Event Addis Media
9.43K subscribers
6.32K photos
15 videos
4 files
4.93K links
Connect with Addis artistic community!

Contact: @Tmanaye
Download Telegram
🔶የጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው ንጉሥ ተብሎ ለሚጠራው ለክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ የሚሆን ግርማ ሞገስ ያለው ሐውልት 6 ኪሎ አምበሳ ግቢ አጠገብ ተሠርቶ ዛሬ ሚያዝያ 27 2018 ዓ.ም በይፋ ተመርቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለታላቁ የጥበብ ሰው ያለውን አክብሮት ለመግለጽ ያስገነባው ይህ ሐውልት፣ በስድስት ኪሎ አካባቢ ወደ ምኒልክና ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ መገናኛ ላይ ቆሟል።

ጥላሁን ገሠሠ ስለ ሀገር፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ እናትና ስለ ጀግንነት ያልዘፈነበት ርዕስ የለም። በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞና በሱዳንኛ ዜማዎቹ ህዝብን ሲያቆራኝ የኖረ ባለውለታ ነው።

ሚያዝያ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. በ68 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለየንም፣ ዜማዎቹ ግን ከትውልድ ትውልድ ተሻግረው ዛሬም የነፍሳችን ምግብ ናቸው።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤18😁9
🔶የኢቲቪው አብዲ ከማል አረፈ

የቀድሞም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (etv) ጋዜጠኛ አብዲ ከማል ባጋጠው የጤና እክል ዛሬ ጧት በአዲስ አበባ እንዳረፈ ተሰምቷል። ሥርዓተ ቀብሩ ዛሬ (ማክሰኞ) ቀትር ላይ በኮልፌ የሙስሊም የመቃብር ስፍር  እንደሚፈፀም የሥራ ባልደረባው ላሉ ኢታላ ጽፏል።

ጋዜጠኛ አብዲ ከማል በኢህአዴግ ጊዜ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን "አኬልዳማ" የተሰኘውን ዶክመንተሪ ጨምሮ የተለያዩ ዘጋቢ ፊልሞችን በማዘጋጀት ይታወቃል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
😢17❤3😱2
🔶ደራሲ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር
በ90ኛ ዓመት የልደት በዓሉ ተዘከረ

የ75ኛው የአርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል በሚከበርበት በዛሬው ዕለት፣ ደራሲ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር የተወለደበት 90ኛ ዓመት የልደት በዓል በወዳጆቹ ተዘክሯል።

የደራሲው ህልፈት 14 ዓመታት ቢቆጠሩም፣ አድናቂዎቹና የጥበብ ወዳጆች በአዲስ አበባ ውቤ በረሃ አካባቢ በሚገኘው ሐውልቱ ስር በመሰብሰብ ለደራሲው ያላቸውን ፍቅር ገልጸዋል።

"እኔ የምሞተው በሰዎች ልብ ውስጥ ስሞት ነው" የሚለውን ንግግሩን በማስታወስ፣ ደራሲው ዛሬም በስራዎቹ እና በታሪኩ በብዙዎች ልብ ውስጥ ህያው ሆኖ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በዚህ ዝግጅት ላይ ደራሲያኑ ዓለማየሁ ገላጋይ፥ዘነበ ወላ፣ኃይለመለኮት መዋዕል እና ሌሎችም ተገኝተዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤34
🔶ድምጻዊ ሳሚ ዳን ለአርሰናል ዘፈነ

ታዋቂዉ የሬጌ አቀንቃኝ ሳሚ ዳን ከ22 ዓመታት በኃላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ላሸነፈው አርሰናል ክለብ ዘፈን ሰርቷል።

ዛሬ ምሸት 12:00 ሰዓት አርሰናልን የተመለከተ አዲስ ዘፈን እንደሚለቅም ይፋ አድርጓል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🤣53❤14👍2👎1
🔶ዳንኤል ክብረት ለባንዳና ባዕዳን መዝሙር ጋበዙ

የብልጽግና ፓርቲ እጩ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር የሆኑት ዳንኤል ክብረት ባንዳና ባዕዳን ላላቸው አካላት መዝሙር መጋበዛቸውን ኖር ሬድዮ ከፌስቡክ ገፃቸው ተመልክቷል።

አቶ ዳንኤል በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፣ ምርጫውን ለማደናቀፍ ጥረት ላደረጉ የውስጥ "ባንዳዎች" እና የውጭ "ባዕዳን" በሚል የዘማሪ ቴዎድሮስ ዮሴፍን "እንዲህ በአራት ነጥብ ሊዘጋ ምዕራፉ" የተሰኘውን መዝሙር ጋብዘዋል።

ዳንኤል "ይሄ ምርጫ እንዳይሳካ ለማደናቀፍ ሞክረው ለነበሩ የውስጥ ባንዳ እና የውጭ ባዳ ይሄንን ጋብዘናል" በማለት በፌስቡክ ገጻቸው ጽፈዋል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
😁37🖕29❤9🤬8🤣4😢3🥰1
🔶የዓለም ዋንጫን በዲኤስቲቪ

የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ 104ቱንም ጨዋታዎች በቀጥታ የሚያስተላልፈው ዲኤስቲቪ ልዩ ቅናሽ ማቅረቡን አስታወቀ

በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በሜክሲኮ አስተናጋጅነት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረውን የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ፣ ዲኤስቲቪ (ሱፐርስፖርት) ሁሉንም 104 ጨዋታዎች በቀጥታ እና በላቀ ጥራት እንደሚያስተላልፍ አስታውቋል።

በዓለም ዋንጫ ታሪክ ትልቁ በሆነው በዚህ ውድድር ላይ 48 ብሔራዊ ቡድኖች በ12 ምድቦች ተከፋፍለው ለ39 ቀናት ብርቱ ፉክክርሚያደርጉ ሲሆን፣ ዲኤስቲቪ ስርጭቱን ተደራሽ ለማድረግ ልዩ ልዩ የቴክኖሎጂና የዋጋ ቅናሽ አማራጮችን ይዞ ቀርቧል።

ልዩ የሱፐርስፖርት የሰርጭት አማራጮች፦
ቻናል 222 (World Cup Central)፦ ዋና ዋና ጨዋታዎች እና ትንተናዎች

ቻናል 223 (World Cup Extra)፦ በተመሳሳይ ሰዓት የሚደረጉ ተጨማሪ ወሳኝ ጨዋታዎች

ቻናል 225 (World Cup Pass)፦ አጫጭር ምስሎች (Highlights)፣ ድጋሚ ስርጭቶችና ዘጋቢ ፊልሞች (24/7)
DStv Stream መተግበሪያ፦ በስልክ፣ በታብሌትና በላፕቶፕ ባሉበት ቦታ ሆነው ለመከታተል።

የዲኮደር እና የፓኬጅ ልዩ ቅናሽ፦ ኩባንያው የዓለም ዋንጫውን ምክንያት በማድረግ ለአዳዲስ ደንበኞች ልዩ ቅናሽ ያቀረበ ሲሆን፣ የዲኮደር ዋጋን 999 ብር ብቻ ማድረጉን ገልጿል።

ደንበኞች በወር 569 ብር ብቻ የሚከፈለውን የ"ጎጆ ፓኬጅ" በመጠቀም ሁሉንም 104 ጨዋታዎች በቀጥታ መከታተል እንደሚችሉ ተቋሙ አስታውቋል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
❤4👍1🔥1
🔶“ሐጀር” እስላማዊ ፊልም ለዕይታ በቃ

በእስልምና ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣትን፣ ሐጀራን የውሃ ፍለጋ ታሪክ የሚያሳየው ይህ ፊልም፤ በተለይም በሶፋ እና በመረዋ ተራሮች መካከል ያደረገችውን ታሪካዊ ሩጫ በፊልም እይታ ያቀረበ ስራ ነው።

ፊልሙ ከአረፋ በዓል ጋር ቀጥተኛ ትስስር ያለው ታሪክ ላይ ያተኮረ መሆኑም ተገልጿል።

ይህንን ፈር-ቀዳጅ ሾል ልዩ ከሚያደርጉት ባህሪያቱ መካከል ፊልሙ ሙሉ በሙሉ ምንም አይነት የቃላት ንግግር የሌለበት (Mime) መሆኑ ሲሆን፣ አጠቃላይ የታሪኩን ይዘትና ልብ የሚነኩ ስሜቶችን በምልክትና በእንቅስቃሴ ብቻ በመግለጽ በ13 ደቂቃ ከፍታ  አጭር ጊዜ ውስጥ የተቋጨ የጥበብ ሾል ነው። ይህ አይነቱ አቀራረብ ታሪኩን ያለምንም የቋንቋ ገደብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማንኛውም ተመልካች ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ የተሰራ መሆኑ ተብራርቷል።

የፊልሙ አዘጋጅ ነጻ ዓለም አብዲ እንደተናገረው፤  ለዚህም በአፋር ክልል የሚገኙ ተራራማ ቦታዎችን 80 በመቶ ያህሉን በአካል በመዘዋወር ምልከታ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የፊልሙ መቼት ሙሉ በሙሉ በአፋር ክልል በሚገኙ ተራራማና ምድረ-በዳ ቦታዎች ላይ ሊቀረጽ ችሏል።

የፊልሙ ባለሙያዎች ለነጃሺ ቲቪ በሰጡት ማብራሪያ፤ ስራው ልብ የሚነኩ የእስላማዊ ታሪክ ህያው ስሜቶችን በኪነ-ጥበብ መድረክ ለማንጸባረቅ በሀገሪቱ የመጀመሪያውና ፈር ቀዳጅ መሆኑን ገልጸው፣ ፊልሙ የፊልም ስታንዳርዱን በአለም አቀፍ ደረጃ ጠብቆ በብቁ ባለሙያዎች የተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤12🎉2😁1
🔶የሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ ሥዕል በ2ሺ ዩሮ ተሸጠ

በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ በተካሄደ የሥዕል ኤግዚቢሽን ላይ፣ ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላ መድረክ ላይ በቀጥታ የሳለው ሥዕል በጨረታ ከ2 ሺህ ዩሮ በላይ መሸጡ ታወቀ።

በዕለቱ ከተካሄደው የሥዕል ሽያጭና የደጋፊዎች አስተዋጽኦ በተሰበሰበው የሕክምና ድጋፍ፣ በአጠቃላይ ከ8 ሺህ ዩሮ በላይ መገኘቱን ጋዜጠኛ መሳይ ወንድሜነህ ያጋራው መረጃ ያመላክታል።

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የሕፃናትና ታዳጊዎች የሥዕል ውድድር የተካሄደ ሲሆን፣ አሸናፊዎቹ ሽልማታቸውን ከሠዓሊ ብሩክ እጅ ተቀብለዋል።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
❤33👏5👍2
🔶ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው አረፈ

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የተለያዩ ባህላዊ እና ሌሎች ይዘቶቸ ያሏቸው የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድማጭ ተመልካች አበርክቷል፡፡

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት እንደነበር ፋና ዲጂታል ከቤተሰቦቹ ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
😢40❤5💔5😱4🥰1
🔶ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ ታሰረች

ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ ስለመታሰሯ ተሰምቷል።

ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ በሙያዋ በሀገር ውስጥ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት ውስጥ የሠራች ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በማኅበራዊ ሚዲያ በምታስተላልፋቸው ትምህርታዊ መልእክቶች በሰፊው ትታወቃለች።

ስለ ኢትዮጵያውያን አንድነት በርካታ ሐሳቦችን ታጋራ ነበር። ሰላምን፣ መደጋገፍንና የሀገርን ታሪክ የሚያንጸባርቁ መልእክቶችን በምትሠራቸው ቪዲዮዎቿ ትታወቃለች።

ጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ የታሰረችው ስለ አርሲ ክርስቲያኖች እልቂት በይፋ በመናገሯ ምክንያት እንደሆነ ተሰምቷል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
😢27❤16🤔4😱2👎1😁1
🔶የድምፃዊ ሰማኸኝ በለው የቀብር ሥነሥርዓት

የድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ቦሌ ቡልቡላ በሚገኘው መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ይፈጸማል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
😭13💔10
🔶ኮሜዲያኑ አልታሰረም !

ኮሜዲያን ምናለ ያረጋል፣ በዚህ ሳምንት በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሉን
የተለያዩ የመረጃ ምንጮች ዘግበዋል።

ነገር ግን ኮሜዲያን ምናለ ያረጋል ታስሯል ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ...ተጨማሪውን ያንብቡ:-https://t.me/NorRadio1/288


ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
👍9❤3
🔶የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፊልም ፌስቲቫል

ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፊልም ፌስቲቫል ከዛሬ አርብ ሰኔ 12፣ እስከ እሁድ ሰኔ 14  ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል።

ፌስቲቫል ላይ በመታደም ከ25 በላይ አዳዲስ አጭር ፊልሞችን ይመልከቱ  ተብላችኋል።

በተጨማሪም ዘርፉ ላይ ካሉ ታላላቅ ባለሙያዎች ጋር ግንኙነት ይፍጠሩ።

ቦታ - አአዩ - ዋናው ግቢ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ፤ ሼህ አላሙዲ አዳራሽ
ሰዓት - ከጠዋት 3 ሰዓት ጀምሮ

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
❤4🔥1
🔶የሮቤል ሚዲቅሳ ኮንሰርት

የድምጻዊ ሮቤል ሚዲቅሳ "ከበር አፍ" የሙዚቃ ኮንሰርት ነገ ቅዳሜ ሰኔ 13 2018 ዓ.ም በቃና ዌርሃውስ በድምቀት ይካሄዳል።

ስለኮንሰርቱ ድምጻዊ ሮቤል በማህበራዊ ትስስር ገፁ "የመጀመርያ የሙዚቃ ኮንሰርቴን ለእናንተ ለተከበራችሁ አድማጮቼ እና አድናቂዎቼ ለማቅረብ ዝግጅታችንን ጨርሰናል። ከእናንተ ጋር በአካል የምንገናኝበት ቀን በመድረሱ ደስ እያለኝ ሰኔ 13 - June 20 በቃና ዌርሃውስ የማይረሳ ምሽት እንድናሳልፍ ሁላችሁንም እጋብዛለሁ"ብሏል።
.
ትኬቶቹን በM-PESA ላይ ማግኘት ይችላሉ
መደበኛ- 800
በር ላይ- 1000
ቪአይፒ- 2000

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
❤9
🔶አንጋፋው ጋዜጠኛ ዳንኤል ታደሰ አረፈ

በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ለበርካታ ዓመታት ከሪፖርተርነት እስከ ከፍተኛ አዘጋጅነት በተለያዩ የሙያ ደረጃዎች ያገለገሉት አንጋፋው ጋዜጠኛ ዳንኤል ታደሠ በህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ጋዜጠኛ ዳንኤል ታደሰ ታኅሣሥ 26 ቀን 1959 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከአባታቸው ታደሰ ዳምጠው እና ከእናታቸው ፈለቀች ዳኜ ተወልደዋል።

ከታኅሣሥ 18 ቀን 1994 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በተለይም በኢትዮጵያ ሬዲዮ ውስጥ ለ24 ዓመታት በሪፖርተርነት፣ በአዘጋጅነት እና በከፍተኛ የሙያ ኃላፊነቶች አገልግለዋል።

የሟቹ ሥርዓተ ቀብር ነገ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ጀምሮ በቅድስት ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ተገልጿል።

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
😢13❤7🕊1💔1
🔶ተማሪዎቹ የመምህራቸውን መፅሐፍ አሳተሙ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ድግሪ የጋዜጠኛኝነት ትምህርት ክፍል ተማሪዎቹ የመምህራቸውን መፅሐፍ አሳተሙ።

ተማሪዎቹ ያሳተሙት የመምራቸውን የዶ/ር ኣርካ አቦታ መጽሐፍ ነው።

“ኣርካ ኣቦታ፤ የሦስት ኮከቦች ንትርክ” መጽሐፍ ህትመት እየተጠናቀቀ ነው ሲሆን ፤ ሽያጩ በይፋ ተጀምሯል፡፡

የገጽ ብዛት ፡ 506 ፤ ዋጋ ፡ 998 ብር
በቀጥታ ለመግዛት
ዶ/ር ኣርካ ኣቦታ
የንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር
1000290218415

ይህ መጽሐፍ በሁለት የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አንጋፋ የሚድያና ኮሚንኬሽን ት/ቤት መምህራን የተዘጋጀ ፖለቲካዊ የህይዎት ምልከታ ነው፡፡

ዶ/ር ኣርካ ኣቦታ ጽፈውት፣ ዶ/ር ተሻገር ሽፈራው አሰናድተውታል፡፡ ብዙ ባልተነገረላቸው ባህላዊ አውዶችና ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች ውስጥ የሚጓዝ መሳጭ ታሪክ ነው፡፡

====================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
❤22👍1🙏1
🔶አዲስ ስታንዳርድ ተሸለመ

አዲስ ስታንዳርድ የነፃ ጋዜጠኝነት የ2026
የዴሞክራሲ አዋርድ ተሸላሚ ሆነ

ናሽንል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ ለአማርኛ፣ ለአፋን ኦሮሞና ለእንግሊዝኛ የዜና አውታሩ አዲስ ስታንዳርድ የ2026 የዴሞክራሲ ሽልማት ሊያበረክትለት መሆኑን ይፋ አደረገ። አሜሪካ 250ኛ የነፃነት በዓሏን በምታከብርበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት፣ አዲስ ስታንዳርድ ይህንን ሽልማት ያገኘው በኢትዮጵያ ውስጥ ነፃ ጋዜጠኝነትንና ዴሞክራሲያዊ ነፃነቶችን ለማስከበር ባሳየው የማይናወጥ ፅናትና መሪነት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የአሜሪካን 250ኛ የነፃነት በዓል ምክንያት በማድረግ በኔድ የዳይሬክተሮች ቦርድ የተመረጡት እነዚህ ሽልማቶች፥ የሃይማኖት፣ የመናገር፣ የፕሬስ፣ የመሰብሰብ እና አቤቱታ የማቅረብ ነፃነቶችን ለሚያስከብሩና ለሚያስፋፉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ዕውቅና ለመስጠት ያለሙ ናቸው።

ኔድ የተሸላሚዎቹን ዝርዝር ይፋ ባደረገበት ወቅት፥ አዲስ ስታንዳርድ የተመረጠው በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ገለልተኛ ዘገባዎችን በማቅረብ ረገድ ለተጫወተው ጉልህ ሚና መሆኑን አስታውቋል።

ድርጅቱ ይህንን ሽልማት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በበርማ፣ ሶሪያ፣ ሩሲያና ኩባ ለሚገኙና በተመሳሳይ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ለነፃነት ለሚታገሉ ተለይተው ለተመረጡ ግለሰቦችና ተቋማትም ያበረክታል።

==================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
❤20
🔶ተሻሽሎ ታተመ

በድጋሚ ተሻሽሎ በልዩ ሁኔታ የታተመው የሃይማኖተ አበው የአንድምታ መጽሐፍ ነገ ሰኔ 20/2018 ዓ.ም ሊመረቅ ነው።

በአብነት ትምሕርት ለብዙ ዓመት የደከሙ በዘንድሮ ዓመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያጠናቀቁት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጆርናሎች አርቲክል ያሳተሙት ዶክተር መምህር ፍቅረ ማርያም ባዘዘው የሃይማኖተ አበው መጽሐፋቸውን ያስመርቃሉ።

ይህ መጽሐፍ የቤተክርስቲያናችን ዓምዶች doctors of the Church የሆኑት ቅዱሳን አባቶች በጉባኤያት የተከራከሩበትን፣ የከፈሉትን መሥዋዕትነት እና የጻፉትን የቀናች ሃይማኖት ምስጢር አጠቃልሎ የያዘ የምሥጢረ ሥላሴ የምሥጢረ ተዋሕዶ እና የነገረ ማርያም እንዲሁም የተለያዩ ነገሮች የተካተቱበት ማኅደር ነው።

መጽሓፉ ከያዛቸው በጥቂቱ:-

⁃ የጥንቱን የሊቃውንት ረቂቅ ዕውቀትና ትውፊት ከዘመናዊው የከፍተኛ ትምህርት ምርምር ስልት ጋር በጥንቃቄ አዋሕዶ የያዘ በመሆኑ ለዘመናችን አንባቢ ልዩ መሳጭ ጥበብን ይዞ ቀርቧል

⁃ የእምነት ተሟጋቹ ቅዱስ አትናቴዎስ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትን ከአርዮስ ክህደት ለመጠበቅ "ዓለምን ብቻውን የተጋፈጠ" የተባለለት የቅዱስ አትናቴዎስ ድርሳናትና ምስጢራዊ ትምህርቶች፣

በቅድስ ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በረዳት ፕሮፌሰርነት መምህር የሆኑት መምህር ፍቅረ ማርያም ባዘዘው ነገ ይህንን መጽሐፍ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ (4ተኛ ፎቅ) ያስመርቃሉ።

በእለቱም የቅድሥት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አባ ኃይለ ገብርኤል ፣ ሊቀ ሊቃውንት ስምአ ኮነ እንዲሁም ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ይገኛሉ።
❤31👍4
🔶የጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ለዓመታት በአድማጮች ልብ የተቀመጠው ተወዳጁ ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ “መቆያ” የራዲዮ ዝግጅት አሁን "እነሆ መቆያ" በሚል ርዕስ በመፅሀፍ መልክ ለአንባቢያን ቀርቧል።

“መቆያ” ስሜት የሚነኩ ታሪኮችን፣ የሕይወት ትምህርቶችን እና የሰው ልጅ ተሞክሮዎችንሬጠሬ በልዩ የአቀራረብ መንገድ ሲያቀርብ የቆየ ታላቅ የራዲዮ ድምፅ ነበር።

አሁን ግን ያ የልብ ድምፅ በጽሁፍ ተሰብስቦ በመፅሀፍ መልክ ተዘጋጅቷል፤ ከድምፅ ዓለም ወደ ጽሁፍ ዓለም የሚያስገባ ልዩ የስሜት ጉዞ ይሰጣል።የ“መቆያ” መፅሀፍ በጃፋር የመፅሀፍ መደብር ይገኛል።

==================
አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/NorRadio1

https://t.me/NorRadio1
❤45👍10🔥4