🔶ይድነቃቸው ሹመቴ
በአሜሪካ ኤምባሲ
ፕሪስቴጅ አዲስ ተወዳጁን እና አንጋፋውን በሀገር ውስጥ በፊልም ሥራዎቹ ፤ በFilm directing እና በድርሰት ዘርፍ የሚታወቀው ስመ-ጥሩ እና አንጋፋው ዳይሬክተር እና ደራሲ ይድነቃቸው ሹመቴን ጋብዟል::
ከዳይሬክተር ይድነቃቸው ሹመቴ ጋር በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና የጥበብ ተሞክሮውን የሚያካፍለን ሲሆን፣ ከእናንተ ከወዳጅና አድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ የፊታችን ማክሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ምላሽ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል።
ፕሪስቴጅ አዲስ ከዳይሬክተር ይድነቃቸው ሹመቴ ጋር አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ እንድታደርጉ በታላቅ አክብሮት ይጋብዛል።
አድራሻ፦ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ (ሳችሞ ሴንተር / Satchmo Center) — ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ
ቀን፦ ማክሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2018 ዓ.ም (July 14)
ሰዓት፦ ከሰዓት 8:00 (8:00 PM Ethiopian Time / 2:00 PM Local Time) 🕘
⌚️ 🎯 ማሳሰቢያ፦ ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ሊያደርግ ስለሚችል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩ።
ከመታወቂያ ጋር መምጣት እንዳይረሳ! 🪪
📎 በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ 👇🖱
https://jazzio.land/register
የፕሪስቴጅ አባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ 👇🖱
https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA
@prestigeaddis
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

👍8❤4
🔶የመምህራኑ የAi ቅሌት
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በመምህራን ከቀረቡ ጥናቶች ከ91% በላዩ ሙሉ ለሙሉ በኤ.አይ በመሰራታቸው ውድቅ መደረጋቸውን ገለጸ
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ካቀረቧቸው 104 የጥናት ጽሑፎች መካከል ከ91% በላይ ማለትም 95ቱን ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል። ፕሮፖዛሎቹ ውድቅ የተደረጉት ሙሉ በሙሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤ.አይ) በመሠራታቸው ነው ተብሏል።
ዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ተማሪዎች ሰው ሰራሽ አስተውሎትን አላግባብ እየተጠቀሙ መሆኑን አስታውቋል።
የዩኒቨርሲቲው የሕግ ትምህርት ክፍል መምህር አቶ ዓለሙ ባልቻ እንደገለጹት፤ ከቀረቡት 104 ፕሮፖዛሎች ውስጥ ዘጠኙ ብቻ ኤ.አይን ሳይጠቀሙ ወይም ኤአይን በአግባቡ በመጠቀም የተዘጋጁ ናቸው።
ዩኒቨርሲቲው ዲጂታል ቴክኖሎጂን በሥርዓተ-ትምህርቱ ውስጥ ለማካተት እየሰራ እንደሆነ ተገልጾአል።
ዩኒቨርሲቲው የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀምን ለመገደብ አዲስ መመሪያ ማውጣቱንም አቶ ዓለሙ ተናግረዋል።
በዚህ መሠረት መምህራን እና ተማሪዎች እስከ 30 በመቶ ብቻ በኤአይ እንዲጠቀሙ ቢፈቀድም፤ የአጠቃቀም መጠኑን ለመለየት ተርኒቲን (Turnitin) የተባለ ሶፍትዌር ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሆነ አብራርተዋል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በትምህርት ዘርፍ አዎንታዊ ጎኖች ቢኖሩትም በጥንቃቄ መጠቀም ያስፈልጋል ያሉት መምህር ዓለሙ በተለይም ጥናታዊ ጽሑፎች የባለቤቱን የፈጠራ ክህሎት ሊያንፀባርቁ ይገባል ብለዋል።
©️ዘገባው የአሐዱ ሬድዮ ነው

🤣11👍8❤7😁1
🔶ደራሲ ቡርሃን አዲስ በትልቅ ዝግጅት ተመሰገነ
"ሰላም ነው የሰጣችሁኝ" ቡርሃን አዲስ
ከ35 በላይ የፍልስፍና ማኅበራዊ ይዘት ያላቸውን መጻሕፍት ለአንባቢያን በማቅረብ ለሚታወቀው ደራሲ ሙሐመድ ዓሊ (ቡርሃን አዲስ) የምሥጋናና ዕውቅና ሥነ ሥርዐት በማርዮት ሆቴል ተካሄደ።
በዛሬው ዕለት በተካሄደው ፕሮግራም ላይ የተገኙ የቅርብ ወዳጆቹ ለደራሲው ያላቸውን አክብሮት ስጦታ በማበርከት ገልጸውለታል። በመርሐ ግብሩ ላይ የሙሐመድ ዓሊ ሥራዎች ቀርበው በጨረታ ተሸጠዋል።
• አንድ መጽሐፍ በ400,000 ብር
• አንድ መፅሃፍ በ250,000 ብር
• አንድ መጽሐፍ በ200,000 ብር
• በርካታ መጻሕፍት ደግሞ በ50,000 እና 25,000 ብር ተገዝተዋል።
ደራሲ ቡርሃን አዲስ በነበረው ድንቅ ድጋፍ ልቡ ተነክቶ፦ "ዛሬ ደስታ አይደለም የተሰማኝ ሰላም ነው የሰጣችሁኝ" በማለት ደስታውን ገልጿል።

❤29🆒6🔥4👍1🙏1
🔶የአህመድ ተሾመ አልበም
ድምጻዊ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ) ሦስተኛ አልበሙን ለአድማጮች ሊያደርስ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።
13 የሙዚቃ ስብስቦችን የያዘውና "ጊዜ አይሄድም" የተሰኘው ይህ አዲስ አልበም በመጪው አርብ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ለአድማጮች ይቀርባል።
በዚህ አልበም ዝግጅት ላይ በግጥምና ዜማ አሰናጅነት ናትናኤል ግርማቸው፣ ምልዕቲ ኪሮስ፣እልፍ አግድ እምሻው ፣ከድር አሊ፣ አቡዲ፣ ወንድወሰን ይሁብ፣ የተሳተፉ ሲሆን በሙዚቃ ቅንብር ሚካኤል ኃይሉ፣ ታምሩ አማረ እና ፋኑ ጊዳቦ እና ሌሎችም ተሳትፈውበታል።
የአልበሙ ጭብጥ ከተስፋና ከጊዜ ጋር የተያያዘ ሲሆን፤ ሁለት ተቃራኒ ሐሳቦችን በአንድ ላይ የያዘ ጥልቅ ፍልስፍናም አለው ተብሏል።
ድምጻዊ አህመድ ተሾመ «እዮሪካ» እና «ኦሜርታ» የተሰኙ አልበሞቹን ከዓመታት በፊት ለአድማጮች አቀርቧል።
«ዲንቢ ለዲንቢ»፣ «ተጠየቂ ናዝሬት»፣ «አውራአምባ» እና «በትዝታው ፈረስ» ሙዚቃዎቹ በበርካታ አድማጮች ዘንድ በብዛት የተወደዱለት ሥራዎቹ ነው።

❤16
🔶 የዕድሜ ገበያ አዲስ መጽሐፍ
በደራሲ አበረ ሸፈራው የተዘጋጀውና «የዕድሜ ገበያ» የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ በመጪው ቅዳሜ ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. እንደሚመረቅ ታውቋል።
ይህ 12 አጫጭር ታሪኮችን በውስጡ የያዘው አዲስ መጽሐፍ 261 ገጾች ያሉት ሲሆን፣ በ599 ብር የሽያጭ ዋጋ ለአንባቢዎች ቀርቧል።
ደራሲ አበረ ሸፈራው ከአንድ ዓመት በፊት «የበርበሬ ዐውሎ ንፋስ» የተሰኘ ሌላ መጽሐፍ አሳትሞ ለአንባቢ ማድረሱ ይታወሳል።
ለህዝብ ክፍት የሆነው የመጽሐፉ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ቅዳሜ ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 እስከ 10:00 ሰዓት ድረስ፣ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው የከተማ ማዕከል ይከናወናል።
በዕለቱ በሚካሄደው መርሃ ግብር ላይ ሰለሞን ሳህለ እና ሕይወት እምሻውን ጨምሮ ታዋቂ ደራሲያን ከመጽሐፉ ውስጥ የተመረጡ ታሪኮችን ለታዳሚው እንደሚያነቡ ታውቋል።

❤12👍4
🔶ለሙዚቃ ዝግጅት የእረፍት ሰዓት ጭማሪ
ፊፋ ለሙዚቃ ዝግጅት ሲባል የእረፍት ሰዓት ደቂቃን ሊጨምር እንደሆነ ተሰምቷል ።
ፊፋ በሳምንቱ መጨረሻ በሚደረገው የአለም ዋንጫ ፍፃሜ የእረፍት ሰዓትን ወደ 20 ደቂቃ ለመጨመር ማቀዱ ተዘግቧል።
በአለም ዋንጫው ፍፃሜ የእረፍት ሰዓት ወቅት ኮልድ ፕለይ ፣ ጀስቲን ቢበር ፣ሻኪራ፣ቢቲኤስ ፣ ማዶና ፣ቡርና ቦይ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ለታዳሚያን እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።
ፊፋ ከዚህ ቀደም የሚቀርበው ዝግጅት 11 ደቂቃዎችን ብቻ እንደሚወስድ ገልፆ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ የእረፍት ሰዓቱን ወደ 20 ከፍ ለማድረግ በሂደት ላይ መሆናቸው ታውቋል።
ፊፋ የሙዚቃ አቀንቃኞቹ በ እረፍት ሰዓት ለሚያቀርቡት ስራዎቻቸው ምንም አይነት ክፍያ እንደማይፈፅም ተዘግቧል።

❤5🔥4👍3👎1🤔1
🔶ያንጎ ራይድ በአሽከርካሪዎችና ተሳፋሪዎች መካከል መተማመንን የሚጨምር «የተሟላ መለያ» ምልክት አስተዋወቀ
የዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ቡድን ያንጎ አካል የሆነው ያንጎ ጉዞ ፣ በአሽከርካሪዎችና በተሳፋሪዎች መካከል ያለውን የመተማመን እና የደኅንነት ደረጃ ለማጠናከር የሚያግዝ «የተሟላ መለያ» (Passenger Profile Badge) የተባለ አዲስ መለያ ምልክት ማስተዋወቁን አስታወቀ።
ይህ አዲስ አሠራር ተሳፋሪዎች ስማቸውን፣ ፎቶአቸውንና ግላዊ መረጃቸውን አሟልተው ሲመዘገቡ የሚያገኙት ልዩ ምልክት ሲሆን፣ አጋር አሽከርካሪዎች የጉዞ ጥያቄ በሚደርሳቸው ወቅት የተሳፋሪውን መለያ ሁኔታ አስቀድመው በግልጽ እንዲመለከቱ ያስችላቸዋል።
በተደረጉ ዳሰሳዎች መሠረት ይህ መለያ በአሽከርካሪዎች ዘንድ የጉዞ ጥያቄዎችን በልበ ሙሉነት የመቀበል ፍላጎትን በ40 በመቶ ጨምሯል። ይህም በተለይ በሌሊት ሰዓታትና ተጨማሪ ጥንቃቄ በሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች የሚፈጠረውን አለመረጋጋት ለመቅረፍ ትልቅ እገዛ አለው ተብሏል።
የያንጎ የኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ ዶክተር የቀናዓለም አበበ እንደገለጹት፣ በመተግበሪያው ላይ የሚገነባው መተማመን ለተሻለ የጉዞ ልምድና ደኅንነት ወሳኝ በመሆኑ ይህ አሠራር በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ታማኝነት የበለጠ ያጠናክረዋል።
ይህ አዲስ መለያ፣ ያንጎ ጉዞ ለተጠቃሚዎቹ ደኅንነት ካዘጋጃቸው የጉዞ መስመርን በቅጽበት መከታተልን፣ የአደጋ ጊዜ (SOS) አገልግሎትንና የጉዞ መስመርን ማጋራትን ጨምሮ ከ25 በላይ ዘመናዊ የመተግበሪያ ውስጥ የደኅንነት አገልግሎቶች መካከል የቅርብ ጊዜው መሆኑ ታውቋል።

❤4
🔶 ካምፓስ ድራማ በምዕራፍ ሁለት
የታሪክ ማጠንጠኛውን በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ገሃዳዊ አለም ላይ አድርጎ ለ 20 ክፍሎች በፋና ቴሌቪዥን ሲተላለፍ የቆየው "ካምፓስ" ተከታታይ ድራማ በምዕራፍ ሁለት ሊመለስ ነው።
በታላቅ ፊልም ፕሮዳክሽን ፕሮዲውስ ተደርጎ ከ ረቡዕ ጥር 20 ቀን 2018 ጀምሮ እስከ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ለ 20 ክፍሎች በምዕራፍ አንድ ሲታይ የቆየውና በተመልካቾች ዘንድ የበዛ ተወዳጅነትና ተከታታይን ያገኘው "ካምፓስ" ተከታታይ ድራማ ከሃምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በምዕራፍ ሁለት መታየት እንደሚጀምር የድራማው ደራሲና ዳይሬክተር አብይ ጌታሁን አስታውቀዋል።
"ካምፓስ" በምዕራፍ አንድ ቆይታው "ሆራይዘን" በተባለ ምናባዊ ዩንቨርሲቲ ውስጥ የተፈጠረ ዩንቨርሲቲ ውስጥ ተማሪ የሆኑ ወጣቶች ህይወት ላይ ያተኮረ ሆኖ በተለየ ደግሞ የዋና ገጸ-ባህሪትዋን (መስከረምን) የህይወት ምስቅልቅል አስቃኝቷል።
በዚሁ ምዕራፍ ሂደት ውስጥም ወጣትነት ሲፈተን አላማ፣ እቅድ፣ በራስ ላይ የነበረ መተማመን በከባድ የህይወት ጥያቄ ሲነቀነቅ፣ ጓደኝነት፣ ሀቀኝነት፣ ፍትወት፣ የገንዘብ ኃያልነት ሲፈተሹም ታይቶበታል።
ተራ የማህበራዊ ድህረ ገጽ የሚመስል ግን ወጣቶችን ወዳልተፈለገ የወሲብ ንግድ የሚመራ ወጥመድ ምን ያህል በተማሪዎች የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖም በጉልህ ታይቶበታል።
በድራማው ቶማስ ቶራ ፣ ቅድስት ገ/ሥላሴ ፣ አበበ የሸዋልዑል ፣ ተስፋዬ ይማም ፣ የኋላሽት ዘሪሁን ፣ ማህሌት የኃላወርቅ እና ሌሎችም ወጣትና አንጋፋ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።

❤11👍9
🔶NBC Ethiopia ቲቪ ማስታወቂያ አውጥቷል
ናሽናል ሚዲያ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ክፍት የስራ ማስታወቂያ መደቦች ላይ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።ለተጨማሪው:- https://t.me/NorRadio1/292
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ናሽናል ሚዲያ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ክፍት የስራ ማስታወቂያ መደቦች ላይ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።ለተጨማሪው:- https://t.me/NorRadio1/292
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤5
🔶አብርሆት ቤተመጻሕፍት ወደ ሥራ ተመልሷል
ለቀናት በሀገር አቀፍ ፈተና ምክንያት ለአንባቢያን ዝግ ሆኖ የቆየው አብርሆት ቤተመጻሕፍት ለሁሉም አንባቢያን ክፍት ሆኗል።
ቤተመጻሕፍቱ በማህበራዊ ትስስር ገፆ" ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ተጠቃሚዎች በሙሉ! ከዛሬ ማለትም ከሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ቤተ-መጻሕፍታችን በመደበኛ ሰዓቱ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል" ብሏል።

👍10❤5
🔶JFm ከስርጭት ታገደ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ጄኤፍኤም (JFM) 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ታሳቢ በሚደረግ ስልጣን ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት ከስርጭት ሙሉ ለሙሉ እንዲታገድ መወሰኑን ኖር ሬድዮ ሰምቷል።
ባለሥልጣኑ ውሳኔውን ያሳለፈው በጣቢያው ላይ ባደረገው የይዘት ክትትልና በአካል ተገኝቶ ባከናወነው የኢንስፔክሽን ምልከታ በርካታ የሕግና የፈቃድ ውል ጥሰቶችን በመለየቱ እንደሆነ ገልጻል...ተጨማሪውን ያንብቡ:- https://t.me/NorRadio1/293
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ነኘፀ

❤7😱7🌚2
🔶የተወዳጁ ደራሲ Albert Camus ምርጥ ስራዎች በሀገር ውስጥ ዕትም ታትሞ ለንባብ ቀርቧል ::
Albert Camus በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከታወቁት ደራሲዎችና ፈላስፎች አንዱ ነበር።
በ1913 በአልጄሪያ (በዚያን ጊዜ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት) ተወለደ። በድሃ ቤተሰብ ውስጥ አደገ፣ አባቱም በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ሞተ። በወጣትነቱ ጋዜጠኛ፣ ደራሲ እና የቲያትር ተዋናይ/አዘጋጅ ሆኖ ሠራ።
በ1957 በሥነ ጽሑፍ የኖቤል ሽልማት አሸነፈ፣ በዚያን ጊዜ 44 ዓመቱ ነበር ።
በ1960 በመኪና አደጋ በ46 ዓመቱ ሕይወቱ አለፈ።
አልበርት ካሙ በተለይ ስለ ሕይወት ትርጉም፣ ነፃነት፣ ኃላፊነት እና "Absurd" (ሕይወት በራሷ ትርጉም የሌላት መሆኗን የሚያስረዳ ሐሳብ) ይጽፍ ነበር።
ከታዋቂ መጻሕፍቶቹ መካከል፦
The Stranger (L'Étranger)
The Plague
The Myth of Sisyphus
The Fall
ካሙ ዛሬም በዓለም ዙሪያ በጣም የሚነበብ ደራሲ ሲሆን፣ መጻሕፍቶቹ በሕይወት ትርጉም፣ በሰው ልጅ ምርጫ እና በሥነ ምግባር ላይ ጥልቅ ሐሳቦችን ያቀርባሉ።
ምንጭ: ጃዕፈር መጽሐፍ መደብር

❤3🔥2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🔶ላዳ ታክሲዎች 50 ዓመት ሞላቸው
የደርግ ስርዓት ከሶቪዬት ሕብረት ጋር የነበረውን ጥብቅ ወዳጅነት ተከትሎ እነዚህ የሩሲያ ምርት የሆኑት 'ላዳ 1200' መኪናዎች በብዛት ወደ ኢትዮጵያ መግባት ጀመሩ። መኪናዎቹ መጀመሪያ ላይ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ለታክሲነት አልነበረም። ለከፍተኛ ባለሥልጣናት አገልግሎት ይውሉ ዘንድ አዲስ አበባ የደረሱት ላዳዎች የመደበኛው ሕዝብ መገልገያ ሆነው በሕዝብ ልብ ውስጥ ነገሡ፡፡
ለ5 አስርት ዓመታት በመዲናዋ ጎዳናዎች በሰማያዊና ነጭ ቀለም ውር ውር የሚሉትን ላዳ ታክሲዎች ያመረተው የሩሲያው ቮልስኪ አውቶሞቢል ፕላንት (ቫዝ ፕላንት) ኩባንያ ዛሬ 60ኛ ዓመቱን ይዟል፡፡
አዲስ አበባ ጎዳናዎች አናብስቱ ታሪካዊ አመጣጥ፣ ወደ ሕዝብ አገልግሎት የተሸጋገሩበት አጋጣሚ፣ ለከተማዋ ኢኮኖሚ የነበራቸው አበርክቶ ጨመሮ በአጠቃላይ በዘመን እርጅና የማይደበዝዝ ሁለንተናዊ አሻራቸውን እንዳላቸው ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ዘግቧል።

❤10👍5🙏1💯1
🔶አንጋፋ ጋዜጠኞች ሊመሰነጉ ነው
በኢትዮጵያ የሚድያ ታሪክ የማይረሳ አሻራ ያኖሩት አዲስ አለም ሓድጉና በልሁ ተረፈ የምስጋና መርሀ ግብር ሊደረግላቸው ነው።
ቅዳሜ ሐምሌ 18 2018 ዓ.ም በወመዘክር መርስኤሀዘን አዳራሽ በሚደረገው የምስጋና መርሀ ግብር የባለሙያዎቹ አድናቂዎች እና ወዳጆች ይታደማሉ።
አዲስ አለም ሓድጉ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በትግርኛ ክፍል በኤዲተርነት እና በጋዜጠኝነት የሠራ ሲሆን ላለፉት 35 አመታትም ሙያውን ወዶና አክብሮ በመሥራት ይታወቃል።
የሚድያ ሰው በልሁ ተረፈ ደግሞ በኢትዮጵያ ሬድዮ ከሳይንስ ማህደር፣ ማንነት ሲፈተሽ እና ዝክረ ሰንበት በተባሉ ፕሮግራሞች ከ30 አመት በላይ የሠራ ሲሆን ሌሎችንም በማብቃት የማይዘነጋ አሻራ ለማኖር የቻለ ነው።
ሰውን በሕይወት ሳለ እናመስግን የሚል መርህ ያነገበው ይህ መሰናዶ የሚድያ ባለሙያዎችን በኑሯቸው የማገዝ ፣ በችግራቸው ጊዜ አብሯቸው የመሆን ግብ የሰነቀ ነው። እንዲህ አይነቱ ባለሙያዎችን የማገዝ ተግባር ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።
ሁለቱም ባለሙያዎች አገር የጣለችባቸውን አደራ የተወጡ ብርቱ ባለሙያዎች ሲሆኑ ነገር ግን በኑሮ መደገፍ እና መመስገን ያለባቸው በመሆኑ ለዚህ መርሀ ግብር ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሠራ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

❤13👏9
🔶የዶ/ር ኣርካ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል
በዶ/ር ኣርካ አቦታ የተዘጋጀው 'የሦስት ኮከቦች ንትርክ' የተሰኘ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል
ይህ መጽሐፍ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አንጋፋ የሚድያና ኮሚንኬሽን ት/ቤት መምህር በሆኑት ዶ/ር ኣረካ አቦታ ተጽፎ በ ዶ/ር ተሻገር ሽፈራው የአርትኦት ሥራው የተሰርላት መጽሐፍ ነው።
መጽሐፉ በይዘት ደረጃ ዶ/ር የፖለቲካዊ እና የህይዎት ምልከታዎች ያጋሩበት ሲሆን ብዙም ባልተነገረላቸው ባህላዊ አውዶችና ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች ውስጥ የሚጓዝ መሳጭ ታሪክ የያዘ ነው ተብሏል።
ይህ በ506 ገፆች ተቀንብቦ በ998 ብር የቀረበው መጽሐፍ ነገ ሐምሌ 18 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ይመረቃል።

❤16🙏2👌2👍1👎1
Forwarded from Kelemat Ads
የቻናል ጥቆማ
ህይወታችን የአስተሳሰባችን ነጸብራቅ ነው። ታላቅ ሕይወት በታላቅ አስተሳሰብ ይጀምራል። የትናንሽ ዕለታዊ ስኬቶች ድምር ታላቅ ስኬትን ያመጣል።
አዕምሯችንን እናሳድግ፤ በየቀኑ ከፍ እንበል፤ ስኬታችንን እንገንባ!
Rise Daily — Where great minds are built through daily discipline !
📌 Join: @SeidEndre
📤 Share with friends: @SeidEndre

❤5👎3👏1
Forwarded from Kelemat Ads
Your product deserves users not just views.
Kelemat Ads is more than an advertising platform we're a growth partner for Ethiopian digital startups.
Before every campaign, we work with you to understand your product, identify your ideal audience, and build a distribution strategy that gives your launch the best chance of success.
Then we promote your product across our network of 140+ carefully selected Telegram channels, with a combined subscriber base of 500,000+.
📌 Strategy before promotion
📌 Targeted distribution
📌 Measurable results
Best for EdTech | AI Products | SaaS | FinTech | Mobile apps | Telegram bots | Online courses |Productivity tools
Applications are now open for a limited number of startups to receive 40% off their first launch campaign.
Ready to apply?
fill out this form and we will get back to you within 24 hours to book your 1:1 strategy call.
form link : https://forms.gle/M1C5kUbLdrcFSjxy9

👌1
🔶 "የፒያሣ ድምፆች" ዐውደርዕይ
መንገዶቹ ቢቀየሩም ድምጻቸው አሁንም ይኖራሉ በሚል ሀሳብ የተዘጋጀው "የፒያሣ ድምፆች" የተሰኘ የዲጂታል አርት ዐውደርዕይ ነገ ይከፈታል።
በዳዊት ክፍሌ የተዘጋጀው ይህ አውደርዕይ ከሐምሌ 22 እስከ ነሐሴ 18 2018 ዓ.ም በፈንድቃ የባሕል ማዕከል በዕይታ ይቆያል ተብሏል።
ይህ ዲጂታል የሥነጥበብ ዐውደርዕይ ድሮዋን ፒያሣ ያስታውሳል ተብሏል።

❤6
🔶የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ አዲስ መጽሐፍ
ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ "አደይ እና ጥቀርሻ" የተሰኘ የግጥም መፅሐፉን በቅርቡ ለንባብ ያበቃል።
ይህ መጽሐፍ የበድሉ ዋቅጅራ ስድስተኛ የሥነግጥም መጸሐፉ ነው።
አስቀድሞ የፍካት ናፋቂዎች፣እውነት ማለት የእኔ ልጅ፣የተስፋ ክትባት፣የወይራ ስር ፀሎት፣የራስ ምስል የተሰኙ አምስት የግጥም መጽሐፍትን ለንባብ አብቅቷል።

👎7❤6🔥4
🔶በቆሎና ንባብ በክረምት
በልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ የተዘጋጀው "በቆሎና ንባብ በክረምት" መሰናዶ የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 25 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በጎተራ ማሳለጫ ይካሄዳል።በዕለቱም የተለያዩ እንግዶች ሀሳቦቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።

❤3👍2🤮1
🔶የዓለም ደራሲያን ድርጅት በኢትዮጵያ
የዓለም ደራሲያን ድርጅት በኢትዮጵያ ዛሬ ስብሰባውን እንደሚያደርግ ተገለፀ።
ኢትዮጵያዊያን ደራሲያን ተሳታፊ የሚሆኑበትና አለም አቀፍ እንደሆነ የተነገረለት ጉባኤ ዛሬ ሐምሌ 22 2018 ከ 10 ሰዓት ጀምሮ በኢሊሊ ሆቴል እንደሚደረግ ታውቋል።
በሥነ-ፅሑፍ ሙያ ላይ የተሰማሩ፣ በአርትዖት የተለየ አሻራ ያኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሚሳተፉበት በዚህ ጉባኤ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑትና በአፍሪካ ሥነ ፅሑፍ ላይ ያጠኑት ዶክተር አቢይ ዳንኤል ወረቀት ያቀርባሉ።
እንዲሁም ፀሐፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ከፅሑፍ አቅራቢዎቹ መካከል ናቸው። የአለም የደራሲያን ማህበር ፕሬዘዳንት ማርጋሬት ኤ አይ ለዚሁ ስብሰባ ሲሉ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን የጉባኤው ቅድመ ዝግጅትም እንደተጠናቀቀ ለማወቅ ተችሏል።
Africa in shaping a common future በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ከአፍሪካ ሥነ ፅሑፍ ጋር የተያያዙ ርዕሰ ጉዳዮች እንደሚቀርቡም ታውቋል።
ይህ ጉባኤ በኢትዮጵያ ሲደረግ የኢትዮጵያ ደራሲያንን በአለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ግንኙነት በማሳደግ የራሱ ሚና እንደሚኖረው ይታወቃል።
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽንም በመፅሐፍ ዝግጅቴ ሥራ ላይ የተሠማራ በመሆኑ መሥራቹ እዝራ እጅጉን ጨምሮ የዝግጅት ክፍሉ አባላት በኢሊሊው ጉባኤ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
©️ተወዳጅ ሚዲያ

❤11👍3