Event Addis Media
9.43K subscribers
6.32K photos
15 videos
4 files
4.93K links
Connect with Addis artistic community!

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
🔶“ሐጀር” እስላማዊ ፊልም ለዕይታ በቃ

በእስልምና ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣትን፣ ሐጀራን የውሃ ፍለጋ ታሪክ የሚያሳየው ይህ ፊልም፤ በተለይም በሶፋ እና በመረዋ ተራሮች መካከል ያደረገችውን ታሪካዊ ሩጫ በፊልም እይታ ያቀረበ ስራ ነው።

ፊልሙ ከአረፋ በዓል ጋር ቀጥተኛ ትስስር ያለው ታሪክ ላይ ያተኮረ መሆኑም ተገልጿል።

ይህንን ፈር-ቀዳጅ ሾል ልዩ ከሚያደርጉት ባህሪያቱ መካከል ፊልሙ ሙሉ በሙሉ ምንም አይነት የቃላት ንግግር የሌለበት (Mime) መሆኑ ሲሆን፣ አጠቃላይ የታሪኩን ይዘትና ልብ የሚነኩ ስሜቶችን በምልክትና በእንቅስቃሴ ብቻ በመግለጽ በ13 ደቂቃ ከፍታ  አጭር ጊዜ ውስጥ የተቋጨ የጥበብ ሾል ነው። ይህ አይነቱ አቀራረብ ታሪኩን ያለምንም የቋንቋ ገደብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማንኛውም ተመልካች ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ የተሰራ መሆኑ ተብራርቷል።

የፊልሙ አዘጋጅ ነጻ ዓለም አብዲ እንደተናገረው፤  ለዚህም በአፋር ክልል የሚገኙ ተራራማ ቦታዎችን 80 በመቶ ያህሉን በአካል በመዘዋወር ምልከታ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የፊልሙ መቼት ሙሉ በሙሉ በአፋር ክልል በሚገኙ ተራራማና ምድረ-በዳ ቦታዎች ላይ ሊቀረጽ ችሏል።

የፊልሙ ባለሙያዎች ለነጃሺ ቲቪ በሰጡት ማብራሪያ፤ ስራው ልብ የሚነኩ የእስላማዊ ታሪክ ህያው ስሜቶችን በኪነ-ጥበብ መድረክ ለማንጸባረቅ በሀገሪቱ የመጀመሪያውና ፈር ቀዳጅ መሆኑን ገልጸው፣ ፊልሙ የፊልም ስታንዳርዱን በአለም አቀፍ ደረጃ ጠብቆ በብቁ ባለሙያዎች የተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤12🎉2😁1
🔶የሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ ሥዕል በ2ሺ ዩሮ ተሸጠ

በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ በተካሄደ የሥዕል ኤግዚቢሽን ላይ፣ ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላ መድረክ ላይ በቀጥታ የሳለው ሥዕል በጨረታ ከ2 ሺህ ዩሮ በላይ መሸጡ ታወቀ።

በዕለቱ ከተካሄደው የሥዕል ሽያጭና የደጋፊዎች አስተዋጽኦ በተሰበሰበው የሕክምና ድጋፍ፣ በአጠቃላይ ከ8 ሺህ ዩሮ በላይ መገኘቱን ጋዜጠኛ መሳይ ወንድሜነህ ያጋራው መረጃ ያመላክታል።

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የሕፃናትና ታዳጊዎች የሥዕል ውድድር የተካሄደ ሲሆን፣ አሸናፊዎቹ ሽልማታቸውን ከሠዓሊ ብሩክ እጅ ተቀብለዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤33👏5👍2
🔶ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው አረፈ

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የተለያዩ ባህላዊ እና ሌሎች ይዘቶቸ ያሏቸው የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድማጭ ተመልካች አበርክቷል፡፡

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት እንደነበር ፋና ዲጂታል ከቤተሰቦቹ ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
😢40❤5💔5😱4🥰1
🔶ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ ታሰረች

ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ ስለመታሰሯ ተሰምቷል።

ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ በሙያዋ በሀገር ውስጥ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት ውስጥ የሠራች ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በማኅበራዊ ሚዲያ በምታስተላልፋቸው ትምህርታዊ መልእክቶች በሰፊው ትታወቃለች።

ስለ ኢትዮጵያውያን አንድነት በርካታ ሐሳቦችን ታጋራ ነበር። ሰላምን፣ መደጋገፍንና የሀገርን ታሪክ የሚያንጸባርቁ መልእክቶችን በምትሠራቸው ቪዲዮዎቿ ትታወቃለች።

ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ የታሰረችው ስለ አርሲ ክርስቲያኖች እልቂት በይፋ በመናገሯ ምክንያት እንደሆነ ተሰምቷል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
😢27❤16🤔4😱2👎1😁1
🔶የድምፃዊ ሰማኸኝ በለው የቀብር ሥነሥርዓት

የድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ቦሌ ቡልቡላ በሚገኘው መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ይፈጸማል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
😭13💔10
🔶ኮሜዲያኑ አልታሰረም !

ኮሜዲያን ምናለ ያረጋል፣ በዚህ ሳምንት በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሉን
የተለያዩ የመረጃ ምንጮች ዘግበዋል።

ነገር ግን ኮሜዲያን ምናለ ያረጋል ታስሯል ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/288


ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍9❤3
🔶የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፊልም ፌስቲቫል

ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፊልም ፌስቲቫል ከዛሬ አርብ ሰኔ 12፣ እስከ እሁድ ሰኔ 14  ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል።

ፌስቲቫል ላይ በመታደም ከ25 በላይ አዳዲስ አጭር ፊልሞችን ይመልከቱ  ተብላችኋል።

በተጨማሪም ዘርፉ ላይ ካሉ ታላላቅ ባለሙያዎች ጋር ግንኙነት ይፍጠሩ።

ቦታ - አአዩ - ዋናው ግቢ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ፤ ሼህ አላሙዲ አዳራሽ
ሰዓት - ከጠዋት 3 ሰዓት ጀምሮ

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
❤4🔥1
🔶የሮቤል ሚዲቅሳ ኮንሰርት

የድምጻዊ ሮቤል ሚዲቅሳ "ከበር አፍ" የሙዚቃ ኮንሰርት ነገ ቅዳሜ ሰኔ 13 2018 ዓ.ም በቃና ዌርሃውስ በድምቀት ይካሄዳል።

ስለኮንሰርቱ ድምጻዊ ሮቤል በማህበራዊ ትስስር ገፁ "የመጀመርያ የሙዚቃ ኮንሰርቴን ለእናንተ ለተከበራችሁ አድማጮቼ እና አድናቂዎቼ ለማቅረብ ዝግጅታችንን ጨርሰናል። ከእናንተ ጋር በአካል የምንገናኝበት ቀን በመድረሱ ደስ እያለኝ ሰኔ 13 - June 20 በቃና ዌርሃውስ የማይረሳ ምሽት እንድናሳልፍ ሁላችሁንም እጋብዛለሁ"ብሏል።
.
ትኬቶቹን በM-PESA ላይ ማግኘት ይችላሉ
መደበኛ- 800
በር ላይ- 1000
ቪአይፒ- 2000

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
❤9
🔶አንጋፋው ጋዜጠኛ ዳንኤል ታደሰ አረፈ

በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ለበርካታ ዓመታት ከሪፖርተርነት እስከ ከፍተኛ አዘጋጅነት በተለያዩ የሙያ ደረጃዎች ያገለገሉት አንጋፋው ጋዜጠኛ ዳንኤል ታደሠ በህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ጋዜጠኛ ዳንኤል ታደሰ ታኅሣሥ 26 ቀን 1959 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከአባታቸው ታደሰ ዳምጠው እና ከእናታቸው ፈለቀች ዳኜ ተወልደዋል።

ከታኅሣሥ 18 ቀን 1994 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በተለይም በኢትዮጵያ ሬዲዮ ውስጥ ለ24 ዓመታት በሪፖርተርነት፣ በአዘጋጅነት እና በከፍተኛ የሙያ ኃላፊነቶች አገልግለዋል።

የሟቹ ሥርዓተ ቀብር ነገ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ጀምሮ በቅድስት ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ተገልጿል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
😢13❤7🕊1💔1
🔶ተማሪዎቹ የመምህራቸውን መፅሐፍ አሳተሙ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ድግሪ የጋዜጠኛኝነት ትምህርት ክፍል ተማሪዎቹ የመምህራቸውን መፅሐፍ አሳተሙ።

ተማሪዎቹ ያሳተሙት የመምራቸውን የዶ/ር ኣርካ አቦታ መጽሐፍ ነው።

“ኣርካ ኣቦታ፤ የሦስት ኮከቦች ንትርክ” መጽሐፍ ህትመት እየተጠናቀቀ ነው ሲሆን ፤ ሽያጩ በይፋ ተጀምሯል፡፡

የገጽ ብዛት ፡ 506 ፤ ዋጋ ፡ 998 ብር
በቀጥታ ለመግዛት
ዶ/ር ኣርካ ኣቦታ
የንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር
1000290218415

ይህ መጽሐፍ በሁለት የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አንጋፋ የሚድያና ኮሚንኬሽን ት/ቤት መምህራን የተዘጋጀ ፖለቲካዊ የህይዎት ምልከታ ነው፡፡

ዶ/ር ኣርካ ኣቦታ ጽፈውት፣ ዶ/ር ተሻገር ሽፈራው አሰናድተውታል፡፡ ብዙ ባልተነገረላቸው ባህላዊ አውዶችና ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች ውስጥ የሚጓዝ መሳጭ ታሪክ ነው፡፡

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
❤22👍1🙏1
🔶አዲስ ስታንዳርድ ተሸለመ

አዲስ ስታንዳርድ የነፃ ጋዜጠኝነት የ2026
የዴሞክራሲ አዋርድ ተሸላሚ ሆነ

ናሽንል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ ለአማርኛ፣ ለአፋን ኦሮሞና ለእንግሊዝኛ የዜና አውታሩ አዲስ ስታንዳርድ የ2026 የዴሞክራሲ ሽልማት ሊያበረክትለት መሆኑን ይፋ አደረገ። አሜሪካ 250ኛ የነፃነት በዓሏን በምታከብርበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት፣ አዲስ ስታንዳርድ ይህንን ሽልማት ያገኘው በኢትዮጵያ ውስጥ ነፃ ጋዜጠኝነትንና ዴሞክራሲያዊ ነፃነቶችን ለማስከበር ባሳየው የማይናወጥ ፅናትና መሪነት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የአሜሪካን 250ኛ የነፃነት በዓል ምክንያት በማድረግ በኔድ የዳይሬክተሮች ቦርድ የተመረጡት እነዚህ ሽልማቶች፥ የሃይማኖት፣ የመናገር፣ የፕሬስ፣ የመሰብሰብ እና አቤቱታ የማቅረብ ነፃነቶችን ለሚያስከብሩና ለሚያስፋፉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ዕውቅና ለመስጠት ያለሙ ናቸው።

ኔድ የተሸላሚዎቹን ዝርዝር ይፋ ባደረገበት ወቅት፥ አዲስ ስታንዳርድ የተመረጠው በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ገለልተኛ ዘገባዎችን በማቅረብ ረገድ ለተጫወተው ጉልህ ሚና መሆኑን አስታውቋል።

ድርጅቱ ይህንን ሽልማት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በበርማ፣ ሶሪያ፣ ሩሲያና ኩባ ለሚገኙና በተመሳሳይ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ለነፃነት ለሚታገሉ ተለይተው ለተመረጡ ግለሰቦችና ተቋማትም ያበረክታል።

==================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
❤20
🔶ተሻሽሎ ታተመ

በድጋሚ ተሻሽሎ በልዩ ሁኔታ የታተመው የሃይማኖተ አበው የአንድምታ መጽሐፍ ነገ ሰኔ 20/2018 ዓ.ም ሊመረቅ ነው።

በአብነት ትምሕርት ለብዙ ዓመት የደከሙ በዘንድሮ ዓመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያጠናቀቁት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጆርናሎች አርቲክል ያሳተሙት ዶክተር መምህር ፍቅረ ማርያም ባዘዘው የሃይማኖተ አበው መጽሐፋቸውን ያስመርቃሉ።

ይህ መጽሐፍ የቤተክርስቲያናችን ዓምዶች doctors of the Church የሆኑት ቅዱሳን አባቶች በጉባኤያት የተከራከሩበትን፣ የከፈሉትን መሥዋዕትነት እና የጻፉትን የቀናች ሃይማኖት ምስጢር አጠቃልሎ የያዘ የምሥጢረ ሥላሴ የምሥጢረ ተዋሕዶ እና የነገረ ማርያም እንዲሁም የተለያዩ ነገሮች የተካተቱበት ማኅደር ነው።

መጽሓፉ ከያዛቸው በጥቂቱ:-

⁃ የጥንቱን የሊቃውንት ረቂቅ ዕውቀትና ትውፊት ከዘመናዊው የከፍተኛ ትምህርት ምርምር ስልት ጋር በጥንቃቄ አዋሕዶ የያዘ በመሆኑ ለዘመናችን አንባቢ ልዩ መሳጭ ጥበብን ይዞ ቀርቧል

⁃ የእምነት ተሟጋቹ ቅዱስ አትናቴዎስ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትን ከአርዮስ ክህደት ለመጠበቅ "ዓለምን ብቻውን የተጋፈጠ" የተባለለት የቅዱስ አትናቴዎስ ድርሳናትና ምስጢራዊ ትምህርቶች፣

በቅድስ ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በረዳት ፕሮፌሰርነት መምህር የሆኑት መምህር ፍቅረ ማርያም ባዘዘው ነገ ይህንን መጽሐፍ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ (4ተኛ ፎቅ) ያስመርቃሉ።

በእለቱም የቅድሥት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አባ ኃይለ ገብርኤል ፣ ሊቀ ሊቃውንት ስምአ ኮነ እንዲሁም ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ይገኛሉ።
❤31👍4
🔶የጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ለዓመታት በአድማጮች ልብ የተቀመጠው ተወዳጁ ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ “መቆያ” የራዲዮ ዝግጅት አሁን "እነሆ መቆያ" በሚል ርዕስ በመፅሀፍ መልክ ለአንባቢያን ቀርቧል።

“መቆያ” ስሜት የሚነኩ ታሪኮችን፣ የሕይወት ትምህርቶችን እና የሰው ልጅ ተሞክሮዎችንሬጠሬ በልዩ የአቀራረብ መንገድ ሲያቀርብ የቆየ ታላቅ የራዲዮ ድምፅ ነበር።

አሁን ግን ያ የልብ ድምፅ በጽሁፍ ተሰብስቦ በመፅሀፍ መልክ ተዘጋጅቷል፤ ከድምፅ ዓለም ወደ ጽሁፍ ዓለም የሚያስገባ ልዩ የስሜት ጉዞ ይሰጣል።የ“መቆያ” መፅሀፍ በጃፋር የመፅሀፍ መደብር ይገኛል።

==================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
❤45👍10🔥4
🔶የፎቶግራፍ ዐውደርዕይ

በአዲስ አበባ የቱሪዝም መዳረሻዎችን የሚያስተዋውቅ ልዩ የፎቶ አውደ ርዕይ ተከፍቷል። ለአስር ቀናት በሚቆየው በዚህ አውደ ርዕይ ላይ በቴክኖ “ካሞን 50 ፕሮ” ስልኮች የተነሱ፣ የሀገሪቱን የተፈጥሮና የታሪክ የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲሁም የሰዎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት የሚያሳዩ ከ100 በላይ ፎቶግራፎች ለዕይታ ቀርበዋል።ዐውደርዕይው በአዲስ አበባ ወጣቶች እና ሕፃናትና ቴአትር ቤት በዕይታ ላይ ይቆያል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤3
🔶አንጋፋዋ ድምፃዊት ራሄል ዮሐንስ አረፈች

አንጋፋዋ ድምፃዊት ራሄል ዮሐንስ ዛሬ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ተሰምቷል።

"አራዳ" "ምኒልክ" "ይዳኘኝ ሰው" እና በርካታ ስራዎቿን ለህዝብ ያበረከተችው ድምፃዊት ራሔል፤ በኪነጥበብ ቆይታዋ 13 ያህል ተወዳጅ አልበሞችን ለህዝብ አበርክታለች፡፡

ነፍስ ይማር!

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😢19🕊1
🔶የአዳም ረታ አዲስ መጽሐፍ ማተሚያ ቤት ገባ

የደራሲ አዳም ረታ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ተሰምቷል።የደራሲው አዲስ መጽሐፍ "መዝሙረ ሄላም" የተሰኘ ርዕስ ያለው ሲሆን ማተሚያ እንደሚገባና በዚህ ክረምት ለንባብ እንደሚበቃ ኤቨንት አዲስ ከቅርብ ምንጮች ሰምቷል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤14👍2
🔶የአስቴር አወቀ አልበምና የሙዚቃ ዝግጅት

ድምጻዊት አስቴር አወቀ ቆየት ያሉ ሙዚቃዎቿን በአዲስ መልክ አዘጋጅታ "ገላ ገላ: የአስቴር ትዝታዎች፪" በሚል ርዕስ  ለአድማጮች ልታቀርብ ነው።

ከዚህ አልበም ጋር በተያያዘ የፊታችን ማክሰኞ ሰኔ 30 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ በሸራተን አዲስ ሆቴል የሙዚቃ ድግስ ተዘጋጅቷል።አስቴር አወቀ የምትገኝበት ይህ ዝግጅት መግቢያው 3ሺ ብር ነው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤23🔥4
🔶 ሲኒማ አምፒር ፈረሰ

በአዲስ አበባ የሚገኘው ታሪካዊው ሲኒማ ኤምፒር መፍረሱ ተሰማ፡፡ በፒያሳ ውስጥ ከመፍረስ ከዳኑት ህንፃዎችና መኖሪያ ቤቶች ሲኒማ አምፒር አንዱ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ይህ ሲኒማ ቤት መትረፉን ተከትሎም በከፍተኛ ገንዘብ የእድሳት ስራ ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

ፈረሰው ከሲኒማ ቤቱ በተጨማሪ በአካባቢው ያሉት እንደሸዋ ሆቴልና ሄርሞን ካፌ፣ጉድ ታይምስ፣ አንበሳ ጫማ ቤት ጭምር መሆኑንም ለመረዳት ችለናል፡፡

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😡38😢20❤5👍2😭2😱1
🔶ገጣሚ ረድኤት ተረፈ ያዘጋጀችው
የግጥምና ሙዚቃ ዝግጅት ዛሬ ይካሄዳል

ገጣሚ ረድኤት ተረፈ ያዘጋጀችውና ግጥምን ከሙዚቃ ጋር አጣምሮ የያዘው “ደበብ ያለ ጨዋታ” የተሰኘው ልዩ የኪነ-ጥበብ ምሽት ዛሬ ማክሰኞ፣ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ዝግጅቱ በብስራተ ገብርኤል አካባቢ በሚገኘው ላፍቶ ሞል ሲኒማ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ለታዳሚዎች እንደሚቀርብ ታውቋል።

የመግቢያ ዋጋ 599 ብር ሲሆን እንደ አዘጋጆቹ ገለጻ ለዝግጅቱ የተመደቡት የወንበር ቦታዎች ውስን በመሆናቸው፣ ፍላጎት ያላቸው የጥበብ ወዳጆች አስቀድመው ቦታቸውን እንዲይዙ አሳስበዋል።

ታዳሚዎች ስለ ፕሮግራሙ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር +251 920 105 731 መገናኘት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤14👎2
🔶ይድነቃቸው ሹመቴ
በአሜሪካ ኤምባሲ

ፕሪስቴጅ አዲስ ተወዳጁን እና አንጋፋውን በሀገር ውስጥ በፊልም ሥራዎቹ ፤ በFilm directing እና በድርሰት ዘርፍ የሚታወቀው ስመ-ጥሩ እና አንጋፋው ዳይሬክተር እና ደራሲ ይድነቃቸው ሹመቴን ጋብዟል::

ከዳይሬክተር ይድነቃቸው ሹመቴ ጋር በሚኖረን ቆይታ የሥራ፣ የህይወት ልምድ እና የጥበብ ተሞክሮውን የሚያካፍለን ሲሆን፣ ከእናንተ ከወዳጅና አድናቂዎቹ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ደግሞ የፊታችን ማክሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ምላሽ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል።

ፕሪስቴጅ አዲስ ከዳይሬክተር ይድነቃቸው ሹመቴ ጋር አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ እንድታደርጉ በታላቅ አክብሮት ይጋብዛል።

አድራሻ፦ አሜሪካን ኢምባሲ ቅጥር ግቢ (ሳችሞ ሴንተር / Satchmo Center) — ከስድስት ኪሎ ወደ ሽሮሜዳ መሄጃ

ቀን፦ ማክሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2018 ዓ.ም (July 14)

ሰዓት፦ ከሰዓት 8:00 (8:00 PM Ethiopian Time / 2:00 PM Local Time) 🕘

⌚️ 🎯 ማሳሰቢያ፦ ማርፈድ ወደ ውስጥ እንዳትገቡ ሊያደርግ ስለሚችል ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩ።

ከመታወቂያ ጋር መምጣት እንዳይረሳ! 🪪

📎 በዝግጅቱ ላይ ለመታደም ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ 👇🖱
https://jazzio.land/register

የፕሪስቴጅ አባል ለመሆን ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ይመዝገቡ 👇🖱
https://forms.gle/ekHY5ez8AWm3uwvUA

@prestigeaddis

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍8❤4
🔶የመምህራኑ የAi ቅሌት

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በመምህራን ከቀረቡ ጥናቶች ከ91% በላዩ ሙሉ ለሙሉ በኤ.አይ በመሰራታቸው ውድቅ መደረጋቸውን ገለጸ

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ካቀረቧቸው 104 የጥናት ጽሑፎች መካከል ከ91% በላይ ማለትም 95ቱን ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል። ፕሮፖዛሎቹ ውድቅ የተደረጉት ሙሉ በሙሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤ.አይ) በመሠራታቸው ነው ተብሏል።

ዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ተማሪዎች ሰው ሰራሽ አስተውሎትን አላግባብ እየተጠቀሙ መሆኑን አስታውቋል።

የዩኒቨርሲቲው የሕግ ትምህርት ክፍል መምህር አቶ ዓለሙ ባልቻ እንደገለጹት፤ ከቀረቡት 104 ፕሮፖዛሎች ውስጥ ዘጠኙ ብቻ ኤ.አይን ሳይጠቀሙ ወይም ኤአይን በአግባቡ በመጠቀም የተዘጋጁ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው ዲጂታል ቴክኖሎጂን በሥርዓተ-ትምህርቱ ውስጥ ለማካተት እየሰራ እንደሆነ ተገልጾአል።

ዩኒቨርሲቲው የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀምን ለመገደብ አዲስ መመሪያ ማውጣቱንም አቶ ዓለሙ ተናግረዋል።

በዚህ መሠረት መምህራን እና ተማሪዎች እስከ 30 በመቶ ብቻ በኤአይ እንዲጠቀሙ ቢፈቀድም፤ የአጠቃቀም መጠኑን ለመለየት ተርኒቲን (Turnitin) የተባለ ሶፍትዌር ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሆነ አብራርተዋል።

ሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በትምህርት ዘርፍ አዎንታዊ ጎኖች ቢኖሩትም በጥንቃቄ መጠቀም ያስፈልጋል ያሉት መምህር ዓለሙ በተለይም ጥናታዊ ጽሑፎች የባለቤቱን የፈጠራ ክህሎት ሊያንፀባርቁ ይገባል ብለዋል።

©️ዘገባው የአሐዱ ሬድዮ ነው

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤣11👍8❤7😁1