Event Addis Media
9.43K subscribers
6.32K photos
15 videos
4 files
4.93K links
Connect with Addis artistic community!

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
🔶ለሙዚቃ ዝግጅት የእረፍት ሰዓት ጭማሪ

ፊፋ ለሙዚቃ ዝግጅት ሲባል የእረፍት ሰዓት ደቂቃን ሊጨምር እንደሆነ ተሰምቷል ።

ፊፋ በሳምንቱ መጨረሻ በሚደረገው የአለም ዋንጫ ፍፃሜ የእረፍት ሰዓትን ወደ 20 ደቂቃ ለመጨመር ማቀዱ ተዘግቧል።

በአለም ዋንጫው ፍፃሜ የእረፍት ሰዓት ወቅት ኮልድ ፕለይ ፣ ጀስቲን ቢበር ፣ሻኪራ፣ቢቲኤስ ፣ ማዶና ፣ቡርና ቦይ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ለታዳሚያን እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።

ፊፋ ከዚህ ቀደም የሚቀርበው ዝግጅት 11 ደቂቃዎችን ብቻ እንደሚወስድ ገልፆ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ የእረፍት ሰዓቱን ወደ 20 ከፍ ለማድረግ በሂደት ላይ መሆናቸው ታውቋል።

ፊፋ የሙዚቃ አቀንቃኞቹ በ እረፍት ሰዓት ለሚያቀርቡት ስራዎቻቸው ምንም አይነት ክፍያ እንደማይፈፅም ተዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5🔥4👍3👎1🤔1
🔶ያንጎ ራይድ በአሽከርካሪዎችና ተሳፋሪዎች መካከል መተማመንን የሚጨምር «የተሟላ መለያ» ምልክት አስተዋወቀ

የዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ቡድን ያንጎ አካል የሆነው ያንጎ ጉዞ ፣ በአሽከርካሪዎችና በተሳፋሪዎች መካከል ያለውን የመተማመን እና የደኅንነት ደረጃ ለማጠናከር የሚያግዝ «የተሟላ መለያ» (Passenger Profile Badge) የተባለ አዲስ መለያ ምልክት ማስተዋወቁን አስታወቀ።

ይህ አዲስ አሠራር ተሳፋሪዎች ስማቸውን፣ ፎቶአቸውንና ግላዊ መረጃቸውን አሟልተው ሲመዘገቡ የሚያገኙት ልዩ ምልክት ሲሆን፣ አጋር አሽከርካሪዎች የጉዞ ጥያቄ በሚደርሳቸው ወቅት የተሳፋሪውን መለያ ሁኔታ አስቀድመው በግልጽ እንዲመለከቱ ያስችላቸዋል።

በተደረጉ ዳሰሳዎች መሠረት ይህ መለያ በአሽከርካሪዎች ዘንድ የጉዞ ጥያቄዎችን በልበ ሙሉነት የመቀበል ፍላጎትን በ40 በመቶ ጨምሯል። ይህም በተለይ በሌሊት ሰዓታትና ተጨማሪ ጥንቃቄ በሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች የሚፈጠረውን አለመረጋጋት ለመቅረፍ ትልቅ እገዛ አለው ተብሏል።

የያንጎ የኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ ዶክተር የቀናዓለም አበበ እንደገለጹት፣ በመተግበሪያው ላይ የሚገነባው መተማመን ለተሻለ የጉዞ ልምድና ደኅንነት ወሳኝ በመሆኑ ይህ አሠራር በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ታማኝነት የበለጠ ያጠናክረዋል።

ይህ አዲስ መለያ፣ ያንጎ ጉዞ ለተጠቃሚዎቹ ደኅንነት ካዘጋጃቸው የጉዞ መስመርን በቅጽበት መከታተልን፣ የአደጋ ጊዜ (SOS) አገልግሎትንና የጉዞ መስመርን ማጋራትን ጨምሮ ከ25 በላይ ዘመናዊ የመተግበሪያ ውስጥ የደኅንነት አገልግሎቶች መካከል የቅርብ ጊዜው መሆኑ ታውቋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
4
🔶 ካምፓስ ድራማ በምዕራፍ ሁለት

የታሪክ ማጠንጠኛውን በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ገሃዳዊ አለም ላይ አድርጎ ለ 20 ክፍሎች በፋና ቴሌቪዥን ሲተላለፍ የቆየው "ካምፓስ" ተከታታይ ድራማ በምዕራፍ ሁለት ሊመለስ ነው።

በታላቅ ፊልም ፕሮዳክሽን ፕሮዲውስ ተደርጎ ከ ረቡዕ ጥር 20 ቀን 2018 ጀምሮ  እስከ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም  ለ 20 ክፍሎች በምዕራፍ አንድ ሲታይ የቆየውና በተመልካቾች ዘንድ የበዛ ተወዳጅነትና ተከታታይን ያገኘው "ካምፓስ" ተከታታይ ድራማ ከሃምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በምዕራፍ ሁለት መታየት እንደሚጀምር የድራማው ደራሲና ዳይሬክተር አብይ ጌታሁን አስታውቀዋል።

"ካምፓስ" በምዕራፍ አንድ ቆይታው "ሆራይዘን" በተባለ ምናባዊ ዩንቨርሲቲ ውስጥ የተፈጠረ ዩንቨርሲቲ ውስጥ ተማሪ የሆኑ ወጣቶች ህይወት ላይ ያተኮረ ሆኖ በተለየ ደግሞ የዋና ገጸ-ባህሪትዋን (መስከረምን) የህይወት ምስቅልቅል አስቃኝቷል።

በዚሁ ምዕራፍ ሂደት ውስጥም ወጣትነት ሲፈተን አላማ፣ እቅድ፣ በራስ ላይ የነበረ መተማመን በከባድ የህይወት ጥያቄ ሲነቀነቅ፣ ጓደኝነት፣ ሀቀኝነት፣ ፍትወት፣ የገንዘብ ኃያልነት ሲፈተሹም ታይቶበታል።
ተራ የማህበራዊ ድህረ ገጽ የሚመስል ግን ወጣቶችን ወዳልተፈለገ የወሲብ ንግድ የሚመራ ወጥመድ ምን ያህል በተማሪዎች የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖም በጉልህ ታይቶበታል።

በድራማው ቶማስ ቶራ ፣ ቅድስት ገ/ሥላሴ ፣ አበበ የሸዋልዑል ፣ ተስፋዬ ይማም ፣ የኋላሽት ዘሪሁን ፣ ማህሌት የኃላወርቅ  እና ሌሎችም ወጣትና አንጋፋ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
11👍9
🔶NBC Ethiopia ቲቪ ማስታወቂያ አውጥቷል

ናሽናል ሚዲያ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ክፍት የስራ ማስታወቂያ መደቦች ላይ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።ለተጨማሪው:- https://t.me/NorRadio1/292


ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5
🔶አብርሆት ቤተመጻሕፍት ወደ ሥራ ተመልሷል

ለቀናት በሀገር አቀፍ ፈተና ምክንያት ለአንባቢያን ዝግ ሆኖ የቆየው አብርሆት ቤተመጻሕፍት ለሁሉም አንባቢያን ክፍት ሆኗል።

ቤተመጻሕፍቱ በማህበራዊ ትስስር ገፆ" ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ተጠቃሚዎች በሙሉ! ከዛሬ ማለትም ከሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ቤተ-መጻሕፍታችን በመደበኛ ሰዓቱ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል" ብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍105
🔶JFm ከስርጭት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ጄኤፍኤም (JFM) 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ታሳቢ በሚደረግ ስልጣን ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት ከስርጭት ሙሉ ለሙሉ እንዲታገድ መወሰኑን ኖር ሬድዮ ሰምቷል።

ባለሥልጣኑ ውሳኔውን ያሳለፈው በጣቢያው ላይ ባደረገው የይዘት ክትትልና በአካል ተገኝቶ ባከናወነው የኢንስፔክሽን ምልከታ በርካታ የሕግና የፈቃድ ውል ጥሰቶችን በመለየቱ እንደሆነ ገልጻል...ተጨማሪውን ያንብቡ:- https://t.me/NorRadio1/293


ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ነኘፀ
7😱7🌚2
🔶የተወዳጁ ደራሲ Albert Camus ምርጥ ስራዎች በሀገር ውስጥ ዕትም ታትሞ ለንባብ ቀርቧል ::

Albert Camus በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከታወቁት ደራሲዎችና ፈላስፎች አንዱ ነበር።

በ1913 በአልጄሪያ (በዚያን ጊዜ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት) ተወለደ። በድሃ ቤተሰብ ውስጥ አደገ፣ አባቱም በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ሞተ። በወጣትነቱ ጋዜጠኛ፣ ደራሲ እና የቲያትር ተዋናይ/አዘጋጅ ሆኖ ሠራ።

በ1957 በሥነ ጽሑፍ የኖቤል ሽልማት አሸነፈ፣ በዚያን ጊዜ 44 ዓመቱ ነበር ።
በ1960 በመኪና አደጋ በ46 ዓመቱ ሕይወቱ አለፈ።

አልበርት ካሙ በተለይ ስለ ሕይወት ትርጉም፣ ነፃነት፣ ኃላፊነት እና "Absurd" (ሕይወት በራሷ ትርጉም የሌላት መሆኗን የሚያስረዳ ሐሳብ) ይጽፍ ነበር።

ከታዋቂ መጻሕፍቶቹ መካከል፦

The Stranger (L'Étranger)
The Plague
The Myth of Sisyphus
The Fall

ካሙ ዛሬም በዓለም ዙሪያ በጣም የሚነበብ ደራሲ ሲሆን፣ መጻሕፍቶቹ በሕይወት ትርጉም፣ በሰው ልጅ ምርጫ እና በሥነ ምግባር ላይ ጥልቅ ሐሳቦችን ያቀርባሉ።

ምንጭ: ጃዕፈር መጽሐፍ መደብር

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ነኘፀ
3🔥2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🔶ላዳ ታክሲዎች 50 ዓመት ሞላቸው

የደርግ ስርዓት ከሶቪዬት ሕብረት ጋር የነበረውን ጥብቅ ወዳጅነት ተከትሎ እነዚህ የሩሲያ ምርት የሆኑት 'ላዳ 1200' መኪናዎች በብዛት ወደ ኢትዮጵያ መግባት ጀመሩ። መኪናዎቹ መጀመሪያ ላይ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ለታክሲነት አልነበረም። ለከፍተኛ ባለሥልጣናት አገልግሎት ይውሉ ዘንድ አዲስ አበባ የደረሱት ላዳዎች የመደበኛው ሕዝብ መገልገያ ሆነው በሕዝብ ልብ ውስጥ ነገሡ፡፡

ለ5 አስርት ዓመታት በመዲናዋ ጎዳናዎች በሰማያዊና ነጭ ቀለም ውር ውር የሚሉትን ላዳ ታክሲዎች ያመረተው የሩሲያው ቮልስኪ አውቶሞቢል ፕላንት (ቫዝ ፕላንት) ኩባንያ ዛሬ 60ኛ ዓመቱን ይዟል፡፡ 

አዲስ አበባ ጎዳናዎች አናብስቱ ታሪካዊ አመጣጥ፣ ወደ ሕዝብ አገልግሎት የተሸጋገሩበት አጋጣሚ፣ ለከተማዋ ኢኮኖሚ የነበራቸው አበርክቶ ጨመሮ በአጠቃላይ በዘመን እርጅና የማይደበዝዝ ሁለንተናዊ አሻራቸውን እንዳላቸው ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ዘግቧል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ነኘፀ
10👍5🙏1💯1
🔶አንጋፋ ጋዜጠኞች ሊመሰነጉ ነው

በኢትዮጵያ የሚድያ ታሪክ የማይረሳ አሻራ ያኖሩት አዲስ አለም ሓድጉና በልሁ ተረፈ የምስጋና መርሀ ግብር ሊደረግላቸው ነው።

ቅዳሜ ሐምሌ 18 2018 ዓ.ም በወመዘክር መርስኤሀዘን አዳራሽ በሚደረገው የምስጋና መርሀ ግብር የባለሙያዎቹ አድናቂዎች እና ወዳጆች ይታደማሉ።

አዲስ አለም ሓድጉ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በትግርኛ ክፍል በኤዲተርነት እና በጋዜጠኝነት የሠራ ሲሆን ላለፉት 35 አመታትም ሙያውን ወዶና አክብሮ በመሥራት ይታወቃል።

የሚድያ ሰው በልሁ ተረፈ ደግሞ በኢትዮጵያ ሬድዮ ከሳይንስ ማህደር፣ ማንነት ሲፈተሽ እና ዝክረ ሰንበት በተባሉ ፕሮግራሞች ከ30 አመት በላይ የሠራ ሲሆን ሌሎችንም በማብቃት የማይዘነጋ አሻራ ለማኖር የቻለ ነው።

ሰውን በሕይወት ሳለ እናመስግን የሚል መርህ ያነገበው ይህ መሰናዶ የሚድያ ባለሙያዎችን በኑሯቸው የማገዝ ፣ በችግራቸው ጊዜ አብሯቸው የመሆን ግብ የሰነቀ ነው። እንዲህ አይነቱ ባለሙያዎችን የማገዝ ተግባር ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።

ሁለቱም ባለሙያዎች አገር የጣለችባቸውን አደራ የተወጡ ብርቱ ባለሙያዎች ሲሆኑ ነገር ግን በኑሮ መደገፍ እና መመስገን ያለባቸው በመሆኑ ለዚህ መርሀ ግብር ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሠራ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
13👏9
🔶የዶ/ር ኣርካ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

በዶ/ር ኣርካ አቦታ የተዘጋጀው 'የሦስት ኮከቦች ንትርክ' የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል

ይህ መጽሐፍ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አንጋፋ የሚድያና ኮሚንኬሽን  ት/ቤት መምህር በሆኑት ዶ/ር ኣረካ አቦታ ተጽፎ በ ዶ/ር ተሻገር ሽፈራው የአርትኦት ሥራው የተሰርላት መጽሐፍ ነው።

መጽሐፉ በይዘት ደረጃ ዶ/ር የፖለቲካዊ እና የህይዎት ምልከታዎች ያጋሩበት ሲሆን ብዙም ባልተነገረላቸው ባህላዊ አውዶችና ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች ውስጥ የሚጓዝ መሳጭ ታሪክ የያዘ ነው ተብሏል።

ይህ በ506 ገፆች ተቀንብቦ በ998 ብር የቀረበው መጽሐፍ ነገ ሐምሌ 18 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  ራስ መኮንን አዳራሽ ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ይመረቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
16🙏2👌2👍1👎1
Forwarded from Kelemat Ads
የቻናል ጥቆማ

ህይወታችን የአስተሳሰባችን ነጸብራቅ ነው። ታላቅ ሕይወት በታላቅ አስተሳሰብ ይጀምራል። የትናንሽ ዕለታዊ ስኬቶች ድምር ታላቅ ስኬትን ያመጣል።

አዕምሯችንን እናሳድግ፤ በየቀኑ ከፍ እንበል፤ ስኬታችንን እንገንባ!

Rise DailyWhere great minds are built through daily discipline !

📌 Join: @SeidEndre
📤 Share with friends: @SeidEndre
5👎3👏1
Forwarded from Kelemat Ads
Your product deserves users not just views.

Kelemat Ads is more than an advertising platform we're a growth partner for Ethiopian digital startups.

Before every campaign, we work with you to understand your product, identify your ideal audience, and build a distribution strategy that gives your launch the best chance of success.

Then we promote your product across our network of 140+ carefully selected Telegram channels, with a combined subscriber base of 500,000+.

📌 Strategy before promotion
📌 Targeted distribution
📌 Measurable results

Best for EdTech | AI Products | SaaS | FinTech | Mobile apps | Telegram bots | Online courses |Productivity tools

Applications are now open for a limited number of startups to receive 40% off their first launch campaign.

Ready to apply?
fill out this form and we will get back to you within 24 hours to book your 1:1 strategy call.

form link : https://forms.gle/M1C5kUbLdrcFSjxy9
👌1
🔶 "የፒያሣ ድምፆች" ዐውደርዕይ

መንገዶቹ  ቢቀየሩም ድምጻቸው አሁንም ይኖራሉ በሚል ሀሳብ የተዘጋጀው "የፒያሣ ድምፆች" የተሰኘ የዲጂታል አርት ዐውደርዕይ ነገ ይከፈታል።

በዳዊት ክፍሌ የተዘጋጀው ይህ አውደርዕይ ከሐምሌ 22 እስከ ነሐሴ 18 2018 ዓ.ም በፈንድቃ የባሕል ማዕከል በዕይታ ይቆያል ተብሏል።

ይህ ዲጂታል የሥነጥበብ ዐውደርዕይ ድሮዋን ፒያሣ ያስታውሳል ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
6
🔶የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ አዲስ መጽሐፍ

ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ "አደይ እና ጥቀርሻ" የተሰኘ የግጥም መፅሐፉን በቅርቡ ለንባብ ያበቃል።

ይህ መጽሐፍ የበድሉ ዋቅጅራ ስድስተኛ የሥነግጥም መጸሐፉ ነው።

አስቀድሞ የፍካት ናፋቂዎች፣እውነት ማለት የእኔ ልጅ፣የተስፋ ክትባት፣የወይራ ስር ፀሎት፣የራስ ምስል የተሰኙ አምስት የግጥም መጽሐፍትን ለንባብ አብቅቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👎76🔥4
🔶በቆሎና ንባብ በክረምት

በልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ የተዘጋጀው "በቆሎና ንባብ በክረምት" መሰናዶ የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 25 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በጎተራ ማሳለጫ ይካሄዳል።በዕለቱም የተለያዩ እንግዶች ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
3👍2🤮1
🔶የዓለም ደራሲያን ድርጅት በኢትዮጵያ

የዓለም ደራሲያን ድርጅት በኢትዮጵያ ዛሬ ስብሰባውን እንደሚያደርግ ተገለፀ።

ኢትዮጵያዊያን ደራሲያን ተሳታፊ የሚሆኑበትና አለም አቀፍ እንደሆነ የተነገረለት ጉባኤ ዛሬ ሐምሌ 22 2018 ከ 10 ሰዓት ጀምሮ በኢሊሊ ሆቴል እንደሚደረግ ታውቋል።

በሥነ-ፅሑፍ ሙያ ላይ የተሰማሩ፣ በአርትዖት የተለየ አሻራ ያኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሚሳተፉበት በዚህ ጉባኤ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑትና በአፍሪካ ሥነ ፅሑፍ ላይ ያጠኑት ዶክተር አቢይ ዳንኤል ወረቀት ያቀርባሉ።

እንዲሁም ፀሐፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ከፅሑፍ አቅራቢዎቹ መካከል ናቸው። የአለም የደራሲያን ማህበር ፕሬዘዳንት ማርጋሬት ኤ አይ ለዚሁ ስብሰባ ሲሉ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን የጉባኤው ቅድመ ዝግጅትም እንደተጠናቀቀ ለማወቅ ተችሏል።

Africa in shaping a common future በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ከአፍሪካ ሥነ ፅሑፍ ጋር የተያያዙ ርዕሰ ጉዳዮች እንደሚቀርቡም ታውቋል።

ይህ ጉባኤ በኢትዮጵያ ሲደረግ የኢትዮጵያ ደራሲያንን በአለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ግንኙነት በማሳደግ የራሱ ሚና እንደሚኖረው ይታወቃል።

ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽንም በመፅሐፍ ዝግጅቴ ሥራ ላይ የተሠማራ በመሆኑ መሥራቹ እዝራ እጅጉን ጨምሮ የዝግጅት ክፍሉ አባላት በኢሊሊው ጉባኤ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

©️ተወዳጅ ሚዲያ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
11👍3
🔶 “ንባብ ለሕይወት” ዐውደ ርዕይ ተከፈተ

“ንባብ ለሕይወት”የመጽሐፍት ዐውደ ርዕይ በኤግዚቪሽን ማዕከል በይፋ ተከፍቷል።

ከ2007 ዓ.ም. ጀምሮ በየዓመቱ ደራሲያንና አንባቢያንን እያገናኘ ያለው “ንባብለሕይወት” የመጽሐፍት ዐውደ ርዕይ ከዛሬ ሐምሌ 24 ቀን ጀምሮ እስከ እሑድ ሐምሌ 27 ቀን ድረስ ይቆያል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጽሐፍት ኤጀንሲ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ እና ሌሎች ተቋማትም የንባብ ለህይወት አካል ናቸው።

በዐውደ ርዕዩ ላይ የልጆች መጽሐፍት፣የታሪክ፣ የፖለቲካ፣ የቢዝነስ (ኢኮኖሚ)፣ ልብወለድ፣ ግጥም፣ የጠፉና አዳዲስ መጽሐፍቶች ጨምሮ በየዘውጉ ይገኛሉ።

ደራሲያንን ማስፈረምና የጋራ ፎቶዎችን መነሳት፣ ከማተሚያ የወጡ አዳዲስ መፅሐፍቶችን በአንባቢያን ማስመረቅ የዐውደ ርዕዩ አካል ናቸው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
10👏2
🔶“የቃል ሊቀ መኳስ” አዲስ መጽሐፍ

በ“እናርጅና እናውጋ” መጽሐፍ ተወዳጅነትን ያተረፈው ጌራወርቅ ጥላዬ “የቃል ሊቀ መኳስ” በሚል ዐዲስ መጽሐፍ መጥቷል።

ኤቨንት አዲስ ቀድማ እንደሰማሁ ከሆነ መጽሐፉ አንድ ሺህ ኮፒ ብዛት፣ በ128 ገጽ ታትሞ በ300 ብር የጀርባ ዋጋ በዚህ ሳምንት ከሕትመት ቤት የወጣ ሲሆን ለአንበባቢ ይፋ የሚሆንበት ቀን ግን ገና እንዳልተወሰነ ነው።

ጌራወርቅ ከዚህ ቀደም በነበረው በ“እናርጅና እናውጋ” መጽሐፍ በ2016ዓ.ም በተካሄደው የክብር አዋርድ “የዓመቱ ምርጥ የግጥም መጽሐፍ” በሚል ዘርፍ አሸናፊ ነበር።

ከመጽሐፍ ባለፈ የሙዚቃ ግጥም ደራሲ ሲሆን የሃሌሉያ ተ/ጻዲቅ “የልቤ ቁምነገር” የሚለው ተወዳጅ ሥራዋ የጌራ ድርሰት ነው። ይህም ሙዚቃ በአፍሪማ አዋርድ እጩ የነበረና በዩጋንዳ በተካሄደው አይኮኒክ አዋርድ ደግሞ “የዓመቱ ምርጥ ዘፈን” በሚል ተሸላሚ ነበር።

ከዓመታት በፊት “ሙሉ አካል ትዝታ” በሚል ልቦለድ እንደሚመጣ ተናግሮ እንደነበር አይዘነጋም።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
114
🔶ቅዳሜ ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም

192 ሚሊዮን ዓለም አቀፍ ተመልካቾች ባሉት አማዞን ፕራይም አማካኝነት የሚተላለፈው እና የኢትዮጵያን በጎ ገጽታ፣ የባህልና የቅርስ ሀብቶች እንዲሁም የከተማችንን አዲስ ገጽታን የሚያስቃኘው “Why Are You Not Here?” የተሰኘው የቴሌቪዥን ተከታታይ ሲሪየስ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በይፋ ለዕይታ ይበቃል።

ይህ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተው ሲሪየስ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ አቅንቶ በሃገሪቷ ፍቅር፣ በባህሏ፣ በቅርሶቿና በህዝቡ እንግዳ ተቀባይነት ስለተማረከ አፍሪካዊ-አሜሪካዊ ገጣሚ የሚተርክ ልዩ ሥራ ነው።

በምርቃቱ ላይ በመገኘትዎ:
• ሁነቱን በነፃ የመታደም እድል ያገኛሉ።
• የዓድዋ ድል መታሰቢያን ይጎበኛሉ።
• ከአለም አቀፍ እንግዶች ጋር የመገናኘትና የመተዋወቅ አጋጣሚ ይኖርዎታል።
ቦታ: ዓድዋ ድል መታሰቢያ
ቀን: ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም
ሰዓት: ከቀኑ 9:00 ሰዓት
መግቢያ: በነፃ

ቦታዎን አሁኑኑ ያስይዙ: EthiopianRSVP.com
ቀድመው ይመዝገቡ፣ ፖስቱንም ለወዳጅዎ ያጋሩ ያድርጉ!

http://www.ethiopiarsvp.com/

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
5👎5🤔1
🔶"በመሃል" ቅዳሜ ይመረቃል

በእመቤት አብዲሳ የተፃፈው  "በመሃል" የተሰኘው  የፈጠራ ሥራ የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 2 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ኧርባን ሴንተር(የከተማ ማዕከል) ይመረቃል።

በምረቃ መርሀ -ግብሩ ላይ የደራሲዋ እንግዶች፣ ወዳጆች የሚታደሙ ሲሆን የመፅሐፍ ዳሰሳን ጨምሮ ልዩ ልዩ መሰናዶዎችም እንደሚኖሩ ይጠበቃል።

የመፅሐፉ ደራሲ እመቤት አብዲሳ ጅግሳ፣ ከተማሪነት ዕድሜዋ ጀምሮ ለቃላትና ለሃሳብ ፍቅር በማሳደሯ ገና በልጅነቷ ወደ ጽሑፍ ዓለም የገባች ጋዜጠኛ ነች።

የኮሙኒኬሽን ባለሙያ እና አሁን ደግሞ ደራሲ የሆነችው እመቤት በጋዜጠኝነት ሙያዋ በታወቁ ጋዜጦች ላይ በርካታ ማኅበራዊና ባህላዊ አጀንዳዎችን ያነሱ ጽሑፎችን ስታቀርብ ቆይታለች። የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ሳለችም  የተለያየ ይዘት ያላቸውን ዘገባዎች፣ ቃለ- መጠይቆችና ፕሮግራሞችን በመሥራት ሰፊ ልምድ አካብታለች። በተጨማሪም በኮሙኒኬሽን ባለሙያነት የተለያዩ ማህበረሰባዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ በመሥራት ላይ ትገኛለች።

እመቤት ባለፉት ዓመታት ያከማቸቻቸውን የሕይወት ምልከታዎች፣ ስሜቶችና ልምዶች በማጣመር «በመሃል» የተሰኘውን የፈጠራ ሥራዋን ለአንባቢዎች አበርክታለች። በ195 ገጾች የተሰናዳው ይህ መጽሐፍ፣ በስፋት የተቃኙ 14 አጫጭር ታሪኮችን እና 43 ግጥሞችን በውስጡ  ይዟል። 450 ብርም እንደሚሸጥ ከደራሲዋ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

በቅርቡ በ «ንባብ ለሕይወት» ኤግዚቢሽን ላይ ከአንባቢያን ጋር የተዋወቀው «በመሐል» መጽሀፍ የደራሲዋ የፅሑፍ ክህሎት የታየበት ደረጃውን የጠበቀ ሥራ ነው ሲሉ ያነበቡት ሀሣብ ሰንዝረዋል።

©️ተወዳጅ ሚዲያ

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
8
🔶የጠላ፣ጠጅና አረቄ ተጠቃሚዎች ቁጥር ጨመረ

በፋብሪካ የሚመረቱ አልኮሎችና ትንባሆ ላይ
የኤክሳይዝ ታክስ መጣል የምርቶቹን ዋጋ አንዲጨምር በማድረጉ የምርቶቹ የተጠቃሚዎች ቁጥር መቀነሱን ጥናት አሳየ፡፡

በሌላ በኩል ግን ጠጅ ፣ ጠላ ፣ አረቄ የመሳሰሉት ምርቶች ተጠቃሚያቸው መብዛቱን በጥናቱ ግኝት ተጠቅሷል፡፡

ጥናቱን ያጠናው በጤናው መስክ ጥናትና ምርምሮችን የሚያካሂደው ፍኖት የተሰኘ ድርጅት ነው ።

ድርጅቱ ይህን ጥናት ይፋ ያደረገው ከስድስት ዓመት በፊት በአልኮል እና በትንባሆ ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ ምን ውጤት እንዳመጣ በአማራ፣ኦሮሚያና በአዲስ አበባ ላይ ያካሄደው ዳሰሳዊ ጥናት ነው ።

በአልኮልና በትንባሆ ምርቶች ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ የተጠቃሚዎችን ቁጥር ከ10 እስከ 20 በመቶ እንዲቀንስ አድርጓል ሲሉ በፍኖት አሶሼት የሄልዝ ኬር ፋይናንሲንግ ባለሙያና አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አስማማው አጥናፉ የጥናቱን ውጤት ጠቅሰው ነግረውናል፡፡

በሌላ በኩል መንግስት የሚያገኘው ገቢ እንዲያድግ ማስቻሉንም በጥናቱ አረጋግጠናል ይላሉ።

የፍኖት አሶሼት መስራች አባል እና የፍኖት ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዶ/ር ፅኑኤል ግርማ በበኩላቸው
እንደ ትንባሆ እና ሲጋራ ምርቶች በህገወጥ መንገድ አሁንም እየገቡ መሆኑን ነግረውናል።

በፍኖት አሶሼት የፋይናንሲንግ ም/ ዳይሬክተር ዶ/ር ግርማ ደዬ በፋብሪካዎች የማይመረቱ፣ የአልኮል መጠናቸውም በማይታወቁ እንደ ጠላ፣ ጠጅ እና አረቄ ያሉ መጠጦች በሰዎች ጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያመጡ ነው ብለዋል ።

በሌላ በኩል በህገወጥ የሚገቡ ምርቶችን መቆጣጠር እንደሚገባም ጠቁመዋል።

©️ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

========
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1
13😁7🫡3🤩2🤣2