሽልማት ላይ ዘንድሮ የፊታችን  ነሐሴ 16 2018 ዓ.ም  በሚደረገው ሥነ ሥርዓት ሽልማቱ መታሰቢያ የተደረገው ለመምህር መኮንን ሸገኔ ነው ብለዋል። በተጨማሪም በየአመቱ  'የመኮንን ሸገኔ ሽልማት' በሚል ዘርፍ  ለተለያዩ ሰዎች እውቅና እንደሚሰጥ ታውቋል።

የአባቷን ታሪክ በማፃፍና ለቁምነገር እንዲበቃ በማድረግ የአንበሳውን ድርሻ የተወጣችው ልጃቸው ካቢው መኮንን ሸገኔ ስትሆን የዛሬ አመት በሰኔ 2017 መኮንን ሸገኔ  የሀገር ባለውለታ" የሚል መጽሐፍ በዕዝራ እጅጉ ተፅፎ መመረቁ ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤6👍3
🔶"የኢንተርቴይንመንት ቢዝነስ ወርክሾፕ"

በኪነጥበብና በኢንተርቴይንመንት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ክህሎታቸውን ወደ ስኬታማ የንግድ ሥራ እንዲቀይሩ የሚያግዝ "የኢንተርቴይንመንት ቢዝነስ ወርክሾፕ" በፒያሳው ክሬቲቭ ሀብ ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ።

ከነሐሴ 25 እስከ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በፒያሳው ክሬቲቭ ሀብ (Creative Hub) በሚካሄደው በዚህ የአምስት ቀናት የሥልጠና መርሃ ግብር ላይ

ተፎካካሪነትን ማሳደግና ዕድሎችን ማስፋፋት፣ ታለንትን ወደ ተዋጣለት ቢዝነስ መለወጥ፣ የራስን የጥበብ ብራንድ መገንባት፣ ከስፖንሰሮችና ከአጋር ድርጅቶች ጋር ውጤታማ የሥራ ግንኙነት መፍጠር በሚሉና በሌሎች መሠረታዊ የዘርፉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ ሥልጠና የሚሰጥ ይሆናል።

በሥልጠናው ላይ ለመሳተፍና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ፍላጎት ያላቸው አካላት በስልክ ቁጥር 0911 36 55 96 በመደወል መመዝገብ እንደሚችሉ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤4
Forwarded from Kelemat Ads
💰 የሀገራችን ቲክቶከሮች እና ዩቲዩበሮች በወር ከ100,000 ብር በላይ እያገኙ መሆናቸውን ያውቃሉ?

ስኬታቸው በተለያዩ ምክንያቶች የሚወሰን ቢሆንም፣ ጥራት ያለው ይዘት ማቅረብ ግን በጣም አስፈላጊ ነው።

Nidan Trading ለኮንቴንት ክሪኤተሮች ስራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድጉ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ይዞላችሁ ቀርቧል፦

🎙 Wireless & Studio Mics – ጥራት ላለውና ከጩኸት የጸዳ ድምፅ
💡 Studio Lights & Softboxes – ለማንኛውም ቦታ ተስማሚ የሆነ ፕሮፌሽናል ብርሃን
🎥 DJI Gimbals – ያልተንቀጠቀጠ እና ለስላሳ የቪዲዮ ቀረጻ
📸 Camera Accessories – ለስራዎ ምቾት የሚሆኑ አስፈላጊ ተጨማሪ ዕቃዎች

🔥 አዳዲስ እቃዎች ሲገቡና ልዩ የዋጋ ቅናሾችን ቀድመው ለማግኘት የNidan Trading ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ! @nidantradingg

👉 ቴሌግራም: @nidantradingg
❤7👎2😁2👌2
🔶ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ

ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ እስከ 3ዐ በመቶ የሚደርስ የበዓል ቅናሽ ማቅረቡን አስታወቀ

በኮንስትራክሽን እና ሪል ስቴት ልማት ዘርፍ በታማኝነት፣ በጥራት እና በፍጥነት ግንባታዎችን በማጠናቀቅ ስመ-ጥር የሆነው ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ፣ በተመረጡ የአዲስ አበባ ክፍሎች ቦሌ አትላስ የሾሪንግ ስራ መጨረሱን እና ለሽያጭ ክፍት መደረጉን እንዲሁም ካዛንቺስ ላይ የግንባታ ሥራውን አምስት ቤዝመንት ጨርሶ ግራውንድ ወለል ላይ በደረሰው ሳይት ላይ በይፋ ለሽያጭ ክፍት ማድረጉን ገልጿል፡፡

ድርጅቱ አዲሱን ምዕራፍ ምክንያት በማድረግ፣ ለመኖሪያና ለንግድ ቤት ገዥዎች እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ልዩ የበዓል ቅናሽ ማቅረቡን ይፋ አድርጓል። ድርጅቱ ባቀረበው መረጃ መሰረት፣ ከ55 ካሬ ሜትር ስቱዲዮ ጀምሮ እስከ ባለ 3 መኝታ 165 ካሬ ሜትር ሰፊ የመኖሪያ አፓርትመንቶች እና የንግድ ሱቆች በሽያጭ ላይ ይገኛሉ።

የመኖሪያና የንግድ ቦታዎቹ ዋጋ በካሬ ሜትር ከብር 80,500 ጀምሮ የተመደበ ሲሆን፣ እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ልዩ የዋጋ ቅናሽ እሰከ መሰከረም 30 -2019 ዓ.ም ብቻ የሚቆይ መሆኑንም ገልጿል፡፡ እንዲሁም ከዛሬ ነሐሴ 20 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአትላስ
ሳይት ላይ የሽያጭ ዘመቻ ጀምሯል።

በተጨማሪም የገበያ የምንዛሬ ጭማሪም ሆነ የግንባታ ዕቃዎች ዋጋ መለዋወጥ ሳይጋረጡ፣ ደንበኞች በተዋዋሉበት የኢትዮጵያ ብር መጠን ብቻ ክፍያቸውንተ አጠናቀው በጊዜው የሚረከቡበት የዋጋ ዋስትና መመቻቸቱም ተገልጿል።

ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የማኅበረሰብ ተሳትፎ ኃላፊነቱን ለመወጣት በአንድ የበጎ አድራጎት ተቋም እና ለሁለት ት/ቤቶች ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤4😁2👍1🔥1
🔶የድምጻዊት ተዓምር ግዛው «በፍቅር» አልበም

የድምፃዊት ተዓምር ግዛው "በፍቅር" የተሰኘ የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ቅዳሜ ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ለአድማጮች ይቀርባል ተብሏል።

ድምፃዊቷ ከዚህ ቀደም «ምነዋ»፣ «መታ መታ» እና «ቸኳኩዬ» በተሰኙ ተወዳጅ ነጠላ ዜማዎችን ለአድማጮች ያቀረበች ሲሆን ይህ የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበሟ ነው።

16 አዳዲስ ዜማዎችን በአንድ ላይ ያካተተው ይህ አልበም፥ ከአርብ ዕለት ጀምሮ በድምፃዊቷ የዩቲዩብ ቻናል እና በተለያዩ የሙዚቃ መተግበሪያዎች አማካኝነት ለህዝብ እንደሚሰራጭ ተጠቁሟል።

በዚህ አልበም ላይ በርካታ ስመ-ጥር የሙዚቃ ባለሙያዎች በግጥም እና ዜማ የተሳተፉ ሲሆን፣ አበበ ብርሃኔ፣ እሱባለው ይታየው (የሺ)፣ ምህረት አብ ደስታ፣ አቤል ሙልጌታ፣ አንተነህ ወራሽ እና ዮሴፍ በቀለ በዜማ ድርሰት ተሳትፈዋል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤7
🔶የድምጻዊ ማሕሙድ አሕመድ አዲስ አልበም

የአንጋፋው ድምጻዊ ማሕሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና የኪነ-ጥበብ ሕይወቱ ማጠቃለያ የሆነውን 26ኛ አዲስ የሙዚቃ አልበሙን ሊለቀቅ እንደሆነ ተሰምቷል።

ላለፉት ስድስት አሰርት ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያኖረው አርቲስቱ፤ ይህንን አልበም ያዘጋጀው የቀደሙትን የሀገር ውስጥ የሙዚቃ ቅርሶች ሳይበረዙና ሳይለወጡ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ በማሰብ እንደሆነ ገልጿል።

አልበሙ 13 ትራኮችን የያዘ ሲሆን ዘመናዊ የሙዚቃ መሣሪያዎችን ከባህላዊ የቅኝት ድምፆች ጋር ያዋሐደ ፤ ይዘቱም ትውልድን፣ ፍቅርን፣ ሀገርን፣ የሕይወት ፍልስፍናን እና ማኅበራዊ እሴቶችን የሚያንጸባርቁ ግጥሞችን አካቷል።

በርካታ ወጣትና አንጋፋ የሙዚቃ አቀናባሪዎች የተሳተፉበት የጋሽ መሐሙድ የመጨረሻ አልበም  ሲሆን፤ አዲሱ ትውልድ የሀገሩን ባህልና ማንነት ሳይለቅ በዘመናዊነቱ እንዲቀጥልበት ጥሪ አቅርቧል።

ይሳቃል ኢንተርቴይመንት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅና ለማሰራጨት ኃላፊነቱን የወሰደው ይህ አልበም፤ በቅርቡ በSpotify፣ Apple Music፣ YouTube እና በሌሎችም ዲጂታል መድረኮች ላይ ለሕዝብ ክፍት የሚሆን ሲሆን፣ ከአልበሙ የተመረጠ አንድ ነጠላ ዜማ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ ለአድማጮች እንደሚለቀቅ ታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤32🥰5😁3🤔2😨1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🔶የቃል ሊቀ መኳስ በጌራወርቅ ጥላዬ!

የቃል ሊቀ መኳስ መስከረም 1 ቀን 2019 ዓ.ም ለንባብ ይበቃል። ከዛሬ ጀምሮ ለገዥ ክፍት ሲሆን ለሸመታችሁ “በየዓመቱ ያምጣችሁ” እንድትሉን፥ እንደ ልጅነታችን “እንቁጣጣሽ” እያልን የቃል ሊቀ መኳስን እንደ ዐደይ አበባ ይዘን መስከረም 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምረን ከደጃችሁ መጥተን እንሰጣለን። በዚያው ወርም በመጽሐፉ ምረቃት ሰበብ እንገናኛለን።

ከአንተ እጅ ልግዛ ለምትሉ | የጀርባ ዋጋ፦ 300 ብር | ዶላር ለሚቀናችሁ 15 $።

ገንዘብ ቤት | ይሥሐቅ እንድሪስ ሰይድ
CBE፦ 1000258038847 - Yishak Endris Seid
Tele Birre፦ 0953821066 - Yishak Endris Seid

ለመስጠቱ እንዲያመቸን ❝screenshot❞ እያደረጋችሁ ከአድራሻ ጋር በውስጥ መስመር ወይም በዚህ @BaleQal አልያ @yiseot19 username ብትልኩልን ደግሞ ለማመሳከሪያነት ይረዳናል።
                         
እንደ አማራጭ | ከአከፋፋይ መሸመት ለምትሹ ደግሞ የተወሰኑ ኮፒዎች መስከረም 2 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በጃዕፈር መጽሐፍት መደብር እናስቀምጣለን።        
                        
ንባብ፦ ቤተልሔም ዓየነው @bettyayu
ምስል፦ ዳንኤል ዕንዬው፣ ዳዊት ምትኩ
ኤዲተር፦ ዳንኤል ዕንየው @Danieleneyew
                         
Telegram፦ https://t.me/GeraworqTilayee

Facebook፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=10008814

tiktok፦https://www.tiktok.com/@baleqal?_r=1&_t=ZS-99JS6giE81Z
3🔥9❤5
Forwarded from Kelemat Ads
🚨 MEDICAL STUDENT SELLS AI-BUILT WEBSITE FOR 22,000 ETB

You don’t need to be a “tech person” to build something people will actually pay for.

Fitsum is a medical student not a developer. Just a few months ago, he had zero coding background.

Today?
💰 He has sold a website he built to a real client for 22,000 ETB.

His secret wasn’t spending years learning traditional programming.
He learned how to build software with AI.

What if you could do the same?
Through the Oriix AI Income Lab – Student Edition, you’ll learn to:
👉 Build functional, sellable websites and software using AI
👉 Package, price, and pitch your work to real clients
👉 Earn a verified certificate demonstrating your practical AI skills

🎓 Regular program cost: 20,000 ETB
For eligible students, Oriix sponsors most of the cost You only pay a 999 ETB commitment fee

📲 Telegram: @Oriix_Support
📞 Phone: +251957323634
🔗 Register: https://oriix.net/student-edition/?utm_source=telegram&utm_medium=paid_social&utm_campaign=student-edition
❤6😁2
🔶የደራሲው ቃለ መጠይቅ
በኢቢኤስ እንዳይተላለፍ ታገደ

ቅዳሜ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ደራሲ ቃልኪዳን ኃይሉ "የቃል ፌርማታ" የተሰኘ አምስተኛ መጽሐፉን አስመልክቶ ከኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ ምልልስ አድርጎ ነበር። ቃለ መጠይቁ ቅዳሜ ነሐሴ 16 ይተላለፋል ተብሎ ሲጠበቅ ሳይተላለፍ ቀርቷል።

በዕለቱ ደራሲው “በሰዓት መጣበብ ምክንያት አናስተላልፍም” የሚል መልእክት ከአዘጋጆቹ የደረሰው ቢሆንም ደራሲዎች የሚቀርቡበበት ሰአት ሌላ ደራሲ አልቀረበም። አጣዳፊ የቀጥታ ስርጭትም አልተላለፈበትም።

በሳምንቱ ቅዳሜ 23 ቃለ መጠይቁ ይተላለፋል ተብሎ ቢጠበቅም ከደራሲ ቃልኪዳን ኃይሉ ቀጥሎ የተቀረፀ የተደረገለት ሌላ ደራሲ ፕሮግራም ተላልፏል።

በቃለ ምልልሱ ውስጥ ጣቢያውን በሕግ የሚያስጠይቅ ይዘት ቃለ ምልልሱ ላይ ያልተደረገ መሆኑን ምንጮቻችን ቢያሳውቁንም ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ግን ቃለ ምልልሱን ካደረገ በኋላ በድጋሚ መጽሐፉን በተለያዩ አካላት ማስገምገም መርጧል ተብሏል።

በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የጠየቅነው ደራሲ ቃልኪዳን ኃይሉ ስለ ቃለ መጠይቁ እጣ ፋንታ ቢጠይቅም ምንም ምላሽ ሳያገኝ መቅረቱን ለመሰረት ሚዲያ አረጋግጧል።

መጽሐፉ ስለ ትውልድ፣ ስለ ነጻነት እንዲሁም ለተወዳጁ ድምጻዊ ለቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) መታሰቢያ መሆኑ የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣብያን ከኢንተርቪው በላይ "የቃል ፌርማታ" የተባለው መጽሐፍ ይዘት ሳያሳስበው እንዳልቀረና ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣብያ ራስን በራስ ሳንሱር እንዲያደርግ አስገድዶታል ተብሏል።

ምንጭ: መሠረት ሚዲያ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤔9❤5
🔶አርትስ ቴሌቪዥን እና ትርታ ኤፍኤም

በቴሌቪዥን እና በሬድዮ ሥርጭት ተቀባይነትን ያተረፉት አርትስ ቴሌቪዥን እና ትርታ 97.6 ኤፍ ኤም ሬዲዮ አብረው ለመሥራት የሚያስችላቸውን ሥምምነት ተፈራርመዋል።

ይህ ስምምነት ሁለቱም ተቋማት ያላቸውን የገበያ ተደራሽነት ለማስፋት እንዲሁም ለአጋር ደንበኞቻቸው የተሻለ የማስታወቂያ አማራጮችን ለማቅረብ የሚያስችል ነው::

አርትስ ቴሌቪዥን እና ትርታ ኤፍኤም ፉክክር ላይ ሳይሆን የጋራ ተጠቃሚነትን በጋራ አብሮ ማደግን መሰረት  ያደረገውን ይህን ስምምነት ከመጪው አዲስ ዓመት አንስቶ ተግባራዊ የሚያደርጉ ይሆናል::

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🔥7❤2
🔶በአማን ፕሮፐርቲስ አማን አዲስ ኤክስፖ

አማን ፕሮፐርቲስ  በሪል ስቴት እና በግንባታ ዘርፉ ባላፉት አምስት ዓመታት ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን ላፍቶ ላይፍ፣ ኒው ላይፍ እና ስካይ ቪው ሪል ስቴቶችን በአንድ ስም በማጠቃለል በአዲስ የብራንድ ስም ወደ ገበያ መግባቱን አስታወቀ።

ድርጅቱ እስካሁን ባደረገው እንቅስቃሴ ሦስት የቤት ግንባታ ቦታዎችን (ሳይቶችን) ሙሉ ለሙሉ በማጠናቀቅ 312 አባወራዎችን የቤትና የሱቅ ባለቤት ያደረገ ሲሆን፣ 64 ዘመናዊ ቪላዎችን ገንብቶ ማስረከቡን ገልጿል።

የአማን ፕሮፐርቲስ እናት ኩባንያ የሆነው አማኔት ግሩፕ በንግድ፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላለፉት 10 ዓመታት ሲንቀሳቀስ የቆየ ሲሆን፣ በብረትና አሉሚኒየም አስመጪነት፣ በቡና ላኪነት እና በወንዝ ዳርቻ ልማት ግንባታዎች የሚታወቅ ነው።

አማን ፕሮፐርቲስ በራሱ የኮንስትራክሽን ድርጅት የሚታገዝ በመሆኑ የግብዓት እጥረትን በማስወገድ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ የማጠናቀቅ፣ የግንባታ ጥራትን የመጠበቅ እና አማራጭ የአከፋፈል መንገዶችን የማቅረብ አቅም እንዳለው አስታውቋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ኩባንያው ከአርብ ነሐሴ 29 እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም በላፍቶ ሞል ግቢ ውስጥ “አማን አዲስ ኤክስፖ” የተሰኘ ኤግዚቢሽን ያዘጋጀ ሲሆን፣ በብስራተ ገብርኤል እና በካዛንችስ የሚያስገነባቸውን ሚክስድ አፓርትመንቶች በልዩ የበዓል ቅናሽ፣ ለደንበኞች እንደሚያቀርብ ገልጿል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤1
🔶ሙዚቀኛ ጆቫኒ ሪኮ ከፕሪስቴጅ አዲስ ጋር

ፕሪስቴጅ አዲስ ከሙዚቀኛ ጆቫኒ ሪኮ ጋር የሚያገናኝ ልዩ የመታሰቢያ እና የውይይት መርሃ ግብር አዘጋጀ

ፕሪስቴጅ አዲስ (Prestige Addis) ከራዲያንት ፊልምስ እና በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር፣ የታዋቂው የቤዝ ጊታር ተጫዋች እና የሮሃ ባንድ መስራች አባል ጆቫኒ ሪኮን የአምስት አስርት ዓመታት የሙዚቃ ጉዞ የሚያከብር ልዩ መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

በመድረኩ ላይ ሙዚቀኛ ጆቫኒ ሪኮ ስለ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመን፣ ስለ አሁኑ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ሁኔታ እንዲሁም ስለ ህይወትና ጥበብ ተሞክሮዎቹ ማብራሪያ የሚሰጥ ሲሆን፣ ከተሳታፊዎች ለሚነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ይህ መርሃ ግብር ማክሰኞ ጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በአሜሪካ ኤምባሲ ግቢ ውስጥ በሚገኘው ሳችሞ ሴንተር (Satchmo Center) እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፣ ፍላጎት ያላቸው ተሳታፊዎች አስቀድመው በተዘጋጀው የመመዝገቢያ ሊንክ አማካይነት መመዝገብ እንደሚችሉ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

🔗 አሁኑኑ ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ 👇
https://jazzio.land/register

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤3🔥1
🔶"አውራ አምባ: በዓለም አዲስ ምዕራፍ"

“አውራ አምባ ለዓለም አዲስ ምዕራፍ” የተሠኘውና 10 ዓመታትን የፈጀ ዘጋቢ ፊልም እሁድ ይመረቃል።

በኢትዮጵያ ልዩ ታሪክ፣ ፍልስፍና እና ማኅበራዊ የአኗኗር ዘይቤ ያለውን የአውራ አምባ ማኅበረሰብ ታሪክና የሕይወት ተሞክሮ የሚዳስሰው “አውራ አምባ ለዓለም አዲስ ምዕራፍ” ዘጋቢ ፊልም ለመጀመሪያ ጊዜ ለእይታ ቀርቦ በይፋ ሊመረቅ ነው።

10 ዓመታትን የፈጀው ዘጋቢ ፊልሙ፣ በታዋቂዋ ትውልደ ኢትዮጵያዊት የፊልም ባለሙያ፣ የቪዲዮ አርቲስት እና አስተማሪ ፕሮፌሰር ሳሌም መኩሪያ የተዘጋጀ ነው። ፕሮፌሰር ሳሌም መኩሪያ  ከዚህ ቀደም ስደት እና የወንዝ ማዕበል የተሰኙ የፊልም ስራወች የሚታወቁ ሲሆን፣ ሥራዎቻቸው በቬኒስ ቢዬናሌ፣ በኒውዮርክ አፍሪካን ፊልም ፌስቲቫል እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የኪነጥበብ መድረኮች ቀርበዋል።

ዘጋቢ ፊልሙ እሁድ ጳጉሜ 1 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ጀምሮ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ ሲኒማ ቤቶች ድርጅት አዳራሽ (አዲስ ሲኒማ ኮምፕሌክስ) በደመቀ ዝግጅት ይመረቃል።

የፊልሙ ምረቃ ለፊልም ባለሙያዎች፣ ለባህልና ማኅበራዊ ጥናት ተመራማሪዎች፣ ለኪነ-ጥበብ ወዳጆች እንዲሁም የአውራ አምባን ማኅበረሰብ ልዩ የህይወት ተሞክሮ ለማወቅ ፍላጎት ላላቸው ሁሉ ጥሩ አጋጣሚ እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤10
🔶"ጎረቤቴ" የግጥም ዝግጅት በፊሊ ኮፊ

"ጎረቤቴ" የተሠኘ የኪነጥበብ ዝግጅት የፊታችን እሁድ ጳጉሜ 1 2018 ዓ.ም ከ11:00 ጀምሮ ሜክሲኮ ቡናና ሻይ በሚገኘው ፊሊ ኮፊ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

የዝግጅቱ አሰናኞች " አዲስ ወቅት ለመቀበል የምናደርገውን ሽር ጉድ የሚያደምቅ እስካሁን ከሠራናቸው ሁሉ ለየት ያለ መድረክ ይዘን መጣን። ጉዱን ለማየት እሁድ 11 ሰዓት ሜክሲኮ ቡናናሻይ የሚገኘው ፊሊ ኮፊ መከሰት!" ብለዋል።

ከታች ባለው ሊንክ ቀድማችሁ ተመዝገቡ!

Register here https://gorebete.wassystem.com/customer/event/12


ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤8
🔶 "አዲሱን ዓመት በምስጋና”

አዲስ ዓመትን ያለፉትን በጎ ተግባራት በማስታወስ እና የሚመጣውን ተስፋ በምስጋና በመቀበል ለማክበር የተዘጋጀ ልዩ የበጎነትና የምስጋና መርሃ ግብር ሊካሄድ ነው።

ዝግጅቱ በTH Group እና በ Sweet Life For All ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ “አዲሱን ዓመት በምስጋና” በሚል መሪ ቃል በርካታ ወጣቶችን፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን፣ የሀገር ባለውለታዎችን እና የበጎነት ተምሳሌቶችን በአንድ መድረክ ያገናኛል ተብሏል።

መርሃ ግብሩ የተለመደ የበዓል ግብዣ ሳይሆን፣ በሕይወታቸውና በስራቸው ለሌሎች መልካም አርአያ የሆኑ ሰዎችን ለማመስገን፣ የበጎነት ታሪኮችን ለማጋራት እና ተስፋን ለማደስ የተዘጋጀ ልዩ መድረክ መሆኑ ተገልጿል።

በዚሁ መሠረት በማህበረሰብ ተሳትፏቸው እና በበጎ ሥራ ላይ ባሳዩት ቁርጠኝነት ተፅዕኖ የፈጠሩ አካላት የክብር እንግዳ ሆነው እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።

ዝግጅቱ ቅዳሜ፣ ነሐሴ 30 ቀን ከሰዓት በኋላ ከ7:30 ጀምሮ ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ፣በሚገኘው ካሌብ ሆቴል ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤4💩2🙏1
🔶"የእናቴ ሮሚዮ" መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

ከእውነተኛው ሕይወት ገጽታዎች የተቀዱ ውብ ታሪኮች የተሰባሰቡበት የጋዜጠኛና ደራሲ ስመኝ ግዛው «የእናቴ ሮሚዮ» እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች መጽሐፍ ነገ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም ይመረቃል።

መጽሐፉ ቀደም ብሎ ለአንባብያን መድረሱን ተከትሎ፣ በዕለቱ በሥራው ላይ ጥልቅ ግምገማና ዳሰሳ ይቀርባል።

በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ታዋቂ የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎች፣ ምሁራን፣ አርቲስቶችና አንባብያን የሚገኙ ሲሆን፣ ከመጽሐፉ የተወሰዱ ታሪኮችም በታዋቂ ተዋንያን አማካኝነት በመድረክ ላይ ይቀርባሉ።

ደራሲዋ መጽሐፍን አስቀድሞ ለንባብ ማብቃት አንባብያን ያዩትንና የተሰማቸውን በነፃነት እንዲገልጹ እንዲሁም ገንቢ ሂስና አስተያየት እንዲሰጡበት ሰፊ መድረክ የሚከፍት መሆኑን ተናግራለች።

ምርቃቱ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አዳራሽ ይካሄዳል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤5